YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በጥፊ እየመታ የሚያስተምረው መፅሐፍ 3ተኛ ዕትም!!!

በአጭር ጊዜ ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ ታትሞ በገበያ ላይ ዋለ!!!

‹‹በጥበብ የመኖር ዕሴት››

ቁጥር 1 ዓለም አቀፍ ሽያጭ የተቀዳጀው THE SUBTLE ART OF NOT GIVING A ... መፅሐፍ ‹‹በጥበብ የመኖር ዕሴት›› በሚል ርዕስ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በድጋሜ ታትሞ በገበያ ላይ ውሏል፡፡

መፅሐፉ በጥበብ የመኖር ዕሴቶችን ሲዘረዝርልዎ እስከ ዛሬ ድረስ እነዚህን ጥበቦች ሳያውቁ በመቆየትዎ ይቆጫሉ፡፡
ግን አይዞዎት አሁንም አልረፈደም! መቼም ቢሆን ደግሞ አይረፍድም!!

ከዚህ በፊት ሲያነቡት እንደነበሩት የሳይኮሎጂ መፅሐፍት አይነት ሳይሆን በልዩ ሁኔታ የሚያሰለጥንዎ ለየት ያለ መፅሐፍ ነው፡፡

ርያን ሆሊደይ የተባለ የከፍተኛ ሽያጭ መፅሐፍት ደራሲ ስለዚህ መፅሀፍ እንዲህ ነው ያለው ‹‹የተሻለ ህይወት መኖር መጀመር ከፈለጉ ይሄንን መፅሐፍ ያንብቡ! መፅሐፉ ፊትዎ ላይ አስፈላጊ ጥፊ እያሳረፈ የሚያስተምርዎ መፅሐፍ ነው!!››

ሶስተኛው ዕትም በገበያ ላይ ስለዋለ በየመፅሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል፡፡
ሰበር ዜና !!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ 30 ሃገራት የሚያደርገውን በረራ አቋረጠ!!

@Yenetube @Fikerassefa
ሰበር መረጃ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከየትኛውም ሃገራት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች ለ14 ቀናት በልዩ ማቆያ የመቆየት ግዴታ ተጥሎባቸዋልም ነው ያሉት።

በዚህ ቆይታቸውም ሙሉ በሙሉ ወጪያቸውን ራሳቸው የሚሸፍኑ ይሆናልም ብለዋል።


Via:- FBC
@Yenetube @Fikerassefa
#እስረኞች ሊለቀቁ ነው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት እንዲለቀቁ ተወሰነ

------ዶ/ር አብይ አህመድ -----

በማረሚያ ቤቶች፣ ቫይረሱ ከገባ ለቁጥጥር አስቸጋሪ ሁኔታ የሚፈጠር በመሆኑ ህጻናትን የያዙ፣ የአመክሮ ጊዜያቸው የደረሰና ቀለል ያለ ክስ ያለባቸው እንዲለቀቁ መወሰኑንም አስታውቀዋል።

Via:- FBC
@Yenetube @Fikerassefa
ሰበር መረጃ #የእምነት ተቋማትን በተመለከተ

------ዶ/ር አብይ አህመድ -----

የእምነት ተቋማትም እንደየአምልኳቸው ሁኔታ ለቫይረሱ ስርጭት ምቹ ሊሆኑ ስለሚችሉ የራሳቸውን ውሳኔ እንዲያሳልፉም ከስምምነት መደረሱን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስታወቁት።

Via:- FBC
@Yenetube @Fikerassefa
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ይቅርታ ጠየቁ!!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በብልጽግና ፓርቲ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር ምሁራን መከፈታቸውን ገልጸው ለተፈጠረው የአገላለጽ ችግር በይፋ ይቅርታ ጠይቀዋል።

ጉዳዩ የሚመለከታቸው ትምህርትን ከውጤት የማያገናኙትን እንጅ በእውቀታቸው ሃገርን እያገለገሉ ያሉትን እንዳልሆነም ገልጸዋል።

Via:- FBC
@YeneTube @Fikerassefa
#ጭፈራ_ቤት_ዝግ_እንዲሆን ተወስኗል - ዶ/ር አብይ አህመድ

ከኮሮና ቫይርስ ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ የሚገኙ ሁሉም ጭፈራ ቤቶች ተዘግተው እንዲቆዪም ውሳኔ ተላልፏል፡፡

Via:- FBC
@Yenetube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የኮሮና ቫይረስ ስጋት በምርጫ ኦፕሬሽን ላይ ስለሚኖረው ተጽእኖ እንዲሁም ሊወሰዱ ስለሚችሉ አማራጭ እርምጃዎች ውይይት ማከናወኑን አስታወቀ፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
190 ሚልየን #ዶላር ከስሪያለው አለ የኢትዮጵያ አየር መንገድ

flyethiopian CEO Tewolde G/Mariam told state TV that the airline has lost $190 m in revenues due to #COVID19 crisis. It's also not flying to about 20 countries that have travels restrictions & has grounded 20-20% of its planes, while & reducing 20-30% of its flights.

- Addis standard
@YeneTube @fikerassefa
ኮሮና ቫይረስ - ኢትዮጵያ

የኮሮና ቫይረስ በመጪው ምርጫ ላይ ተጽዕኖ ያሳድር እንደው ለመለየት ምርጫ ቦርድ "assessment" እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት የኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ነው።

#ምርጫ2012
@Yenetube @Fikerassefa
YeneTube
ኮሮና ቫይረስ - ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ በመጪው ምርጫ ላይ ተጽዕኖ ያሳድር እንደው ለመለየት ምርጫ ቦርድ "assessment" እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት የኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ነው። #ምርጫ2012 @Yenetube @Fikerassefa
"ለተራዘመ ጊዜ ችግሩ የሚቀጥል ከሆነ እና ምርጫ ቦርድ ስራውን መከወን የሚቸገር ከሆነ፤ በሚያደርጉት ጥናት መሰረት ውይይት የሚደረግ ይሆናል። የቦርዱ assessment ቀርቦ፣ የጋራ ስምምነት ሲደረስበት የመጨረሻው ውጤት የሚገለጽ ይሆናል"

- ጠ/ሚ አብይ
@Yenetube @Fikerassefa
አብን - ጎንደር ከተማን ችግር አስመልክቶ

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ከትላንትናው ዕለት ጀምሮ በጎንደር ከተማ እና አካባቢው የፀጥታ ችግር እንዳለ ለማወቅ ችሏል። የችግሩ መነሻ እና ከዚህ ደረጃ የደረሰበትን ምክንያት ምን እንደሆነ በትኩረት በማጣራት ላይ እንገኛለን።

ይህ በእንዲህ እንዳለ መንግስት ሕግ አስከብራለሁ ብሎ በሚንቀሳቀስበት ማንኛውም ሁኔታ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ እንዲያደርግ እና የዜጎች ሰብዓዊ መብት በጠበቀ መልኩ እንዲሆን አብን ይጠይቃል። ጉዳዩን በትኩረት በመከታተል ከሕዝባችን ጎን እንደምንቆም ለማሳሰብም እንወዳለን።

-አብን
@Yenetube @Fikerassefa
ከዘውዲቱ ሆስፒታል የትላከ መልክት:-

ወደ ዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ከመምጣቶ በፊት እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች ይገንዘቡ

• ለአንድ ታካሚ አንድ አስታማሚ ብቻ ነው መግባት የሚፈቀደው

• አሁን ያለውን የ#COVID-19 ስርጭትን ለመግታት ማንኛውንም ታካሚዎች ባሉበት ሆነው በስልክ ብቻ ለመጠየቅ ይሞክሩ

• ለድንገተኛ ህክምና እና የሀኪም ቀጠሮ ከሌላቹ በስተቀር ወደ ሆስፒታላችን ባለመምጣት  ከ#COVID-19 ስርጭት እራሶን እና ቤተሰቦን ይጠብቁ

• እድሜያችሁ ከ 40 አመት በላይ ሆኖ ተላላፊ ያልሆነ ህክምና (ስኳር፣ ደም ግፊት፣ ልብ ፣ ኩላሊት) ክትትል ያላችሁ በቀጠሮ ቀን የእርሶ ጤና አስችኳይ ሕመም ከሌሎት መድሀኒቱን የሚወስድሎት ወጣት ሰው ከቀጠሮ ካርድ ጋር አብረው እየላኩ ያለቀቦትን መድሀኒት ያሉበት ሆነው እዲወስድሎት ያድርጉ

• መግቢያ በሮች ላይ የሆስፒታሉ ሰራተኞች አድርጉ የሚሏችሁን በአግባቡ ተግባራዊ አድርጉ (እጅን መታጠብ፤ የሙቀት ልየታ፤ ርቀትን ጠብቆ መሰለፍ . . .)

• በሚያስነጥሱበት እና በሚያስሉበት ጊዜ አፎን እና አፍንጫዎን በክንዶ ወይም መሀረብ/ሶፍት ይሽፍኑ

• አገልግሎት ለማግኘት በሚቆዩበት ጊዜ፤ ሰልፍ እና ወረፋ ሲጠብቁ ርቀቶን ቢያንስ በ1 ሜትር ይጠብቁ


ዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል
@YeneTube @Fikeeassefa
በአዲስ አበባ ውሃ በሌለባቸው ቦታዎች ለማቅረብ የተላለፈ ጥሪ

"በአዲስ አበባ ውሃ በሌለባቸው ቦታዎች ለማከፋፈል ብዙ የውሃ ማመላለሻ ቦቴዎች ያስፈልጋሉ።ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች በጤና ሚኒስቴር በኩል የውሃ ማመላለሻ ቦቴዎች ለጥቂት ቀናት ማቅረብ የምትችሉ እስከ ቅዳሜ መጋቢት 12 2012 ከረፋዱ 6 ሰዓት ድረስ በ0911649824 ወይንም 0920552119 በመደወል እንድትመዘገቡ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

ለዚህም እቅድ ለማውጣት ፣ በፈረቃ ለመጠቀም እና ለተቀላጠፈ ስምሪት እንዲመች የባለቤት ስምምነት ፣ የመጫን አቅም ፣ የሹፌር ስልክ ፣ ታርጋ ቁጥር ፣ እና የመሳሰሉት በምዝገባ ወቅት የሚጠየቁ መረጃዎች ናቸው።የጤና ሚኒስቴር የውሃ ማመላለሻ ላላቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦች ይህንን መልዕክት በማጋራት እንድትተባበሩን በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ስም በአክብሮት ይጠይቃል።"

-የኢፌድሪ ጤና ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
በሀገራት የታገዱ፣ በአየር መንገዱ የተሰረዙ እና በከፊል የሚሰሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎች!

- በሀገራት የታገዱ በረራዎች:
ሶማልያ፣ ጅቡቲ፣ ግብፅ፣ ሊባኖስ፣ ሱዳን፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ኳታር፣ ኩዌት፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ናሚብያ፣ ባህሬን፣ ቻድ፣ ካሜሮን፣ ኒጀር፣ ማዳጋስካር፣ አንጎላ፣ ኮንጎ ብራዛቪል፣ ማሊ፣ ሴኔጋል፣ ኮንጎ ኪንሻሳ፣ ርዋንዳ፣ ናይጄርያ (በከፊል)።

- በአየር መንገዱ የተሰረዙ በረራዎች:
ጣልያን፣ አየርላንድ፣ ስፔን፣ ስዊዘርላንድ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ፊሊፒንስ፣ ፈረንሳይ።

- ከዜጎች ውጭ ሌሎች ተጓዦችን የማይቀበሉ ሀገራት:
ካናዳ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ቤልጂየም፣ ኦስትሪያ፣ ህንድ፣ ሩሲያ፣ ኖርዌይ፣ ስዊድን፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ ኬንያ፣ ማሌዥያ።

Via:- Eliasmeseret
@Yenetube @Fikerassefa
ፈረንሳይ ዛሬ ከ1617 ሰው በቫይረሱ ተጠቅቷል 78 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ሞተዋል። በአጠቃላይ ፈረንሳይ 12,612 በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ሲኖሩ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት እስከ ዛሬ በፈረንሳይ 450 ሰው ሞቷል።

@Yenetube @Fikerassefa
ጣሊያን ዛሬ ከ5,986 ሰው በቫይረሱ ተጠቅቷል 627 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ሞተዋል። በአጠቃላይ ጣሊያን 47,021 በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ሲኖሩ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት እስከ ዛሬ በጣሊያን 4,032 ሰው ሞቷል።

የሟቾችና የተጠቂዎች ቁጥር በጣሊያን ዛሬ አሻቅባል ከሌላው ጊዜ በተለየ።
@Yenetube @Fikerassefa
ኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች በቁጥር :-

- ጀንዋሪ 19: 100 ተጠቂ
- ጀንዋሪ 24: 1,000 ተጠቂ
- ጀንዋሪ 28: 5,000 ተጠቂ
- ፌብራሪ 12: 50,000 ተጠቂ
- ማርች 6: 100,000 ተጠቂ
- ማርች 14: 150,000 ተጠቂ
- ማርች 18: 200,000 ተጠቂ
- ማርች 19: 225,000 ተጠቂ
- ማርች 20: 250,000 ተጠቂ

@Yenetube @FikerAssefa
Protect your self from Virus⬆️
እራሳችሁን ጠብቁ ከቫይረሱ

ለወዳጆ ምልክቱን አስተላልፉ
በዳዉሮ ዞን እና ኮንታ ልዩ ወረዳ ለ15 ቀናት መብራት እንደሚቋረጥ ተገልጿል።

ለረጅም ጊዜ የዳዉሮ እና ኮንታ ህዝብ ሲያገለግል የነበረዉ የአባ ሳብስቴሽን የመሬት መደርመስ አደጋ ስለደረሰበት የቦታ ለዉጥ ለማድረግ ከ15/7/2012 .ዓ.ም ጀምሮ ለ15 ቀናት መብራት እንደሚቋረጥ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዩትሊቲ ተገልጿል።

ምንጭ:የዳዉሮ ዞን መ/ኮ/ጉ መምሪያ
@YeneTube @FikerAssefa