YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የመጀመሪያዋ ሰለባ የሆኑት የ60 ዓመት ኢትዮጵያዊት እናት የቀብር ስነ ስርዓት በድጋሚ ተከናወነ።

የመጀመሪያው የቀብር ስነ ስርዓት ያለ ሟች ቤተሰብ እውቅና እንዲከናወን አድርገዋል የተባሉ አንድ የአዲስ አበባ ከተማ የየካ ክፍለ ከተማ ኃላፊም ከስራቸው መባረራቸውን ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። 

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ባለፈው እሁድ መጋቢት 27፤ 2012 ህይወታቸው ያለፈው ኢትዮጵያዊት እናት የመጀመሪያ የቀብር ስነ ስርዓት የተፈጸመው የዕለቱ ዕለት፣ ምሽት ሶስት ሰዓት ገደማ፣ በቀጨኔ የመቃብር ስፍራ ነበር።

በቀብር ስነ ስርዓቱ ላይ እንዲገኙ ያልተደረጉት ቤተሰቦቻቸው ባቀረቡት ቅሬታ የሟች አስክሬን በነጋታው 10 ሰዓት ገደማ ከተቀበረበት ተቆፍሮ ወጥቶ፤ ከሁለት ሰዓት በኋላ በለቡ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በድጋሚ መቀበሩን ጉዳዩን በቅርበት የተከታተሉ የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ምንጮች ገልጸዋል። 

ተጨማሪ ለማንበብ ⬇️

https://bit.ly/2yK5KsI
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን 50 በመቶ የኪራይ ቅናሽ አደረገ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን 18ሺህ 153 የንግድ እና የመኖሪያ ቤቶች ላይ ከሚያዚያ ወር ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የ50 በመቶ የኪራይ ቅናሽ ማድረጉን አስታወቀ።

ቅናሹ የሚመለከታቸው ቤቶች በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ከተሞች የሚገኙ ሲሆን የተደረገው የኪራይ ቅናሽ የኮርፖሬሽኑ ገቢ ከ120 ሚሊዮን ወደ 60 ሚሊዮን ዝቅ እንደሚያደርገውም ነው የተገለፀው።

Via:- EBC
@Yenetube @Fikerassefa
በድሬዳዋ ላላቹ ለመላው የታክሲ አሽከርካሪዎች የተጀመረውን የትራንስፓርት አገልግሎት የበለጠ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እየተደረገ ያለው ጥረት የበለጠ ስኬታማ ለማድረግ ሁሉም የታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ አሽከርካሪዎች አገልግሎት ሲሰጡ የንፅህና መጠበቂያ ማሟላት እንዲሁም አፀባራቂ መልበስ እና በተሽከርካሪው ላይ ስለመከላከል መልዕክት በመለጠፍ ሃላፊነታችሁን እንድትወጡ ተብላቿል፡፡

እንዲሁም በኮሮና መከላከል ግብረ ሃይል ውሣኔ መሠረት የትራንስፓርት እንቅስቃሴው እስከ ምሽቱ 3፡00 ሰዓት ብቻ መሆኑን የድሬዳዋ ፖሊስ አሳውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ምክር ቤቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በአብላጫ ድምፅ አፀደቀ!

የሕህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው የአስቸኳይ ስብሰባ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ረቂቅ በአንድ ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ አፀደቀ።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ28 ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀት በሙሉ ድምጽ አጸደቀ።

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 2ኛ ልዩ ስብሰባው የ2012 በጀት ዓመት የፌደራል መንግስት የተጨማሪ በጀት እና የወጪ አሸፋፈን ማስተካከያ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል።

ምክር ቤቱ ያፀደቀው የገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ያቀረቡትን የ28 ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀት የውሳኔ ሃሳብ መሆኑን የኢቢሲ ዘገባ ያመላክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
#65
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 9 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው!

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 442 ሰዎች መካከል ዘጠኙ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ይህንንም ተከትሎ በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 65 ከፍ ብሏል።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠው ዘጠኙም ግለሰቦች የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው።

➡️ከግለሰቦቹ መካከል #ሰባቱ ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ፤ አንድ #ኤርትራዊ ቀሪዋ ደግሞ የ #ህንድ ዜግነት ያላት ናት።

➡️አራቱ ኢትዮጵያዊያን ከዱባይ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በለይቶ ማቆያ ክትትል ሲያደርጉ የነበሩ መሆኑንም ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

➡️ሁለቱ የቱርክ፤ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት ደግሞ የእንግሊዝ አገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆን፤ ሁሉም በለይቶ ማቆያ ውስጥ ክትትል ሲያደርጉ መቆየታቸውን አውስተዋል።

➡️የ20 ዓመቷ ህንዳዊት የአሜሪካ እንዲሁም የ40 ዓመቱ ኤርትራዊ ደግሞ የዱባይ ጉዞ ታሪክ ያላት ናቸው።

➡️በጽኑ ህሙማን ክፍል ከሚገኙት ሁለት ግለሰቦች መካከል አንዱ የጤና መሻሻል በማሳየቱ ከክፍሉ መውጣቱንም ዶክተር ሊያ ተናግረዋል።

➡️እስካሁን ባለው ሂደትም በኢትዮጵያ ለሶስት ሺህ 232 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ መደረጉን ጠቁመው፤ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል 57ቱ የህክምና ክትትል ይገኛሉ።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የወጣውን መመርያ የተላለፉ 67 የታክሲ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ፡፡

በከተማዋ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የወጣውን መመርያ የተላለፉ 67 የታክሲ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ወቅታዊውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል በከተማ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ ተሽከርካሪዎች የሰዎችን ንክኪ ለመቀነስ የመጫን አቅማቸውን በግማሽ ቀንሰው ተሳፋሪው እጥፍ እንዲከፍል መመሪያው ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፡፡

የታክሲ አሽከርካሪዎቹ ይፋ ከተደረገው ታሪፍ ውጪ ተገልጋዮችን ሲያስከፍሉ የተገኙ ስልሳ ሰባት የታክሲ አሽከርካሪዎች በብር አምስት ሺ መቀጣታቸውን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ኮማንደር አህመድ መሀመድ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።ከገንዘቡ ቅጣት በተጨማሪ እንደ ወንጀሉ አፈፃፀም እየታየ መንጃ ፈቃድ የማገድና በህግ የመጠየቅ ስራዎች ይሰራል ብለዋል፡፡

Via Addis Ababa PS
@YeneTube @FikerAssefa
ሞሃ የለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ አክሲዮን ማህበር ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የግማሽ ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡ ሞሃ የለስላሳ መጠጦች ለመርጃ ማዕከሉ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችንም ሰጥቷል፡፡

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ልዩ ስብሰባ ለኮቪድ -19 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አባላትን ለመሰየም የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ በአብላጫ ድምፅ አጸደቀ።

ምክር ቤቱ በልዩ ስብሰባው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትና የጉዳትን መጠን ተከታትሎ በየጊዜው ለምክር ቤቱ ሪፖርት የሚያቀርብ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አባላትን የሰየመው ከምክርቤቱ አባላት መካከል ነው።

በዚህ መሰረት፡
1ኛ - አቶ ጴጥሮስ ወልደሰንበት --- የቦርዱ ሰብሳቢ
2ኛ - አቶ ተስፋዬ ዳባ ------------የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ
3ኛ- ወይዘሮ ፋንታዬ ወንድም -----የቦርድ አባል
4ኛ- አቶ ሽኩሪ መሀዲን-----------የቦርዱ አባል
5ኛ- ዶክተር ብሩክ ላጲሶ ----------የቦርድ አባል
6ኛ- ወይዘሮ ሞሚና መሀመድ------ የቦርድ አባል
7ኛ - አቶ በሻላ ገመቹ ------------- መርማሪ ቦርድ አባላት ሆነው ተሰይመዋል።

የአባላቱ ሹመትም በምክር ቤቱ በ12 ተቃውሞ በ5 ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል።የመርማሪ ቦርድ አባላቱም በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ መፈፀማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ባዮ-ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ጋር በመተባበር የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ በቅርቡ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ።

Via ELU
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የክፍያ ስርዓቱን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል አደረገ!

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዚህ በፊት በማዕከላት ብቻ ይሰበስብ የነበረውን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩልም ሊሰበሰብ እንደሆነ ዛሬ ሚያዝያ 02 ቀን 2012 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡ጋዜጣዊ መግለጫውን የሰጡት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራ ተሊላ፣ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ደመቀ ሮቢና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ ዮሐንስ ሚሊዬን ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራ ተሊላ በጋዜጣዊ መግለጫው ወቅት ተቋሙ ከድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞቹ የሚሰበስበውን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል ለማድረግ የዘረጋው ዘመናዊ አሰራር ወይም የኦንላይን ዲጅታል የክፍያ ስርዓት በአሁን ወቅት አጠናቆ ከመጪው ሳምንት ረቡዕ ሚያዝያ 07 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ብለዋል፡፡

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
ሀዋሳ የሚገኘው ሮሪ ሆቴል ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ሆቴሉን ለህክምና ባለሙያዎች ታማሚዎችን ለመርዳት የሚያደርጉት ጥረት አጋዥ ለመሆን በሮሪ ሆቴል የመኝታ የቁርስ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ገልጿል ።

@Yenetube @Fikerassefa
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አሮጌ ጫማ ለማደስ በተከራዩት ቤት ውስጥ መትረዬስና ክላሽን-ኮቭ ጠመንጃ ሸሽገው የተገኙ ሁለት ተጠርጣሪዎች ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በጥናት ላይ ተመስርቶ ከፍርድ ቤት የመበርበሪያ ትእዛዝ በማውጣት መጋቢት 22 ቀን 2012 ዓ/ም በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው ሳጥን ተራ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በአንድ የአሮጌ ጫማ ማደሻ ቤት ላይ ባደረገው ፍተሻ ሰባት ክላሽን ኮቭ እና አንድ መትረዬስ ጠመንጃ ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር ይዞ ምርመራ እያጠራ መሆኑን የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዲቪዚዮን ኃላፊ ኮማንደር ጌታነህ በቀለ ገልፀዋል፡፡

Via Addis Ababa Police Commission
@YeneTube @FikerAssefa
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ከእጅ ንኪኪ ነጻ የሆነ መታጠቢያ ማሽን ሰርቷል።

ይህ ማሽን በእጅ መንካካት ሳያስፈልግ በእግር ብቻ በመጫን ዉሃ እና የእጅ ማጽጃ ሳሙና በመጠቀም ንጽህናን መጠበቅ የሚያስችል ነው።

ምንጭ: ዩንቨርስቲው
@YeneTube @FikerAssefa
አምቦውሃ ካምፓኒ ሳኒታይዘር ማምረት የጀመረ ሲሆን ምርቶቹ ተጋላጭ ለሆኑ አካባቢዎች በነፃ እንደሚታደል ታውቋል።

ምንጭ: Samuel Getachew
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ የታክሲ ትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ተደረገ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት የታክሲ ትራንስፖርት ታሪፍ ማስተካከያ ማድረጉን አስታወቀ። በተስተካከለው ታሪፍ መሰረት ዝቅተኛው 3 ብር ሲሆን ከፍተኛው ደግሞ 12 ብር ከ50 ሣንቲም ሆኗል።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ኮማንደር አህመድ መሐመድ በሰጡት መግለጫ ወረርሽኙን ለመግታት የወጣው መመሪያ በዋናነት በተሽከሪካሪዎች የመጫን አቅምና በታሪፍ ላይ ያተኩራል።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
በባሕር ዳር የሚገኘው የአማራ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስትዩት ነገ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማድረግ ይጀምራል፡፡

ከባለፈው ሰኞ ጀምሮ በሙከራ ሂደት ላይ የነበረው ቤተ ሙከራው ከነገ ጀምሮ መመርመር እንደሚችል የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ማረጋገጫ እንደሰጠው ታውቋል፡፡ቤተ ሙከራው አሁን ባለው አቅም በቀን እስከ 100 ናሙናዎችን መመርመር ይችላል፤ ነገር ግን የሰው ኃይል አቅሙ ካደገ ከዚያም በላይ መመርመር እንደሚችል ተመላክቷል፡፡በቀጣይ ደግሞ ጎንደር፣ ደሴና ደብረ ብርሃን ምርመራው እንደሚጀመር ታውቋል፡፡

ምንጭ: አብመድ
@YeneTube @FikerAssefa
#3

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ሟቾች ቁጥር 3 መድረሱን ዶክተር ሊያ ታደሰ በፌስቡክ ገፃቸው አስታውቀዋል!!

@Yenetube @FikerAssefa