YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.89K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በዘንድሮው ጠቅላላ #ምርጫ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለክልል ምክር ቤቶች የሚያቀርባቸውን ዕጩዎች ለመለየት የቅድመ ዕጩ ምዝገባ መጀመሩን አስታወቀ፡፡ ፓርቲው የተወዳዳሪዎች ምልመላ መመሪያውንም ይፋ አድርጓል።

Via Ethiopia Election
@YeneTube @FikerAssefa
በምዕራብና ደቡብ ኦሮሚያ አካባቢዎች አንጻራዊ ሰላም እየታየ መምጣቱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ!

በምዕራብና ደቡብ ኦሮሚያ አካባቢዎች ተከስቶ የነበረው የጸጥታ ችግር በፀጥታ ሃይሉ በተወሰዱ እርምጃዎች አንጻራዊ ሰላም እየታየበት መምጣቱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።በደቡብና በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና የጸጥታ ችግሮች መታየት ከጀመሩ ሰነባብቷል።
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል አራርሳ መርዳሳ እንዳሉት፥ በአካባቢው የለውጥ እንቅስቃሴውን ለማደናቀፍ ላለፈው አንድ ዓመት የታጠቁ ሃይሎች ችግር ሲፈጥሩ ቆይተዋል።

እነዚህ ሀይሎች በአካባቢው የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና የጸጥታ አካላትን እስከ በመግደል መድረስ በአካባቢው ማህበረሰብ ስጋት ፈጥሮ ቆይቷል።ታጣቂ ኃይሉ ባለሀብቶችን፣ ግለሰቦችን፣ የመንግስት አመራሮችና የጸጥታ ኃይል አባላትን ሳይቀር በመግደል በከተሞችና ገጠር አካባቢም በርካታ ጥፋቶችን አድርሷል።ሆኖም መንግስት ችግሮችን በውይይት ለመፍታት ጥረት ሲያደርግ ቢቆይም ሊሳካ ሳይችል መቅረቱን ያነሱ ሲሆን፥ መንግስትም የህግ የበላይነትን ለማስከበር ወደ እርምጃ መግባቱን ኮሚሽሩ ገልጸዋል።

በምዕራብ ወለጋ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች፤ በደቡብ ኦሮሚያ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች ታጣቂ ኃይሉ የሚንቀሳቀስባቸው ቦታዎች መሆናቸውንም ኮሚሽነሩ አመልክተዋል።በመሆኑም የመንግስት የጸጥታ አካላት ከህዝቡ ጋር በመተባበር በታጣቂ ቡድኑ ላይ በተወሰደው እርምጃ አሁን ላይ አንፃራዊ ሰላም እየታየ መሆኑን ገልጸዋል።ህብረተሰቡ ለጸጥታ አካላት እያደረገ ያለውን ትብብርም አጠናክሮ እንዲቀጥልም ኮሚሽነር ጀነራል አራርሳ ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
መንግሥት ማዳበርያ አስኪያስገባ አስመጪዎች የወደብ እንዲከፍሉ ተገደዱ!

ማዳበሪያውን ማስገባት ለሚቀጥሉት ኹለት ወራት ይቀጥላል የኢትዮጵያ መንግሥት 1.5 ሚሊዮን ቶን ማዳበሪያ እያስገባ መሆኑን ተከትሎ በጅቡቲ ወደብ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ሊገቡ የነበሩ ኮንቴይነሮች የወደብ ኪራይ እየከፈሉ በጅቡቲ ወደብ እንዲቆዩ ተደርገዋል። ማንነታቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ በአስመጪ እና ላኪነት ሥራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት፣ ጅቡቲ ወደብ የደረሱት እቃዎች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ መደረግ ከተጀመረ ሦስት ሳምንት ሆኖታል። ይህም በመሆኑ ምክንያት ለከፍተኛ ወጪ እና ኪሳራ መዳረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት በ1328 የትምህርት መስኮች የዕውቅና ፈቃድ እና የዕውቅና ፈቃድ ዕድሳት የተሰጣቸው 763 የትምህርት መስኮች ሲሆኑ ያልተሰጣቸው ደግሞ ለ565 መሆናቸውን ኤጀንሲው ገለጸ፤

እስከ ታህሳስ 2012 ዓ.ም. የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ብዛት 246 ደርሷል።
የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ በ2012 የመጀመሪያው ግማሽ አመት 497 ካምፓሶች ላይ በ1045 የትምህርት መስኮች የእውቅና ፈቃድ እንዲሁም 132 ካምፓሶች ላይ በ283 የትምህርት መስኮች የእውቅና ፈቃድ እድሳት እንዲሰጣቸው የተለየያዩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጥያቄ አቅርበውለታል፡፡

ባጠቃላይ 629 ካምፓሶች በ1328 የትምህርት መስኮች የእውቅና ፈቃድ እና እውቅና ፈቃድ እድሳት ጥያቄዎች ተቋማት ለኤጀንሲው አቅርበውለታል፤ የቀረቡ ጥያቄዎች መነሻ በማድረግ ባካሄደው የሰነድና የመስክ ግምገማዎች ውጤት መሰረት 365 ካምፓሶች ላይ ለ763 የትምህርት መስኮች የእውቅና ፈቃድ እና እድሳት ሰጥቷል፤ በ264 ካምፓሶች ለ565 የትምህርት መስኮች ደግሞ አለመስጠቱን ኤጀንሲው አሳውቋል፡፡የእውቅና ፈቃድ እና እውቅና ፈቃድ እድሳት የተሰጣቸው ምክንያት ለየትምህርት መስኩ የተቀመጡትን መስፈርቶች አሟልተው በመገኘታቸው ነው፤ የእውቅና ፈቃድ እና የእውቅና ፈቃድ እድሳት ያልተሰጠባቸው የትምህርት መስኮች የመመዘኛ መስፈርቶችን አሟልተው ባለመገኘታቸው ነው፡፡

እስከ ታህሳስ 2012 ዓ.ም.ድረስ ባለው ወቅታዊ መረጃ መሰረት የእውቅና ፈቃድ አግኝተው ተማሪ ማስተማር የሚችሉ ተቋማት ብዛት 247 ደርሷል፡፡ የተቋማት ዝርዝር መረጃ ወቅታዊ ተደርጎ እስከ የካቲት 20 2012 ዓ.ም ድረስ በድረ-ገጽ እና በፌስ ቡክ ገጹ ለህዝብ ይፋ መደረጉን ኤጀንሲው ገልጿል፡፡

ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተማሪዎችን መዝግቦ ማስተማር የሚችለው ለኤጀንሲው ጥያቄ አቅርቦ ከተገመገመ በኋላ በተገኘው ውጤት መሰረት ፈቃድ ማግኘቱ ሲገለጽለት ብቻ መሆኑ ታውቆ መላው ህብረተሰብ የተለመደውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ኤጀንሲው ጥብቅ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

ምንጭ:HERQA
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ በገንዘብ እጥረት የተነሳ ፕሮጀክቶች ለማቆም ጫፍ ደርሶ ነበር

ከፍተኛ የገንዘብ ቀውስ ውስጥ ወድቆ የነበረው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በ2012 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ያለበትን የብድር ወለድ ለመክፈል እንዲሁም ለህዳሴ ግድብ ግንባታ እና ለሌሎች ትላልቅ ፕሮጀክቶች ማስገንቢያ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰባት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር መበደሩን ይፋ አደረገ። ይህንንም ተከትሎ ድርጅቱ ከንግድ ባንክ የወሰደው ብድር ወደ 271 ቢሊዮን ብር ገደማ ሲደርስ፣ አጠቃላይ ዕዳውን ከ300 ቢሊዮን ብር በላይ እንዲሆን አድርጎታል።

Via:- Addis Maleda
@YeneTube @Fikerassefa
ኦፌኮ ለኢሳት በላከው ማሳሰቢያ "የኦሮሚያ ቤተ ክህነት መግለጫ በፓርቲያችን ጽ/ቤት ዉስጥ እንደተሰጠ ተደርጎ የቀረበው መረጃ እውነት አይደለም" ብሏል።

Via:- ኦፌኮ / ኤልያስ መሰረት
@Yenetube @Fikerassefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኤምባሲው በሳኡዲ አረቢያ ደማም በአሰሪዎቿ ታግታ የነበረችውን ኢትዮጵያዊት አለቅቄያለው ብሏል።

ህይወቷን ለመቀየር የዛሬ ሰባት አመት ሳኡዲ አረቢያ ደማም ከተማ የገባችው ኢትዮጵያዊት ትዕግስት ፍስሃ አሰሪዎቿ የመብት ጥሰቶችን በተደጋጋሚ በማድረስ ከምትሰራበት ቤት እንዳትወጣና እንዳትንቀሳቀስ ያደርጓታል።ለሰባት አመታት በዚህ አይነት ጭንቅ፣ እንግልት እንዲሁም እገታ የቆየችው እህታችን፣ በቅርቡ ኤምባሲው በህይወት እንዲደርስላት፣ አሰሪዎቿ ያልከፈሏትን የአንድ አመት ከዘጠኝ ወር ደመወዝ እንዲያስከፍልላት እና ለአገሯ አፈር እንዲያበቃት ትጠይቃለች። ኤምባሲው በደማም ከተማ ካለው የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር ጋር በመተባበር እህት ትዕግስት ፍስሃ ከታገተችበት ቤት እንድትወጣ እና ያልተከፈላትን ደመወዝ ለአሁኑ አስር ሺህ አራት መቶ የሳኡዲ ሪያል (10 400 ሳ.ሪ) እንድታገኝ(በቀጣይ ቀሪውን እንድታገኝ ጥረት የሚደረግ ይሆናል) ያደረገ ሲሆን፣ በቅርቡም ወደ አገር እንድትሸኝ የሚያደርግ ይሆናል።

ምንጭ: በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ
@YeneTube @FikerAssefa
መቀሌን ዋና ማእከሉ ለማድረግ ያቀደው ኖርዝ ስታር አየር መንገድ የመስች ጉባኤውን አደረገ፡፡

በርካታ ታዋቂ ሰዎችን፣ ባለሃብቶችን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ያቀፈው እና በመቋቋም ላይ ያለው ድርጅት በአገሪቱ እየመጡ ያሉትን በርካታ ማሻሻያዎች መነሻ በማድረግ ወደ ስራው ለመግባት መነሳቱን አስታውቋል፡፡
በተለይ ከኤርትራ ጋር የተደረገው እርቅ፣ አዲሱ የኢንቨስትመንት አዋጅ የግል አየር መንገዶች ላይ የነበረውን የአውሮፕላን መቀመጫ ገደብ ማንሳቱ እንዲሁም መንግስት በግዙፉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ድርሻ ለመሸጥ መነሳቱ በዘርፉ ለመሳተፍ እንዳነሳሳቸው የሃሳቡ ባለቤት አቶ መኮንን አሰፋ ተናግረዋል፡፡
በ2017 ይፋ የተደረገ ጥናት እንደሚያሳው 60 ሚሊየን እና ወደ 50 ሚሊየን ህዝብ ያለባቸው ደቡብ አፍሪካ እና ኬንያ እንደቅደም ተከተላቸው በአገራቸው ከ 5 ሺ እና 2 ሺ አውሮፕላኖች በአገራቸው ይገኛሉ፡፡ከ110 ሚሊየን ህዝብ በላይ ባላት ኢትዮጵያ ይህ ቁጥር በተጠቀሰው የፈረንጆቹ አመት 140 አውሮፕላኖች ብቻ ነበር፡፡ ከዚህም ሁሉም በሚባል ደረጃ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የተያዘ ነው፡፡

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
ግብፅን ለ30 አመታት በፕሬዝዳንትነት የመሯት ሆስኒ ሙባረክ መሞታቸው ተሰምቷል።

እ.አ.አ በ2011 የተቀሰቀሰው የአረቡ አብዮት ሰለባ የነበሩት ሆስኒ ሙባረክ በ91 አመታቸው ህይወታቸው ማለፉን ፍራንስ 24 ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ የአመራሮች ሥልጠና በዛሬው እለት መካሄድ ጀምሯል፡፡ ስልጠናው በኦሮሚያ ክልል ጅማ ከተማን ጨምሮ በሰንዳፋ ፣ አዳማ እና ባቱ ከተሞች እየተካሄደ ነው፡፡
በስልጠናው ትኩረት የሚደረገው በብልፅግና ፓርቲ መሠረታዊ አስተሳሰቦች ምንነትና ይዘት ላይ እንደሚሆን ታውቋል።
@Yenetube @Fikerassefa
ሰበር ዜና!

ክሳቸው ከተቋረጠላቸው 63 ግለሰቦች መካከል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊው ክርስቲያን ታደለ፤ ኮሎኔል ቢኒያም ተወልደ እና ኤርሚያስ ጠቅል አመልጋ ይገኙበታል፡፡

ምንጭ:አሐዱ ቴሌቪዥን
@YeneTube @FikerAssefa
በተጨማሪም

ኮ/ል ቢኒያም ተወልደ

ረ/ፕሮፌሰር ተሰማ ኤልያስ

አቶ ሳሙኤል በላይነህ

አቶ አሮስ ቃኒሶ ክሳቸው ከሚቋረጥላቸው መካከል እንዳሉበት ሸገር ታይምስ ዘግባለች፣ ሙሉ ዝዝራቸው እንደደረሰን የምናቀርብ ይሆናል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የቀድሞ የሜቴክ ሀላፊ ብርጋዴል ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ክሳቸው አልተቋረጠም።

Via Tesfaye Getinet
@YeneTube @FikerAssefa
በጊንጪ ከተማ በሚገኝ የፖሊስ ካምፕ ላይ የቦንብ ጥቃት ደረሰ!

በትናንትናው ዕለት በኦሮሚያ ክልል ጊንጪ ከተማ በሚገኝ የፖሊስ ካምፕ ላይ የቦንብ ጥቃት ደርሷል፡፡በከተማው ትናንት ከምሽቱ 2 ሰዓት በደረሰው በዚህ ጥቃት በወቅቱ በስራ ላይ በነበሩ ሁለት የፖሊ አባላት ላይ በጭስ የመታፈን መጠነኛ ጉዳት ከመድረሱ በቀር የከፋ አደጋ አለመድረሱን የክልሉ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ገልፀዋል፡፡ጥቃቱን በማድረስ የተጠረጠሩ ስድስት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም አቶ ጌታቸው በተለይ ለኢቲቪ ተናግረዋል፡፡ድርጊቱን ፈጽመዋል በሚል የተጠረጠሩ ግለሰቦች ማንነት እስካሁን በተደረገው ምርመራ አለመታወቁን ተናግረዋል፡፡

ምንጭ: ኢቲቪ
@YeneTube @FikerAssefa
የጠብታ አምቡላንስ መስራች አቶ ክብረት አበበ ለመጀመሪያ ጊዜ ማህበራዊ ሀላፌነትን ከመወጣት ጎን ለጎን ቢዝነስ ሞዴልን በማዘጋጀት 1 ሚሊዮን ዶላር ተሸላሚ በሚያደርገዉ ሳን ካልፕ ሽልማት ላይ እጩ ሆኑ፡፡

Via:- Arts TV
@YeneTube @Fikerassefa
የኢራን የጤና ሚንስትር ዴኤታ ኢራጅ ሀሪጂ(በስተግራ የሚታዩት) በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የሚንስቴር መስሪያቤቱ ቃል አቀባይን ጠቅሶ አሶሼትድ ፕረስ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa