YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትሩን ያበሳጨው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቀባበል

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማክሰኞ የካቲት 10 ቀን 2012 ዓ.ም. ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ (ዶ/ር) ጋር ለመገናኘት ወደ ጽሕፈት ቤታቸው ያመሩ ሲሆን፣ በዕለቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን የጫነው ተሽከርካሪ ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት አካባቢ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት በር ላይ ሲደርስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የእንኳን ደኅና መጡ አቀባበል ለማድረግ እየጠበቋቸው ነበር፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የፕሮቶኮል ኃላፊዎች የመኪናውን በር ከፍተው ሚኒስትሩ እንዲወጡ ሲጠየቁ የሚጠብቁት ሰው እንዳለ ይገልጻሉ፡፡ ከዚያም ወዲያው ይጠበቁ የነበሩት ግለሰብ የፖምፒዮ ፎቶግራፈር መሆናቸውን የተረዱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ (ዶ/ር) በብስጭት ፊታቸውን አዙረው ወደ ጽሕፈት ቤታቸው ሲያቀኑ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከኋላ ተከትለው ሰላምታ ሲያቀርቡላቸው በምሥሉ ላይ ይታያሉ፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ያደረጉትን ውይይት ከጨረሱ በኋላ ዓብይ (ዶ/ር) ከፖምፒዮ የፕሮቶኮል ኃላፊዎች ፈቃድ ውጪ መኪና እያሽከረከሩ ምሳ ወደሚበሉበት ቦታ ወስደዋቸዋል፡፡

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ።

ሹመቱ ጨፌ ኦሮሚያ እያካሄደ ባለው መደበኛ ጉባኤ የጸደቀ ሲሆን፥ አቶ ሽመልስ አብዲሳም ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሆነው የተሾሙት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ሌሎች ሹመቶችን ለጨፌው እያቀረቡ ሲሆን፥ በዚህም ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒን ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አድርገው አቅርበዋል።በጉባኤው የህዝቡ አንድነት እንዲጠናከርና የህብረተሰቡ ችግር እንዲቀረፍ እየተሰራ መሆኑ ተነስቷል።አቶ ሽመልስ ባደረጉት ንግግርም ዜጎች ሀገር ወዳድ እንዲሆኑ የክልሉ መንግስትና በየደረጃው ያለው መዋቅር ይሰራል ብለዋል።አያይዘውም በክልሉ የዜጎች መፈናቅል እንዳይኖር ሲሰሩ መቆየታቸውንም ጠቅሰዋል።

በኢኮኖሚው ረገድ ህግና ደንቦች አርሶ እና አርብቶ አደሩን መሰረት አድርገው ይወጣሉም ነው ያሉት አቶ ሽመልስ። የህዝቦች መልካም ግንኙነት እንዲጠናከርና መቀራረብ እንዲኖር የሚሰራው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል።አቶ ሽመልስ አብዲሳ ጨፌ ኦሮሚያ ሚያዚያ ወር 2011 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ እንደሾማቸው የሚታወስ ነው።ጨፌው እያካሄደ ባለው ጉባኤ በዛሬው እለት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የረቂቅ ሕግ አዘገጃጀት ሥርዓትን ለመወሰን የወጣ አዋጅን ማጽደቁ ይታወሳል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ። ሹመቱ ጨፌ ኦሮሚያ እያካሄደ ባለው መደበኛ ጉባኤ የጸደቀ ሲሆን፥ አቶ ሽመልስ አብዲሳም ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሆነው የተሾሙት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ሌሎች ሹመቶችን ለጨፌው እያቀረቡ ሲሆን፥ በዚህም ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒን ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አድርገው አቅርበዋል።በጉባኤው የህዝቡ አንድነት እንዲጠናከርና የህብረተሰቡ…
በመቀጠልም ጨፌ ኦሮሚያ የተለያዩ ሹመቶችን አፅድቋል፥ በዚህም መሠረት፦

1. ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ - የኦሮሞ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት፣
2. አቶ ፈቃዱ ተሰማ - የጨፌ ኦሮሚያ የመንግሥት ተጠሪ፣
3. አቶ አዲሱ አረጋ - በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ፣
4. አቶ ጀማል ከድር- የኦሮሚያ ከተሞች ልማት እና ቤቶች ቢሮ ኃላፊ
5. አቶ ጌታቸው ባልቻ - የኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ
6. አቶ ጅቢሪል መሐመድ - የኦሮሚያ አስተዳደር እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ
7. አቶ ቦጋለ ፈለቀ - የኦሮሚያ የኢንተርፕራይ እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ
8. አቶ ካሳሁን ጎፌ - የኦሮሚያ ገቢዎች ባለሥልጣን ኃላፊ
9. አቶ ዳንኤል አሰፋ - የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ
10. አቶ ከበደ ዴሲሳ - የኦሮሚያ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ
11. አቶ ተሾመ ግርማ - የኦሮሚያ ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኃላፊ

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሚያ ቤተ ክህነት አደራጅ ኮሚቴ አባላት ክህነታቸው ተይዟል ሲል ቀዱስ ሲኖዶሱ አወጀ።

የቅዱስ ሲኖዶሱ ምልዓተ ጉባኤ ከየካቲት 9 እስከ 11/2012 ዓ.ም ድረስ ያደረገውን አስቸኳይ ስብሰባ ተከትሎ ዛሬ ከሰዓት ላይ መግለጫ ሰጥቷል።

የሲኖዶሱን መግለጫ በጽሁፍ ያቀረቡት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሲሆኑ በሚከተሉት ላይ የቅዱስ ሲኖዶሱን አቋም አሳውቀዋል።

https://telegra.ph/detail-02-19
OBS : OMN : LTV

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንግስት በሶስት መገናኛ ብዙሃን ላይ እርምጃ እንዲወስድ ጠየቀች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቤተ ክርስቲያኒቱና በምእመናን ላይ እየደረሰ ያለውን ችግር አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል፡፡

ቤተክርስቲያኗ ለኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን በላከዉ መግለጫ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ኦኤም ኤን፣ ኤል ቲቪ እና ኦሮሚያ ብሮድካስት ሰርቪስ ወይም ኦቢኤስ የተሰኙ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ከጥቂት ጊዜያት ወዲህ በጥንታዊትና ሐዋርያዊት በሆነችዋ እንዲሁም ለአገርና ለወገን ባለውለታና ባለታሪክ በሆነችው ቤተ ክርስቲያናችን የከፈቱት የስም ማጥፋት ዘመቻ እያካሄዱ ናቸው ብላለች።
መገናኛ ብዙሃኑ ታሪክን እያበላሹ የተሳሳተ መረጃ ለሕዝብ እያስተላፉ ይገኛሉም ብላለች ቤተክርስቲያኗ።

ከዚህም የተነሳ ከ60 ሚሊዮን ያላነሰ ተከታይ ያላትን ቤተ ክርስቲያን ክብሯንና ልዕልናዋን ዝቅ ባደረገ መልኩ የሚያስተላልፉት የተሳሳተ መረጃ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ብቻ ሳይሆን አገራዊ ቀውስ ለማምጣት እየተደረገ ያለ ጥረት በመሆኑ የሚመለከተው የመንግሥት አካል አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ የጣቢያዎቹ ኃላፊዎች ከብዙኃን መገናኛ ሕግ እና ደንብ አኳያ በሕግ እንዲጠየቁ ለወደፊቱም ከእንዲህ ዓይነት ሕገወጥ ድርጊት እንዲታቀቡ መንግሥትም በዚሁ ላይ አስፈላጊውን ውሳኔ እንዲያሳልፍልን ቅዱስ ሲኖዶስ ጠይቋል፡፡

Via:- Ethio FM
@YeneTube @Fikerassefa
👍1
በኢትዮጵያው በተከሰከሰው የቦይንግ 737 አውሮፕላን የሟቾች ጠበቆች በቦይንግ ኩባንያ ላይ የመሠረቱት ክስ ዛሬ በቺካጎ ፍርድ ቤት እንደሚታይ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ኩባንያው ስለ አውሮፕላኑ ስሪት፣ ዲዛይን እና ስለደረሱት አደጋዎች ሙሉ ሰነዶችን እንዲሰጣቸው ነው ጠበቆቹ የከሰሱት፡፡ ጠበቆቹ ኩባንያው ቁልፍ መረጃዎችን ከምርመራው ቡድን እንደደበቀ ያምናሉ፡፡

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
#ኦነግ #OLF #ABO

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከ350 በላይ የሚሆኑ አባሎቹ በመንግስት መታሰራቸውን አስታወቀ።

ፓርቲው እንዳስታወቀው በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ከ350 በላይ አባሎቼ እና ደጋፊዎቼ በጅምላ ታስረውብኛል ብሏል።

ፓርቲው እንዳስታወቀው በቀጣዩ አገር አቀፍ ምርጫ ለመወዳደር ዝግጅት እያደረገበሚገኝበት በዚህ ወቅት ይህ የጅምላ እስር መፈጸሙ አሳስቦኛል የተጀመረውን የዲሞክራሲ ጭላንጭልም ያከስማል ብሏል።

ሰሞኑን ባልታወቀ ሁኔታ በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች የጅምላ እስራት በዘመቻ መልኩ በኦነግ አባላት እና ደጋፊዎች ላይ ተፋፍሞ ይገኛል፡፡ ይህን የጅምላ እስራት እየፈጸመ የለዉ አካል የኦሮሚያ ፖሊስ እንደሆነም ፓርቲው አስታውቋል።

የጅምላ እስሩ በተለይም ከአንድ ሳምንት ወድህ ብቻ በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች (በ7 የኦሮሚያ ዞኖች እና በ26 ወረዳና የከተማ አስተዳደሮች) በጅምላ ከታሰሩት አባላቶቻችን እና ደጋፊዎቻችን መካከል እስከ አሁን ባገኛነዉ መረጃ መሰረት ወደ 350 የሚጠጉ የፓርቲው አመራሮች እና አባላት ታስረውብኛል መንግስት በአስቸኳይ ይፍታቸው ሲል አሳስቧል።

Via:- Ethio FM
@YeneTube @Fikerassefa
መንግስት በታገቱት የደንቢ ደሎ ዪንቨርሲት ተማሪዎች አጥጋቢ ምላሽ የማይሰጥ ከሆነ በኦሮሚያ ክልል የሚማሩ የአማራ ተማሪዎች ወደቦታቸው እንዲመለሱ አደርጋለው ሲል የአማራ ወጣቶች ማህበር አሳሰበ፡፡

የአማራ ወጣቶች ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ አስናቀ መንገሻ ለአሐዱ እንደተናገሩት ከሁለት ወራት በፊት በደንቢዶሎ ዩንቨርስቲ 17 የአማራ ተወላጅ ተማሪዎች የታገቱ ሲሆን በኦሮሚያ ክልል 40ሺ የሚሆኑት ደግሞ ከትምህርት ገበታቸው መፈናቀላቸውን አንስተዋል::

መንግስት በታገቱ ተማሪዎች ላይ አፋጣኝ ምላሽ የማይሰጥና ሀላፊነቱን የማይወጣ ከሆነ በሁሉም የኦሮሚያ ክልል ዩንቨርሲቲዎች የሚማሩ የአማራ ተወላጅ ተማሪዎች ወደየቤታቸው እንዲመለሱ ለማድረግ በቅርቡ መግለጫ እንደሚሰጥ የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ አስናቀ ተናግረዋል፡፡

#Bringbackourstudents

Via:- Ahadu radio
@YeneTube @Fikerassefa
"ተባርኮ የተሰጠን ጽላት[ፈይሳ አዱኛ] አለን” ያሉት ማደናገርያ መኾኑን አረገጠናል፣ ምእመናን በዚህ እንዳይሳሳቱ ሲሉ በመግለጫው አሳስበዋል።

@YeneTube @Fikerassefa
ሜቴክ ‹‹ኢንተግሬትድ ኢንዱስትሪያል ቴክኖሎጂ ኮርፖሬሽን›› በሚል ስያሜ በድጋሚ ሊቋቋም ነው!

በርካታ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ ባለመቻሉና ከዚሁ ጋር በተገናኘ የአገር ሀብት እንዲባክን አድርጓል ተብሎ የሚወቀሰው የኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ)፣ ‹‹ኢንተግሬትድ ኢንዱስትሪያል ቴክኖሎጂ ኮርፖሬሽን›› በሚል ስያሜ በድጋሚ ሊቋቋም ነው።ሜቴክን በድጋሚ ለማቋቋም የተረቀቀው ማቋቋሚያ ደንብ፣ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መላኩን ሪፖርተር ከታማኝ ምንጮች ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ሜቴክ ‹‹ኢንተግሬትድ ኢንዱስትሪያል ቴክኖሎጂ ኮርፖሬሽን›› በሚል ስያሜ በድጋሚ እንደሚቋቋም፣ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 25/1984 መሠረት እንደሚተዳደርም ረቂቅ ደንቡ ይገልጻል።

ሜቴክ ኢንተግሬትድ ኢንዱስትሪያል ቴክኖሎጂ ኮርፖሬሽን በሚል መጠሪያ በድጋሚ ከተቋቋመ በኋላ፣ እንዲያሳካቸው የሚፈለጉ ዓላማዎችንም ረቂቅ ደንቡ ይዘረዝራል። ከተዘረዘሩት ዓላማዎች መካከል የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ለማፋጠን፣ እንዲሁም የዕውቀትና የፋይናንስ እጥረትን ለመፍታት በሚያስችለው መንገድ ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ኩባንያዎች ጋር በአጋርነት መሥራት አንዱ ሲሆን፣ ለወታደራዊ አገልግሎት የሚውሉትን ጨምሮ በማንኛውም ቴክኖሎጂ ላይ መመራመር፣ ማልማትና ወደ ፋብሪካ ውጤትነት መቀየር ሌላው የኮርፖሬሽኑ ዓላማ እንደሚሆን ተመልክቷል።

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
ግራ አጋቢው ዘመን
አዲስ መፅሐፍ በገበያ ላይ

የወባ ትንኞችን ከመግደል ሀሳቦችን ወደ መግደል፤
ከስራ አጥነት ወደ ስራ አልባነት እያመራን ነው… ምን ይሻላል?

ግራ አጋቢው ዘመን መፅሐፍ መፍትሄ አለው፡፡

መፅሐፉ እንዴት ከጀግንነት ወደለየለት ብሔርተኝነት፣
ከኃይማኖተኝነት ደግሞ ወደ ሽብርተኝነት እያመራን እንዳለን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡ መጨረሻችንስ?

መልሱ ግራ አጋቢው ዘመን መፅሐፍ ውስጥ ይገኛል፡፡

እንኳን ወደ ግራ አጋቢው ዘመን መፅሐፍ ግራ ተጋብተው መጡ!!

የእውነት ይሄ መፅሐፍ አስተሳሰባችሁን ያሰፋዋል!!

በየመፅሀፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል!!
ባይብል ኮድ

ስለ እያንዳንዳችን ዕጣ ፈንታ ጨምሮ በአለም ላይ ያሉ መሪዎች ስለሚገደሉበት ቦታ፣ ስለሚገድሏቸው ሰዎች ስም…

በአለም ላይ ስለተከናወኑ ነገሮችና ወደፊትም ስለሚከናወኑ ነገሮች ሁሉ በስም፣ በቀንና በቦታ ሳይቀር ከዛሬ ሶስት ሺ አመት በፊት…

በየቤታችን በሚገኘው መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ በኮድ ተቀጧል!!

በአንድ ምሽት ሽያጭ ብቻ ሪከርድ የያዙት ባይብል ኮድ ቁጥር 1፣ ቁጥር 2 እና የመጨረሻው ቁጥር 3 ኮዶቹን እየፈቱ ያስደምሙናል፡፡

ሶስቱንም መጽሐፎች በየመፅሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኟቸዋል፡፡
@teklutilahun
Forwarded from HEY Online Market
Galaxy A51 (2019)
Display: 6.4"
Storage: 128 GB
Camer: 48 MP + 5 MP
Battery: 4000 mAh
Ram: 6 GB

Price : 13,200 Birr

Contact US @heymobile
0925927457
0953964175
0910695100
@HEYOnlinemarket
Forwarded from YeneTube
📌 Minoxidil የወንዶች ፀጉርና ፂም ማሳደግያ

📌 ፀጉሮት እየሳሳ አስቸግሮታል አልያም ፂም ማብቀል ይፈልጋሉ ? መፍትሔውን ይዘንሎት መተናል

ከቆዳችን ስር የሚገኘውን የፀጉር ጉጥ በማንቃት የሳሳን ፀጉር ወደ ቀድሞው የሚመልስ

📌📌 በ"FDA" እውቅናና ማረጋገጫ የተሰጠው ደግሞም በebay ፣ amazon እና በመሳሰሉት የ online መገበያያዎች ላይ "5" ★★★★★ ኮኮብ ያገኘ ነው

በቀን 2 ጊዜ ለሚጠቀሙ ሰዎች በ 1 ወር ውስጥ ውጤት የሚያሳይ

📞 0993944661
📞 0953928523
Forwarded from YeneTube
ሁሉንም ሰብስቦ በአንድ ላይ የያዘ የግብይት ድረገፅ
በድረ ገፁ ላይ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት ዕቃዎቹን መሸጥ ይችላል።
ከ2700 በላይ ዕቃዎች

@SebsibieEthiopia
www.sebsibie.com
📞 0953707070
83ኛው የሰማዕታት ቀን በአዲስ አበባ 6 ኪሎ የሰማዕታት መታሰቢያ ሀውልት አደባባይ እየተከበረ ነው።

ዕለቱ አባት አርበኞችና የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት ነው እየተከበረ ያለው።የሀገር መከላከያና የፌደራል ፖሊስ ማርሽ ባንድ አባላት በስፍራው በመገኘት የተለያዩ ጣዕመ ዜማዎችን አሰምተዋል።ዕለቱ በ1929 ዓ.ም በወቅቱ የኢትዮጵያ አገረ ገዢ በነበረው ሮዶልፎ ግራዚያኒ በግፍ የተጨፈጨፉ ከ30 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን የሚታወሱበት ነው።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
አዲስ የመንግሥት ሠራተኞች ውሎ አበል ደንብ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀረበ!

የኢፌዴሪ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አዲስ የመንግሥት ሠራተኞች ውሎ አበል ደንብ አዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ማቅረቡን አስታወቀ።በኮሚሽኑ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አለባቸው ዓለሙ፣ ረቂቅ ደንቡ ካለው ነባራዊ ሁኔታ በመነሣት በጥናት ላይ ተመሥርቶ መዘጋጀቱን አመልክተዋል።ደንቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ተመርምሮ ማስተካከያ ከተደረገበት በኋላ፣ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመርቶ ተግባር ላይ እንዲውል የሚደረግ መሆኑም ተጠቁሟል።ከሐምሌ 1 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ ስራ ላይ የዋለው የመንግስት ሠራተኞች የቀን ውሎ አበል መመሪያ እንደሚያመለክተው የመንግሥት ሠራተኛው በየትኛውም ክልል ሄዶ ቢሰራ ከፍተኛ ደመወዝ አለው የሚባለው 225 ብር የሚታሰብለት ሲሆን፤ አነስተኛ ደመወዝ ተከፋይ ነው የሚባለው ደግሞ በቀን የሚያገኘው 111 ብር ነው።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
ህዝብዊ የድጋፍ ሰልፍ በሀዋሳ ከተማ እንደሚደረግ ተገለጸ!

አርብ የካቲት 13/2012 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ማግስት ጀምሮ በሀገራችን እያስመዘገቡ ያሉትን ለውጥ በመደገፍና ለውጡን ለማስቀጠል ህዝቡ ከጎናቸው የሚቆም መሆኑን ለማረጋገጥ ታላቅ ህዝባዊ የምስጋናና የድጋፍ ሰልፍ እንደሚደረግ ተገለጸ።በመሆኑም የከተማው ነዋሪዎችና የሲዳማ ህዝብ የሚያደርጉት ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ፍጽም ሰላማዊና የደመቀ እንዲሆን የዞኑና የከተማው አስተዳደር አስፈላጊውን ዝግጅት ያጠናቀቁ መሆኑን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ህዝብ ግንኙነት ጽህፈት ቤትን ጠቅሶ ደቡብ ቲቪ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሸገር ዳቦ ማምረቻ ፋብሪካ ግንባታ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ደረሰ!

በሜድሮክ እህት ኩባንያ ‹‹ሆራይዘን ፕላንቴሽን›› እየተገነባ ያለው የሸገር ዳቦ ማምረቻ ፋብሪካ ተጠናቆ ሥራ ሊጀምር የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ እንደደረሰ የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ:: በሆራይዘን ፕላንቴሽን የእቅድ ቢዝነስ ልማትና ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አቶ ይበልጣል ሽመልስ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት ግንባታው ከተጀመረ ወራትን ያስቆጠረው የሸገር ዳቦ ማምረቻ ፋብሪካ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሷል።የመሰረት ድንጋይ ከተጣለ ጀምሮ ሥራው በጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እየተመራ እንደነበር የተናገሩት ሥራ አስኪያጁ በቀን 18 ሰዓት በመስራት ግንባታውን ማፋጠን እንደተቻለና ጎን ለጎንም የማሽነሪዎችንና የሌሎች ግብዓቶችን ግዢ ተፈፅሞ ሀገር ውስጥ መግባታቸውን ገልጸዋል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
ከ20 አመታት በፊት ከኢትዮጵያ የወጣው ታሪካዊው የዘውድ ቅርስ ወደ አገር ተመለሰ።

ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት ከሀገር የወጡ በርካታ ቅርሶች እንዳሏት ይታወቃል፡፡ከነዚህ መካከል አንዱ የሆነው እና ከ20 አመታት በፊት ባልታወቀ ሁኔታ ከኢትዮጵያ የወጣዉና ከ400 ዓመታት በላይ እድሜ ያለው የኢትዮጵያ ታሪካዊ የዘውድ ቅርስ ነዉ፡፡የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀዉ፤ቅርሱ ተሰርቆ ለ20 አመታት ያህል በኔዘርላንድ እንደነበር የተነገረ ሲሆን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴርና በሌሎችም ትብብር ቅርሱን ወደ አገር ቤት መመለስ እንደታቸለ አስታዉቋል፡፡

ለቅርሱ መመለስ እና መገኘት የትውልደ ኢትዮጵያውያን ትብብር ቅርሱ ሚና ከፍተኛ እንደነበር የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡በዛሬዉ እለት ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ለብሔራዊ ሙዚየም የርክክብ ስነ ስርዓት መደረጉንም ሰምተናል፡፡ኢትዮጵያ በጣሊያን እና ከዚያም ቀደም በነበሩ ወራራዎች ወቅትዊና ታሪካዊ ቅርሶቿ በአዉሮፓዉያኑ እንደተበዘበዘች የዘርፉ ምሁራን ይናገራሉ፡፡በቅርቡም የአፄ ቴዎድሮስ ፀጉር ቁንድላ ከአገረ እንግሊዝ ወደ አገር መመለሱ አይዘነጋም፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa