YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.89K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ኦሎምፒክ ኮሚቴ እና አትሌቲክ ፌዴሬሽን በኮሮና ቫይረስ ምክኒያት የቃላት ጦርነት ውስጥ ገብተዋል!

በመጪው ሃምሌ ወር ይካሄዳል ተብሎ ለሚጠበቀው የቶኪዮው ኦሎምፒክ አትሌቶች ሆቴል ገብተው ይሰልጥሉ አይሰልጥኑ የሚለው የኦሎምፒክ ኮሚቴ እና አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቃላት ጦርነት ውስጥ ግብተዋል።የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ደራርቱ ቱሉ ከ 100 በላይ አትሌት አንድ ሆቴል በግባት የለበትም፣ ይህ ለህይወታቸው ያሰጋል በሚል ውሳኔ ማሳለፋቸው ይታወሳል።ይህንን የተቃወመው በአሸብር ወ/ጊዮርጊስ የሚመራው የኦሎምፒክ ኮሚቴ ግን ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባገኘሁት ፈቃድ መሰረት አትሌቶችን ሆቴል አስገባለሁ ሲል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫው ላይ አትሌት ሃይሌ ገብረ ስላሴ እና ገብረ እግዚአብሄር ገብረ ማሪያም እንዲሁም አባ ዱላ ገመዳ ተገኝተው ነበር።‹‹ሃይሌን እና ገብረ እግዚአብሄር ራሳቸው ቢሆኑ የማያደርጉትን ለሌላ አትሌት ለምን ይወስናሉ፤ ከኮሚቴው ይልቅ እኛ እንቀርባቸዋለን›› ሲሉ አትሌት ደራርቱ ወቅሰዋቸዋል። ‹‹የአትሌቶች ዝግጀት አካላዊ ንክኪ ያለው በመሆኑ፤ ምግብ ሲበሉ እና በአውቶቡስ ሲጓጓዙ የኮሮና ቫይረስ መጋለጣቸው ስለማይቀር ይህንን ውሳኔ አሳልፌአለሁ›› ሲሉም ዛሬ ጠዋት በኢቲቪ ቀርበው ተናግረዋል።

‹‹እኔ አሻንጉሊት አይደለሁም፣ ልንሰራ ነው የተቀመጥነው›› ያሉት ደራርቱ ‹‹የፈረደበት ብሄር ገበቶ ከሆነ ቢታረም፣ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ሎጂሰትቲክስ እንጂ እንደዚህ አይነት ውሳኔ መስጠት አይችልም። አትሌቶቹ ልጆቼ ናቸው፤ ባሉበት ልምምድ መስራታቸውን ይቀጥላሉ፤ ኦሎምፒክ ኮሚቴ እያለ ያለው ግብፅ አባይ ላይ እያለች ያለውን ነው፤ እንዴት ነው በአትሌቲክስ ጉዳይ ፌዴሬሽኑ የማያገባው›› ሲሉ ደራርቱ ተናረግዋል።

ምንጭ:አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አስገዳጅ ምክንያት ካልገጠመን በቀር ቤት እንቆይ:፡
@YeneTube @FikerAssefa
አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ከመጋቢት 14( ነገ) ጀምሮ ከግቢ መውጣትም ሆነ መግባትም ተከልክሏል።

- ተጨማሪውን ከፎቶው ላይ ያንብቡት
@Yenetube @Fikerassefa
ለአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ማህበራሰብ በሙሉ ⬆️

- ካፌ ያልሆኑ ተማሪዎች አስፈላጊውን ገንዘብ ከፍለው ካፌ እንዲጠቀሙ ይደረጋል።

- ቱሪስቶች ወደ ዩንቨርስቲ ግቢዎች መግባት አይቻልም

- ከተማሪ ካፍቴሪያ ውጪ የሆኑ ማንኛውም ምግብ ቤቶች ስታፍ ካፍቴሪያዎች ዝግ ይሆናሉ።

- ትምህርት በኢሜል ይቀጥላል........


----ተጨማሪ ከፎቶው ላይ ያንብቡ ----

@Yenetube @Fikerassefa
ለደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ሰራተኞች በሙሉ

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መመሪያ መሰረት ተማሪዎች የቫይረሱን ምልክቶችና መከላከያ መንገዶቹን ጠንቅቀው በማወቅ እራሳቸውን እንዲከላከሉ አሳስቧል፡፡በመሆኑም ተማሪዎች በዶርማቸው ሆነው ኃላፊነት በተሞላበት መንገድ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት እንዲቻል ዩኒቨርሲቲው እያሳሰበ ከሰኞ መጋቢት 14/2012 ዓ.ም ጀምሮ፡-

1. ማንኛውም ተማሪ ለማንኛውም አይነት አገልግሎት ከግቢ መውጣትም ሆነ መግባት የማይችል መሆኑን፣

2. የNon-Cafe ተጠቃሚ ለሆኑ ተማሪዎች በግቢ ውስጥ ባሉት ሶስቱ የተማሪ ካፊቴሪያዎች እንዲመገቡ የተመቻቸ መሆኑን፣

3. ከአሁን በፊት ከግቢው ለተግባር ልምምድ የወጡ ተማሪዎች በተመደቡበት ቦታ እየሰሩ እንዲጠብቁ፣

4. በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ቤተሰብ የሄዱ ተማሪዎች ወደ ግቢ መግባት እንደማይችሉና ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመሆን ጥንቃቄ እያደረጉ እንዲቆዩ፣

5. ተማሪዎች ወደ ዋናው ምግብ ቤት ሲገቡም ሆነ ሲመገቡም ሳይተፋፈጉ /በቡድን ሳይሆኑ በተናጠል/ ተገቢውን ርቀት ጠብቀው እንዲስተናገዱ እያሳሰብን የመመገቢያ የሰዓት ፕሮግራም በየኮሌጆቻቸው ሊወጣ የሚችል መሆኑን፣

6. የጋራ መጠቀሚያ በሆኑት ፑል ቤቶች፣ዲ.ኤስ.ቲቪ /DSTV/፣ካፍቴሪያዎች ላይ በቡድን ሆኖ መቀመጥና መጠቀም የማይቻል መሆኑን፣

7. የተማሪዎችን ደህንነት ለማረጋገጥ ሲባል ሁሉም መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች መግባት አይችሉም፡፡ሆኖም ለስራው የሚያስፈልጉ የዩኒቨርሲቲው የምግብ ቤት ሰራተኞች፣ ከትምህርት ክፍል በላይ ያሉ የአካዳሚክ ኃላፊዎች/ዲኖችና ተባባሪ ዲኖች/፣ንዑስ የስራ ሂደት መሪዎችና ዳይሬክተሮች፣ ሁሉም ሹፌሮች፣የውሃና የመብራት ጥገና ሰራተኞች፣የክሊኒክ ሰራተኞች፣ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጆች መምህራን፣የአመራር ጸሐፊዎች፣ሁሉም የጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት ሰራተኞች ከበር ላይ እጃቸውን እየታጠቡ እንዲገቡ የተወሰነ መሆኑን፣ እያሳወቀን ሰራተኞችና ተማሪዎች ቫይረሱን ለመከላከል የሚወሰዱ ጥንቃቄዎችን እንዲወስዱ ዩኒቨርሲቲው በጥብቅ ያሳስባል፡፡

-ደብረ ብርሃን ዩንቨርስቲ
@YeneTube @FikerAssefa
ለዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በሙሉ

የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የ(COVID-19) ቅድመ መከላከልና ጥንቃቄ ሲባል የሚከተሉት ውሳኔዎች አስተላልፏል:-

1. የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ እንቅስቃሴዎችን በመገደብ መግታት የሚቻል በመሆኑ ተማሪዎች ከሰኞ መጋቢት 14/2012 ዓ.ም ጀምሮ ከግቢ መውጣት የማይችሉ መሆኑን

2. ከግቢ ውጭ የሚኖሩ ተማሪዎች በሙሉ እስከ ነገ መጋቢት 14/2012 ዓ.ም ድረስ ወደ ግቢ እንዲገቡ እና የካፌ ተጠቃሚ ያልሆናቹ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው የምግብና መኝታ አገልግሎት እንድታገኙ ያመቻቸ መሆኑ

3. ከዩኒቨርሲቲው ሰራተኛ ውጭ የሆነ ማንኛውም ሰው በቀጣይ እስኪፈቀድ ጊዜ ወደ ዩኒቨርሲቲው መግባት የማይችል መሆኑን እንገልፃለን።

-ዩንቨርስቲው
@YeneTube @FikerAssefa
የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው እና በቫይረሱ የተጠረጠሩ ሰዎች የህክምና ክትትል እያደረጉ የሚገኙበት የየካ ኮተቤ ሆስፒታል
- 22 ዶክተሮች
- 150 ነርሶች
- 500 አልጋዎች ገደማ አሉት
* ሆስፒታሉ እስከ አርብ 174 ሰዎች አስተናግዷል

ምንጭ (ፎቶ)፦ ፎርቹን
@Yenetube @Fikerassefa
በአርባ ምንጭ ከተማ በኮሮና ቫይረስ ጋር የተጠረጠረ የ36 ዓመት ግለሰብ በለይቶ ማቆያ ክትትል እየተደረገለት እንደሚገኝ የዞኑ ጤና መምሪያ ገለጸ

የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊና የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ተሻለ ማናዬ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የ36 ዓመት ግለሰብ ጉንፋን መሰል ምልክቶች ታይቶበት አርባምንጭ ሆስፒታል ለህክምና በመጣበት ተጠርጥሮ ለጥንቃቄ ሲባል ለይቶ ማቆያ መዕከል ላይ እንዲቆይና የባለሙያ ክትትል እየተደረገለት ይገኛል፡፡

ግለሰቡም በቀን 07/07/2012 ዓ.ም. ለአንድ ቀን በኬንያ ለንግድ የተንቀሳቀሰ በመሆኑና ኬንያ ደግሞ የኮሮና ቫይረስ የተገኘበት አገር በመሆኑ ምክንያት ግለሰቡ ሊጠረጠር ችሏል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ግለሰቡ በመልካም የጤንነት ሁኔታ ላይ ይገኛል ያሉት አቶ ተሻለ ከግለሰቡ ጋር ንኪኪ ያላቸዉን ሰዎች የመለየት ስራም እየተሰራ ይገኛል፡፡ ከተጠርጣሪዉ ግለሰብ በዛሬዉ ዕለት ናሙና ተወስዶ በምርመራ እንዲረጋገጥ ከክልል ጤና ቢሮ ጋር በጥምረት እየተሰራን ይገኛል ፡፡

ህብረተሰቡ በምርመራ ባልተረጋገጠ መረጃ መረበሽና መደናገር እንደሌለበት አቶ ተሻለ አሳስበዋል፡፡
@Yenetube @FikerAssefa
ኤምሬትስ ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ሁሉንም የመንገደኛ በረራዎቹን፣ ከመጪው ረቡዕ ጀምሮ እንደሚሰርዝ አስታውቋል።
@Yenetube @FikerAssefa
የፀረ ኤች አይ ቪ መድሃኒት ያልጀመሩና ያቋረጡ ሰዎች ለኮቪድ19 ከፍተኛ ተጋላጭ ናቸው ተባለ!

የዓለም አቀፍ ወረርሺኙ ኮቪድ19 በሽታ የመከላከል አቅማቸው ዝቅተኛ የሆኑ ሰዎች ላይ ጫናው የበረታ እንደሆነ የዓለም የጤና ድርጅት በተደጋጋሚ አስታውቋል። በኢትዮጵያ ከ 600 ሺህ በላይ ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ዜጎች አሉ ተብሎ ሲገመት ከዚህ ውስጥ ከ 110 ሺህ በላዩ ቫይረሱ እንዳለባቸው ተመርምረው ያላወቁ፣ አውቀው መድሃኒት መውሰድ ያልጀመሩና ጀምረው ያቋረጡ እንደሆኑ ሪፖርቶች ያሳያሉ።ኤች አይ ቪ ኤድስን ጨምሮ በተለያዩ የጤና ጉዳዮች ላይ አተኩሮ የሚሰራው የፖፑሌሽን ኢትዮጵያ ባልደረባ የሆኑት ቤዛዊት አድማሱ እንደሚሉት መድሃኒታቸውን ባግባቡ እየወሰዱ ያሉ እና በሽታ የመከላከል አቅማቸው በመደበኛ ሁኔታ ላይ ያሉ ሰዎች የተለየ ስጋት የለባቸውም። ነገር ግን አምስቱን የኮቪድ19 የመከላከያ እርምጃዎች ለራሳቸውም ሆነ ለሌሎች ዝቅተኛ የበሽታ መከላከል አቅም ላላቸው ሰዎች ሲባል ባግባቡ መተግበር ይገባቸዋል ይላሉ።

‹‹ ቫይረሱ ይኖርብኛል ብለው ለመጠርጠር በቂ ምክንያት ቢኖራቸውም ሄደው ለመመርመር ያልደፈሩ፣ ሃኪም የኤች አይ ቪ ቫይረስ እንዳለባቸው ቢያረጋግጥላቸውም መድሃኒቱን ያልጀመሩ ወይም ጀምረው ያቋረጡ ሰዎች ግን ቢቻል ዛሬ ወይም ነገ መድሃኒቱን መጀመር አለባቸው›› ሲሉ ያስጠነቅቃሉ።‹‹ ከዚህ ባሻገር የአመጋገብ ስርአታቸውን እና የበሽታ መከላከል አቅምን የሚቀንሱ እንደ ሱስ ያሉ ልምዶችን በፍጥነት ማቆም እና የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚመከሩ እርምጃዎችን ሳያወላውሉ መፈፀም አለባቸው›› እንደ ቤዛዊት ገለጻ።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
ኬንያ ከካርጎ ውጭ ያሉትን ሁሉንም አለምአቀፍ በረራዎች አቋርጣለች። በዛሬው እለት በሀገሪቱ 8 አዲስ ተጠቂዎች የተመዘገቡ ሲሆን ከ20- 57 እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ናቸው። ከሰው ጋር በተያያዘ ባሮች ላልተወሰነ ጊዜ እንዲዘጉ የተወሰነ ሲሆን የቀብር ስነ ስርዓቶች የቅርብ ዘመዶች ብቻ በተገኙበት እንዲፈጸም ተወስኗል።

@YeneTube @FikerAssefa
በምዕራብ አርሲ ዞን ከወትሮ የተለየ በረዶ ጣለ!

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ወቅቱን ያልጠበቀ እና ከወትሮ የተለየ በረዶ ጣለ።ከወትሮ የተለየ በረዶው ምዕራብ አርሲ ዞን ኮፈሌ ወረዳ አሾካ ቀበሌ መጣሉን የዞኑ የመንግስት ኮሙዪኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቋል።በረዶው በአካባቢው ያለውን መንገድ እና መኖሪያ ቤቶች መሸፈኑም ነው የተገለፀው።በአካባቢው የጣለው በረዶም የትራፊክ እንቅስቃሴውን እያስተጓጎለ መሆኑን የገለፀው ጽህፈት ቤቱ፤ አሽከርካሪዎች በስፍራው ላይ በጥንቃቄ እንዲያሽከረክሩም አሳስቧል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
በጣሊያን ዛሬ 5,560 ሰዎች በቫይረሱ የተጠቁ ሲሆን 651 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ሞተዋል። በአጠቃላይ ጣሊያን 59,138 በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ሲኖሩ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት እስከ ዛሬ በጣሊያን 5,476 ሰው ሞቷል።

@Yenetube @Fikerassefa
በባህርዳር ከተማ የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የተቋቋመው ግብረ ሀይል በከተማው ስብሰባ ማካሄድን ከልክሏል። በመጠጥ ቤቶች፣ ምሸት ቤቶች፣አዝማሪ ቤቶች፣ ውስኪ ቤቶች ውሰጥ በጋራ ተሠብስቦ መጠጣት ሆነ ከፍቶ አገልግሎት መስጠትንም ከልክሏል።

ምሽት ላይ መንገድ ዳር ቁሞ መገኘትን ከልክሏል። ስፖርት ቤቶች እና መዋኛ ቦታዎች አገልግሎት እንዳይሰጡም ከልክሏል። መንገድ ላይ መጫዎትንም ከልክሏል።

#ElU
@Yenetube @Fikerassefa
#Update

ሁሉም የአበባ እርሻ ድርጅቾት ወደ አውሮፓ (በተለይም ሆላንድ)የሚላኩ አበባዎች በመቆማቸው ምክንያት 50,000 የሚጠጉ ሰራተኞች ስራ ሊያቆሙ እንደሚችሉ ተነግሯል ይህ የሆነው ኮሮና ቫይረስ በአውሮፓ በከፍተኛ መጠን በመስፋፋቱ ነው።

@Yenetube @Fikerassefa
የጀርመኗ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል በቫይረሱ ከተያዘ ዶክተር ጋር መገናኘታቸውን ተከትሎ ወደ ለይቶ ማቆያ ክፍል ገብተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from HEY Online Market
iPhone 11 (New)
Condition : Packed
Storage: 64GB
Color: Grey
💵Price 32,000

Contact us
0953964175 @Heymobile
0925927457
091069510
Join our channel and keep learning American English Beginners- Advanced
Communicative English
General English
English for Specific Purpose
Social English
Business English
TOEFL IELTS SAT GMAT GRE KET
Morning Sessions
Afternoon Sessions
Night Sessions
Weekend Sessions
Flexible Sessions
Group Classes/ Mini Group/Private/ VIP/
Report Writing
Thesis Writing
Academic Writing
Research Writing
Project Writing
Proposal Writing
Scholarship Consultation

USA Canada England China Europe
+251 921 309530
☑️ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
👉https://tttttt.me/SCHOOLOFAMERICAN
የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የባቡር ትራንዚት አገልግሎት የተሳፋሪውን ቁጥር 50 በመቶ እንደሚቀንስ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ገለጸ!

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የአዲስ አበባ ባቡር ትራንዚት አገልግሎት ከዛሬ ጀምሮ የተሳፋሪውን ቁጥር 50 በመቶ በመቀነስ አገልግሎት እንደሚሰጥ የትራንስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ገልጸዋል፡፡ህዝቡ በሚሳፈርበበት ጊዜ ርቀት ጠብቆ በመቆም የበኩሉን አስተዋፆ እንዲያበረክትም ሚኒስትሯ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa