YeneTube
119K subscribers
31.4K photos
484 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የአማራ ክልል መንግሥት 7 ሺህ 650 ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ ወሰነ፡፡

የአማራ ክልል መንግሥት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በክልሉ በሚገኙ ማረሚያ ቤቶች ያሉ 7 ሺህ 650 ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱና የታራሚዎች ቁጥር እንዲቃለል የማድረግ ርምጃ ወሰደ፡፡ የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መሥሪያ ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ዓለምሸት ምሕረቴ እንዳስታወቁት በየደረጃው ከሚገኙ ማረሚያ ቤቶች በጥንቃቄ ተለይተው እና በይቅርታ ቦርድ ተመርምረው የቀረቡ ታራሚዎች የይቅርታው ተጠቃሚ ተደርገው ነው የታራሚዎችን ቁጥር በመቀነስ የኮሮና ወረርሽኝን የመከላከል ርምጃው የተወሰደው፡፡

በይቅርታ እንደፊቱ የሚደረጉ ታራሚዎችን ዝርዝር በተመለከተም ከሰው መግደል ውጭ በሆኑ ወንጀሎች ተፈርዶባቸው በመታረም ላይ የሚገኙ 12 የሚያጠቡ እናቶችና ሁለት ሕጻናትን ይዞ በመታረም ላይ የሚገኝ አንድ ወንድ ታራሚ፣ በአመክሮ የመፈቻ ጊዜያቸው እስከ አንድ ዓመት የቀራቸው 950 ታራሚዎች እና ቀላል ወንጀል ፈጽመው እስከ አንድ ዓመት የእስር ጊዜ የቀራቸው 6684 ታራሚዎች፣ ከሰው መግደል ውጭ በሆኑ ወንጀሎች ተፈርዶባቸው በመታረም ላይ የሚገኙ ሦስት የውጭ ዜጋ ታራሚዎች እንደሚገኙበት አቶ ዓለምሸት አስታውቀዋል፡፡በይቅርታ ከሚፈቱት ታራሚዎች መካከል 7527 ወንዶች ሲሆኑ ቀሪዎቹ 123 ደግሞ ሴቶች መሆናቸውን አቶ ዓለምሸት አመላክተዋል፡፡

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
የደሴ ከተማ አስተዳድር ከነገ ጀምሮ በከተማው የሚገኙ የገቢያ ቦታዎች እንደሚዘጉ አስታወቀ። ወደ ከተማው ጫት ማስገባት እንደማይቻል እንዲሁም የባለ 3 እግርና የጋሪ ትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚቋረጥ ገልጿል።

Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
#NewsAlert

የ2012 ምርጫ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት በወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እንደማይካሄድ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የምርጫ 2012 ኦፕሬሽን እቅድ እና የጊዜ ሰሌዳ ላይ የፈጠረውን ችግር ገምግሞ ያሳለፈውን ውሳኔ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

ቦርዱ በተፈጠረው ሁኔታ የተነሳ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ምርጫውን ማካሄድ የማይቻለው መሆኑን በመረዳት ያወጣውን የጊዜ ሰሌዳ በመሰረዝ በሰሌዳው መሰረት መከናወን ያለባቸው ተግባራት ለጊዜው እንዲቆሙ መወሰኑን አስታውቋል።

የወረርሽኙ ሥጋት ተወግዶ ሁኔታዎች ሲመቻቹ እንደገና ግምገማ በማድረግ አዲስ የምርጫ ኦፕሬሽን እቅድና ሰሌዳ በማውጣት እንቅስቀሴውን የሚያስጀምር እንደሚሆንም ነው ያስታወቀው።

ቦርዱ ባደረጋቸው ምክክሮችና የዳሰሳ ጥናት ላይ በግልጽ የተለዩ፣ በኮቪድ 19 የማይስተጓጎሉ፣ የቦርዱን የምርጫ አፈጻጸም ዝግጁነት የሚጨምሩ፣ ሁኔታው ተቀይሮ ተቋሙ ወደ መደበኛ ተግባሩ ሲመለስ በተገቢው ሁኔታ ምርጫን ለማስፈጸም የሚያሥችል ሁኔታን የሚፈጥሩ ተግባራትን እያከናወነ መቆየት እንዳለበት ወስኗል፡፡

በህገ መንግስቱ በተቀመጠው መሰረትም በስራ ላይ የሚገኘው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የስልጣን ጊዜው ከሚያበቃበት አንድ ወር አስቀድሞ ቦርዱ አጠቃላይ ምርጫውን ማድረግ የማይችል መሆኑን ምክር ቤቱ ተገንዝቦ፣ ከዚህ አንጻር የሚሰጠው ውሳኔ ቢኖር ለመነሻነት ያገለግለው ዘንድ ይህ ውሳኔ እንዲሁም ቦርዱ ያደረገው የዳሰሳ ጥናት ሰነድ ለህዝብ ተወካዮች እንዲተላለፍለት ምርጫ ቦርዱ ወስኗል፡፡

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዙሪያ አለም አቀፍ መረጃ!

➡️ በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የሞቱት ሰዎች ቁጥር(3,412) በቻይና ከሞቱት(3,305) በልጧል።

➡️ በ24 ሰዓት ውስጥ በብሪታኒያ 3009 አዲስ ተጠቂዎች የተገኙ ሲሆን 374 ሰዎች ሞተዋል።

➡️ በተመሳሳይ በጣሊያን 4,053 አዲስ ተጠቂዎች ሲመዘገቡ 837 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል።

➡️ በአለም አቀፍ ደረጃ የተጠቁት ሰዎች ቁጥር ከ800,000 ያለፈ ሲሆን የሟቾችም አሃዝ ቁጥር ከ40,000 በልጧል።ከሟቾቹ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ከጣሊያንና ከስፔን ናቸው።

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 26 ደርሷል፡፡ ዛሬ በተደረገው ተጨማሪ የላብራቶሪ ምርምራ ቫይረሱ የትገኘበት የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ ሲሆን የአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ አገልግሎት ሳይጀመር በፊት መጋቢት 9 ከአውስትራሊያ ወደሀገር ውስጥ የገባ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ እንደሆን ጤና ሚኒስቴር ይፋ እድርጓል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዙሪያ የአፍሪካ መረጃ!

➡️48 የእፍሪካ ህብረት አባላገራት ቫይረሱን ሪፖርት አድርገዋል።

➡️5,414 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል።

➡️172 ሰዎች ተይዘው ሞተዋል።

➡️387 ሰዎች አገግመዋል።

ምንጭ:CDC Africa
@YeneTube
YeneTube
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአማራ፣ ደቡብ እና ኦሮሚያ ክልሎች ለእያንዳንዳቸው 15 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ድጋፍ እንደሚያደርግ የከተማው ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ አስታውቀዋል። የከተማ አስተዳደሩ ለክልሎቹ የሚያደርገው 45 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ድጋፍ ከከተማው በጀት ላይ የሚበረከት እንደሆነም ተገልጿል። የከተማ አስተዳደሩ የኮሮናን ወረርሽኝን አስመልክቶ የሚደረጉ ድጋፎችን ለመረከብ የሚሆኑ…
የአዲስ አበባ ከተማ ም/ል ከንቲባ ታከለ ኡማ የተወሰኑ ወገኖች ዛሬ የከተማ መስተዳድሩ ለክልሎች ያደረገው የገንዘብ ድጋፍ ለምን ለሦስት ክልል ብቻ ተሰጠ የሚል ተገቢ ጥያቄዎችን እያነሱት እንደሆነ መገንዘባቸውን ጠቅሰው፣ ስለሆነም የተቀሩት ክልሎችም በተያዘላቸው ጊዜ ገደብ ይደርሳቸዋል ብለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በአራቱ ከተሞች የየትኛዎቹ ተቋማት ሰራተኞች እና የበጎ አድራጊ አገልግሎት ሰጭዎች በልዩ ፈቃድ እንዲንቀሳቀሱ ተወሰነ?

የአማራ ክልል የኮረና ወረርሽኝ መከላከልና መቆጣጠር ኮማንድ ፖስት በዛሬው እለት ያሳለፍቸውን አዳዲስ ውሣኔዎች አስመልክቶ የተሰጡ ተጨማሪ ማብራሪያዎች፡-

የባህርዳር፣ እንጅባራ፣ አዲስ ቅዳምና ቲሊሊ ከተሞች የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመከላከልና ለመቆጣጠር የክልሉ ኮማንድ ፓስት ባወጣው መግለጫ ላይ የተሰጠ ተጨማሪ ማብራሪያ፦

ቀደም ብሎ በተሰጠው መግለጫ ላይ እንደተጠቀሰው የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የኮማንድ ፓስት እና የግብረ ሐይል አስፈፃሚና ልዩ ልዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሰራተኞች እና የበጎ አድራጊ አገልግሎት ሰጭዎች በልዩ ፈቃድ እንዲንቀሳቀሱ ተወስኗል።
በዚህም መሰረት፦

1.የመንግስትና የግል ጤና ተቋማት ሰራተኞች እንዲሁም የጤና ጥበቃ ቢሮ ፤ የመምሪያና ጽሕፈት ቤት ሰራተኞች በተቋማቸው መታወቂያ፣
2.የጸጥታ ሃይሎች ያለምንም የፈቃድ ወረቀት፣
3. የክልል ዞን እና ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት እና መምሪያዎች በተቋማቸው መታወቂያ፣
4.የአማራ ብዙሐን መገናኛ ድርጅት እና ሌሎች የሚዲያ አባላት በተቋማቸው መታወቂያ ሥራቸውን እንዲያከውኑ፣
እንዲሁም፦

በተቋማት ኃላፊዎች ውሳኔ መሠረት ልዩ የመንቀሳቀሻ ፈቃድ የሚሰጣቸው ደግሞ የሚከተሉት ናቸው፦
1.የውሃ መስኖና ኢነርጂ ቢሮ፣ መምሪያና ጽህፈት ቤት እንዲሁም የከተሞች የውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ፣
2.ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ፣ መምሪያ እና ጽህፈት ቤቶች ፣
3. የመብራት ሐይል፣ ቴሌኮሙዩኒኬሽን፣
4. መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ መምሪያ እና ጽህፈት ቤቶች ፣
5. የምግብ ዋስትናና አደጋ መከላከል ተቋም
6. እሳት አደጋ መከላከል እና ጽዳትና ውበት፣
7.የፋብሪካ ሰራተኞች እና ቫይረሱን ለመከላከል የሚውል ግብአት የሚያቀርቡ ተቋማት
8.ሃይማኖታዊ ክዋኔን የሚፈጽሙ አባቶች፣
9.የባሕር ዳር ከተማ የአባይ ድልድይ ፕሮጀክት ሰራተኞች፣
10. የግብርና ቢሮና በስሩ የሚገኙ ተቋማት
11. የአጋር አካላት ድንገተኛ/ኢመርጀንሲ/ አመራርና ሰራተኞች
12.የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት እና ጠቅላይ አቃቢ ህግ ናቸው።
13.ሌሎች አስገዳጅ ማህበራዊ ክስተቶችና አገልግሎቶች እንደአስፈላጊነቱ በክልሉ የኮሮና ቫይረስ መከላከልና መቆጣጠር ጥምር ግብረ ሐይል እውቅና መሠረት ይስተናገዳሉ።
እነዚህን ጉዳዮች ተፈጻሚ ለማድረግ:-

1. ስራቸውን እንዲከውኑ የተፈቀደላቸው ሰራተኞች የመንቀሳቀሻ ልዩ ባጅ ይሰጣቸዋል።
2. በተመሣሣይ እንዲንቀሳቀሱ ለተፈቀደላቸው ተሽከርካሪዎች የመንቀሳቀሻ ልዩ ፈቃድ የሚሰጣቸው ይሆናል።
የፋብሪካና የባሕር ዳር አባይ ድልድይ ሰራተኞች በተቋማቸው መታወቂያ መደበኛ ስራቸውን እንዲያከናውኑ ተፈቅዷል።
በተባበረ ጥረት የገጠመንን ችግር እናልፈዋለን!!!
የአማራ ክልል የኮረና ወረርሽን መከላከልና መቆጣጠር ኮማንድ ፖስት
መጋቢት 22/2ዐ12 ዓ.ም
ባሕር ዳር

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
ትራምፕ አሜሪካዊያን ከፊታቸው ለተደቀነው አስከፊ ጊዜ እራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ተናገሩ፡፡

ሁኔታው እጅግ አሳስቦኛል ያሉት ትራምፕ መጪዎቹ ቀናቶች በስቃይ የተሞሉ መሆናቸውን አሳስበዋል፡፡በቀጣዮቹ ሳምንታት ውስጥ 2 መቶ ሺህ አሜሪካዊያንን ህይወት ሊያሳጣ እንደሚችል ዎርስንኢንግ የተሰኘ ተቋም ግምቱን አስቀምጧል፡፡ይህ በጣም አሰቃቂ እና በጣም ከባድ ህመም ለመግታትና እያንዳንዱ አሜሪካዊ ወደፊት ለሚጠብቀው አስቸጋሪ ቀን ዝግጁ እንዲሆን እፈልጋለሁ ብለዋል ማለታቸውን ሲ ኤን ኤን ዘግቧል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ኮቪድ-19ን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት በበጎ ፈቃደኝነት መሳተፍ ለሚፈልጉ የጤና ባለሙያዎች ከሌላ ቦታ መጥተው ለ14 ቀናት በለይቶ ማቆያ ለሚገኙ ሰዎችን የማማከር አገልግሎት ለመስጠት የምትፈልጉ የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ፎርሙን በመሙላት መመዝገብ ትችላላችሁ። #Share በማድረግ ለሌሎችም ብታጋሩት መልካም ነው።

👇👇👇👇
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSe3r2m90dESOk5qbkem-2XGh8FkC5TWtEMWo1-A39fIqH0YWA/viewform?vc=0&c=0&w=1&fbclid=IwAR1j2oTvzfH4UftYmk4EFzLKH2DuGiB57OZ3dx4eUgl_khygOMPlgpfE_bs
የጋምቤላ ክልል ከዛሬ ጀምሮ ለ14 ቀናት የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲቋረጥ ወሰነ።

የክልሉ መንግስት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በሚል የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።በዚህም መሰረት ወደ ጋምቤላ ከተማ የሚገቡም ሆነ የሚወጡ ከፍተኛና መለስተኛ ሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ከዛሬ መጋቢት 23/2012 ዓ.ም ጀምሮ ለ14 ቀናት እንዲቆም ተወስኗል፡፡

ከክልሉ ርዕሰ ከተማ ወደ ሁሉም የክልሉ ዞንና ወረዳዎች የሚደረጉ የህዝብ ማመላለሻ ከመጫን አቅማቸው 50 በመቶ ቀንሰው ህዝብ እንዲያመላልሱ ውሳኔ ተላልፏል፡፡በክልሉ የሚገኙ ሁሉም የከተማ የህዝብ ማጓጓዣ ባጃጅ፣ ሚኒባስና ሌሎች የህዝብ ማጓጓዣዎች ከዛሬ መጋቢት 23/2012 ዓ/ም ለተከታታይ 14 ቀናት የታገደ ሲሆን የመንግስትም ይሁን የግል ሞተር ሳይክሎች ከአሽከርካሪው በስተቀር ሰው መጫን ተከልክሏል፡፡

ጭፈራ ቤቶች፣ ጫት ቤቶችና ሺሻ ቤቶች የቫይረሱን ተጋላጭነት ስለሚጨምሩ ሙሉ በሙሉ እንዲዘጉ የተወሰነ ሲሆን ወደ ክልሉ ምንም ዓይነት ጫት እንዳይገባ ተወስኗል፡፡በርካታ የመንግስት ሰራተኞች ያለባቸው መስሪያ ቤቶች ሰራተኛን በመቀነስ እንዲሁም በእድሜ የገፉ፣ ህፃናት የሚያጠቡና ነፍሰ ጡር እናቶች ቤታቸው ሆነው ስራ እንዲሰሩ መወሰኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ተናግረዋል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በተቋረጡ በረራዎችና በተፈጠረው የመንገደኞች ቁጥር መቀነስ ክፉኛ ቢጎዳም የካርጎ(የጭነት) አገልግሎት ፍላጎት በከፍተኛ ደረጃ ማደጉን ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ተወልደ ገ/ማሪያም ተናግረዋል።ይህንንም አጋጣሚ በመጠቀም ስራ ፈተው የቆሙትን 60% የሚሆኑትን የመንገደኞች አውሮፕላኖች ጭምር ለማሰማራት እንደታቀደ ጨምረው ገልጸዋል ።

ምንጭ: ፎርቹን
@YeneTube @FikerAssefa
በሸዋሮቢት ከተማ የኮሮና ቫይረስን ስርጭት ለመከላከል ሲባል ከነገ መጋቢት 24/2012ዓ.ም ጀምሮ ባጃጅና ጋሪ አገልግሎት እንዳይሰጡ ተወሰኗል።

-የከተማ ከንቲባው ጽ/ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
በቀን እስከ 400 የኮቪድ 19 መርመራ የሚያደርጉ መሳሪያዎች ወደ ስራ ገቡ!

በአርማዎር ሃንሰን የምርምር ኢንስቲትዮት እና በብሄራዊ የእንስሳት ጤና ምርመራና ጥናት ማዕከል የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተጀመረ።ሁለቱ ተቋማት 4 አርቲ ፒሲአር ማሽኖች በመጠቀም በቀን ውስጥ እስከ 400 የኮሮና ቫይረስ ምርመራ እንደሚያደርጉ ነው የተነገረው።ለዚህም የሚያስፈልጉ 4 አርቲ ፒሲአር ማሽኖች በተቋማቱ ሁለት ሁለት እንደሚገኙ ተነግሯል።

ለቤተ ሙከራ ባለሙያዎች የሚያስፈልጉ ስልጠናዎችን ጨምሮ የምርመራ ቁሳቁሶች እና ሌሎች አስፈላጊ ግብዓቶች መቅረባቸውን ኢትዮጵያ የማህበረሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸው ቶሌራ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።የኮሮና ቫይረስ የምርመራ ሂደትም በብሄራዊ የቤተ ሙከራ አቅም ግንባታ አስተባባሪነት የሚካሄድ ነው ተብሏል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 3 የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ተገኙ።
በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ተጠቂዎች ቁጥር 29 ደርሷል።

የመጀመሪያዋ ታማሚ የ33 አመት ሴት ስትሆን የጉዞ ታሪኳ ብራዚል : ጁቡቲ : ህንድ እና ኮንጎ ብራዛቪል ተጉዛ ነበር።

ሁለተኛ ታማሚ የ26 አመት የስራ ባህሪው ከተለያዩ ተጓዥ መንገደኞች ጋር ግንኙነት አለው።

ሶስተኛው ታማሚ :- 32 አመተ ሲሆን ከዚህ ቀደም በሽታው ከተረጋገጠበት ግለሰብ ጋር ግንኙነት የነበረውና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ሆኖ ክትትል ሲደረግለት ነበር።

@Yenetube @Fikerassefa
የጅማ ከተማ አስተዳደር በከተማው መንገዶች የጸረ ተህዋሲ መድሃኒት ርጭት አካሄደ።

አንድ የኮሮና ተጠቂ የተመዘገበባት ድሬዳዋ ከተማ፣ ነገ በመንገዶቿ ላይ የጸረ ተህዋሲ መድሃኒት ርጭት እንደሚደረግላት የከተማው አስተዳደር አስታውቋል።

@Yenetube @Fikerassefa
የኢትዮዽያ አየር መንገድ የሰው ማጓጓዣ አውሮፕላኖቹን ወንበር በማስወገድ የጭነት (cargo) አገልግሎት እንዲሰጡ ሊያደርግ ነው።

የአዲስ ፎርቹን ዘገባ ያንብቡ⬇️
https://addisfortune.news/ethiopian-airlines-reroutes-to-cargo-flights/
የጤና ሚኒስቴር በስራ ላይ ያልሆኑ የጤና ባለሙያዎች ለበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዲመዘገቡ ጥሪ አቀረበ

ጥሪ የተደረገላቸው:-

- በጤና ሙያ ተመርቀው ወደ ሥራ ላልተሰማሩ

- መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት ለሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች

- በጡረታና በተለያዩ ምክንያቶች ከሥራ ለተገለሉ የጤና ባለሙዎች

- ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን

- ለጤና ተማሪዎች

http://www.moh.gov.et/ejcc/am/node/201