YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 46 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 46 ሰዎች አንዷ እስራኤላዊት ስትሆን የተቀሩት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ በፆታ ወንድ(29) ሴት(17) ናቸው

➡️ዕድሜያቸው ከ12-79 የሆኑ

➡️34 የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው

➡️4 በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው

➡️8ቱ የጉዞ ታሪክም ሆነ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ የሌላቸው

➡️ተጨማሪ 8 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ ያገገሙት ቁጥር 167 ደርሷል

➡️የተገኙት ከአዲስ አበባ(13)፣ ከትግራይ ክልል ሁሉም የጉዞ ታሪክ ያላቸው (3)፣ ከአማራ ክልል ሁሉም የጉዞ ታሪክ ያላቸው(15)፣ ከሶማሎ ክልል (11)፣ ድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች (4) በኮሮና የተያዙ በድምር 46 ሰዎች ናቸው።

➡️በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 701 ደርሷል።

@YeneTube @FikerAssefa
6ኛው ሞት ተመዝግቧል!

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት 6ኛው ሞትም ተመዝግቧል።በተጓዳኝ ህመም በፅኑ ህክምና ክፍል የነበረች የ32 አመት እናት የሆነች የአዲስ አበባ ነዋሪ ትናንት በተደረገላት ህክምና ቫይረስ ከተገኘባት በኋላ ትናንት ሌሊት ህይወቷ አልፏል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ጥራት ሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ ባለስልጣን አራት ትምህርት ቤቶችን ለአንድ ዓመት አገደ።

ባለሰልጣኑ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የትምህርት ቤት ክፍያቸውን እስከ 70 በመቶ እንዲቀንሱ መመሪያ ቢያስተላልፍም ትምህርት ቤቶቹ ግን 100 ፐርሰነት ክፍያ አስከፍለው ነው።ለአንድ ዓመት ከታገዱት ትምህርት ቤቶች መካከልም 3ኤም ትምህርት ቤት፣ገነት መሰረተ ክርስቶስ፣ሮማን አካዳሚ እና ለምለም ትምህርት ቤቶች በ2013 ዓመት ተማሪ እንዳይቀበሉ ተወስኖባቸዋል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
EBC መንግሥት የ191 ሚሊዮን ብር ካሽ እገዛ እንዲያደርለት ጠይቋል። ኮርፖሬሽኑ ይህንን የጠየቀው በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የማስታወቂያ ገቢ በመቀነሱ ለሰራተኞች ደመውዝና ለሳተላይት ኪራይ ክፍያ የሚሆን ገንዘብ በማስፈለጉ መሆኑን ፎርቹን ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከ10 000 በላይ የሚሆኑ ሴተኛ አዳሪዎች ተለይተው ድጋፍ መሰጠት ተጀምሯል ተባለ፡፡

የአዲስ አበባ ሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ቢሮ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ ለችግር የተጋለጡ ከ10 000 በላይ ሴተኛ አዳሪዎችን መለየቱን ተናግሯል፡፡ በሆቴሎች፣ በመንገድ ላይ እና በተለያዩ መጠጥ ቤቶች ውስጥ የሚሰሩ ሴቶች በኮሮና ቫይረስ የተነሳ ለችግር መጋለጣቸው ተነግሯል፡፡በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ለችግር ለተጋለጡ ዜጎች የሚደረገው ድጋፍ እነዚህን የህብረተሰብ ክፍሎችም ያካተተ መሆኑን ሸገር ከቢሮው ሰምቷል፡፡በአዲስ አበባ ሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ቢሮ የተለዩት ከ10 000 በላይ የሚሆኑ ሴተኛ አዳሪዎች ዝርዝር ሁኔታ ለአዲስ አበባ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ መተላለፉንም ሰምተናል፡፡

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል የተፈጠረው ምንድን ነው? #BBC

ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ በትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ አካባቢዎች ነዋሪዎች የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት ተቃውሞ በማሰማት ላይ እንደሆኑ በማኅበራዊ መገናኛ መድረኮች ላይ ሲነገር ቆይቶ ነበር።ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይም ጉዳዩን በተመለከተ በሽሬ እንደስላሴ እና በዋጅራት አካባቢዎች የመልካም አስተዳደር፣ የመሰረተ ልማት እንዲሁም ከሥራ ዕድል ጋር የተያያዙ በርካታ ጥያቄዎችን በማንሳት የተቃቀውሞ ሰልፎች እንደተካሄዱ ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያውን ጨምሮ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ይህንንም ተከትሎ የትግራይ ክልል መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሰኞ ዕለት ባወጣው መግለጫ በአሁኑ ወቅት በክልሉ በየትኛውም ቦታ "የተካሄደ ሰላማዊ ሰልፍም ሆነ የተፈጠረ የሰላም መደፍረስና ግርግር ፈፅሞ ያልተሰማና መሬት ላይ የሌለ ነው" በማለት ዘገባዎቹን አስተብብሏል።መግለጫው ጨምሮም "በሽረ እንዳስላሰና አከባቢው እንዲሁም በዋጅራትና አከባቢው ሰላማዊ ሰልፎች ተካሄዱ፣ ፍትህ መጓደል አለ የሚባለው የተፈበረከ ሐሰተኛ፣ የበሬ ወለደ ወሬ ነው" ሲል አጣጥሎታል።ነገር ግን ቢቢሲ ከአካባቢዎቹ አስተዳዳሪዎችና ከነዋሪዎች እንደተረዳው በተለያዩ አካባቢዎች ጥያቄዎችን በማንሳት ለቀናት የዘለቀ ተቃውሞዎችና የመንገድ መዝጋት ክስተቶች አጋጥመዋል።

የተቃዋሚው አረና ትግራይ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ አምዶም ገብረስላሰ ማይሃንሰን እና ደደቢት በተባሉ የትግራይ ክልል አካባቢዎች የተነሱ ሕዝባዊ ቅዋሜዎች አሁንም አንዳልበረዱ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።አቶ አንዶም ገብረስላሰ እንደሚሉት ለተቃውሞዎቹ መቀስቀስ ምክንያቶቹ ከዚህ ቀደምም ሲንከባለል የቆየ የወረዳነት ጥያቄ ሲሆን ተገቢ ምላሽ አላገኘንም ያሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ወደ ምዕራብዊ ዞን የሚወስደውን የዳንሻ መንገድ ከዘጉ ዘጠኝ ቀናት አስቆጥረዋል፤ አሁንም ቢሆን "ጥያቄውም አልተፈታም፤ መንገድም አልተከፈተም" ብለዋል።

ሙሉ ዘገባው ➡️https://telegra.ph/What-happened-in-Tigray-Via-BBC-05-26
ባለስልጣናት እና አመራሮች ሀብታቸውን በ42 ቀናት እንዲያስመዘገቡ ቀነ ገደብ ተሰጣቸው። የፌደራል የስነምግባርና የፀረሙስና ኮሚሽን፤ በጊዜ ገደቡ የሀብት ምዝገባ በማያከናውኑት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ በኮሮና ቫይረስ በክልሉ ተይዘው ከነበሩት 7 ሰዎች ስድስቱ ማገገማቸውን አስታውቋል።በሀገራችን ዛሬ 8 ሰዎች ማገገማቸው በጤና ሚኒስቴር ከተገለፀ ሲሆን ሁለቱ ከላይ የተጠቀሱት ሲሆኑ ስድስቱ ደግሞ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ናቸው።

@YeneTube @FikerAssefa
በቴሌግራም @Orangebusinessnetwork ን በመጎብኘት ለእርሶ እና ለድርጅቶ እድገት የሚረዱ መረጃዎች ፤ሀብቶችን እና ማበረታቻዎችን ያገኙ!

የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ
T.me/Orangebusinessnetwork
⬆️ኮቪድ 19ን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ የወጣ ሪፖርት ፣

ቫይረሱ የተገኘባቸው ክ/ከተማዎችና የተያዙ ሰዎች ቁጥር :

1. ልደታ 122
2.አዲስ ከተማ 69
3.ቦሌ 54
4.ጉለሌ 38
5.ኮልፌ ቀራኒዮ 38
6.ንፋስ ስልክ ላፍቶ 27
7.የካ 25
8.አራዳ 18
9.አቃቂ ቃሊቲ 8
10.አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያሉ 18 ሲሆኑ በድምር በከተማዋ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 436 ነው።

Via Addis Ababa City P.S
@YeneTube @FikerAssefa
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መሬት ወስደው በሚገባ ያላለሙ 20 ኢንቨስተሮችን መሬት መቀማቱን አስታወቀ።

የክልሉ የአካባቢ መሬት አስተዳደርና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ገለታ ሃይሉ እንዳሉት በክልሉ በግብርና ኢንቨስትመንት የተሰማሩ ባለሃብቶችን የስራ እንቅስቃሴ በመገምገም የወሰዱትን መሬት ሳያለሙ በተገኙ 18 የእርሻና 2 በእጣን ማምረት የተሰማሩ የኢንቨስትመንት ባለሃብቶች ፈቃድና የመሬት ውላቸው ተሰርዟል።በክልሉ 103 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል አስመዝግበው ውል በመግባት 8 ሺህ 376 ሄክታር መሬት በእርሻ ኢንቨስትመንት ዘርፉ ተሰማርተዋል።ይሁንና እነዚህ ባለሃብቶች መሬቱን ባለማልማታቸው ወደ መሬት ባንክ እንዲገባ ተደርጓልም ብለዋል።ይህ መሬትም በቀጣይ የማልማት አቅም ላላቸውና መስፈርቱን አሟልተው ለሚቀርቡ ባለሃብቶች እንደሚሰጡም ሃላፊው ገልጸዋል።11 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ላይ ደግሞ በቀጣይ በገቡት ውል መሰረት የታዩባቸውን ክፍተቶች በመቅረፍ እንዲያለሙ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል ተብሏል።

ባለፉት ዓመታት እርምጃ በተወሰደባቸው 13 ፕሮጀክቶች ተይዞ የነበረው 5 ሺህ 385 ሄክታር መሬት በባንክ እዳ ተይዞ መቆየቱንም አስታውሰዋል፡፡አሁን ላይ በባንክ ዕዳ ተይዞ የነበረውን መሬት ጨምሮ 10 ሺህ ሄክታር መሬት የማልማት አቅም ላላቸው ባለሃብቶች ለመስጠት ክልሉ ዝግጁ ማድረጉንም ኃላፊው ገልጸዋል ፡፡ቢሮው በእርሻ ኢንቨስትመንት ዘርፉ የሚሰማሩ ባለሃብቶች ለሃገር እድገት የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ ክልሉ ከ56 ሺህ ሄክታር በላይ የእርሻ መሬት ማዘጋጀቱንም ተናግረዋል።በመሆኑም የማልማት አቅም ያላቸው ኢንቨስተሮች ወደ ክልሉ መጥተው ኢንቨስት እንዲያደርጉም ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
በቀጣይ የምርት ዘመን የ12 በመቶ የምርት አቅርቦት እጥረት ሊከሰት እንደሚችል ተጠቆመ!

ግብርና ሚኒስቴር በቀጣይ ዓመት የምርት ዘመን ላይ የ12 በመቶ የምርት አቅርቦት እጥረት ሊያጋጥም እንደሚችል አስታወቀ። ሊያጋጥም ይችላል የተባለው የምርት እጥረት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና የበረሃ አንበጣ በመከሰቱ ነው ተብሏል።በኢትዮጵያ ከተከሰተ ዓመት ሊሞላው የአንድ ወር ጊዜ የቀረው የበረሃ አንበጣ በቀጣይ የምርት ዘመን ላይ የአራት በመቶ እንዲሁም በዓለም ዐቀፍ ደረጃ ወረርሽኝ በመሆን ዓለምን እያመሰ በሚገኘው ኮቪድ-19፣ የስምንት በመቶ፣ በድምሩ በ12 በመቶ የምርት ማሽቆልቆል ዋነኛ ምክንያቶች መሆናቸውን የኢትዮጵያ ግብርና ሚኒስቴር የእጽዋት እድገት ዳይሬክተር ኢሳያስ ለማ ለአዲስ ማለዳ ጠቁመዋል። የበረሃ አንበጣ በምሥራቅ አፍሪካ ኹሉም አገሮች ላይ ስጋት መሆኑን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ፣ በተለይም በኢትዮጵያ ላይ ወቅቱ የዝናብና ሰብል የሚለማበት ጊዜ ከመሆኑ እና አገሪቱ በአብዛኛው በግብርና ልማት የምትለማበት ከመሆኑ አንፃር ስጋቱ ከፍተኛ እንደሆነ ገልጸዋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል በወባ በሽታ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ከአምናው ጋር ሲነፃፀር በ73 በመቶ መጨመሩን የአማራ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡ በዚህ አመት 411 ሺህ 744 ሰዎች በወባ የተያዙ ሲሆን የ2 ሰዎች ሕይወት አልፏል።የኮሮናን ወረርሽኝ ለመቆጣጠር የተሰጠው ትኩረት ለወባ በሽታ መጨመር አንድ ምክንያት መሆኑን ኢንስቲቱዩቱ ገልጿል።

Via ELU
@YeneTube @FikerAssefa
በሊባኖስ በተፈጠረው ኢኮኖሚያዊ ቀውስ አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን የሆኑ ከ250ሺ የሚልቁ ስደተኛ የጉልበት ሰራተኞች ለማህበራዊ ቀውስ ተጋልጠዋል።

በኮሮና ወረርሽን ስጋት በሃገሪቱ የተጣለው የእንቅስቃሴ ዕገዳ በርካቶች ኢትዮጵያውያን እንደሆኑ የተነገረላቸውን ሴት የቤት ሰራተኞች ፤ የግንባታ እና የጽዳት ሰራተኞች ከስራቸው ተፈናቅለው ጎዳና መውጣታቸው ተነግሯል።ለወትሮም በሊባኖስ አስተዳደራዊ ችግር እና የሙስና መንሰራፋት ከቋፍ አድርሶት የነበረውን የሃገሪቱን ኢኮኖሚ የኮሮና ወረርሽን ይብሱን አንኮታኩቶታል።ከዶላር አንጻር የሃገሪቱ የመግዛት አቅም ስልሳ በመቶ ተዳክሟል።የሃገሪቱ የስራ አጥነት መጠንም ሰላሳ አምስት በመቶ ከፍ ብሏል። አርባ አምስት ከመቶ የሚሆኑ ሊባኖሳውያን ከድህነት ወለል በታች ደረጃ መድረሳቸውን የአሶሽየትድ ፕረስ ዘገባ ያመለክታል።በዚህ ሁኔታ ውስጥ ደግሞ አብዛኞቹ ከኢትዮጵያ እና ከፊልጲንስ የሆኑ እና ቁጥራቸው 180,000 የሚሆኑ የቤት ሰራተኞች የችግሩ ሰለባ ናቸው።

ሰራተኞቹ በስራ ላይ በነበሩባቸው ጊዜያት ለከፍተኛ የጉልበት ብዝብዛ ይጋለጡ እንደነበርም ዘገባው አመልክቷል።አብዛኞቹ በሕገ ወጥ መንገድ ሊባኖስ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ በመሆናቸው እና መብታቸውን ሊያስጠብቅላቸው የሚችል አካል አለመኖሩ ችግሩን እንዳወሳሰበው ባንቺ ይመር የተባለች ኢትዮጵያዊት እና በሊባኖስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የቤት ሰራተኞችን ለመታደግ ዘመቻ የጀመረ ቡድን መስራች ለአሶሽየትድ ፕረስ ተናግራለች።ከአሰሪዎቻቸው የሚባረሩ እነዚሁ የቤት ሰራተኞች መውደቂያቸውንም ጎዳና እና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ደጅ አድርገዋል ብላለች። ስደተኞቹ ወደ ሃገራቸው የመመለስ ጽኑ ፍላጎት ቢኖራቸውም የመጓጓዣ ወጪውን የመሸፈን አቅም የላቸውም።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
በኡንዱሉ ወረዳ ከባድ አውሎ ነፋስ ቀላቅሎ የጣለ ዝናብ በመኖሪያ ቤትና በእንስሳት ላይ ጉዳት አደረሰ!

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በኡንዱሉ ወረዳ አልሀመር ቀበሌ በቀን 17 /9/ 2012 ዓ/ም ከባድ አውሎ ነፋስ ቀላቅሎ የጣለ ዝናብ በመኖሪያ ቤትና በእንስሳት ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡ የአልሀመር ቀበሌ ስራ አስኪያጅ አቶ ናስር አህመድ እንዳሉት በቀን 17/2012 ዓ/ም ከቀኑ 10:30 ሰዓት አካባቢ አውሎ ነፋስ ቀላቅሎ በጣለው ዝናብ በ30 ቆርቆሮና በ15 ሳር ቤቶች በድምሩ በ45 መኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት ማድረሱን ገልጸዋል፡፡በተመሳሳይ የሁለት ፍየሎችና የአንድ አህያ በድምሩ የሶስት እንስሳት ህይወት መጥፋቱን ጭምር ነው ስራ አስኪያጁ አቶ ናስር አክለው የገለጹት፡፡ ጉዳት የደረሰባቸው አካላት በበኩላቸው፣ ቤታቸውን ለመስራት አቅም እንደሌላቸው ገልጸው፣ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል።

መረጃውን ያገኘነው ከመንጌ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ነው
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል በዛሬው ዕለት በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠውን 15 ሰዎች ጨምሮ በአጠቃላይ በክልሉ 44 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በአማራ ክልል በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ፦
➡️ ምዕ/ጎንደር - 29 ሰዎች
➡️ ማ/ጎንደር - 3 ሰዎች
➡️ ጎንደር ከተማ - 1 ሰው
➡️ ደሴ ከተማ - 1 ሰው
➡️ ባህር ዳር ከተማ - 4 ሰዎች
➡️ አዊ - 3 ሰዎች
➡️ ሰ/ሸዋ - 2 ሰዎች
➡️ ሰ/ወሎ - 1 ሰው

ምንጭ፦ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ
@YeneTube @FikerAssefa
በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 100,000 አለፈ።

በአሜሪካ አጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 100,103 በላይ የደረሰ ሲሆን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1.7 ሚሊዮን አልፏል። እንዲሁም ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 469,049 በላይ ሆኖ ተመዝግቧል።

Via @tesfaget55
@YeneTube @FikerAssefa
በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ የነበሩ ጥያቄያቸውን በሰላማዊ መንገድ ለክልሉ መንግሥት ለማቅረብ ተስማምተዋል፡፡

በትግራይ ክልል የሰሜን ምዕራብ ወረዳ ቀበሌ ማይ ሓንሰ ነዋሪዎች ከተማይቱ የወረዳው ማእከል እንድትሆን ሲጠይቁ መሰንበታቸውንና “ የክልሉ መንግሥት መፍትሄ ይስጠን” በሚልም ለአንድ ሳምንት መንገድ ዘግተው የነበረ ሲሆን ነዋሪዎቹ የክልሉ መንግሥት ቀርቦ ጥያቄያቸው እንዲሰማቸው ጠይቀው ነበር።

በዚህ መሰረት በነዋሪዎቹና በመንግሥት አካላት መካከል በተደረገው ውይይት መንገዱን እንዲከፍቱና ጥያቄያቸውን በህጋዊ መንገድ ለማቅረብ መስማማታቸውን የወረዳው አስተዳደር አቶ ሀብቶም አበራ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

ነዋሪዎቹ ጥያቄያቸው ለክልሉ መንግሥት የሚያቀርብላቸው 14 አባላት ያሉት ኮሚቴ ማቋቋማቸውን ገልፀዋል። መንገዱም ከዛሬ ከሰአት ጀምሮ መከፈቱንም ጨምረው ተናግረዋል።

#BBC
@Yenetube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የለቅሶዉ ያስከተለው መዘዝ አዲስ አበባ

አዲስ አበባ ዉስጥ በልደታ ክፍለ ከተማ፣ በወረዳ 3 ፣ ቀጠና 5 ፣ መንደር 3 (በተለምዶ አብነት የሚባለው አካባቢ) የኮሮና ተሕዋሲ በርካታ ሰዎችን በመልከፉ ወይም በመያዙ ምክንያት የአካባቢዉ ነዋሪዎች በሙሉ ከሌሎች አካባቢዎች ነዋሪዎች ጋር እንዳይገናኙ ታገዱ።እርምጃዉ የተወሰደዉ በነዋሪዎቹ ፈቃድና ይሁንታ ነዉ ተብሏል።የመንደሩ ነዋሪዎች ከወትሮ እንቅስቃሴቸዉ እንዲታቀቡ፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንዲጠቀሙ ፖሊስ ጠንካራ ቁጥጥር እያደረገ ነዉ።

በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችም ይህንን ስራ እያስተባበሩ መሆኑን የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ሰለሞን ሙጬ ተመልክቷል።ኢትዮጵያ ዉስጥ በኮቪድ 19 የሞቱት የ4ኛው ሰው ቤተሰቦችን ለማስተዛዘን ለቅሶ ተቀምጠው የነበሩ ከ30 በላይ የመንደሩ ነዋሪዎች በኮሮና በተኅዋሲ መያዛቸዉን እርምጃዉን ከሚያስተባብሩ ወጣቶች አንዱ ገልጿል።መንደር 3 አንድ መቶ ያህል መኖሪያ ቤቶች ይገኛሉ ተብሎ ተገምቷል።


ምንጭ:- DW በሰለሞን ሙጬ
@Yenetube @Fikerassefa
የሳኡዲ አቪየሽን ይፋ እንዳደረገው ሳኡዲ የአገር ውስጥ በረራ ለመጀመር ዝግጅቷን አጠናቃለች።

ከመጋቢት 21 ጀምሮ በረራዎችን አቋርጣ የነበረችው ሳኡዲ አረቢያ ቀስ በቀስ ዓለም አቀፍ በረራዎችንም ለመጀመር እቅድ እያወጣች ነው።

Via:- BBC
@Yenetube @Fikerassefa