⬆️⬆️በዛሬው እለት ሞሮጎሮ፣ ሩቩማ እንዲሁም ንጆምቤ በሚባሉ የታንዛኒያ ግዛቶች ከሚገኙ 5 እስር ቤቶች ተፈትተው 77 ዜጎቻችን ዳሬ ሰላም ከተማ ደርሰዋል። ሌሊቱን ከዳሬሰላም ተነስተው ነገ የካቲት 16 ቀን 2012 ከጠዋት በ1፡30 ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ይደርሳሉ።
ዘመድ እና ቤተሰቦቻቸው እንዲቀበሏቸው መረጃውን እንድናስተላልፍላቸው በጠየቁን መሰረት የስም ዝርዝራቸውን እንደሚከተለው አቅርበናል ብሏል በዳሬሰላም የኢትዮጵያ ኤምባሲ።
#ሼር_በማድረግ_ይተባበሩ
@YeneTube @FikerAssefa

ሰበር ዜና
በአምቦ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለመደገፍ በወጡ ሠልፈኞች ላይ በተወረወረ ቦምቡ ጉዳት ደረሰ
ዛሬ፣ እሁድ፣ ጠዋት ለጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ እና ለፓርቲያቸው ድጋፋቸውን ለመስጠት ሠልፍ በወጡ ሠልፈኞች ላይ በተወረወረ ቦምብ ቢያንስ 29 ሠዎች መቁሰላቸውን የአምቦ ከተማ አስተዳደር እና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ ለቢቢሲ ተናገሩ።
ኃላፊው አቶ ሂንሰርሙ ደለሳ እንዳሉት ቦንቡ የተወረወረው ለድጋፍ ሰልፍ በወጡ ፈረሰኞች ላይ ነው።
ጉዳት ካጋጠማቸው መካከል የህክምና እርዳታ ተደርጎላቸው ከሆሰፒታል የወጡ እንዳሉ ሁሉ የተለያዩ የጉዳት መጠን ያስተናገዱ መኖራቸውን አቶ ሂንሰርሙ ተናግረዋል።
ከወንጀሉ ጋር ተያይዞ ተጠርጥረው የተያዙ ሰዎች መኖራቸውን የተናገሩት ኃላፊው "በጫካ ውስጥ ታጥቆ የሚንቀሳቀስው ኃይል ወንጀሉን ሳይፈፅም እንደማይቀር እንጠረጥራለን" ብለዋል።
በጥቃቱ በርካታ ፈረሶችም መጎዳታቸውን ቢቢሲ ከአምቦ ከተማ ነዋሪዎች ባገኘው መረጃ ለማወቅ ችሏል።
ምንጭ:- BBC
@YeneTube @Fikerassefa

14 ህገ ወጥ 14 ክላሽንኮቭ ጠብመንጃ በቁጥጥር ስር ዋለ!
በኢሉ አባቦር ዞን ቡሬ ወረዳ በህገወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ 14 ክላሽንኮቭ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ ገለፀ፡፡የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ታረቀኝ አሰፋ ለኢዜአ እንደገለፁት የጦር መሳሪያው የተያዘው የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 አማ 21199 በሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ከጋምቤላ ወደ አዲስ አበባ በመጓጓዝ ላይ እንዳለ ነው። መሳሪያዎቹ ዛሬ ጠዋት 2 ሰዓት ተኩል አካባቢ በቡሬ ከተማ በተደረገው ፍተሻ በተሽከርካሪው ውስጠኛ አካል በላሜራ በተበየደ ቦታ ውስጥ ተደብቀው ተገኝተዋል።
Via ETV

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምስጋናውን አቀረበ!
ትናንት በመስቀል አደባባይ በተካሄደው የድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ መላው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችና የፀጥታ አካላት ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በጋራ ላከናወኑት የፀጥታ ስራ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን ምስጋናውን አቀረበ።ሰላም ወዳዱ የከተማዋ ነዋሪ ዝግጅቱ ከመጀመሩ ጀምሮ እስከ ፍፃሜው ለፀጥታ ሀይሉ ያሳየው ትብብር እጅጉን የሚያስመሰግን ነው ያለው ኮሚሽኑ በቀጣይም በከተማችን በሚደረጉ ዝግጅቶች አጋርነቱን አጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።ዝግጅቱ በሰላም እንዲጠናቀቅ ሀላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ የፌደራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አመራርና አባላት ኮሚሽኑ ምስጋናውን አቅርቧል።
ምንጭ:- የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

ቦንብን ያፈነዱት ቁጥጥር ስር ውለዋል...
ዛሬ በአምቦ ከተማ ለዶክተር አብይ አህመድና ለለውጥ አመራሩ የድጋፍ ሰልፍ ሲካሄድ የቦንድ ጥቃት ያደረሱ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የከተማዋ ከንቲባ አስታወቁ፡፡
የከተማዋ ከንቲባ አቶ ሃይሉ ዲሪሳ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የቦምብ ጥቃቱ የደረሰው ወደ አምቦ እየገቡ በነበሩ ፈረሰኞች ሲሆን፤ከ10 በላይ ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡ተጎጅዎች በአምቦ ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው፡፡
ጥቃት ያደረሱት ሰዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የገለጹት ከንቲባው፣ጉዳዩን ፖሊስ በቅርበት እየተከታተለው ሲሆን መግለጫ እንደሚሰጥበት አስታውቀዋል።
t.me/Yenetube
የከተማዋ አስተዳደርም ጉዳዩን እየተከታተለው መሆኑን ጠቅሰው፤ ምንም እንኳን ይህ አደጋ ቢያጋጥም የድጋፍ ሰልፉ በተሳካ ሁኔታ መካሄዱን አመልክተዋል፡፡
Via:- EPA
@YeneTube @Fikerasssefa

ዕለታዊ ዜና በዩቲዩብ ቻናላችን ለመጀመር ቅድመ ዝግጅት እያደረግን እንገኛለኝ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያላደረጋችህ አድርጉ ⬇️
https://www.youtube.com/channel/UCUYai_rLTnhWlfUayTOsC1Q?sub_confirmation=1

በዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች ላይ ዛቻና ማስፈራሪያ ይደርሳል ተባለ!
በዘንድሮው ዓመት በበርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ተቀስቅሶ የነበረውን ረብሻ ተከትሎ በዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች ላይ የተለያዩ ዛቻና ማስፈራሪያዎች እየደረሰ መሆኑ ተጠቆመ።በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ደቻሳ ጉርሙ፤ በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በአሁኑ ወቅት የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሆኖ መስራት ፈታኝ እየሆነ የመጣና በተለይም የፀጥታ ስጋት ባለባቸው አካባቢዎች ፕሬዚዳንቶቹ የተለያዩ ማስፈራሪያዎችና ዛቻ ስለሚደርስባቸው በስጋት ውስጥ ሆነው እየሰሩ ነው።ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተማሪዎችን በሐይማኖትና በብሔር በማጋጨት የዩኒቨርሲቲ አስተዳደሮችን ለማጥቃት የሚደረግ ሙከራ መኖሩን የገለፁት ዳይሬክተሩ፤ በዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች ላይም በየጊዜው ዛቻና ማስፈራሪያዎች ይደርሳል ብለዋል።
Via EPA

ዶክተር አሚር አማን በሥጦታ ያገኙትን 1 ሚሊዮን ብር ለሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን አበረከቱ፡፡
የቀድሞው የጤና ሚኒስትር አሚር አማን (ዶክተር) ከኢትዮጵያ ጤና ክብካቤ 1 ሚሊዮን ብር ተበርክቶላቸዋል፡፡ለዶክተር አሚር ዕውቅናው የተሰጣቸው መንግስት ከግሉ ዘርፍ ጋር በቅርበትና በትብብር እንዲሠራና በዘርፉ መሻሻሎች እንዲመዘገቡ ላደረጉት አስተዋጽኦ እንደሆነ በምስጋናና ዕውቅና መርሀ ግብሩ ላይ ተገልጧል፡፡ለኢትዮጵያ የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ያደረጉት የ 1 ሚሊዮን ብር ድጋፍም ሌሎች ባለሀብቶች እና ድርጅቶች ከሥራ ፈላጊዎች ጎን እንዲቆሙ ለማበረታታት እንደሚያስችል ታምኖበታል፡፡ ብዙዎቹ ዘርፉን ከደገፉ ደግሞ የመነሻ መሥሪያ ገንዘብ የሌላቸው ብዙ የጤና ሙያ ተመራቂዎች ሥራ እንዲፈጥሩና ማኅበረሰባቸውን እንዲያገለግሉ ያግዛል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት አሚር አማን (ዶክተር) የዕውቅና ሽልማቱ ለአንድ ሰው ሳይሆን በግሉ ዘርፍና በጤና ሚኒስቴር በኩል ለተጀመረው መልካም ግንኙነት የተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ መንግሥት ባለበት የበጀት ውስንነት የተነሳ ሳይቀጥራቸው የሚቀሩ ባለሙያዎችን በመቅጠር የግሉ ዘርፍ እየፈጠረ ላለው የሥራ ዕድልም ምሥጋና አቅርበዋል፡፡የኢትዮጵያ የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን እስከ 2012 በጀት ዓመት ማገባደጃ ለ 3 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ማቀዱ ይታወሳል፡፡
Via AMMA

የአብን ሥራ አስፈፃሚ አመራሮች፦
1. አቶ በለጠ ሞላ - ሊቀመንበር
2. አቶ የሱፍ ኢብራሂም - ም/ሊቀመንበር
3. አቶ አዲስ ኃረገወይን - የፖሊሲ ስትራቴጂ ኃላፊ
4. አቶ ጣሂር ሞሐመድ - የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
5. ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃ/ማርያም - የውጭ ጉዳይና ዓለማቀፍ ግንኙነት
6. አቶ ጋሻው መርሻ - የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ
7. አቶ መልካሙ ፀጋዬ - የፅሕፈት ቤት ኃላፊ
8. አቶ ጥበበ ሰይፈ - የሕግና ስነምግባር ኃላፊ
9. አቶ ክርስቲያን ታደለ - የፓለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ ናቸው።
Via፦ አብን

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ከአብን ሊቀመንበርነት በአቶ በለጠ ሞላ ስለመተካታቸው ከነገሩኝ:
"በቅርቡ ሪፎርም እያረግን ነበር፣ አንዱ ዋናው የሪፎርሙ አካል ደግሞ ተቋማዊ ለውጥ ማድረግ ነበር። ሁለተኛው ደግሞ አዲስ የስራ አስፈፃሚ አባላትን መምረጥ ነበር። እኔ በሊቀመንበርነት ያገለገልኩበት ሁለት አመት በቂ ነው ብዬ አስባለሁ። በአዲስ መንፈስ ስራ ሊሰራ የሚችል አዲስ አመራር እንዲመረጥ አድርገናል። ይህ በግል ፈቃዴ የተደረገ ነው። ፓርቲው ውስጥ አሁንም የማእከላዊ ኮሚቴ አባል ነኝ፣ በአባልነቴም እቀጥላለሁ።"
Via:- eliasmeseret

በአማራ ክልል አዊ ዞን ጃዊ ወረዳ ሰዋታምፕ ቀበሌ 2ሕጻናትን ይዘው ለማስለቀቂያ 400 ሺህ ብር የተጠየቁ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የወረዳው ፓሊስ አስታወቀ። ሕጻናቱም በሰላም ተለቀዋል።
@YeneTube @Fikerassefa
@YeneTube @Fikerassefa
የትግራይ ክልል መንግስት የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትሮች መለስ ዜናዊ እና ሀይለማሪያም ደሳለኝ የምጣኔ ሀብት አማካሪ በነበሩት አቶ ነዋይ ገብረዓብ ሞት የተሰማውን ሀዘን ገለጸ። አቶ ነዋይ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ማለዳ አርፈዋል።
#ELU
@YeneTube @Fikerassefa
#ELU
@YeneTube @Fikerassefa
ምርጫ ቦርድ የፓለቲካ ፓርቲዎች ማሟላት የሚገባቸውን ዝርዝር ጉዳዮች እስከ መጋቢት 3 እንዲያሟሉ አሳሰበ!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሟሟላት የሚገባቸውን ዝርዝር ጉዳዮች እስከ መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ.ም እንዲያሟሉ አሳሰበ።በፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና ምርጫ አዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሰረት በቦርዱ ሀገር አቀፍ እና የክልል ፓርቲዎች ማሟሟላት ያለባቸው ግዴታ ለማስፈጸም የወጣው መመሪያ ቁጥር 3/2012 መሰረት የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ ማሟላት የሚገባቸውን ዝርዝር ሁኔታ የሚያስረዱ ሰነዶች ማዘጋጀቱ እና ለፓርቲዎች እንዲደርሳቸው ማድረጉ አስታውሷል፡፡ለእያንዳንዱ ፓርቲም በደብዳቤ ሟሟላት የሚገባቸውን ሁኔታዎች ሁሉ እስከ መጋቢት 03 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ አሟልተው እንዲያቀርቡ ቦርዱ እንዳስታወቀ ተጠቁሟል።ሆኖም እስከአሁን ሰነዶቻቸውን ያስገቡ ፓርቲዎች ቁጥር ዝቅተኛ መሆኑን ቦርዱ በዛሬው ዕለት ገልጿል።በመሆኑም ሟሟላት የሚጠበቅባቸው ዝርዝር ሁኔታዎችን የሚያስረዱ ሰነዶች የደረሳቸው የፓለቲካ ፓርቲዎች በሙሉ መጋቢት 3 ቀን 2012 ከመድረሱ በፊት ሟሟላት የሚገባቸውን በሙሉ አሟልተው የምዝገባ ስርአቱን እንዲጀምሩ አሳስቧል።
Via FBC

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምርጫው እንዲራዘም ጠየቀ!
የኢትዮጽያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምርጫ 2012ትን በተመለከተ በሰጠዉ መግለጫ ምርጫዉ እንዲራዘም መወሰኑን አስታወቀ።ምክር ቤቱ “ከምርጫ የአገር ህልዉና ይቅደም” በሚል ርዕስ አርብ የካቲት 13/2012 በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ባደረጉት ዉይይት ምርጫዉ መራዘም አለበት ሲሉ በአብላጫ ድምፅ መወሰናቸዉን አስታውቋል።ምክር ቤቱ የካቲት 7/2012 75 የፖለቲካ ፓርቲዎች በተገኙበት ባደረገው ውይይት ከአገር ህልዉና የምርጫ ሊቀድም ስለማይገባ፣ ፓርቲዎቹ ምርጫዉ ይራዘም የሚል ሐሳብ ማንፀባረቃቸውን ገልጿል።
Via Addis Maleda

የከፍተኛ የኤሌክትሪክ መስመር ማሻሻያ ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት በተወሰኑ አካባቢዎች ይቋረጣል።
በአዲስ አበባ ከተማ በአንዳንድ አካባቢዎች ለማሻሻያ ሥራ ሲባል የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እንደሚቋረጥ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቋል ።
በዚሁ መሰረት
ነገ ማክሰኞ የካቲት 17 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 እስከ ቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ፣
• በሳሪስ አቦ ቤ/ክ፣ በቦሌ ቡልቡላ ኮንዶሚኒየም፣ በቡልቡላ ማርያም ማዞርያ፣ በክሬሸር፣ በባሌስቴራ ፋብሪካ፣ በGW2 ውሃ፣ በአደይ አበባ፣ በሳሪስ አዲስ ሰፈር፣ በአዋሽ ቆዳ ፋብሪካ እና አካባቢዎቻቸው፣
እንዲሁም በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ስዓት ድረስ፣
• በጎላጎል ወደ መገናኛ፣ በገቢዎች፣ በቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል፣ በሻላ መናፈሻ፣ በቦሌ ጤና ጣቢያ፣ በመገናኛ በከፊል፣ በኢትዮፕላስቲክ፣ በየነገው ሰው ት/ቤት፣ በ17/24 ታክሲ ማዞርያ፣ በአዲሱ የወጣቶች ማዕከል ስታዲየም እና አካባቢዎቻቸው፣
ረቡዕ የካቲት 18 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 እስከ ቀኑ 6:00 ሰዓት ድረስ፣
• በፈጥኖ ደራሽ፣ በኮልፌ ኮፕሪሄንሲፍ ት/ቤት፣ በደጉ ሆቴል፣ በታይዋን ገበያ፣ በኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል እና አካባቢዎቻቸው፣
በዚሁ ቀን በተመሳሳይ ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ስዓት ድረስ፣
• በቦሌ መድሃኒያለም ቤ/ክ፣ በአያት ሆስፒታል፣ በብራስ ሆስፒታል፣ በሚሊኒየም አዳራሽ፣ በቦሌ ሚኒ፣ በኢትዮፕላስቲክ፣ በየነገው ሰው ት/ቤት፣ በ17/24 ታክሲ ማዞርያ፣ በአዲሱ የወጣቶች ማዕከል ስታዲየም እና አካባቢዎቻቸው፣
በከፍተኛ የኤሌክትሪክ መስመር ላይ የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን ሲባል የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥ በመሆኑ ነዋሪዎች እና ደንበኞች ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳስቧል ፡፡
Via:- Addis Ababa City administration
@Yenetube @Fikerassefa

የዙምባብዌ ቢሊየነር ከኢትዮ ቴሎኮም ፈቃድ ለማግኘት እየተንቀሳቀሱ ነው
በዙምባብዌው ቢሊየነር ስትራይቭ ማሲያዋ ባለቤትነት የሚተዳደረው ኢኮኔት ግሎባል የተባለው ኩባንያ በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት ከኢትዮ ቴሎኮም ፈቃድ ለማግኝት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ብሉምበርግ ዘገበ፡፡
#addisMaleda
@YeneTube @Fikerassefa
በዙምባብዌው ቢሊየነር ስትራይቭ ማሲያዋ ባለቤትነት የሚተዳደረው ኢኮኔት ግሎባል የተባለው ኩባንያ በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት ከኢትዮ ቴሎኮም ፈቃድ ለማግኝት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ብሉምበርግ ዘገበ፡፡
#addisMaleda
@YeneTube @Fikerassefa
በተለያዩ ምክንያቶች በእሥር ላይ የሚገኙ ግለሰቦች ክስ እንዲቋረጥ መንግሥት ወሰነ።
በተለያዩ ምክንያቶች በእሥር ላይ የሚገኙ ግለሰቦች ክስ እንዲቋረጥ መንግሥት መወሰኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕረስ ሴክሬታሪ ኃላፊ ንጉሱ ጥላሁን አስታውቀዋል። በሀገሪቱ የሰው ህይወት መጥፋት፣ ግጭት፣ መፈናቀል እና የሀይማኖት ተቋማት ላይ ጥቃት መከሰቱን ያወሱት የጽህፈት ቤት ኃላፊው በእነዚህ ሁኔታዎች መረጃ የተገኘባቸው 1 ሺህ 682 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ሆነው ጉዳያቸው እየታየ መሆኑን አስታውቀዋል።
ከሙስናና በህገ ወጥ መንገድ ከማዘዋወር ጋር በተያያዘ ደግሞ 470 ሚሊዮን 6 መቶ ሺህ ብር ታግዶ ጉዳዩ እየታየ እንደሆነም ነው የገለጹት። ይሁን እንጂ በታጋሽነት እና የፖለቲካ ምኅዳሩን ለማስፋት ሲል የተወሰኑት ክስ እንዲቋረጥ መንግሥት መወሰኑን ነው አቶ ንጉሱ የተናገሩት። በዚህም መሠረት የ60 ሰዎች ክስ ማቋረጡን ገልጸዋል። ክሳቸው የተቋረጠላቸው በየትኛው አግባብ፣ በምን ሁኔታ፣ እነማን እንደሆኑ እና ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮችን በተመለከተ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ነገ ማብራሪያ እንደሚሰጥም አስታውቀዋል።በለውጡ ሂደት ብቻ 43 ሺህ 531 ዜጎች ምሕረት እንደተደረገላቸውም አቶ ንጉሱ አስታውሰዋል።

ሊደመጥ የሚገባው!!! ሕውሓት ከብልፅግና ጋር ሊመክር እንደሆነ ተሰምቷል። ለዚው ጉዳይ ኮሚቴም መቋቋሙ ታውቋል ⬇️
https://youtu.be/wUI0T0oRfDM
https://youtu.be/wUI0T0oRfDM
YouTube
Ethiopia : ሰበር መረጃ ፡ ህውሃት እና ብልጽግና ፓርቲ እርቅ ለመፍጠር ኮሚቴ አቋቋሙ
We are YeneTube official subscribe us for more videos and to enjoy!