YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
"ከዛሬ ጀምሮ በተወሰነው መሰረት
በተለያየ መንገድ፣ ለተለያየ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ውጭ የነበሩ ወገኖቻችን ወደ ኅብረተሰቡ ከመቀላቀላቸው በፊት ሁለት ሳምንታት ለየት ብለው የሚቆዩባቸውን ስፍራዎች አሰናድተናል።በተለይም ለቆይታ ጊዜው ወጪያቸውን ለመሸፈን ለማይችሉ ዜጎቻችን ሙሉ ወጪያቸውን እኛ እንሸፍናለን።"

-ም/ል ከንቲባ ታከለ ኡማ
@YeneTube @FikerAssefa
ለእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ሠራተኞች በሙሉ

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የCOVID-19 ወረርሽኝ የመከላከል ግብረ-ሃይል ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ያለፉ ቀናት ስራውን ገምግሞ፤ ክፍተቶችን ለመሙላትና የመከላከል ስራውን ውጤታማ ለማድረግ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል፡፡

1ኛ. ከሰኞ መጋቢት 14/2012 ዓ.ም ጀምሮ ተማሪዎች በማንኛውም ጉዳይ ከዩኒቨርሲቲው ግቢ መውጣት አይችሉም፡፡ ውጭ ለሚመገቡ (non-cafe) ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው የምግብ አገልግሎት ይሰጣል፡፡

2ኛ. ከግቢ ውጭ የምትኖሩ ተማሪዎች እስከ ነገ መጋቢት 14/2012 ዓ.ም ከቀኑ 12፡00 ሰዐት ድረስ እንድትገቡ፤ ከተቀመጠው ቀንና ሰዐት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን ዩኒቨርስቲው አያስተናግድም።

3ኛ. ከወረርሽኙ ስራ ጋር የተያያዘ ካልሆነ ከዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች ውጪ ማንኛውም ባለጉዳይ ላልተወሰነ ጊዜ ወደ ዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ መግባት ተከልክሏል፡፡ አስቸኳይ ለሆኑ ጉዳዮች የሚመለከተውን አካል በተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች ማግኘት እንደምትችሉ እንገልጻለን፡፡

4ኛ. ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ሰራተኛ ለውሳኔው ተፈጻሚነት የሚጠበቅበትን አስተዋፅኦ እንዲያደርግ እንዲሁም በግብረ-ሃይሉ የሚሰጡ የመከላከል የጥንቃቄ መልእክቶችን በመተግበር ራሱንና ማህበረሰቡን ከወረርሽኙ እንዲከላከል ጥሪ እናቀርባለን፡፡

-የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የCOVID-19 ወረርሽኝ የመከላከል ግብረ-ሃይል
@YeneTube @FikerAssefa
ባህር ዳር ዩንቨርስቲ በተደጋጋሚ የተላኩ መረጃዎች #ጥንቃቄ ይደረግ:-

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ምንም እንኳን ለማንኛውም ተማሪ ከግቢ መውጣትም ሆነ መግባት ፈፅሞ የተከለከለ ቢሆንም አሁንም ድረስ ተማሪዎች ከግቢ በአጥር እየዘለሉ እየወጡ እና ተመልሰው እየገቡ እንደሚገኙ ተነግሮናል።

ከግቢ እንዳይወጡ ተከልክለው የተቀመጡ ተማሪዎች ላይ በአንዳንድ ተማሪዎች ምክንያት በሽታ ከውጭ ይዘው ዩኒቨርሲቲውን በሙሉ ሊበክሉ ስለሚችል የግቢ አስተዳደር በግቢው ቅጥር ዙርያ ከፍተኛ ቁጥጥር ጥበቃ ከዚህም በተጨማሪ አስተማሪ እርምጃ ሊወስድ ይገባዋል።

ከዚህም ሌላ የግቢው አስተዳደር አሁንም ቢሆን በሩን ዘግቶት በግቢው ውስጥ ያለው ጥንቃቄ ግን በጣም አሳዛኝ ነው።

ለዚህም ዋነኛው ምክንያት በግቢው ውስጥ ያለው የምግብ ቤት እጥረት ሲሆን ተማሪዎች አሁንም ምግብ ለመግዛት ተፋፍገው እየተገፋፉ የሚህገኙበት ሁኔታ መኖሩ ነው።

ተጨማሪ የምግብ ቤት ሊከፈት እንዲሁም ያለው ላውንጅ በስነ ስርዓት አገግሎት ሊሰጥ እንደሚገባ ተማሪዎች ጠቁመዋል።

@Yenetube @FikerAssefa
ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች የ14 ቀናት የለይቶ ማቆያ ግዴታ ዛሬ ይጀመራል

ወደ ኢትዮጵያ በሚመጡ ሁሉም መንገደኞች ላይ ተፈፃሚ የሚሆነው የ14 ቀናት በልዩ ማቆያ ማዕከል የመቆየት ግዴታ ዛሬ እንደሚጀመር የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች በስካይ ላይት እና ጊዮን ሆቴሎች ለ14 ቀናት ተለይተው ይቆያሉ ብሏል።

ቆይታቸውም በራሳቸው ወጪ የሚሸፈን ይሆናል።

ዲፕሎማቶች ደግሞ በኤምባሲዎቻቸው ተለይተው እንደሚቆዩ የጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

የትራንዚት ተጓዦችም እስከ ቀጣዩ ጉዟቸው ድረስ በስካይ ላይት ሆቴል ተለይተው ይቆያሉም ነው የተባለው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ 30 ሀገራት የሚያደርገውን በረራ በጊዜያዊነት ማቆሙ መግለፁ ይታወሳል።

- FBC
@Yenetube @FikerAssefa
በኮሎምቢያ ማረሚያ ቤት ከኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ጋር በተያያዘ በተቀሰቀሰ አመፅ ከ23 ሰዎች በላይ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተሰማ። አመፁ በመዲናዋ ቦጎታ በሚገኝ ትልቅ ማረሚያ ቤት ውስጥ የተነሳ ሲሆን፥ ከሞቱት በተጨማሪ 83 እስረኞች መቁሰላቸውን የሃገሪቱ ፍትህ ሚኒስትር አስታውቀዋል።

-FBC
@Yenetube @Fikerassefa
ዳሽን ባንክ የኮሮና ስርጭት የሚያስከትለውን ጫና ለመቀነስ የክፍያ ማሻሻያዎችን አደረገ!

ዳሽን ባንክ በአሁኑ ወቅት የዓለም ስጋት የሆነው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በአገሪቷ ኢኮኖሚ ላይ የሚያስከትለውን ጫና ለመቀነስ ከዛሬ ጀምሮ የተለያዩ የክፍያ ማሻሻያዎችን እንደሚያደርግ አስታወቀ። የዳሽን ባንክ ማርኬቲንግ እና የደንበኞች አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ አስቻለው ታምሩ እንደገለፁት ባንኩ ቀድሞ ደንበኞች በኤቲኤም ያወጡ የነበረውን የገንዘብ መጠን ከአራት ሺህ ወደ አስር ሺህ ብር ያሳደገ መሆኑን ገልጸዋል።ደንበኞች ማንኛውንም ገንዘብ በሚያወጡበት ጊዜም የነበረው የአገልግሎት ክፍያ ሙሉ በሙሉ ነፃ መደረጉንም ተናግረዋል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
በኮሮና ቫይረስ መከሰት ምክንያት በሸቀጦች ላይ ዋጋ የሚጨምሩ ነጋዴዎችን ንብረት እንደምትወርስ ኤርትራ አስጠነቀቀች፡፡

በኤርትራ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የፍጆታ ዕቃዎች ላይ ‘ምክንያታዊ ያልሆነ’ የዋጋ ጭማሪ መታየቱን የሀገሪቱ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል።በተለይም በአሥመራ ከተማ በእህል፣ ዘይት፣ ስኳርና የጽዳት ዕቃዎች ላይ የዋጋ ጭማሪ መስተዋሉን የገለጸው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ድርጊቱ የሕዝቡን ኑሮ የሚጎዳ በመሆኑ ከባድ ርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉና ዕቃዎችን በሚደብቁ ነጋዴዎች ላይ የንግድ ፍቃድን ከመንጠቅ አንስቶ እስከ ንብረት መውረስ የሚደርስ ርምጃን እንደሚወስድም እንዳስታወቀ ቢቢሲ ዘግቧል።በኤርትራ አንድ ሰው በኮሮና ቫይረስ መያዙ ከሰሞኑ ተረጋግጧል፤ ግለሰቡ ከውጭ የገባ መሆኑም ታውቋል፡፡

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
የዶ/ር ካትሪን ሐምሊን የቀብር ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ይፈጸማል!

የኢትዮጵያ የፌስቱላ ሆስፒታል መሥራች የዶ/ር ካትሪን ሐምሊን የቀብር ሥነ-ሥርዓት በዛሬው ዕለት በጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተክርስቲያን ይፈጸማል። የዶክተር ካትሪን ሐምሊን ቤተሰቦች እና ወዳጅ ዘመዶች በተገኙበት በመኖሪያ ቤታቸው የአስከሬን ሽኝት እየተደረገ ነው።ዶክተር ካትሪን ሐምሊን በ96 ዓመታቸው መጋቢት 9 ቀን 2012 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
ሁሉም የአገሪቷ የየብስ ድንበሮች ከዛሬ ጀምሮ ከመድሀኒትና ከምግብ በስተቀር የሠዎች ዝውውር እንዳይከናወንባቸው ታግዷል!

ሁሉም የአገሪቷ የየብስ ድንበሮች ካዛሬ ጃምሮ ከመድሀኒትና ከምግብ በስተቀር የሠዎች ዝውውር እንዳይከናወንባቸው መታገዱን የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አስታወቁ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት፤ የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመቆጠር ሲባል ድንበርሩን መዝጋት አስፈልጓል።ይሄንንን እንዲያሥፈጽምም ለአገሪቷ የጸጥታ ተቋማት ትእዛዝ ተላልፏል።እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ፤ ድንበሩን ከመዝጋት በተጨማሪ የመንግሥት ተቋማት እንደየሥራ ባህሪያቸው ሠራተኞቻቸው ቤታቸው ሆነው እንዲሠሩ ማመቻቸት እንዳለባቸው ውሣኔ ተላልፏል።ጫት ቤት ሺሻ ቤት እና መጠጥ ቤቶች የተጨናነቀ ሠው እያሥተናገዱ ሥለሆነ ከዛሬ ጀምሮ የጸጥታ ሀይሎች ቁጥጥሩን በማጠናከር እርምጃ እንዲወስዱ ትዛዝ እንደተላለፈላቸው አስታውቀዋል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
ስፔን 4517 አዲስ ተጠቂዎች የተገኘባት ሲሆን 462 አዲስ ሞት ከትናንት ጀምሮ ባለው ጊዜ ተመዝግቧል። እስካሁን በቫይረሱ የተጠቁት ቁጥር 33,089 ሲሆን የሟቾች ቁጥር ደግሞ 2182 ደርሷል ።

@YeneTube @FikerAssefa
ኡጋንዳ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የተጓዙትን እያደነች ነው!

ባሳለፈው ቅዳሜ አንድ ግለሰብ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጉዞ ኡጋንዳ ከደረሰ በኋላ የኮሮናቫይረስ ተጠቂ መሆኑ መረጋገጡን ተከትሎ የአገሪቱ ባለስልጣናት ከግለሰቡ ጋር ንክኪ ነበራቸው ያሏቸውን 84 ተጓዦች በማደን ላይ ናቸው።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኮቪድ19ን ስርጭት ለመግታት የሚደረግ የዝግጅት ሥራን አስመልክቶ፣ ከደህንነት ዘርፍ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።በዓለም-አቀፍ ደረጃ ካለው የመዛመት ፍጥነት አንጻር፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ ቫይረሱ የያዛቸው ሰዎች ቁጥር ከመጨመሩ ጋር ተያይዞ፣ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች የተውጣጡ ንዑሳን ኮሚቴዎች የተመሰረቱ ሲሆን፥ ከእነዚህ አንዱ የደህንነት ንዑስ ኮሚቴው ነው። ውይይት ከተካሄደም በኋላ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሚከተሉት ዐበይት እርምጃዎች የሚተገበሩ መሆኑን ይፋ አድርገዋል፦

1. ከዛሬ መጋቢት 14 ቀን አንስቶ፣ የደህንነት ዘርፉ በቁጥር የበዛ ሰው የሚሳተፍባቸውን ስብሰባዎች የሚያስቆም እና ማሕበራዊ ርቀትን መጠበቅን የሚያስተገብር ይሆናል።

2. የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጨምሮ፣ የመንግሥት ተቋማት ማሕበራዊ ርቀትን ተፈጻሚ ማድረግ እና ስብሰባን ሲያካሂዱ ቫይረሱን የመከላከል ቅድመ ጥንቃቄዎችን ተፈጻሚ ማድረግ አለባቸው።

3. የመንግሥት ተቋማት የተቀጣሪዎቻቸውን ሁኔታ በማጣራት እንደየሁኔታው አንዳንዶች በቤታቸው ሆነው የሚሰሩበትን
መንገድ ማመቻቸት


4. የሕዝብ መጓጓዣ አገልግሎት ሰጪዎች አጨናንቆ ተሳፋሪዎችን መጫን የማይችሉ ሲሆን፥ ይህን ማድረጋቸው በትራፊክ
ፖሊስ እና በበጎ ፈቃደኞች አማካኝነት ቁጥጥር የሚደረግበት
ይሆናል።

5. ብሔራዊ የመከላከያ ሠራዊት እና ፖሊስ ውስጣዊ ቅድመዝግጀት በማካሄድ በሀገር ደረጃ የቫይረሱን ስርጭት የመከላከል ሥራን ለማስፈጸም መዘጋጀት።

6. በተጠቃሚው ማኅበረሰብ ላይ ሕገወጥ የዋጋ ጭማሪን የሚያደርጉ ተቋማት ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎች የሚቀጥሉ ይሆናል።

7. መገናኛ ብዙሀን በትኩረት በየደረጃው ግንዛቤን የማሳደግ ሚና መጫወት ይጠበቅባቸዋል።

8. ብሔራዊ የመከላከያ ሠራዊት በድንበር አካባቢ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በሙሉ ይገታሉ። ይህ እርምጃ ወደ ሀገሪቱ የሚገቡ ሸቀጦችና አስፈላጊ መገልገያዎችን አይጨምርም። በተጨማሪም፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ቫይረሱ በፍጥነት ቢዛመት ክልሎች ለይቶ ማቆያና ማከሚያ እንዲሁም የሕክምና ባለሙያዎቻቸውን እያዘጋጁ መሆኑን ገልጸዋል። አክለውም፣ ፌደራል መንግሥት የኮቪድ19ን የመከላከል ሥራን ለመሥራት 5 ቢሊየን ብር መመደቡን አስታውቀዋል።

ምንጭ: ፋና
@YeneTube @FikerAssefa
የአቃቂ ቃሊቲ መናኸሪያ የኮሮና ቫይረስን ስርጭትን ለመከላከል የሙቀት መመርመሪያ መሳሪያን መጠቀም ጀመረ፡፡

መናኸሪያው ተሳፋሪዎችን እና አሽከርካሪዎችን ሙቀትመለካት መጀመሩን ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ከግል ንጽሕና ጋር በተያያዘ አሽከርካሪዎች እና ተሳፋሪዎች በንጹህ ውሃ እና ሳሙና እጃቸውን እየታጠቡ ወደ መኪና የሚገቡ እንዲገቡ የተደረገ ሲሆን መኪኖችም ተሳፋሪዉ ከመግባቱ በፊት ተገቢውን የጽዳት ሥራ በኪሚካል እንደሚደረግላቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡

-ከትራንስፖርት ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
ደቡብ አፍሪካ 128 አዲስ ተጠቂዎችን ያስተናገደች ሲሆን በአጠቃላይ 402 ሰዎች እስካሁን ተጠቅተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
እራሳቸውን ለይተው የነበሩት የራይድ አሽከርካሪዎች ከኮረናነጻ መሆናቸው ተነገረ

አዲስ አበባ ውስጥ ዘመናዊ የታክሲ አገልግሎት የሚሰጠው የራይድ ሁለት አሽከርካሪዎች የኮሮናቫይረስ ጥርጣሬ አድሮባቸው እራሳቸውን ለይተው ከቆዩ በኋላ በተደረገላቸው ምርምራ ነጻ ሆኑ ሲል ድርጅቱ አስታወቀ።

የራይድ ታክሲ መስራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሳምራዊት ፍቅሩ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ያሳፈሩትን ሰው በመጠርጠራቸው እራሳቸውን ለይተው የቆዩት ሁለት ሾፌሮች እንደነበሩ፤ ነገር ግን ሁለቱም ተመርምረው ነጻ ሆነው መገኘታቸውን ተናግረዋል።

ራይድ አስራ አምስት ሺህ ሾፌሮችን በመያዝ አገልግሎት እንደሚሰጥ የተናገሩት ሥራ አስፈጻሚዋ፤ የኮሮናቫይረስ በአዲስ አበባ ውስጥ መገኘቱን ተከትሎ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ጨምረውም ሾፌሮች ከተሳፋሪ ጋር ስለሚኖራቸው ግንኙነት እንዲሁም የእጃቸውንና የመኪናቸውን ንጽህና በጸረ ተህዋሲያን እንዴት መጠበቅ እንዳለባቸው እንደሚያስተምሩ ጠቅሰዋል።

ከዚህ ባሻገርም የተሳፋሪዎችንም ሆነ የሾፌሮችን ጤንንት ለመጠበቅ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብልና ጓንት እንዲጠቀሙ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

-BBC
@Yenetube @Fikerassefa
ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ንግድ እና መምሪያ ቤት የተላከ ⬆️

ጭፈራ ቤቶችን በተመለከተ ይህ ደብዳቤ ከደረሳችሁ ቀን ጀምሮ ቤታችሁን እንድትዘጉ የሚል ማሳሰቢያ አስተላልፏል ምክንያቱም የአለም ስጋት የሆነውን ኮሮና ቫይረስን ለመከላከ መሆኑን በደብዳቤ ላይ ተገልጷል ።

@Yenetube @Fikerassefa
የቦትስዋና ፕሬዝዳንት ኤሪክ ሞጊዚሲ ማሳሲ ለአራት ቀናት ራሳቸውን ማግለል በለይቶ ማቆያ ውስጥ ማድረግ መጀመራቸውን መንግሥት በፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት በኩል በዛሬው እለት አስታውቋል ፡፡

ራስን ማግለል ውሳኔው የመጣው ለስራ ጉዞ ወደ ጎረቤት ናሚቢያ ሄደው ከተመለሱ በኋላ ነው ፡፡ በዊንሆክ ፕሬዝዳንት ሀጌ ጂንግቦ በተደረገው ቃለ መሀላ ላይ ተገኝተዋል።

- CGTN
@YENETUBE @Fikerassefa
👍1
በአዲስ አበባ ለረዥም ጊዜ መንገድ ዳር የቆሙ ተሽከርካሪዎችን የማስነሳት ስራ ጀመረ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ለመንገድ ትራፊክ መጨናነቅ ምክንያት ከሆኑ ነገሮች መካከል በየጎዳናዎቹ ላይ ያለአግባብ ለረዥም ጊዜ የሚቆሙ የንግድ ፣ በብልሽት እና በተለያዩ ምክንያቶች የሚቆሙ ተሽከርካሪዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ችግሩን ለመቅረፍ የሚያስችል ተግባር በመጀመሩ መንገድ ዳር የቆሙ ተሽከርካሪዎችን ከመጋቢት 3/2012 ዓ.ም ጀምሮ እያስነሳ ይገኛል፡፡

ኤጀንሲው ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን እና ከከተማዋ የሠላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ደንብ ማስከበር አገልግሎት ዘርፍ ጋር በመተባበር ሲሆን የተሽከርካሪዎቹ ባለቤቶች ንብረቶቻቸውን ከመንገድ ዳር እንዲያስነሱ ከአምስት እስከ ሰባት ቀን ጊዜ ማስታወቂያ ከተለጠፈ በኃላ በክሬን የማስነሰቱን ስራ እየተከናወነ ነው፡፡ከየመንገዱ ዳር በክሬን የሚነሱ ተሽከርካሪዎች ለሚቆዩበት ሶስት ቦታዎች የተዘጋጁ ሲሆን እስከ አሁን ስምንት ተሽከርካሪዎች ተነስተዋል፡፡

የተሽከርካሪ ባለቤቶቹ በሚሰጣቸው የጊዜ ገደብ ተሽከርካሪዎቻቸውን የማያስነሱ ከሆነ ተሽከርካሪዎቹ በሚነሱበት ወቅት ለሚደርስባቸው ጉዳቶች ኤጀንሲው ተጠያቂ የማይሆን ሲሆን ለክሬን ማስነሻ ኪራይ ክፍያ፣ ተሽከርካሪዎቹ ለሚቆዩበት ቦታ የፓርኪንግ እና የጥበቃ አገልግሎት ክፍያን ጨምሮ ባለንብረቶች ይከፍላሉ፡፡ በቀጣይም በከተማዋ በተለያዩ ቦታዎች በተለያዩ ምክንያቶች ለረዥም ጊዜ መንገድ ዳር ቆመው የሚገኙ ተሽከርካሪዎችን የማስነሳቱ ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ተብሏል።

ምንጭ: የከ/መ/ ፕሬስ ሴክሬተሪያት
@YeneTube @FikerAssefa
አል ኢምራን መስጂድ አስተዳደር የተወሰዱ እርምጃዎች :-

-ለሰላት መስጂድ ስንመጣ በየመሃላችን ሁለት ሰው ሊያሰግድ የሚችል ቦታ ርቀት አድርገን መቆም።

-ወደ መስጂድ ስንገባ እጃችንን በሳሙና ታጥበን መግባት።

- መስጂድ ሲመጣ ህፃናትን ይዞ አለመምጣት።

-ሰላምታ በቃላት መለዋወጥ....የመሳሰሉት
እርምጃዎች ተውስደዋል ሁላችንም ብንተገብረው መልካም ነው።

@Yeneyube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 አራብሳ ለሚ ኮብልስቶን ማምረቻ አከባቢ ስኳር እና ኬሚካል ከቀይ አፈር ጋር በመቀላቀል ማር ነው ብሎ ለመሸጥ ሲያዘጋጅ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ግለሰቡ ሙሉ መኖሪያ ግቢ ተከራይቶ ህገ - ወጥ ተግባሩን ሲፈፅም በቁጥጥር ስር ሊውል የቻለው ፖሊስ በጥርጣሬ ባደረገው ማጣራት ነው ፡፡በቦሌ አራብሳ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል መከላከል አባል ሳጅን ድንበሩ ጥላሁን እንደገለፁት ለስራ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ከፍተኛ ጭስ ከግቢው ሲወጣ ተመልክተው ሲጠይቁ እንጀራ እየጋገርን ነው የሚል ምላሽ ቢሰጣቸውም ተጠራጥረው ባደረጉት ማጣራት ህገ- ወጥ ድርጊት እየተፈፀመ መሆኑን በማረጋገጥ ለሚመለከተው የአስተዳደር አካል ሪፖርት አድርገዋል፡፡

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘም አንድ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት ይገኛል ብለዋል፡፡በቦሌ ክ/ከተማ የወረዳ 11 ንግድና ኢንዱስትሪ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ አድነው ወልዴ በበኩላቸው ግለሰቡ መርካቶን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ማር ነው ብሎ ያዘጋጀውን ባዕድ ነገር ሲሸጥ እንደቆየ ገልፀዋል፡፡

Via Addis Ababa Police Commission
@YeneTube @FikerAssefa