የሕወሓት እና የብልፅግና ሃብት ክፍፍል ውዝግብ
የኢሕአዴግን ንብረት ለብልፅግና እና ሕወሓት ለማከፋፈል በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተላለፈውን የእኩል ድርሻ ክፍፍል ውሳኔ እንደማይቀበለው ብልፅግና ፓርቲ አስታወቀ።የአባሎችችን ቁጥር የተለያየ በሆነበትና ‹‹እኩል ባላዋጣንበት፣ እኩል የምንካፈልብት አግባብ የለም›› ያለው ብልፅግና 25 በመቶ ለሕወሓት አይገባም ሲል ለምርጫ ቦርድ አቤቱታ አቅርቦ እየታየለት መሆኑን ለአሐዱ ቴሌቪዥን ተናግሯል።
የፖለቲካ ፓርቲዎች አስተዳዳሪው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም የኢሕአዴግ ወራሽነትን በተመለከተ ለቀረበለት ጥያቄ፤ 3ቱ ድርጅቶች (የቀድሞዎቹ አዴፓ፣ ኦዴፓ እና ደኢሕዴን) ኢሕአዴግ ያፈራውን 75 በመቶ እንዲወርሱና ቀሪው 25 በመቶ ለሕወሓት እንዲሰጥ ሲል መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡በጋራ እያላችሁ ያፈራችሁትን ንብረት ተካፈላችሁወይ ሲል አሐዱ ቴሌቪዥኝ የጠየቀው ብልፅግና የንብረት ክፍፍሉ ብዙ ውስብስብ ጉዳዮች አሉበት ብሏል፡፡ ንብረቱ ኦዲት መደረግ ስለሚገባው ክፍፍሉ መዘግየቱንም አሳውቋል፡፡በተያያዘ ብልፅግናን ተቀላቅለው የትግራይ ቅርንጫፍን መሰረቱ የተባሉት የሕወሓት የቀድሞ አመራርና አባላት በንብረት ክፍፍሉ ላይ የሚኖራው ድርሻ እንዴት ይስተናገዳል የተባለው ብልፅግና ገና እያሰብኩበት ነው፤ አልተወሰነም ብሏል፡፡
ምንጭ:አሐዱ ቴሌቪዥን
@YeneTube @FikerAssefa

ኢትዮጵያ የአመቱ ምርጥ የቅድመ ታሪክ ቅሪተ አካልና መካነ ቅርስ ሥፍራዎች መዳረሻ ሀገር በሚል በጀርመን በየአመቱ በሚካሄደው የፓትዋ ሽልማት አሸናፊ ሆነች።
የፓሲፊክ አካባቢ ተጓዦች ማህበር (ፓትዋ) ሽልማት በየአመቱ በጀርመን በሚካሄደው የበርሊን የዓለም የቱሪዝም ንግድ ትርዒት ላይ የሚሰጥ የእውቅና ስነ ስርዓት ነው።
በዘንድሮው የፓትዋ ሽልማት በተለያዩ ዘርፎች 13 የዓለም ሀገራት አሸናፊ መሆናቸውን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያም የቅድመ ታሪክ ቅሪተ አካልና መካነ ቅርስ ሥፍራዎች መዳረሻ ሀገር በሚለው ዘርፍ በቀዳሚነት አሸንፋለች።
በሌላ በኩል የኢፌዴሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው ከሰሃራ በታች ምርጥ የቱሪዝም ሚኒስትር በሚል ተመርጠዋል።
Via:- FBC

YeneTube
አንጋፋው መኢአድ እና ባልደራስ ሊዋሀዱ ነው በእስክንድር ነጋ የተመሰረተው ባልደራስ እና በአቶ ማሙሸት አማረ የሚመራው የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ «መኢአድ” ነገ አርብ የካቲት 27,2012 አዲስ አበባ ላይ ጋዜጠኞችን ጠርተው የውህደት ፊርማቸውን እንደሚያደርጉ ፊደል ፓስት የደረሰው መረጃ ያሳያል። ውህደታቸው በመጪው ነሀሴ ለሚደረገው ብሔራዊ ምርጫ ጠንከር እና ገዘፍ ብሎ ለመፎካከር ያለመ ነው።…
መኢአድ እና ባልደራስ በመዋሃድ በስምምነት የጋራ ሰነድ ፈርመዋል ። በአሁኑ ሰአትም በአገራዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ እየሰጡ ነው በመግለጫው የሰሞኑ የመገናኛ በዙሃን ትኩረት የሆነው የህዳሴ ግድብን ጨምሮ ሰፋፊ ሃገራዊ ጉዳዮች ተነስተዋል ሙሉ መግለጫውን በዩትዩብ ቻናላችን ከደቂቃዎች በኋላ እናጋራቹሃለን።
@YeneTube @Fikerassefa
@YeneTube @Fikerassefa
የታላቁ ኅዳሴ ግድብ የድጋፍ ሰልፍ!
ዩናይትድ ስቴትስ እና የዓለም ባንክ በታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ላይ የያዙትን አቋምና ጣልቃ ገብነት የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ ሊደረግ ነው።በዚህም በመጋቢት 13 ወይም 21 በአገር አቀፍ ደረጃ ሊደረግ የታሰበው ትዕይንተ ሕዝብ፤ በሕግ ባለሙያዎች፣ በዲያስፖራው ማኅበረሰብ ተወካዮች እና በአርቲስቶች አስተባባሪነት እንደሚካሄድ ተነግሯል።
ምንጭ:አሐዱ ቴሌቪዥን
@YeneTube @FikerAssefa
ዩናይትድ ስቴትስ እና የዓለም ባንክ በታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ላይ የያዙትን አቋምና ጣልቃ ገብነት የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ ሊደረግ ነው።በዚህም በመጋቢት 13 ወይም 21 በአገር አቀፍ ደረጃ ሊደረግ የታሰበው ትዕይንተ ሕዝብ፤ በሕግ ባለሙያዎች፣ በዲያስፖራው ማኅበረሰብ ተወካዮች እና በአርቲስቶች አስተባባሪነት እንደሚካሄድ ተነግሯል።
ምንጭ:አሐዱ ቴሌቪዥን
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ ዉሳኔን ኮንና የሱዳንን አቋም አድንቃለች።
የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀዉ አረብ ሊግ በህዳሴ ግድብ ላይ የግብፅ አቋም ያለምንም ማስረጃ ማፅደቁ ፍረደ ገምድልነት ነዉ ብሏል፡፡የአረብ ሊግ ዉሳኔ የታላቁን ህዳሴ ግድብ እዉነታ ያልተረዳ እንደሆነም ኢትጵዮጵያ ወቅሳላች፡፡
ሱዳን የአረብ ሊግ ያስተላለፈዉን ዉሳኔ መቃወሟም የአገሪቱ ወጥ አቋም እና ምክንያታዊነት የሚገልፅ ነዉ ብሏል የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫዉ፡፡ለዚህም የኢትዮጵያ መንግስት ለሱዳን መንግስት እና ህዝብ ያለዉን አድናቆት እና ክብር ገልጧል፡፡
ኢትዮጵያ ከአረቡ አለም ጋር በርካታ ዘመናትን ያስቆጠረ የታሪክ፤የባህል ፤የንግድእና በሌሎችም ዘርፎች ጥሩ ግንኙነት አላት ያለዉ መግለጫዉ በአንዲት ሉአላዊት አገር ላይ እንደዚህ አይነት ዉሳኔ ሊጉ ማስተላለፉ ያሳዝናል ብሏል፡፡ የአሁኑ ዉሳኔም የአረብ ሊግ በአለም አቀፍ ደረጃ ለሠላም ለፍትህና እና ለትብብረ የሚኖረዉን ሚና ጥያቄ ምልክት ዉስጥ የሚከት እና ታማኝነቱ ላይ ጥርጣሬ የሚያስነሳ እንደሆነም እንስቷል፡፡
ኢትዮጵያ የራሷን ሀብት የአሁኑን እና የመጪዉን ትዉልድ ተጠቃሚ ለማድረግ በፍትሃዊ እና የአለም አቀፉን የዉሃ ሀብት አጠቃቀም መመሪያን ተከትላ ግድቡን እንደምትገነባም አስታዉቃለች፡፡በመጨረሻም የአረብ ሊግ የወሰነዉን ዉሳኔ መልሶ በመርመር ፍረደ ገምድልነትን ትቶ ሚዛናዊ አመለካከት እንደሚኖረዉ ኢትዮጵያ ሙሉ እምነት አለኝ ብላለች፡፡
Via Ethio FM

ባልደራስ እና መኢአድ ተዋሀዱ እንዲሁም በአባይ ጉዳይ አቋማቸውን ገለፁ።
መግለጫው ላይ ተገኝተን ያጠናከርነውን ዘገባ ተመልከቱት።
⬇️⬇️⬇️
https://youtu.be/SFc5obuw8Jw
መግለጫው ላይ ተገኝተን ያጠናከርነውን ዘገባ ተመልከቱት።
⬇️⬇️⬇️
https://youtu.be/SFc5obuw8Jw
የአሜሪካው ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤይድ) በምስራቅ አፍሪካ የበረሃ አንበጣን ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት ተጨማሪ የ10 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ይፋ አደረገ።
@YeneTube @Fikerassefa
@YeneTube @Fikerassefa
ከደምቢዶሎ ዩንቨርሲቲ የታገትን ተማሪዎች ነን በማለት በሀሰት ሕብረተሰቡን አደናግረዋል የተባሉ ሁለት ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ
ከደንቢ ደሎ ዩንቨርስቲ የታገትን ተማሪዎች እኛ ነን በማለት የተሳሳተ የሀሰት ወሬ አውርተዋል ተብለው ተጠርጥረው የካቲት 3 ከባህርዳር ከተማ ተይዘው ለፌደራል ፖሊስ ተላልፈው የተሰጡት ና በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በእስር ላይ የሚገኙት የአንደኛ ደረጃ እና የሁለተኛ ደረጃ 2 ሴት ተማሪዎች ቅድስት በጋሻው እና ሸዋዬ ጌትነት ለ 3 ጊዜ በአራዳ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበው የ10 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተሰጠ።
የካቲት 25 ረፋድ ላይ በአራዳ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበው “ፖሊስ ምርመራዬን አልጨረስኩም፣ የምስክር ቃል እቀበላለው፣ተባባሪዎቻቸውን የነበሩትን መያዝ አለብኝ ፣የስልክ ምርመራ እንዲሰጠኝ ወደ ኢንሳ ደብዳቤ ልኬ መልስ እየጠበኩ ስለሆነ ተጨማሪ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ይሰጠኝ ” ሲል ችሎቱን ጠይቋል።
ጠበቆች በበኩላቸው ፖሊስ ልጆቹን ከተረከበበት ቀን ጀምሮ ተመሳሳይ ስራዎችን ነው እየሰራ ያለው ስለዚ የጠየቀው የምርመራ ጊዜ ሊሰጠው አይገባም ደንበኞቻችንን አስሮ ለማቆየት ነው። ፖሊስ በቂ ስራ አልሰራም ስለዚ የጠየቀው የምርመራ ጊዜ መሰጠት የለበትም ሲሉ የተከራክረዋል አክውም ፖሊስ ተጨማሪ ስራ ይቀረኛል የሚል ከሆነ ተጠርጣሪዎቹ በዋስትና ወተው ክሳቸውን ይከታተሉ ሲሉ ተከራክረዋል።
የግራ ቀኙን ክርክር የሰማው ችሎት የፖሊስ የምርመራ መዝገብ አይቶ ውሳኔ ለመስጠት ለየካቲት 27 2012 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቶ ነበር ።
ዛሬ ረፋድ ላይ አራዳ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮ ችሎት የፖሊስ መዝገብን ተመልክቶ ከጉዳዩ ውስብስብነት ና ክብደት አንፃር ተጠርጣሪዎቹ በዋስትና ቢወጡ ተመልሰው ይመጣሉ ብለን ስለማንገምት 10 ተጨማሪ የምርመራ ግዜ ለፖሊስ በመስጠት ለመጋቢት 7/ 2012 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል።
ተጠርጣሪዎቹ ለ3 ጊዜ በአራዳ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮ ችሎት የቀርቡ ሲሆን የመጀመሪያ ችሎታቸውን የካቲት 4/ 2012 ቀርበው 11ቀን የምርመራ ጊዜ ለፖሊስ የተፈቀደ ሲሆን በሁለተኛ የጊዜ ቀጠሮ የካቲት 15/ 2012 ፖሊስ ምርመራዬን አልጨረስኩም በማለቱ ችሎቱ ተጨማሪ የ8 ቀን የምርመራ ጊዜ ሰቶ ለየካቲት 25 2012 ተለዋጭ ቀጠሮ እንደተሰጠ የጊዜ ቀጠሮ መዝገቡ ያስረዳል።
Via:- ዋዜማ ራዲዮ
@Yenetube @Fikerassefa

❤1
Forwarded from የሀ Digital Art
Taking place over two days Saturday 7th & Sunday 8th March. https://www.facebook.com/events/848716598903708/
Brought to you in partnership with Noah Real Estate, Rainbow Bed Foam and Beyond, British Council Ethiopia, Eternal Media & Communication, @artsmailinglist @saryanevents, EthioCrypto, @yenetube, @Yegarawebhost @johnnyvideoproduction, @officialkuriftuwaterpark, Bored Cellphone Addis Ababa, @woinidigitalart, @jayineedarts— At Noah Plaza, Addis Ababa, Ethiopia.
@yehadigitalart

የኮሮና ቫይረስ በአሜሪካ የተፈበረከ ሊሆን እንደሚችል የኢራን ባለስልጠናት ገለፁ
የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] በአሜሪካ የተፈበረከ ወይም ከዚህ ሁሉ እልቂት ጀርባ አሜሪካ ዋናዋ ተዋናይ ልትሆን እንደምትችል የኢራኑ ብሔራዊ አብዮት ጠባቂ ሃይል ኃላፊ መግለፃቸው ተጠቆመ።
'አርቲ' (RT) የተባለው የሩሲያ የዜና ተቋም፣ የኢራን ባለስልጣናትን ፍንጭ አድርጎ እንደዘገበው የኮሮና ቫይረስ አሜሪካ፣ ኢራንና ቻይናን ለማጥፋት የፈጠረችው በሽታ ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬ እንዳላቸው ዘግቧል። የኢራን ባለስልጣናት ጉዳዩን ይፋ ለማድረግ ተጨባጭ ማስረጃ በማፈላለግ ላይ መሆናቸውንም ዘገባው አስታውቋል፡፡
የኢራኑ ብሔራዊ አብዮት ጠባቂ ኃይል ኃላፊ ሁሴን ሳላም እንደገለጹት ኢራን በቫይረሱ ሳቢያ ለሚደርስባት እንግልትና ስቃይ አትሸነፍም ያሉ ሲሆን የአሜሪካን ሴራ የሚያጋልጥ መረጃ እጃችን ሲገባ የበደሏን አፀፋ እንመልሳለን ሲሉም ተደምጠዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የዓለም ጤና ድርጅት የቫይረሱን ትክክለኛ መነሻ ምክንያት በተመለከተ የደረሰበት ድምዳሜ የለም።
Via:- ASHAM TV

የአለም ባንክ ለአዲስ አበባ ከተማ ተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብር 25 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ለመስጠት ወሰነ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በፌስቡክ ገፃቸው እንዳስታወቁት፥ የገንዘብ ድጋፉ ለትምህርት ቤት ምገባ መርሃ ግብር ማህበራዊ መሰረተ ልማት ለማቅረብ የሚውል ነው።ዓለም ባንክ ያደረገው የገንዘብ ድጋፍ የከተማ ልማት ሴፍቲ ኔት መርሃ ግብር አካል መሆኑንም አስታውቀዋል።
Via FBC

በኮሮና ቫይረስ እየተሰቃየች ላለችው ቻይና ድጋፍ ለማድረግ 22 ኢትዮጵያዊያን ወደ ዉሃን ከተማ ሊያቀኑ ነው።
ወደ ቻይና ለማቅናት የተሰባሰበው ይህ 22 አባላት ያሉት ይህ ቡድን ከህክምና ጀምሮ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የተሰማሩ ናቸው።ቡድኑም ኮሮና ቫይረስ ለመጀመሪያ ጊዜ በተከሰተባት ውሃን ከተማ ለማቅናት ማሰቡን የቡድኑ አስተባባሪ አቶ ጸጋ ለገሰ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግሯል።እንደ ጸጋ ገለጻ ከሆነ ይህ ቡድን ወደ ቻይና ውሃን ከተማ በማቅናት ለቻይና አለንልሽ አብረን ነን የሚል መልዕክት ከማስተላፍ ባለፈ ለተጎጂዎች የህክምና፣የጉልበት ፣የሞራል እና ሌሎች ድጋፎችን ለማስተላለፍ አልሟል።
ቡድኑ ለዚህ አላማውም ገንዘብ ከአንድ የግል ኩባንያ ድጋፍ ማግኘቱን የገለጸ ሲሆን ለጊዜው ፓስፖርት ያላችውን ሰዎች ለዚህ ጉዞ መምረጡን አስታውቋል።የቪዛ እና ሌሎች ድጋፎችን ለማግኘት ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት እና ለቻይና ኢምባሲ ማመልከቻ አስገብተው በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን አስተባባሪው ተናግሯል።22 አባላት ያለው ይህ ቡድን ወደ ቻይና የሚያደርገው ጉዞ የአገራትን ግንኙነት ለማሳደግ እንደሚጠቅም አስተባባሪው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ( ቅንጅት) መስራች አባላት ስም ዝርዝርን እንዲያጣራ ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ጥያቄ አቀረበ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቀድሞ አዋጅ ተመዝግበው የሚገኙ የፓለቲካ ፓርቲዎች በአዲሱ ህግ ላይ ተቀመጡትን መስፈርቶች እንዲያሟሉ መጠየቁ ይታወሳል፡፡ በዚህም መሰረት ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ በአዲሱ አዋጅ በተደነገገው መሰረት 7,214 ( ሰባት ሺህ ሁለት መቶ አስራ አራት) ተጨማሪ መስራች የፓርቲ አባላትን አስፈርሞ እስከ መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ እነዲያቀርብ ተገልጾለት ነበር፡፡
ፓርቲው ጥር 26 ቀን 2012 ዓ.ም ከ8 ክልሎች የተሰበሰበ የመስራች አባላት ፊርማ የያዘ ሰነድ ለቦርዱ አቀርቧል፡፡ በመሆኑም የቀረበው ሰነድ ላይ የሚከተሉትን ቦርዱ አስተውሏል፡፡
-ቦርዱ ከእያንዳንዱ ገጽ ላይ በተወሰደ እና ወካይ ሊሆን የሚችል ናሙና ባደረገው ማጣራት፣ ጥሪ ካደረገባላቸው 50 ፈራሚዎች መካከል፣ አንዱ ብቻ ፈርሞ ሲገኝ 49ኙ ግን በተለያየ ምክንያት ፊርማቸውን አለማኖራቸውን አረጋግጧል።( አብዛኛው የተሳሳተ ስልክ ነው፣ አልፈረምኩም የሚሉ ምላሾችና የማይሰራ መስመር ሆነው ተገኝተዋል)
-የፓርቲው ማመልከቻ ላይ የፓርቲው ሊቀመንበር ቢፈርሙም፣ የተሰበሰበው ፊርማ ቃለ መሃላ ላይ የፈረመው ሌላ ግለሰብ መሆኑን፣ ሃላፊነቱም አለመገለጹን
-የአያት ስም ያላስመዘገቡ፣ ስለአባልነታቸው በፊርማቸው ያላረጋገጡ፣ እድሜ፣ ጾታ፣ የምዝገባ ቀናቸው የማይታወቅ ፈራሚ ስሞችም በጉልህ ተገኝተዋል፡፡
በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 እና አዋጁን ለማስፈጸም የወጣው አዋጅ መሰረት በአባልነት ያልተመዘገበን ሰው የተመዘገበ በማስመሰል የሌለን ሰው እንዳለ ማስመሰል ሃሰተኛ ስምና ፊርማ ማዘጋጀት በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡ በአዋጁ መሰረት ቦርዱ ሊወስድ ከሚችላቸው ምዝገባን ከመከልከልና ከማገድ በተጨማሪ አግባብ ባለው የወንጀል ህግ መሰረትም ሊጠየቅ እንደሚችል የህጉ ድንጋጌዎች ያዛሉ፡፡
ቦርዱ ከላይ ከተጠቀሱት ምክንያቶች በመነሳት ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ( ቅንጅት) ያቀረባቸው የመስራች አባላት ፊርማ ስም ትክክለኛ ለመሆናቸው ማረጋገጥ አልቻለም፡፡ ስለዚህም የፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን ጉዳዩን ተመልክቶ ህጋዊ ማጣራት እንዲያደርግ በዛሬው እለት የካቲት 27 ቀን 2012 ዓ.ም አስተላልፏል፡፡
- ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

በውሃና በለስላሳ ምርቶች ላይ የታዩ አላግባብ የዋጋ ጭማሪዎች ማሰተካከያ እንዲደረግባቸው ተጠየቀ!
ተሻሽሎ የወጣው የኤክሳስ ታክስ አዋጅ ከጸደቀ ወዲህ ለገበያ የሚቀርቡ የውሃ እና የስላሳ ምርቶች ላይ ያለአግባብ ጭማሪ መስተዋሉን ተከተሎ የገንዘብ ፣ የገቢዎች እና የንግድ ሚኒስቴሮች ከአምራች ድርጅቶች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡የንግድ ሚኒስቴር ባጠናው ጥናት መሰረትምኤክሳይስ ታክስ አዋጁ ከወጣ በኋላ ከ6 እስከ 7 ብር ይሽጥ የነበረው ግማሽ ሊትር ውሃ ወደ 9 ብር ማሻቀቡ ተገልጿል፡፡በሌላም በኩል ከ10 እስከ 12 ብር የሚሸጡ የለስላሳ መጠጦች አሁን ከ15 እስከ 19 ብር በመሸጥ ላይ እንደሚገኙ በጥናቱ ተመላክቷል፡፡
የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ ÷ የኤክሳስ ታክስ ዓላማ ከዚህ በፊት በማምረቻ ወጪ ላይ የተመሰረተውን አሰራር በመቀየር ሲፈጠሩ የነበሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች በመቅረፍ ገቢ በአግባቡ መሰብሰብ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡ነገር ግን በታክሱ ከማምረቻ ወጪ ወደ የፋብሪካ ማምረቻ ዋጋ መቀየሩን እንደምክንያት በመውሰድ በአንዳንድ ገበያዎች ላይ በተለይም በታሸገ ውሃና ለስላሳ የመሸጫ ዋጋ ላይ አላግባብ የሆኑ የዋጋ ጭማሪዎች በመታየታቸው ሊታረሙ እንደሚገባ ሚኒስትር ዴኤታው አሳስበዋል፡፡
በተለይም የውሃ ዘርፍ ለማበረታታና የፕላስቲክ የማሸጊያዎች አካባቢዎችን እንዳይበክሉ ለማድረግ እየተወሰዱ ያሉ መልካም እርምጃዎች ከግንዛቤ በማስገባት በጣም ዝቅተኛ ኤክሳስ ታክስ የተጣለበት ዘርፍ ከመሆኑ አንፃር የዋጋ ጭማሪ መኖር የለበትም ተብሏል፡፡
አያይዘውም ዘርፎቹ ያጋጠሟቸው ችግሮች ካሉ በሂደት ከመንግስት ጋር በመሆን ችግሮቹን ለመፍታት በቅርበት መስራት እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል፡፡የውሃ እና የለስላሳ አምራች ድርጅቶች ማህበር ፕሬዘዳንት ኢንጅነር ጌትነት በላይ በበኩላቸው ÷በኤክሳይስ ታክስ አዋጅ ምክንያት ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ እንዳለተደረገ ገልጸዋል፡፡በአንጻሩ በአንድ እሽግ ምርት ላይ 60 ብር ይሸጥ የነበረው 56 ብር እየተሸጠ መገኘቱን ጠቁመው፥ በገበያ ሰንሰለት ላይ የሚታዩ ችግሮችን በመፈተሸ ማስተካከያ እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡

ባለፉት ሁለት ቀናት የካቲት 25 እና 26 ቀን 2012 ከታንዛኒያ ኪሊማንጃሮ እና ማንኛራ ከተባሉ ክልሎች ከ እስር ቤት 172 ዜጎቻችን ተፈትተው ወደ አገራቸው ተመልሰዋል ።
ምንጭ: በዳሬሳላም የኢትዮጵያ ኤምባሲ
@YeneTube @FikerAssefa
ምንጭ: በዳሬሳላም የኢትዮጵያ ኤምባሲ
@YeneTube @FikerAssefa
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEmpJPx72XxnzEFGQg
🔖እናስተዋዉቅዎ! AmAzON BrAnD® ገበያ
ሱቅ ለሱቅ መሄድ ሳይጠበቅቦት ባሉበት ቦታ ሆነው ውስን እቃዎችን በማይታመን ዋጋ ሚገኙበትን ማወቅ ይፈልጋሉ እንግዲያውንስ ይሄን የቴሌግራም ቻናላችንን ሊንክ በመጫን የፈለጉትን ይምረጡ ይዘዙ
.
ብራንድ ጫማዎች የወንድም የሴትም
ብራንድ ልብሶች የወንድም የሴትም
ብራንድ ሸሚዞች ቲሸርቶች
ብራንድ ቱታዎች ሹራቦች እንዲሁም ጃኬቶች በወንድም በሴትም
ብራንድ ቦርሳዎች
የእጅ ጌጣጌጦች
ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
ሀገር ውስጥ ውስን የሆኑ መዋብያ እቃዎች ሽቶዎች
.
እንዲሁም በግል የቴሌግራም አካውንት ማዘዝ የምትፈልጉ እቺን ሊንክ በመጫን ያናግሩን @KALID67 እንዲሁም በስልክ ቁጥራችን +251954833467 ደውለው ይዘዙን
.
በተጨማሪም አዲስ አበባ ለምትገኙ ደንበኞቻችን ይዘዙን ያሉበት ድረስ እናመጣለን ክፍለ ሀገር ለምትገኙ ደንበኞቻችን ባዘዙን በ48ሰአት ውስጥ በፖስታ ቤት ወይም በሹፌር እናደርሳለን ታማኝነት መገለጫችን AmAzON BrAnD® ገበያ
online shopping is always a good idea!!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ በነገው እለት ወደ ዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ ያቀናሉ።
የዞኑ የህዝብ ግኑኝነት መምሪያ እንዳሳወቀው ነገ የካቲት 28/2012 በዞኑ ዋና ከተማ ታርጫ ተገኝተው ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ይወያያሉ።ጠ/ሚሩን ለመቀበልም አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉም ተገልጿል።