YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሹመዋል።

ከዚህ ቀደም የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ሀላፊም ሆነው ሰርተዋል።ከመቀሌ ዮንቨርስቲ በህክምና ትምህርት ዲግሪ ያገኙ ሲሆን ከጣልያኑ ፓርማ ዩንቨርስቲ በአለም አቀፍ ጤና ላይ ያተኮረ ትምህርት ተከታትለው ከስምንት አመት በፊት ሁለተኛ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።

Via:- Tesfay Getnet
@Yenetube @Fikerassefa
ለኢትዮጵያ ክብር ብዙዎች ዋጋ ከፍለዋል ። ይህን በፍጹም አንረሳውም ። ካራማራ ላይ ከጠላት ጋር ተናንቀው ህይወታቸውን ለሀገራቸው ክብር የሰጡ ጀግኖቻችንን እንዘክራለን።

ክብር ለጀግኖቹ !
@YeneTube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ ፕሬዝዳንት እንደተሾመለት ዋዜማ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። አዲሱ ፕሬዝዳንት አቢ ሳኖ ትናንት የሹመት ደብዳቤ የደረሳቸው ሲሆን ዛሬ ስራ እንደሚጀምሩ ይጠበቃል።

Via:- Wazema Radio
@YeneTube @Fikerassefa
የኦጋዴን ጦርነት፡ የሲያድ ባሬ ወረራ ሲታወስ

የኦጋዴን ጦርነት ተብሎ የሚታወቀው በኢትዮጵያና ሶማሊያ መካከል የተደረገው ጦርነት የዛሬ 42 ዓመት የካቲት 26/1970 ዓ.ም. ነበር የተጠናቀቀው።

በ1966 ዓ.ም ሶማሊያ የአረብ ሊግን ተቀላቀለች። በወቅቱ የሶማሊያ መሪ የነበረው ሜጀር ጄኔራል ሲያድ ባሬ ኢትዮጵያን ወረረ። ጦርነቱ የተጀመረ ሰሞን የሲያድ ባሬ [ዚያድ ባሬ] ጦር በሶቪዬት ኅብረት ይደገፍ ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥት ደግሞ ከዩናይትስ ስቴትስ ጋር ወዳጅነት አለው። በወቅቱ በቀዝቃዛ ጦርነት ውስጥ የነበሩት ሶቪዬት ኅብረትና አሜሪካ ምሥራቅ አፍሪካ ገቡ።

https://www.bbc.com/amharic/amp/news-51749412?__twitter_impression=true
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ከዓለም የኢንተርኔት ሶሳይቲ ፕሬዝዳንት አንድሪው ሱሊቫን ጋር በጋራ ለመስራት በሚያስችሏቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ፡፡

ከውይይቱ ጎን ለጎን ከዓለም አቀፍ ኢንተርኔት ሶሳይቲ በመጡ የቴክኒካል ባለሙያዎች ለኢመደኤ ሠራተኞች በዓለም አቀፍ በይነ-መረብ እና ደህንነት ዙሪያ ግንዛቤ ሊያዝባቸውና ጥንቃቄ ሊደረግባቸው በሚገቡ ጉዳዮች ላይ ገለጻ ተሰጥቷል፡፡
Via:- Elu
@Yenetube @Fikerassefa
በአዲስ አበባ ከተማም 33 ማዕከላት በኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ ሲስተም የተገናኙ ሲሆን፤ ማንኛውም ደንበኛ የቅድመና የድህረ ክፍያ አገልግሎቶች በየትኛውም ማዕከል ማግኘት ይችላል፡፡

Via:- EEU
@YeneTube @Fikerassefa
ከዚያድ ባሬ መራሹ የሶማሊያ ወራሪ ኃይል ጋር በነበረን ተጋድሎ ወሳኝ ድል ላስመዘገብንበት የካራማራ ድል በዓል እንኳን አደረሳችሁ።

የ1967ቱ የሶማሊያ ወረራ ሀገራችን ከአብዮት ፍንዳታው ጭጋግ ባልወጣችበትና የእርስ በርስ ግጭት ላይ በነበረችበት ጊዜ የተከሠተ ነው። ኢትዮጵያን የወረሩ አብዛኞቹ ኃይሎች እንደሚሠሩት ስሕተት ዚያድ ባሬም ተሳሳተ። ሀገር የደከመች መስሎት ኢትዮጵያን የማሸነፊያ ጊዜ የደረሰለት መሰለው። በዚህ የተሳሳተ ስሌት ተመርቶ ወረራውን ፈጸመ። በመጀመሪያ አካባቢ እንዳሰበውም የጎላ መከላከል ሳይገጥመው ሰፊ የሀገራችንን መሬት ማካለል ችሎ ነበር።

ነገር ግን ኢትዮጵያውያን እንደፍግ ተኝተው እንደ እቶን በተነሡ ጊዜ ምን እንደሚያደርጉ በዚህ ወረራ ጊዜ ታየ። በአጭር ጊዜ “የእናት ሀገር ጥሪ” የተሰባሰቡ፣ በቂ የሥልጠናም ሆነ የዝግጅት ሁኔታ ያልነበራቸው፣ ነገር ግን ከየትም የማይበደሩት የሀገር ፍቅርና የማሸነፍ ወኔ ያላቸው ውድ ኢትዮጵያውያን ወረራውን በስኬት መቀልበስ ቻሉ።
መንግሥታትን በሀገር ውስጥ ክዋኔያቸው በአንድም በሌላም ልንመዝናቸው እንችላለን። ነገር ግን የሀገርን ሉዓላዊነትና ዳር ድንበር ለማስጠበቅ የሚከፈሉ መሥዋዕትነቶች በየትኛውም ዘመን ቢፈጸሙ የሀገራችን ታሪካዊ ኩራት ናቸው።

የደርግ መንግሥትም በአጭር ጊዜ ጥሪ አቅርቦ፣ አሠልጥኖና አደረራጅቶ የሀገርን ክብር ለማስመለስ ያደረገው ተጋድሎና ያስመዘገው ድል የሁላችንም የኢትዮጵያውያን የአልበገር ባይነትና ለሀገር የመሥዋዕትነት የመክፈል ታሪካችን አካል ነው።

ሁሌም በውስጣችን ክፍተት ሲኖር የውጭ ጠላት እንጋብዛለን፤ ስንጠናከር ግን የታፈርንና የተከበርን እንሆናለን። በዚህ አጋጣሚ ከኢትዮጵያውያን ጎን ተሠልፈው የተዋጉትንና ውድ ሕይወታቸውን የሠዉትን የኩባ እና የየመን ወታደሮችን ውለታ ታሪክ ሲዘክረው ይኖራል።

ክብር ሀገርን ለማቆየት ራሳቸውን መሥዋዕት ላደረጉ ኢትዮጵያውያን!
@YeneTube @Fikerassefa
ሱዳን ቅሬታዋን አቀረበች 👌

የአረብ ሊግ ምክር ቤት በኅዳሴ ግድብ ጉዳይ ከግብፅ ጎን እንደሚቆም ለመግለፅ በተዘጋጀ የውሳኔ ሐሳብ ረቂቅ ሱዳን ቅሬታ እንዳላት መግለጿን የመካከለኛው ምሥራቅ የዜና ወኪል ዘገበ።

ሱዳን የአረብ ሊግ በውዝግቡ ጣልቃ ሊገባ አይገባም የሚል አቋም አላት።

በ153ኛው የአረብ ሊግ ምክር ቤት ስብሰባ ያለ ማሻሻያ የጸደቀው የውሳኔ ሐሳብ «ግብፅ በአባይ ወንዝ ላይ ያላት ታሪካዊ መብት ሊሸራረፍ አይገባም» የሚል ነው ተብሏል። ሜና እንደዘገበው የውሳኔ ሐሳቡ ሲጸድቅ ሱዳን በይፋ ቅሬታዋን ገልጻለች

#ሚና #እሸትበቀለ
@Yenetube @Fikerassefa
YeneTube
ሱዳን ቅሬታዋን አቀረበች 👌 የአረብ ሊግ ምክር ቤት በኅዳሴ ግድብ ጉዳይ ከግብፅ ጎን እንደሚቆም ለመግለፅ በተዘጋጀ የውሳኔ ሐሳብ ረቂቅ ሱዳን ቅሬታ እንዳላት መግለጿን የመካከለኛው ምሥራቅ የዜና ወኪል ዘገበ። ሱዳን የአረብ ሊግ በውዝግቡ ጣልቃ ሊገባ አይገባም የሚል አቋም አላት። በ153ኛው የአረብ ሊግ ምክር ቤት ስብሰባ ያለ ማሻሻያ የጸደቀው የውሳኔ ሐሳብ «ግብፅ በአባይ ወንዝ ላይ ያላት ታሪካዊ…
በዘገባው መሠረት ኢትዮጵያ ከታችኛው ተፋሰስ አገሮች ጋር ሚዛናዊ ስምምነት ላይ ሳትደርስ ግድቡን በውኃ ለመሙላትም ሆነ ሥራ ለማስጀመር በተናጠል የምትወስደውን እርምጃ እንደሚቃወም የአረብ ሊግ ገልጿል።

በአሜሪካ እና በዓለም ባንክ የተዘጋጀው ስምምነት «ፍትኃዊ፣ ትክክለኛው እና ሚዛናዊ» እንደሆነ የገለጸው ምክር ቤቱ ኢትዮጵያ እንድትፈርም የአረብ አገሮች እንዲያግባቡ ጥሪ ማቅረቡን ሜና ዘግቧል።

«የውሳኔ ሐሳቡ በሁሉም አገሮች ቢደገፍም ሱዳን ተነሳሽነት አላሳየችም። እንዲያውም ሱዳን በውሳኔ ሐሳቡ ስሟ እንዳይካተት ጠይቃለች» ሲሉ አንድ ጉዳዩን የሚያውቁ የመረጃ ምንጭ መናገራቸውን #ሜና ዘግቧል።

አረብ ሊግ ለግብጽ ጥብቅና የቆመበት የውሳኔ ሐሳብ ጥቅሟን እንደማያስከብር የሞገተችው ሱዳን በውሳኔ ሐሳቡ ምክንያት “በአረቡ ዓለም እና በኢትዮጵያ መካከል ውዝግብ ይቀሰቀሳል” የሚል ሥጋቷን እንደገለጸች የሜና ዘገባ ይጠቁማል።

ምንጭ:- እሸት በቀለ
@Yenetube @Fikerassefa
በአዲስ አበባ ሊካሄድ የነበርው ጉባኤ መተላለፍ

የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን(UNECA) በአዲስ አበባ ሊያካሂድ የነበረውን ጉባኤ ለሌላ ቀጠሮ አስተላለፈ፡፡

አህጉራዊ የኢኮኖሚ ኮሚሽኑ ስብሰባውን ያስተላለፈው በአለም አቀፍ ደረጃ በፍጥነት እየተስፋፋ ባለው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

በቫይረሱ ስጋት ምክንያት ባይተላለፍ ኖሮ ጉባኤው ከ13 ቀናት በኋላ በአዲስ አበባ ሊደረግ እቅድ ተይዞለት እንደነበርም ሰምተናል፡፡

ጉባኤው በአፍሪካ የፋይናንስ፣ የፕላንና የኢኮኖሚ እድገት ሚኒስትሮች ደረጃ ይካሄዳል ተብሎ የነበረ ሲሆን ባለስልጣናቱ በአህጉሪቱ የምጣኔ ሀብት ሁኔታ ላይ ይመክሩበታል ተብሎ ሲጠበቅ እንደነበርም ነው ለማወቅ የተችሏል፡፡

Via:- አዲስ ነገር
@YeneTube @Fikerassefa
በህዳሴ ግድብ ድርድር ላይ ይህን አድርጉ፣ ይህን አታድርጉ፣ ይህንን ፈርሙ የሚል ዓይነት አካሄድ ተገቢነት የሌለውና ድፍረት የተቀላቀለበት አካሄድ” መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለፁ።

ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህን የተናገሩ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ዛሬ 12ኛ መደበኛ ጉባዔውን ባካሄደበት ወቅት ነው።

Via:- FBC
@Yenetube @Fikerassefa
ግብፅ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያን በመቃወም ለዓረብ ሊግ ያቀረበችውን ሰነድ ሱዳን እንደማትቀበለው አስታወቀች

ግብፅ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያን በመቃወም ለዓረብ ሊግ ያቀረበችውን ሰነድ ሱዳን እንደማትቀበለው አስታውቃለች፡፡

በግብጽ ካይሮ በተካሔደው የዓረብ ሊግ 153ኛ የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ግብጽ በግድብ ዙሪያ የሊጉ አባል አገራት ከጎኗ እንዲቆሙ ያቀረበችውን ሰነድ ላይ ነው ሱዳን ያላትን ልዩነት የገለፀችው፡፡

በስብሰባው ላይ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሽኩሪ፣ የአረብ ሀገራት በግድቡ ዙሪያ ከግብጽ እና ሱዳን ጎን እንዲቆሙ ጥያቄ አቅርበው ነበር፡፡

ነገር ግን ሱዳን በህዳሴ ግድብ ላይ የዓረብ ሊግ ከግብፅ ጋር ለመቆም ያሳለፈውን የትብብር ውሳኔም እንደምትቃወም አስታውቃለች፡፡

በግብጽ የተዘጋጀውን ሰነድ እንደማትቀበል ያስታወቀችው ሱዳን ከሰነዱ ስሟ እንዲወጣም አድርጋለች፡፡

ግብጽ ኢትዮጵያን በመወንጀል ለሊጉ ያቀረበችው ረቂቅ የድጋፍ ሰነድ፣ የዓረብ ሀገራት ኢትዮጵያን በመቃወም ከግብጽና ሱዳን ጋር እንዲቆሙ የሚጠይቅ ነው፡፡

የዓረብ ሊግም ግብጽ በአባይ ዉሀ ላይ ያላትን ታሪካዊ መብት የሚደግፍ እና የኢትዮጵያን የተናጥል ውሳኔ የሚኮንን ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ይሁንና ሰነዱ አይመለከተኝም ያለችው ካርቱም ከህዳሴ ግድብ ጋር ተያይዞ ሊጉ ከግብፅ እና ሱዳን ጋር እንዲቆም የሚጠይቀውን ረቂቅ የድጋፍ ሰነድ ውድቅ አድርጋለች፡፡

በግብጽ የቀረበው ሰነድ፣ ኢትዮጵያን የሚያስቀይም ከመሆኑም ባለፈ የሀገሯን ብሔራዊ ጥቅም እንደሚጋፋም ነው ሱዳን በስብሰባው ላይ ያነሳችው፡፡

ሱዳን እንደዚህ ያሉ ሰነዶች እና መግለጫዎች በግድቡ ዙሪያ የሚደረጉ ድርድሮችን ሊያደናቅፉ እና የዓረብ እና የኢትዮጵያን ግንኙነት የበለጠ ሊያበላሹ እንደሚችሉ አንስታ መከራከሯ አግራሞት መጫሩም አህራም የተሰኘው የግብፅ ሚድያ ዘግቧል፡፡

Via:- ETV
@YeneTube @Fikerassefa
🎉የሀ የዲጅታል አርት ክፍት ሊሆን ሁለት ቀን ብቻ ቀርቶታል

ቅዳሜ እና እሁድ ከጠዋት 4:00 ጀምሮ እስከ ቀኑ 11:30 በኖህ ፕላዛ፣ ከአለም ሲኒማ አጠገብ እንገናኝ።

መግቢያ በነፃ

@yehadigitalart
1
ብልፅግና የሀገር ህልውናን ለመታደግ ድርብ ሃላፊነት የወሰደ ፓርቲ ነው ሲሉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።

https://www.fanabc.com/ብልፅግና-የሀገር-ህልውናን-ለመታደግ-ድር/
1
ስለ ኮሮና ቫይረስ የተሳሳቱ መረጃዎች እየተሰራጩ ነውና ተቋማት ግንዛቤ መስጠቱ ላይ ሊበረቱ ይገባል ተባለ፡፡

#Shager FM
@YeneTube @Fikerassefa
1
አንጋፋው መኢአድ እና ባልደራስ ሊዋሀዱ ነው

በእስክንድር ነጋ የተመሰረተው ባልደራስ እና በአቶ ማሙሸት አማረ የሚመራው የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ «መኢአድ” ነገ አርብ የካቲት 27,2012 አዲስ አበባ ላይ ጋዜጠኞችን ጠርተው የውህደት ፊርማቸውን እንደሚያደርጉ ፊደል ፓስት የደረሰው መረጃ ያሳያል።

ውህደታቸው በመጪው ነሀሴ ለሚደረገው ብሔራዊ ምርጫ ጠንከር እና ገዘፍ ብሎ ለመፎካከር ያለመ ነው።
በመኢአድ በኩል  ፕሬዚዳንቱ አቶ ማሙሸት አማረን  ሲወከሉ በባልደራስ ደግሞ አቶ እስክንደር ነጋ ተወክለው ፊርማ ይፈራረማሉ።

Via:- Fidelpost
@YeneTube @Fikerassefa
ኢትዮጵያ ከካይሮ አምባሳደሮቿን በአስቸኳይ ጠራች

ኢትዮጵያ በካይሮ እና ብራስልስ ያሉትን ጨምሮ ስምንት አምባሳደሮቿን በአስቸኳይ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ መጥራቷ ተሰምቷል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም ያገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው ግብጽ፣ ሱዳን፣ አውሮፓ ህብረት (ቤልጂየም) ፣ ሞሮኮ፣ ኩባ፣ አልጀሪያ፣ አውስትራሊያ እና እንግሊዝ ያሉ አምባሳደሮች በአስቸኳይ ወደ አዲስ አበባ መጥተው ሪፖርት እንዲያደርጉ ተነግሯቸዋል ተብሏል።

አምባሳደሮቹ የተጠሩት ኢትዮጵያ በነዚህ አገራት አዲስ አምባሳደሮችን የመሾም ፍላጎት ስላላት እንደሆነ ተገልጿል።

ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የገጠማትን የፖለቲካ አለመረጋጋት መፍትሔ ለመስጠት መጠነ ሰፊ ማሻሻያዎችን በማድረግ ላይ ብትሆንም በግብጽ ላይ ወስዳው የነበረውን የዲፕሎማሲ የበላይነት ማስጠበቅ ተስኗታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የግብጽን የዲፕሎማሲ የበላይነት ለመቀልበስ እና ብሔራዊ ጥቅምን ለማስከበር ለኢትዮጵያ ቁልፍ እና ስትራቴጂክ በሚባሉ አገራት እና ተቋማት አዲስ አምባሳደሮችን ለመመደብ በሒደት ላይ ናቸው።

ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከትናንት በስቲያ ለ15 ሰዎች የአምባሳደርነት ሹመት መስጠታቸው ይታወሳል።

Via:- Ethio FM
@YeneTube @Fikerassefa