YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.89K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የተለያዩ የመንግስት ዩንቨርስቲዎች ሳይንስና ከፈተኛ ትምህርት ሚኒስትር ትላንት የላከውን መግለጫ ያልተገበሩ ዩንቨርስቲዎች እንዳሉ መልክት እየደረሰን ይገኛል።

ዩንቨርስቲዎች የፊት ለፊት ትምህርት እንዲቀር ሳይንስና ከፈተኛ ትምህርት ሚኒስትር ስላሳሰበ እንድትተገብሩት እንመክራለን።

ይህ ለተማሪዉ ደንነት አስፈላጊ ነው!!
@Yenetube @Fikerassefa
በሀገር ውስጥ የተመረተ የንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር በከተማዋ ወደሚገኙ የከነማ ፋርማሲዎች እና ጤና ጣቢያዎች በመሰራጨት ላይ ይገኛል!

በከተማዋ እየተሰራጨ ያለው የንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር 200 ሺህ ሊትር የሚሆን ሲሆን በከነማ ፋርማሲዎች ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርብ ይሆናል፡፡

ከነገ ጀምሮ ህብረተሰቡ ከከነማ ፋርማሲዎች የንጽህና መጠበቂያውን ማግኘት እንደሚችል ማሳወቅ እንወዳለን፡፡

Via Mayor Office of Addis Ababa
@Yenetube @Fikerassefa
አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ዶርም ሆነው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ መልክት አስተላልፏል።
@Yenetube @Fikerassefa
#ኮሮና ካለበት ርቆ ለመገኘት ይህን ተግብሩ

1. አጭር ርቀት ጉዞዎችን በእግር መጏዝ

2. የተጨናነቁ ሰአታትን አሳልፎ መንቀሳቀስ

3. ማንኛውንም ስብሰባ ለጊዜው ብናቆም

4. ከሊፍት ይልቅ ደረጃን መጠቀም

5. የበር እጀታዎችንና የደረጃ ድጋፎችን በባዶ እጅ አለመተሻሸት

#ሼር_Share_
@Yenetube @Fikerassefa
ኮሮናን ለማሸነፍ-

1. የእጅና የእጅ ስልክ ንፅህናን መጠበቅ

2. ከሌሎች ጋር ካለን ቀጥተኛ ንክኪና የትንፋሽ ቅርርብ መቆጠብ

3. ለመከላከል ስለሚጠቅም ገለል ራቅ ብሎ መቆየት

4. ፍራቻን አለመንዛት: ከስግብግብነት መታቀብ

5. ለሌሎች ምሳሌ መሆን: በርቱ

@Yenetube @Fikerassefa
ኢትዮጵያ አዲስ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ አለመኖሩ ተገለፀ።

እንዲሁም አምስቱ ታማሚዎች ጥሩ ጤና ላይ እንደሚገኙ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
@Yenetube @Fikerassefa
በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የኮሮናቫይረስ ከተገኘበት ጃፓናዊ ጋር ንክኪ ነበራቸው ከተባሉት 113 ግለሰቦች መካከል 74ቱ ነፃ መሆናቸውን ታወቀ።
@Yenetube @Fikerassefa
በአዲስ አበባ ቴአትር ቤቶችና ሲኒማ ቤቶች ዝግ ሆነው ይቆያሉ ተባለ

ቴአትርና ሲኒማ ቤቶቹ እንዲዘጉ ትዕዛዝ የተላለፈው ትናንት ሲሆን ይህንን ተከትሎም ሁሉም ትያትር ቤቶችና ሲኒማ ቤቶች ዝግ መሆናቸው ይታወቃል። በትናንትናው እለት ሴንቸሪ ሲኒማ ለተጠቃሚዎቹ በቴሌግራም ገፁ ላይ ባስተላለፈው መልዕክትም ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ለቀጣይ 15 ቀናት ዝግ እንደሚሆን አስታውቋል።

- BBC
@YeneTube @Fikerassefa
በአዲስ አበባ በሚገኙ ሁሉም መናሃሪያዎች የውሃ ማጠራቀሚያዎችን እያሰራጨ መሆኑን የትራንስፖርት ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

በመዲናዋ በሚገኙ ሁሉም መናሃሪያ ላይ የውሃ ማጠራቀሚያ ማጠራቀሚያ ታንከር እና የአልኮል ቁሳቁሶች ተደራሽ ለማድግ እየተሰራ መሆኑን ባለስልጣኑ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል፡፡

ቃሊቲን ጨምሮ በመዲናዋ ባሉት መናሃሪያዎች የሚከፋፈሉ አስር ሮቶዎች ተገዝተው የማከፋፈል ስራ በዛሬው እለት መጀመሩን ሰምተናል፡፡

ከአዲስ አበባ ተነስተው ወደ ተለያዩ የሃገሪቱ ክልሎች የሚጓዙ ሃገር አቋራጭ ተሸከራካሪዎች ላይ ባይረሱን ለመከላከል የሚረዱ ቁሳቁሶች በየመናሃኒያ ጣቢያው ተደራሽ እንዲሆኑ ለማድረግ ሮቶዎቹን የመግዛት ስራ ተጠናቆ ወደ መናሃሪያዎቹ የማጓጓዝ ስራ መጀመሩን ሰምተናል፡፡

በትራንስፖርት ባስልጣን የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ይግዛው ዳኘው ለጣቢያችን እንደነገሩን ከሁሉም በላይ በሽታውን ለመከላከል በትራንስፖርት አገልግሎቱ ላይ የተለያዩ የመከላከያ ስራዎች በመሰራት ላይ እንገኛለን ብለውናል፡፡

አገር አቋራጭ ተሸከርካራች ላይ ህዝቡ ለመሳፈር ወደየመናሃሪያው ሲመጣ እጁን ታጥቦ እንዲሳፈር በማሰብ የተለያዩ የጥንቃቄ ቁሳቁሶች ወደ ስፍራው እየተላኩ መሆኑንም ነግረውናል፡፡

ተቋሙ በምክትል ዋና ዳሬክተር የሚመራና ዘጠኝ አባላት ያሉት ኮሚቴ አቋቋሞ ወደ ስራ እንደተገባና በቀጣይም በትራንስፖርቱ ላይ ተግባዊ የሚደረጉ የመከላከያ ስራዎች ተግባራዊ እንደሚሆኑም ሰምተናል፡፡

Via:- Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa
የብልጽግና ፓርቲ የትግራይ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱን በመቀለ ከተማ መክፈቱን አስታወቀ። ፓርቲው አቶ ነብዩ ስሑልሚካኤል የብልጽግና ፓርቲ የትግራይ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሀላፊ እንዲሆኑም ሹሟል።

@Yenetube @Fikerassefa
አሜሪካ ኤምባሲ ክፍት መሆኑን ለጠየቃችሁን

አሜሪካ ኤምባሲ ዛሬ ክፍት መሆኑን አረጋግጠናል። መሄድ ትችላላችሁ።

@Yenetube @Fikerassefa
ኮሮና ቫይረስ በኢራን :-

- ዛሬ 135 ሰው ሞቷል

- ዛሬ በቫይረሱ የተጠቁ 1,178 ሰዎች

- ኢራን በቫይረሱ ምክንያት የሞቱ ቁጥራቸው 988 ደርሷል።

- ኢራን በአጠቃላይ በቫይረሱ የተጠቁ 16,169 ደርሷል።

@Yenetube @FikerAssefa
ኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ

በነጻ የስልክ መስመር 8335 ላይ አጋጥሞ የነበረው ችግር የተቃለለ ሲሆን አሁን መስመሩ አገልግሎት መስጠት የጀምረ ሲሆን በተጨማሪም 952 ንም፡፡ መጠቀም ይቻላል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
ኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ልታውጅ እንደምትችል የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

#Ethiocoronavirus
@Yenetube @Fikerassefa
YeneTube
አሜሪካ ኤምባሲ ክፍት መሆኑን ለጠየቃችሁን አሜሪካ ኤምባሲ ዛሬ ክፍት መሆኑን አረጋግጠናል። መሄድ ትችላላችሁ። @Yenetube @Fikerassefa
The US Embassy Addis is suspending immigrant and non-immigrant visa appointments through March 27."We will resume routine visa services as soon as possible but are unable to provide a specific date at this time",the embassy said in a statement.

For emerg appointment-251-115 582424.
#ከቫይረሱ_ነፃ_ነው_ምርጫ ቦርድ

በኮሮና ቫይረስ ምልክቶች ተጠርጥሮ፤ ምርመራ የተደረገለት የምርጫ ቦርድ የቴክኒክ ድጋፍ ሰጪ የውጭ ሀገር ባለሙያ፤ ከቫይረሱ ነጻ መሆኑ ተረጋግጧል። ቦርዱ ለቅድመ ጥንቃቄ በሚል ሰራተኞቹ ከቤታቸው ሆነው ስራቸውን እንዲያከናውኑ አድርጎ ነበር።

@Yenetube @Fikerassefa
ከአንድ ወር በፊት ጭንቅ ላይ የነበሩት በቻይና የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ተማሪዎች አሁን ከጭንቅ ወጥተው ለኢትዮጵያዊያን ምክራቸውን መለገስ ጀምረዋል።

ተማሪዎቹ ተረጋጉ ኮሮናን ለመከላከል ድንጋጤ ሳይሆን ጥንቃቄ ማድረግ ነዉ የሚበጀዉ እያሉ ነዉ።

ዕዉቀትን ፍለጋ ከአገራቸዉ እና ከቤተቦቻቸዉ ተለይተዉ በአገረ ቻይና ዉሃን ግዛት ትምህርታቸዉን ሚከታተሉ ከ300 በላይ ኢትዮጵያዉያን ይገኛሉ፡፡

ታዲያ ዛሬ ላይ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ስጋት የሆነዉ የኮሮና ቫይረስ መነሻ ቦታዉ እነዚህ ኢትዮጵያዉያን ዜጎች በከተሙበት በዉሃን ግዛት ነበር፡፡

የኮሮና ቫይረስ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሰራጨ መምጣቱን ተከትሎም የቻይና መንግስት ምንም አይነት እንቅስቃሴ በዚች ግዛት እንዳይደረግ ዉሳኔ ማሳለፉ የሚታወስ ሲሆን እነዚህ ኢትዮጵያዉያን ተማሪዎች ቤታቸዉ ዘግተዉ ከተቀመጡ እነሆ 2 ወራት አስቆጥረዋል፡፡

አሁን ላይ ኮሮና ከቻይናም አልፎ መላዉ አለምን እያደረሰ ሲሆን ኢትዮጵያም ገብቷል፡፡

በዚህም ምክንያት በህብረተሰቡ ዘንድ አንዳንድ አላስፈላጊ ድንጋጤ እና ፍራቻዎች እየተስተዋሉ ይገኛሉ፡፡

እኛም በቫይረሱ መነሻ በሆነችዉ ዉሃን ግዛት የሚኖሩ ኢትዮጵያዉን ተማሪዎች ችግሩን እንዴት ተቋቁመዉ ዛሬ ያሉበት ደረጃ ላይ እንደደረሱ ጠይቀናል፡፡

በግዛቲቱ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማህበር ሊቀመንበር ወይዘሮ ዛህራ አብዱል ሃዲ ያሳለፉትን ተሞክሮ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ስትናገር ፤ከኮሮና ቫይረስ እንዴት እራስን መጠበቅ እንደሚቻል እኛ ጥሩ ምሳሌ ነን ብላለች፡፡

“ቫይረሱ የተነሳባት በዉሃን ግዛት ብንገኝም ጥንቃቄ በተሞላዉ መንገድ እራሳችን በመጠበቃችን ዛሬ ላይ ደርሰናል” ፤ለዚህም ኢትዮጵያዉያን ከድንጋጤ ተላቀዉ መከላከሉ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ጠይቃለች፡፡

በሽታዉን ለመከላከል ሲባል ተማሪዎቹ ለ2 ወራት በቤት ዉስጥ እንድንቆይ በመደረጋችን ከቫይረሱ አምልጠናል በዚህም አንድም ተማሪ በቫይረሱ እንዳልተያዘ አስታዉቃለች፡፡

አሁን ላይ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በመላዉ አለም እየጨመረ ቢመጣም በአገረ ቻይና ግን እየቀነሰ መምጣቱ ይነገራል በዉሃን ከተማ ያለዉ የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ መሻሻል እያሳየ እንደሚገኝ ተማሪዎቹ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

Via:- Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa