YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ልቤን ያመኛል !!

ከ 7000 በላይ ሕፃናት የልብ ህክምና ለማግኘት ወረፋ በመጠባበቅ ላይ ናቸው።

6710 ላይ "A" ብለው በመላክ ለልብ ሕክምና ማዕከል ድጋፍ ያድርጉ።

ከአሁን ጀምሮ የቻሉትን ያክል ይላኩ በአንድ Text አንድ ብር ብቻ ነው የሚቆርጠው።


እንደላካችሁ Screenshot ላኩልን

እናመሰግናለን
እናመሰግናለን
በቀልዱም ተዝናኑ ⬆️
መልዕክቶች እየደረሱን ነው እናመሰግናለን።
ወደ 6710 መላካችውን ቀጥሉ 🙏
:
:
:
:
ሁላችንም የራሳችን ልጆ ላይ ቢደርስ ብለን ከወዲው የልብ ማዕከሉን እናጠናክር።
ነገ አርብ በ13/06/12 በሀዋሳ ከተማ ታላቅ ህዝባዊ የምስጋናና የድጋፍ ሰልፍ ይካሄዳል ብሏል ከተማ አስተዳደሩ።

@YeneTube @FikerAssefa
#update

በተጨማሪ ሀዋሳ ሲአን ቅዳሜ 14/2012 በሚሊንየም አዳራሽ ስብሰባ ጠርቷል ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና እንደሚገኝ የስብሰባው አስተባባሪ ጠቁሞኛል።

@YeneTube @Fikerassefa
ለቀድሞው የጤና ሚኒስቴር ዶ/ር አሚር አማን የምስጋና እና የእውቅና ኘሮግራም ተካሄደ፡፡

@YeneTube @Fikerassefa
👍1
ዶክሌ በህይወት አለ !! #FakeNewsAlert

ስለ ኮሜዲያን ወንዶሰን መሸሻ (ዶክሌ) በሾሻል ሚዲያ የሚወራ ወሬ ከእውነት የራቀ ነው።

ዶክሌ በህይወት አለ ረጅም እድሜ እና ጤና ለዶክሌ እንመኛለን።

ያረጋገጠው ነዋሪነቱን በአሜሪካ ያደረገው #ተቦርነ_በየነ የቀድሞ የኢሳት ፕሮግራም መሪ የአሁን Ethio360 ተቀላቅሎ እየሰራ የሚገኝ።

//የሚታመን ምንጭ ነው//

ሼር አድርጉ በፌስብክ ገፃችሁ!!

@YeneTube @Fikerassefa
የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር እና ተቃዋሚያቸው ሬክ ማቻር በመጭው ቅዳሜ የአንድነት ሽግግር መንግሥቱን ለመመስረት #እንደተስማሙ ዘ ዴይሊ ሞኒተር ዘግቧል፡፡

ኪር መንግሥታቸውን ዛሬ ይበትናሉ፤ ነገ ደሞ ማቻርን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት አድርገው ይሾማሉ፡፡

Via:- Wazema
@Yenetube @Fikerassefa
ስለ ኮሮና ቫይረስ ብቻ የምንዘግብበትን ቻናል ተቀላቀሉ።

⬇️⬇️⬇️⬇️

https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEjsbjPMSsije0LoiQ
በሀዋሳ እና በሱሉልታ ከተሞች ለብልጽግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ በመደረግ ላይ ይገኛል።

@YeneTube @Fikerassefa
#ምርጫ2012

ምርጫ ቦርድ በተለያዩ ጫናዎች ስር ነው። ከመንግሥት ጣልቃ ገብነት ነጻ እንደሆነ ቢነገርና ምርጫውም ነጻና ፍትሐዊ ይሆናል ተብሎ ቢጠበቅም፣ አካሄዱ ግን ወደዛ እንዳልሆነና እንደማይመስል ያብራራሉ። ጠቅላይ ሚስትሩ በተወካዮች ምክር ቤት ያደረጉትን ንግግርና የሰጡትንም ምላሽ፣ ይልቁንም ከምርጫ ጋር የሚገናኙ ነጥቦች አወዛጋቢ ከመሆናቸው ላይ ቦርዱ ላይ ተጽእኖ ሊኖር እንደሚችል ማሳያዎችም እንዳሉ ግዛቸው ያነሳሉ። ነገር ግን ቦርዱ በማላዊ የሆነውን ሁኔታ አጢኖ ከወዲሁ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ሲሉ በማላዊ የሆነውን አብራርተዋል።

https://telegra.ph/Addismaleda-02-21
በተመሳሳይ በቢሾፍቱ እና በሰንዳፋ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄዷል።

@YeneTube @Fikerassefa
በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ነዋሪዎች በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለውን ለውጥና የብልፅግና ፓርቲን በመደገፍ ሰልፍ እያካሄዱ ነው።

በድጋፍ ሰልፉ ላይ የፊቼ ከተማ ነዋሪዎችን ጨምሮ ከዞኑ 13 ወረዳዎች የተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

ነዋሪዎቹ በፊቼ ስታዲየም በመገኘት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና ለብልፅግና ፓርቲ ያላቸውን ድጋፍ ገልፀዋል።
ድጋፋቸውን ለማመላከትም የሰንጋ እና የተለያዩ ስጦታዎችን ይዘው መገኘታቸው ነው የተገለፀው።

Via:- FBC
@YeneTube @Fikerassefa
የጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሀመድ የተመራና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር ደዔታ ክቡር ተስፋሁን ጎበዛይ እንዲሁም የአገር መከላከያ ከፍተኛ አመራሮች ያካተተ የአገራችን ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ከየካቲት 12-13 ቀን 2012 ዓ.ም በሳዑዲ ዓረቢያ ሪያድ የስራ ጉብኝት አድርጓል፡፡

በቆይታውም የልዑካን ቡድኑ ከሳዑዲ አረቢያ የጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ፈያድ ቢን ሃመድ አል-ሩዋሊና የሳዑዲ ዓረቢያ የመከላከያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በመገናኘት በሁለትዮሽና ቀጠናዊ የሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይቶችን አካሂዷል፡፡ በውይይቶቹ በኢትዮጵያና ሳዑዲ ዓረቢያ መካከል በመከላከያ ዘርፍ ያለውን የሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከርና በሌሎች ቀጠናዊ የጋራ ስጋቶች ዙሪያ በትብብር መስራትና የልምድ ልውውጥ ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ምክክርና የሃሳብ ልውውጦች ተደርገዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ በሪያድ የሚገኘውን የእስላማዊ ጸረ-ሽብርተኝነት ወታደራዊ ጥምረት ማዕከል (The Islamic Military Counter Terrorism Coalition (IMCTC)) ዋና ጽ/ቤት በመጎብኘትም ከማዕከሉ አመራሮች ጋር ሽብርተኝነት በመከላከል ረገድ በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አድርጓል፡፡

ምንጭ: በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ
@YeneTube @FikerAssefa