YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የሕዳሴን ግድብ ግንባታና የዉኃ ቀሞላልን በተመለከተ ሱዳን ግብፅና ኢትዮጵያ በሚያካሂዱት ድርድር ዩናይትድ ስቴትስ ኢትዮጵያ ላይ እያሳረፈች ያለዉን ጫና ታንሳ ሲሉ በዋሽንግተን እና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን በአሁኑ ሰአት በዩናይትድ ስቴትስ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፊት ለፊት የተቃዉሞ ሰልፍ ወጥተዋል።

ከሰልፉ አስተባባሪዎች አንዱ የሆኑት አቶ ጥበቡ አሰፋ ለዶቼ ቬለ እንደተናገሩት የአባይ ጉዳይ የኢትዮጵያዉያን ሁሉ ህልዉና ነዉ። በዩናይትድ ስቴትስ የምንገኝ ኢትዮጵያዉያን የአባይ ጉዳይ ያገባናል፤ ጉዳዩን ችላ ብለን አንተዉም ያሉት ሰልፈኞቹ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም ጥሪያቸዉን አስተላልፈዋል።

ሰልፈኞቹ አሜሪካ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ለአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር ይህንኑ ጥያቄያቸዉን በደብዳቤ መልክ አዘጋጅተዉ በእጅ እንደሚሰጡ የሰልፉ አስተባባሪ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

Via :- DW Photo :- BBC
@Yenetube @Fikerassefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል መደረግ ያለባቸው ጥንቃቄዎች

Video :- Al alin
ከሲዳማ ህዝብ የክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ታስረው የቆዩና የጠቅላይ አቃቤ ህግን የክስ ስረዛ ተከትሎ የተፈቱ ግለሰቦች ዛሬ በርካታ ህዝብ በተገኘበት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
ናይጄሪያ ኮሮና ቫይረስ የገባባት ሶስተኛዋ አፍሪካዊት ሀገር ሆናለች።

ሰላም እደሩ ቸር ወሬ ያሰማን!!
@YeneTube @Fikerassefa
Forwarded from HEY Online Market
#ኦሪጂናል ሞባይል ስልኮች ዋስትና

🔸SAMSUNG
#GALAXY A SERIES 
A10S 2019 /32 GB/ 5,599ብር
A20S 2019 /32 GB/ 7,199ብር
A30S 2019 /64 GB/ 8,499 ብር
A50 2019 /64 GB/ 9,499 ብር
A50 2019 /128 GB/ 10,499 ብር
A50S 2019 /128 GB/ 4GB 11,199
A50S 2019 /128 GB/ 6GB 11,999
A51 2020 /128 GB/ 6GB 12,799 ብር
A70 2019 /128 GB/ 6GB 13,899 ብር

🔸SAMSUNG #GALAXY M SERIES 
M10 (2019) /32 GB/ 5,699 ብር
M10S (2019) /32 GB/ 6,200 ብር
M30S (2019) /36 GB/ 9,200ብር

አድራሻ :- ከቦሌ መድሃኔአለም ቤተ ክርስቲያን ወደ ቦሌ ብራስ የሚወስደው መንገድ ላይ

Contact US
0953964175
0925927457
0910695100
@Roviii

@HEYOnlinemarket
ብልፅግና ፓርቲ ትግራይ ክልል ቢሮ ሊከፍት ነው።

የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አወሉ አብዲ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ብልጽግና አገር አቀፍ ፓርቲ በመሆኑ ከትግራይ ክልል ጋር በሚኖረው ሕገ መንግሥታዊ ግንኙነት መሠረት አደረጃጀቱን በማስፋት በቅርቡ በክልሉ በሁሉም ዞኖች፣ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ጽሕፈት ቤቶችን ይከፍታል፡፡ብልጽግና ፓርቲ በትግራይ ክልል ነባራዊ ሁኔታ እስካሁን ትርጉም ባለው መልኩ እንቅስቃሴ እንዳልተደረገ የገለጹት አቶ አወሉ፤ ነገር ግን አሁን በአዲስ መልክ የትግራይ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ተቋቁሞ ሥራውን እየሰራ ስለሆነ በቅርብ ጊዜ በክልል፣ በዞኖች፣ በወረዳና በቀበሌ ደረጃ እንቅስቃሴ ይደረጋል ብለዋል።

Via:- EPA
@YeneTube @FikerAssefa
የኮሮና ቫይረስ አስጊ የሚባል ደረጃ ላይ ደርሷል - ዶ/ር ቴድሮስ

የኮሮና ቫይረስ አስጊ የሚባል ደረጃ ላይ እና ዓለም አቀፍ ስጋት ሊሆን የሚችልበት አቅም ላይ መድረሱን የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ገለፁ።የዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም አስተያየት የተሰማው በተለያዩ የዓለም ሀገራት እየተስፋፋ የመጣውን የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ባለበት ወቅት ነው።ባለፉት ሁለት ቀናት ከቻይና በበለጠ በሌሎች ሀገራት አዳዲስ የቫይረሱ ተጠቂዎች መገኘታቸውም ተጠቁሟል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ሊያስመርት በዕቅድ ከያዛቸው አውቶቡሶች መካከል 20 ዘመናዊና ምቹ አውቶቡሶችን ከቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ ተረክቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ አገራት ቁጥር አራት ደርሷል።

ግብጽ፣አልጀሪያ እና ናይጀሪያ ከዚህ በፊት ቫይረሱ የተከሰተባቸው አገራት ሲሆኑ ከደቂቃዎች በፊት ደግሞ ሁለት ደቡብ አፍሪካዊያን በዚሁ ቫይረስ መጠቃታቸውን የአገሪቱ ኒወስ 24 የተሰኘው ተነባቢ ጋዜጣ ዘግቧል።

ደቡብ አፍሪካዊያኑ በጃፓን ክሩዝ መርከብ ላይ ተቀጥረው ይሰሩ የነበሩ ሲሆን ከሌሎች አገራት ዜጎች ጋር መጠቃታቸውን የጃፓን መንግስት መናገሩን እና በቶኪዮ የደቡብ አፍሪካ ኢምባሲ ማረጋገጡን ዘገባው ጠቁሟል።

በዚች የጃፓን መርከብ ላይ 12 ደቡብ አፍሪካዊያን ተቀጥረው ይሰሩ የነበረ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ #ሁለቱ በቫይረሱ መጠቃታቸው እና ህክምና ላይ መሆናቸው ተጠቁሟል።

Via:- Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
አሜሪካ ለቀጣዩ የኢትዮጵያ ምርጫ ከ30 ሚሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ አደረገች።

አገሪቱ 30 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ያደረገችው በአሜሪካ የልማት ተራድኦ ዩኤስአይዲ በኩል ነው።

ስምምነቱን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ እና የድርጅቱ ተወካዮቭ ዛሬ ረፋድ በአዲስ አበባ ሸራተን ሆቴል ተፈራርመዋል።

ይህ ገንዘብ ቀጣዩ ምርጫ ተዓማኒ፣በቴክኖሎጂ የታገዘ እና ግልጸኝነት የሰፈነ እንዲሆን የሚያደርጉ ስራዎች ለማከናወን ያግዛል ተብሏል።

Via:- Ethio FM
@YeneTube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ ሂሞፊልያ ሶሳይቲ Haemophilia Youth of Africa (HYA) ባዘጋጀው Leadership training ላይ ኢትዮጵያን በመወከል ሞሪሺየስ በተዝጋጀው ፕሮግራም ላይ ከተሳተፉት 7 የአፍሪካ ሃገራት አንዱ መሆን ቸሏል። ሂሞፊልያ ማለት የደም አለመርጋት ችግር ሲሆን በኢትዮጵያ 10,000 ሕሙማን አሉ ተብሎ ሲገመት ሆኖም ግን 333 ብቻ ሕክምና በማግኘት ላይ ናቸው።
ለበለጠ መረጃ:- +251912081185
www.ethiohemophiliayouth.com

📌ከሞሪሺየስ
የካቲት 18 ቀን 2012 ዓ/ም በአዲስ አበባ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ክልል ቆሬ አካባቢ ተብሎ በሚጠራዉ ስፍራ በደረሰው የትራፊክ አደጋ ከሞቱት መካከል የ11 ወር ህጻን እና ነፍሰ ጡር ሴት እንደሚገኙበት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ ፡፡

የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-56868 ኢት የሆነ ከባድ ተሸከርካሪ እንጨት ጭኖ ከብስራተ ገብርኤል ወደ መካኒሳ አቅጣጫ እየተጓዘ ዓለም ሰላም ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ሲደርስ 30 ሜትር ያህል ርቀት ካለዉ ድልድይ ላይ በመውደቅ እና ከድልድዩ ስር የሚገኝ መኖርያ ቤት ጥሶ በመግባት የሞትና የአካል ጉዳት እንዲከሰት ምክንያት ሆኗል፡፡

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ አደጋ መርማሪ ዋና ሳጅን አዳነ ሙሉ እንደገለጹት በመኖሪያ ቤቱ በአክስቱ እቅፍ ውስጥ የነበረ የ11 ወር ህጻን እና ህጻኑን ያቀፈችዉ ነፍሰ ጡር አክስቱ እንዲሁም በወቅቱ መኪናውን ሲያሽከረክር የነበረው አሽከርካሪ በአደጋው ህይወታቸው ማለፉን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም በመንገድ ላይ ስትጓዝ የነበረች አንዲት ሴት እንዲሁም መኖሪያ ቤቱ ውስጥ የነበሩት የሟች ህጻን ወላጅ እናት እና የህጻኑ ሞግዚት የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ዋ/ሳጅን አዳነ ሙሉ ተናግረዋል፡፡ የአደጋው መንስኤም በመጣራት ላይ ይገኛል፡፡ አሽከርካሪዎች የተሸከርካሪያቸውን ደህንነት ዘወትር መፈተሽና ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል ያሉት ዋና ሳጅን አዳነ ሙሉ በተለይም ከባድ ጭነት ጭነው በሚጓዙበት ወቅት በመታጠፊያና በቁልቁለታማ መንገዶች ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ ፍጥነታቸውን ቀንሰው ሊያሽከረክሩ እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Via Addis Ababa Police Commission
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ከዓለም ሲወዳደሩ ያሉበት ደረጃ ይፋ ተደረገ

እ.አ.አ 2016 ጀምሮ መቀመጫውን የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ያደረገው የዓለም ዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ ማእከል የተሰኘ ተቋም ሁለት ሺህ ዩኒቨርሲቲዎችን አወዳድሮ ባወጣው ደረጃ መሠረት አምስት ኢትዮጵያውያን ዩኒቨርሲቲዎችን ተካትተዋል።

ማእከሉ ደረጃውን ለማውጣት ዩኒቨርሲቲዎቹ በየአገራቸው ያላቸውን ደረጃ፣ የሚሰጡትን የትምህርት ጥራት፣ ራሳቸው ያስተማሯቸውን ተማሪዎች የመቅጠር ምጣኔ፣ የፋኩሊቲያቸው ጥራት እንዲሁም በጥናት እና ምርምር ዘርፍ ያላቸው ብቃት በመስፈርትነት ተጠቅሟል።

በዚሁ መሠረት ከሁለት ሺህ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አዲስ አበባ (1 ሺህ 040ኛ) ፣ ጎንደር (1 ሺህ 547ኛ) ፣ መቀሌ (1 ሺህ 588ኛ) ፣ ጅማ (1 ሺህ 786ኛ) እና ባሕር ዳር (1 ሺህ 780ኛ) ደረጃ በመያዝ የተካተቱ ዩኒቨርሲቲዎች ሆነዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የአሜሪካኖቹ ሀርቫርድ፣ ማሳቹስቴትስ ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ እና ስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ከአንደኛ እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡

ከአንድ እስከ 10ኛ ደረጃ ካሉ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ከእንግሊዞቹ የኦክስፎርድ (4ኛ) እና የካምፕሪጅ (5ኛ) ዩኒቨርሲዎች በስተቀር በሙሉ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ናቸው፡፡

ማእከሉ ፖሊሲ፣ ስልታዊ እይታ ብሎም መንግሥታት እና ዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት እና ምርምር ውጤታቸውን ለማሻሻል የሚያስችሏቸው የምክር አገልግሎቶች የሚሰጥ ግንባር ቀደም ተቋም መሆኑንም ከድረ ገጹ ላይ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

ማእከሉ እ.አ.አ 2012 ጀምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ የሚሰጥ መሆኑም ተመልክቷል።

ምንጭ:- የዓለም ዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ ማእከል
@YeneTube @Fikerassefa
የአውሮፓ ህብረት መጪውን ምርጫ የሚታዘብ ልኡክ እንደሚልክ ይፋ አደረገ!

የአውሮፓ ህብረት የውጪ ግንኙነት እና የደህንነት ፖሊስ ጉዳዮች ተወካይ እና የኮሚሽኑ ምክትል ፕሬዘዳንት ጆሴፍ ቦሬል ዛሬ ጠዋት ከጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) ጋር ባደረጉት ምክክር በነሐሴ ወር ለሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ ህብረቱ ታዛቢዎቹን እንደሚልክ ይፋ አደረጉ።ጆሴፍ በትዊተር ገፃቸው ይፋ እንዳደረጉትም መጪው ምርጫ ለኢትዮጵያ መረጋጋት እና ዴሞክራሲን ለማምጣት ወሳኝ መለኪያ እደሆነ ገልፀው ህብረቱ ለዐቢይ አህመድ የለውጥ አጀንዳ ያለውን ድጋፍ ያረጋገጠበት ምክክር እንደነበርም ተናግረዋል።ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ በተመሰሳይ በግል የትዊተር ገፃቸው ላይ ይፋ እንዳደረጉት ከምክትል ፕሬዘዳንቱ ጋር ‹‹ኢትዮጵያ ስለጀመረችው የብልፅግና ጉዞ እና በቀጠናው ስላሉ መሻሻሎች መክረናል›› ብለዋል።የአውሮፓ ህብረት ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ያካሄደቻቸውን አገር አቀፍ ምርጫዎች በተደጋጋሚ መታዘቡ ይታወሳል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
መነሻው ከሚሴ በማድረግ ወደ ደራ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 400 ጩቤዎችን በቁጥጥር ስራ ማዋሉን የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

የአስተዳደሩ ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር መርሀጽድቅ ታዬ እንደተናገሩት ከሆነ በዛሬው እለት ከጠዋቱ 12 ስአት አካባቢ መነሻውን ከሚሴ ያደረገና ወደ ደራ ሲዘዋወር የነበረ 400 ጩቤ ፣ 4 የክላሽ ካርታ መያዣ እንዲሁም በኢትዪጵያ ንግድ ባንክ ጉንዶ መስቀል ቅርንጫፍ አካውንት ደብተር 82 ሺ 444 ብር ይዞ ሲዘዋወር የነበረን ከተጠረጣሪው አቶ ታደሰ ጀማ ገመዳ ጋር በሸዋሮቢት ከተማ 04 ቀበሌ በቁጥጥር ስር ማዋሉንና በተጠርጣሪው ላይም ጥልቅ የሆነ ምርመራ በመደረግ ላይ መሆኑን ገልጸው ምርመራውም ተጠናቆ በሚመለከተው አካል ህጋዊ ውሳኔ ሲተላለፍ ለህብረተሰቡ እንደሚያሳውቁ ተናግረው፡፡

ምንጭ: የሸዋሮቢት ከ/አስ/ከ/ጽ/ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
መድረክ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ መተዳደሪያ ደንቡን አሻሻለ!

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ከዚህ ቀደም አንድ የጥምረቱ አባል የሌላ ጥምረት አባል መሆን አይችልም የሚለውን የመተዳደሪያ ደንቡን አንቀጽ አሻሻለ።ጥር 23/2012 በጠራው አስቸኳይ ጉባኤ ላይ ደንቡን ያሻሻለው መድረክ ለዚህ ውሳኔ መነሻ የጥምረቱ አባላት ይህ አንቀፅ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በጋራ እንዳይሰሩ እያገዳቸው መሆኑን በማንሳታቸው ነው ሲሉ የመድረክ ጸሃፊ ደስታ ዲንቃ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

ጠቅላላ ጉባኤው በዚህ ጉዳይ ላይ ብቻ ውሳኔ ማሳለፉን የተናገሩት ደስታ የምርጫ ቦርድ ተወካይም በጉባኤው ተገኝተው መታዘባቸውን ተናግረዋል። ትብብር ለዴሞክራሲያዊ ፌደራሊዝም የተሰኘው እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር፣ የኦሮሞ ፌደራሊሰት ኮንግረስ እና የኦሮሞ ብሔራዊ ፓርቲ አዲስ ጥምረት መስርተው ከምርጫ ቦርድ የምስክር ወረቀት ለማግኘት ጥያቄ ማቅረባቸው ይታወሳል። ቦርዱም ኦፌኮ አባል የሆነበት መድረክ መተዳደሪያ ደንብ መስራቸው ፓርቲዎቹ የሌላ ጥምረት አባል መሆን እንደማይችሉ ስለሚገድብ ይህ እንዲታይ መጠየቁ ይታወሳል።

ምንጭ: አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa