YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የጃፓኑ ጠቅላይ ሚንስትር፡ “ወረርሽኙ ሲገታ የዓለም ጤና ድርጅት መገምገም አለበት”

የጃፓኑ ጠቅላይ ሚንስትር ሽንዞ አቤ፤ ወረርሽኙ ካለፈ በኋላ የዓለም ጤና ድርጅት መገምገም አለበት አሉ።

ሆኖም ግን መንግሥታቸው ድርጅቱን መደገፍ እንደማያቆም ገልጸዋል።

“አሁን የዓለም ጤና ድርጅትን የምንደግፍበት ወቅት ነው። ያለንበት ሁኔታ እልባት ሲያገኝ ግን ድርጅቱ መፈተሽ አለበት። እውነታው ብዙ ጉዳዮችና ፈተናዎች መኖራቸው ነው” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህን አስተያየት የሰጡት፤ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አገራቸው ለድርጅቱ የምታደርገውን ገንዘብ ድጋፍ እንደምታቆም ይፋ ካደረጉ ከቀናት በኋላ ነው።

Via:- BBC
ምስል፦ ጌቲ ኢሜጅስ
@Yenetube @Fikerassefa
ጀርመን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን መቆጣጠሯን ገለጸች

የጀርመን ጤና ሚኒስትር የንስ ስፓን በአገራቸው በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መቀነስ ማሳየቱን ተከትሎ አገራቸው ወረርሽኙን መቆጣጠሯን ተናገሩ።

ሚኒስትሩ እንዳሉት ከቅርብ ቀናት ወዲህ ከበሽታው የሚያገግሙት በበሽታው ከሚያዙት ሰዎች ቁጥር በቋሚነት እየጨመረ መሄዱ የእንቅስቃሴ ገደቡ ውጤታማ እንደሆነ ያሳያል ብለዋል።

"ዛሬ ወረርሽኙ መቆጣጠር የሚቻል መሆኑን ተገንዝበናል" ሲሉ በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተናገሩት ሚኒስትሩ የአገራቸው የጤና እንክብካቤ ሥርዓት እስካሁን በወረርሽኙ ምክንያት ከአቅሙ በላይ የሆነ ችግር እንዳላጋጠመው ተናግረዋል።

Via:- BBC
@Yenetube @Fikerassefa
በአፍሪካ በኮሮና የተያዙ ሰዎች ቁጥር ባለፈው ሳምንት በ51%፤በተሕዋሲው የሞቱ ሰዎች 60% መጨመሩን ዶ/ር ቴድሮስ ተናገሩ።«የመመርመሪያ ቁሳቁሶች ለማግኘት ባለው ወቅታዊ ፈተና ምክንያት ትክክለኛው ቁጥር ሪፖርት ከተደረገው ሊበልጥ ይችላል» ብለዋል።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
“በማንኛውም ጊዜ ጠንቃቃና ዝግጁ ሆኖ መገኘት የጠቢብነት መገለጫ ነው”

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህ


በማንኛውም ጊዜ ጠንቃቃና ዝግጁ ሆኖ መገኘት የጠቢብነት መገለጫ ነው።የምናውቀውንና የምናምነውን መተግበር ሲያቅተን ለምን ? ብለን መጠየቅ ይኖርብናል።በከፍታ የሚኖር እኛነታችንን ከልዕልና ወደ ዝቅታ የሚገፋብንን አጋጣሚ በሌሊት ጨለማ እንደሚመጣ ውስጥ አዋቂ ሌባ መቁጠር ነው።

በጨለማ ውስጥ አድብቶ ሀብታችንን ሊቀማ የሚመጣን ውስጥ አዋቂ ሌባ ጠመንጃ ታጥቀን አንመልሰውም።ጩቤ ታጥቆ መጠበቅም ቢሆን ብዙም ከጉዳት አያድነንም።

በጨለማ ከሚመጣ ውስጥ አዋቂ ሌባ በሚገባ መከላከል የምንችለው በአዕምሯዊ ብርሃን ነው። አዕምሯዊ ብርሃን ማለት ልቡና ነው። ልብ ማድረግ ማለት መረጃን መቀበል፣ ማሰላሰል፣ ማገናዘብና ባገናዘቡት ልክ መተግበር ነው። ጨለማ ሁሉ በብርሃን ይሸነፋል።ጥፋትም

የሚሸነፈው በልቡና ነው። ጠንቃቃና ሥነ ምግባራዊ መሆን ከልቡና የሚገኝ ነው። ነገሮችን ልብ እንበል፤ ጊዜ ሰጥተን እናሰላስል፣ እንገንዘብ፣ ከዚያም በተገነዘብነው ልክ እንተግብር፣ ባወቅነው ልክ እንኑር።

ከስሜት ርቀን፣ በልቡና ተመርተን የሰውን ልጅ የማስተዋል ደረጃ በሚመጥን ምግባርና ሰብአዊነት የምንደምቅበት ፣ ኢትዮጵያዊነትን ደግሞ በአልማዝ የምናስጌጥበት ታሪካዊ ወቅት ላይ እንገኛለን። ወደታች ስንሄድ ጨለማ ነው። ወደ ላይ ስንሄድ ብርሃን። ወደ ላይ ወደ ዕውቀትና ምግባር ከፍታ እንሂድ። በብርሃንም መንገድ እንመላለስ፡፡

Via:- EPA
@Yenetube @Fikerassefa
የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ለሁለተኛ ጊዜ በሀዋሳ ከተማ ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ የኬሚካል እርጭት ዛሬ በዓል ዋዜማ ከ12:00 ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል።

ወቅቱም የትንሳኤ በዓል እንደመሆኑ ህብረተሰባችን በዓሉን ለማክበር በሚያከናውናቸው ሀይማኖታዊና የበዓሉ ስነ-ስርዓቶች ላይ ያለምንም ቸልተኝነት የበሽታውን ስርጭት ለመከላከል የሚተላለፉ መልዕክቶችን ተግባራዊ በማድረግ ፣ በከብት እርድ ፣ በገበያ ቦታዎች፣ በቤት ውስጥ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳይዘነጋ ሲል የከተማው ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ አስታውቋል ።

@Yenetube @Fikerassefa
ጥብቅ ማሳሰቢያ ለስጋ ቤቶች (ሉካንዳ ቤቶች) በሙሉ;-

የኮሮናን ቫይረስ ወረርሽኝም ሆነ ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን ስርጭት ለመከላከልና ለመከላከል ሲባል በፌዴራል ደረጃ አዋጅ መውጣቱ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግዴታዎች መፈፀም የበሽታውን ስርጭት ለመግታት አስተዋፅኦ የሚያደርግ በመሆኑ ሁሉም ስጋ ቤት (ሉካንዳዎች) ለተግባራዊነቱ አስፈላጊውን ትብብር እንድታደርጉ የአዲስ አበባ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ጥሪውን ያስተላልፋል።

ዋና ዋና ግዴታዎች !!!

1. ማንኛውም ስጋ ቤት (ሉካንዳ) ስጋ አስገብቶ ከመሸጡ (አገልግሎት ላይ እንዲውል) ከመደረጉ በፊት ሙሉ ለሙሉ ስጋ ቤቱንና መጠቀሚያ ቁሳቁሶችን በውሃ ሳሙናና በረኪና በመጠቀም መፀዳት አለበት፣

2. ማንኛውም ስጋ ቤት (ሉካንዳ) የሚያስገባው ስጋ ህጋዊ እና ከታወቀ ቄራ ታርዶ የቀረበ መሆን አለበት፣

3. ማንኛውም በስጋ ቤት (በሉካንዳ) የሚሰራ ሰራተኛ የስጋ ሽያጭ በሚያከናውንበት ጊዜ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል (ማስክ)፣ ቆብ፣ ጋዎን መጠቀም አለበት፣

4. በማንኛውም በስጋ ቤት (በሉካንዳ) ገንዘብ የሚቀበልና ስጋ የሚቆርጥ ሰራተኛ መለየት አለበት፣

5. በማንኛውም ስጋ ቤት (ሉካንዳ) ውስጥ ለሰራተኞች የእጅ ሳሙናና ውሃ ተዘጋጅቶ በየጊዜው እጃቸውን በመታጠብ አገልግሎት መስጠት አለባቸው፣

6. በማንኛውም ስጋ ቤት (ሉካንዳ) ሽያጭ በሚከናወንበት ወቅት ተገልጋዮች ከመሸጫ መስኮቱ 1 (አንድ) ሜትር ርቀው እንዲቆሙና እንዲገለገሉ መደረግ አለበት፣

7. በማንኛውም ስጋ ቤት (ሉካንዳ) ድርጅት ውስጥ የተገልጋይ ቁጥር ከሁለት በላይ በሚሆንበት ወቅት ድርጅቱ ተገልጋዮችን እያንዳንዳቸው ርቀታቸውን በየሁለት እርምጃ ጠብቀው እንዲቆሙና እንዲገለገሉ መደረግ አለበት፣

8. ከምግብ ቤቶች ጋር የተያየዙ ሉካንዳ ቤቶች ውስጥ ያልበሰለ ስጋ (ቁርጥ/ጥሬ ስጋ፣ ያልበሰለ ክትፎ) ለምግብነት ማቅረብ ለበሽታው ስለሚያጋልጥ የተከለከለ ነው፣

ምንጭ:- አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
@Yenetube @FikerAssefa
ህብረተሰቡ ከልኳንዳ ቤቶች ስጋ ሲገዙ በቄራ ውስጥ ስለመታረዱ ማረጋገጥ አለባቸው ዶ/ር ገ/እግዚአብሔር ገ/ዮሐንስ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ አሳስበዋል ።

@Yenetube @Fikerassefa
በኢትዮጵያ በመንገድ ስራ ተቋራጭነትእና በአማካሪ ድርጅትነት የተሰማሩ ድርጅቶች 12 ባለሃብቶች የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያግዝ 15 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር አበረከቱ ፡፡

በዛሬው እለት በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋናው መ/ቤት በተዘጋጀው በዚሁ መርሃ ግብር ላይ አስራ ሁለት አገር በቀል የመንገድ ግንባታ ስራ ተቋራጮች ናቸው የ15.3 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ያደረጉት ፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይም የሰንሻይን ኢንቨስትመንት ግሩፕ እና ኮንስትራክሽን ባለቤት የክብር ዶ/ር ሳሙኤል ታፈሰ ተቋራጮችን በመወከል የብር ስጦታውን ለተቋቋመው የብሔራዊ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አባላት አስረክበዋል፡፡

በመድረኩ ላይም እኛ በመንገድ ግንባታ ዘርፍ እየተሳተፍን ያለን የደረጃ አንድ ተቋራጮች ወቅታዊው ወረርሽኝ በህይወት፣ በጤና፣በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ ይበልጥ ሀገራዊ የከፋ ጉዳት እንዳያስከትል ከመንግስት ጎን በመቆም በራሳችን ተነሳሽነት ድጋፍ በማድረጋችን ደስተኞች ነን ብለዋል ፡፡ በቀጣይም ይህን መሰሉ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል፡፡

ባለሃብቶቹ ለወጎኖቻቸው ያበረከቱትን የገንዘብ ድጋፍ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ሃብታሙ ተገኘ እንዲሁም የብሔራዊ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ እና የንግድ እና ኢንደስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋናው አርጋው ተረክበዋል ፡፡

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሃብታሙ ተገኘ የተከሰተውን አስከፊ ወረርሽኝ ለመከላከል በሚደረገው ሂደት ባለሃብቶቹ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

የብሔራዊ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ እና የንግድ እና ኢንደስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋናው አርጋው በበኩላቸው ባለሃብቶቹ ሀገራዊ ሃላፊነታቸውን በመወጣት ለወገኖቻቸው ላሳዩት አለኝታነት ያላቻውን ምስጋና እና አድናቆት ገልጸዋል::

የገንዘብ ድጋፉን ያበረከቱት ድርጅቶች እና የገንዘብ መጠን
ተ.ቁ የተቋራጭ ስም የገንዘብ መጠን

1. ሰንሻይን ኮንስትራክሽን - 2 ሚሊዮን ብር
2. አለማየሁ ከተማ - 2 ሚሊዮን ብር
3. ኤን ኬ ኤች ኮንስትራክሽን - 2 ሚሊዮን ብር
4. ተክለብርሃን አምባዪ ኮንስትራክሽን - 2 ሚሊዮን ብር
5. ዮቴክ ኮንስትራክሽን - 2 ሚሊዮን ብር
6. ራማ ኮንስትራክሽን - 1 ሚሊዮን ብር
7. ሜልኮን ኮንስትራክሽን -1 ሚሊዮን ብር
8. እንይ ኮንስትራክሽ -1 ሚሊዮን ብር
9. ማርካን ኮንስትራክሽን - 1 ሚሊዮን ብር
10. ፓወርኮን ኮንስትራክሽን -500 ሺብር
11. ዮንአብ ኮንስትራክሽን - 500 ሺ ብር

12. ራባ እና ሶን ኃ /የተ/ የግ/ማ 300 ሺብር

ድምር 15 ሚሊዮን 300 ሺ ብር

Via:- ERA
@Yenetube @Fikerassefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕከት.
@YeneTube @Fikerassefa
የኢሰመኮ ጋዜጣዊ መግለጫ

- የመዘዋወር ነጻነትን በተመጣጣኝ መንገድ ብቻ ስለመገደብ

- በመዘዋወር ነጻነትና የትራንስፖርት ገደብ ላይ በቅድሚያ ማስጠንቀቂያ መስጠት ያስፈልጋል።

https://bit.ly/34Lxrxf
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ለተለያዩ አካባቢ ወጣቶች የበዓል ስጦታ አበረከቱ።

ለተለያዩ አካባቢዎች 40 በሬዎች የተከፋፈሉ ሲሆን ስጦታዎቹ ከባለሀብቶች የተሰባሰቡ ናቸው። ወጣቶቹም ስጦታውን በመቀበል ለየአካባቢው አቅመ ደካማ ነዋሪዎች የሚያከፋፍሉ ይሆናል።ኢንጂነር ታከለ በከተማዋ በተለያየ አካባቢ ለሚገኙ ወጣቶች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ወጣቶቹ ለከተማ አስተዳደሩ ጥሪ የሰጡትን ፈጣን ምላሽም አድንቀዋል።በየአካባቢዎቹ የሚገኙ አቅመ ደካማዎችን በመደገፍ ወጣቶቹ እያሳዩ ያሉት ተነሳሽነት አርአያ የሚሆን ነው ብለዋል።

Via Mayor office
@YeneTube @FikerAssefa
የፌዴራል የመንግስት ሰራተኞች የስራ መግቢያና መውጫ ሰዓት ማስተካከያ ተደረገበት!

በኮሮና ቫይረስ መከላከል ብሔራዊ ግብረ-ሃይል ውሳኔ መሰረት የፌዴራል የመንግስት ሰራተኞች የስራ መግቢያና መውጫ ሰዓት መሻሻሉን የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር በዛብህ ገብረየስ ለኢዜአ እንዳሉት በኮሮና ቫይረስ መከላከል ብሔራዊ ግብረ-ሃይል ውሳኔ መሰረት የፌዴራል የመንግስት ሰራተኞች የስራ መግቢያ ሰዓት ጠዋት 1 ሰዓት ከ30 የስራ መውጫ ሰዓት ደግሞ ከቀኑ 9 ሰዓት ከ30 እንዲሆን ተወስኗል።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ለፋሲካ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 10፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ለፋሲካ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልካም ምኞት መልዕክታቸው “ትንሳኤን ስናስብ ምን ጊዜም በህሊናችን የሚመጣ አንድ ነገር አለ፤ ከህማማት በኋላ ደስታ ከሞት በኋላ ትንሳኤ፤ ከጨለማ በኋላ ብርሃን እንደሚመጣ እናውቃለን” ብለዋል።

ይህ ያለንበት ወቅት የተለየ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ፥ ኮሮና ቫይረስ ዓለምን ያለጦር መሳሪያ እንደወረረ እና ሀያላንን ለማንቀጥቀጥ ጊዜ እንዳልፈጀበት ነው ያነሱት።

ይህ ቫይረስ በሀገሪቱ ብዙዎችን መያዙን፣ የሰው ህይወት መቅጠፉን እና በኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ሃይማኖታዊ ህይወታችን ላይ ተፅእኖ ማሳደሩን፤ የወረርሽኙ ወደፊት ምን ዓይነት ፈተና እና ችግር ይከተለን በሚል ስጋት የምናስታግደው የስነ ልቦና ተፅእኖም ቀላል አለመሆኑን ተናግረዋል።

“ከገጠመን የበለጠ ፈተና እንዳይገጥመን እንደ መንግስትና እንደ ህዝብ እስከምን ድረስ ራሳችንን ማዘጋጀት እንዳለብን ሁላችንም እንደ አንድ ልብ መክረን እና እጅ ለእጅ ተያይዘን ለተግባራዊነቱ መትጋት ይገባናል” ብለዋል።

ቫይረሱ ለሚያስከትለው ሀገራዊ ፈተናና ችግር በሚገባ ከተዘጋጀን ያለከባድ ችግር ልንወጣው እንችላለንም ነው ያሉት፥ ፈተናውን የምናልፈው በዝግጅታችን መጠንና ለተግባራዊነቱ ባለን ፅናት ልክ መሆኑን በመጠቆም።

ያለጥርጥር ይህ የወረርሽኝ ጊዜ ያልፋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ማድረግ የሚገባውን ነገር ሁሉ ካደረግን የፈተናውን ጊዜ እናሳጥራለን ብለዋል።

“ከላይ እስከታች በተሰማራንበት መስክ፣ በተሰጠን ሀላፊነት እና ባገኘነው እውቀት የሚገባንን ከሰራን የችግሩ ጊዜ የከፋ ጉዳት ሳያመጣ በአጭሩ ያልፋል፤ የኢትዮጵያ የትንሳኤ ዘመንም ይረዝማል” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ለህክምና ባለሙያዎች ጥበብን፣ ግንባር ቀደም ሆነው ለተሰለፉ ጀግኖች ሀይልና ብርታትን፣ ትግሉን እያገዙ ላሉ ደጋግ ልቦች በረከትን፣ በቫይረሱ ለተያዙት መዳንን፣ በወረርሽኝ ምክንያት ለተጎዱ ፅናትን እና ለህዝቡ ደግሞ መታዘዝን ተመኝተዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
ሲ.አር.ሲ የተባለ የቻይና አለም አቀፍ የሥራ ተቋራጭ 15ሺ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ለትራንስፖርት ዘርፍ ድጋፍ አደረገ፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
ሰለ ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች ተጨማሪ ማብራሪያ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈፀም በወጣው የትራንስፖርት ዘርፍ አፈፃጸም መመሪያ መሰረት የቤት ተሽከርካሪዎች (ኮድ-2) ፈረቃ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ መተግበር ይጀምራል።

በዚህም መሰረት የሰሌዳ ቁጥራቸው መጨረሻ ጎዶሎ የሆነ ተሽከርካሪዎች መንቀሳቀስ የሚችሉት ሰኞ፣ ረቡዕ እና አርብ ሲሆን ፥ የሰሌዳቸው የመጨረሻ ቁጥር ሙሉ ወይም ዜሮ የሆኑ ተሽከርካሪዎች ደግሞ መንቀሳቀስ የሚችሉት ማክሰኞ፣ ሀሙስ እና ቅዳሜ ብቻ ነው።

እሁድ እለት ደግሞ ሁሉም ተሸከርካሪዎች መንቀሳቀስ ተፈቅዶላቸዋል።

አንዳንድ ግለሰቦች ከስራቸዉ ፀባይ አንፃር በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ፣ በደንቡ ወይም በአፈፃፀም መመሪያዉ የተገለፁት ጉዳዮች ላይ በቀጥታ የሚሳተፋ ሰዎች ከባለስልጣኑ በሚሰጣቸዉ ልዩ የይለፍ ፈቃድ ብቻ እንዲንቀሳቀሱ ይደረጋል።

Via:- ትራንስፖርት ሚኒስቴር
@Yenetube @Fikerassefa
በዩናይትድ ስቴትስ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 710,331 ደርሷል። ትናንት ብቻ 30,579 ሰዎች የተያዙ ሲሆን 2,618 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል። እስከዛሬ የሞቱትም ቁጥር 37,150 ሲሆን 42,154ቱ አገግመዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር በዛሬው እለት ድጋፍ ለሚሹ ለ949 የኅብረተሰብ ክፍሎች የትንሳኤ በዓል መዋያ ድጋፍ አበረከተ።

ሚያዝያ 10/2012 ዓ.ም በዛሬው ቀን የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ከኒቲባ አቶ ሰብስቤ ቡናቤና የከተማው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሻምበል ሸዋ በከተማው በሚገኙ በቀድሞው 11ዱም ቄበሌያት በመዘዋወር ድጋፍ ለሚሹ ለ949 የኅብረተሰብ ክፍሎች የትንሳኤ በዓል መዋያ የፉርኖ ዱቄት፣የሳሙናና ፓስታ ድጋፍ አበረከቱ።የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እና መቆጣጠር በተቋቋመው የሃብት አሰባሰብ ግብረ ኃይል ከተሰበሰበው የተወሰደ 237 ኩንታል ፉርኖ ዱቄት ፣ 95 ካርቶን ፓስታና 950 ሳሙና ድጋፍ ለሚሹ ለ949 የማኅበረሰብ ክፍሎች ለትንሳኤ በዓል መዋያ የሚሆን ለእያንዳንዳቸው 25 ኪሎ ፉርኖ ዱቄት፤2 ፓስታና፣ ሳሙና ድጋፍ አድርገዋል።

Via Arbaminch city Admin
@YeneTube @FikerAssefa
የማላዊ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሀገሪቱ መንግስት ያወጀውን የ21 ቀን የእንቅስቃሴ ገደብ ውድቅ አርጓል።

Via CGTN
@YeneTube @FikerAssefa
#105
በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 105 ደረሰ!

ባለፉት 24 ሰዓታት ምርመራ ከተደረገላቸው 659 ሰዎች መካከል 9 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር ገለጸ። በዚህም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር 105 ደርሷል።

@YeneTube @FikerAssefa