YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ፖምፔዮ በግደቡ ዙሪያ የሚካሄደው ውይይት በቅርቡ መቋጫ እንደሚያገኝ ጠቆሙ!

የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከአሜሪካው አቻቸው ማይክ ፖምፔዮ ጋር ዛሬ ከሰዓት በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፔዮ፤ የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ ግንኙነት በርካታ ዓመታትን አስቆጥሯል ያሉ ሲሆን፤ ከ1930ዎቹ ጀምሮ ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሲያካሂዱ መቆየታቸውን አስታውሰዋል።በአሜሪካዋ ዋሽንግተን ዲ.ሲ በርካታ ቁጥር ያለው የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ መኖሩን የጠቆሙት ፖምፒዮ በዛሬው መግለጫቸው በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ እና በመጪው ምርጫ ላይ የአገራቸውን አቋም አንጸባርቀዋል።

የህዳሴው ግድብ ድርድር ትኩረቱን ስቶ የውሃ ድርሻ ክፍፍል ላይ ሆኗል ተባለ
የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ
ፕሬዝደንት ትራምፕ ሦስቱንም አገራት ሊያስማማ የሚችል ስምምነት እንዲፈጠር ቅድሚያ የሰጡት ጉዳይ ነው ብለዋል ማይክ ፖምፔዮ።የግድቡ ግንባታ በአሜሪካ የገንዘብ ሚንስትር እና በዓለም ባንክ አደራዳሪነት ሲካሄድ መቆየቱን እና የየአገራቱ የውጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ልዩነቶቻቸውን ለመፍታት ወደ ዋሽንግተን በተደጋጋሚ መጓዛቸውን አስታውሰዋል።

ፖምፒዮ "የመግባቢያ ነጥቦች እየተጠናቀቁ ወደ ስምምነት ተቃርቧል። አሁንም ግን የሚቀር ሥራ አለ" ብለዋል። "የሦስቱ አገራት መሪዎችም ሆኑ አሜሪካ፤ የሁሉንም አገራት ፍላጎት ያማከል ስምምነት እንዲደረስ ነው ጥረት ሲደረግ የቆየው። ብዙ ሥራ ይቀረናል፤ በቀጣዩ ወር ግን እንደሚጠናቀቅ ተስፋ አደርጋለሁ" ብለዋል።

ምርጫ
"የአብይ አስተዳደር ተጠያቂ እና ሁሉን አሳታፊ በሆነ የዲሞክራሲ ሥርዓት ያምናል፤ አሜሪካም እንዲሁ" ያሉት የቀድሞ የሲአይኤ አለቃ ማይክ ፖምፔዮ፤ ስለቀጣዩ ምርጫ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር መወያየታቸውን ተናግረዋል።ቀጣዩ ምርጫ ነጻ እና ታዓማኒነት ያለው ሆኖ ሁሉንም እንደሚያሳትፍ ተወያይተናል ብለዋል።

አንበጣ መንጋን መከላከል
በአፍሪካ ቀንድ የተከሰተውን አንበጣ መንጋ ለመከላከል አሜሪካ ድጋፍ እንደምታደርግ አስታውቀዋል። በኬንያ፣ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል አሜሪካ የ8 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ እንደምታደረግ አስታውቀዋል።

በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው ለውጥ
በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉት የለውጥ ሥራዎች ሕዝቡን በረዥም ጊዜ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ናቸው ያሉት ፖምፔዮ፤ "በእዚህ ላይ የእኛ አስተዋጽኦ በተቻለን መጠን መደገፍ ነው" ብለዋል።"እንዲህ ዓይነት ትልልቅ ለውጦች ሲካሄዱ ውጤቶች በፍጥነት ላይታዩ ይችላሉ" ያሉት ፖምፔዮ፤ በአፍሪካ መዲና ከሴት ርዕሰ ብሔር ጋር ተገናኝተው መወያየታቸው እንዳስደነቃቸው አልሸሸጉም።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
በምዕራብ ጉጂ ዞን ዱግዳ ዳዋ ወረዳ 59 ኩንታል ካናቢስ አደንዛዥ እጽ ተያዘ!

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ዱግዳ ዳዋ ወረዳ 59 ኩንታል የካናቢስ አደንዛዥ እጽ ተያዘ።የጉጂ ዞን ፖሊስ መምሪያ ወንጀል መከላከል ሃላፊ ኮማንደር አዳሙ አባተ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ በዱግዳ ዳዋ ወረዳ 59 ኩንታል የካናቢስ አደንዛዥ እጽ በዛሬው ዕለት ተይዟል።አደንዛዥ እጹ በአንድ የጭነት ኤፍ ኤስ አር ተሽከርካሪ ተጭኖ ከሻሸመኔ ወደ ሞያሌ በመጓዝ ላይ እያለ ነው በህዝብ ጥቆማ የተያዘው።በወሩ ለሁለተኛ ጊዜ መሰል አደንዛዥ እጽ መያዙን የገለጹት ኮማንደር አዳሙ፥ በአካባቢው የሚስተዋለውን የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ለሰዐታት ተቋርጦ የነበረው የሞባይል ዳታ ኢንተርኔት እና የጥሪ አገልግሎት ተመልሷል መስራት ጀምሯል።

የብሮድባንድ አገልግሎት እና የSMS አገልግሎት ብቻ ነበር ሲሰራ የነበረው።

ለምን ተቋረጠ ? የሚለውን አጥርተን እናቀርባለን።
@YeneTube @Fikerassefa
አሜሪካ በአባይ ግድብ ዙሪያ ከታዛቢነት ወደ አደራዳሪነት ስለማደጓ የሱዳን መንግስት ቃል አቀባይ መናገራቸው ahramonline ዘግቧል።
@YeneTube @Fikerassefa
የየካቲት 11ን 45ኛ አመት የምስረታ በዓል አስመልክቶ የብልፅግና ፓርቲ የአባል አመራር ዶ/ር አብርሀም በላይ የሰጡት መግለጫ።

እጅግ የተከበርከውና ከባድ የህይወት መስዋእትነትን ጨምሮ ውድ ዋጋ በመክፈል እና መራራ ትግል በማካሄድ ለራስህ ብቻ ሳይሆን ለወገኖችህ የሚተርፍ ድል ያስመዘገበከው መላው የትግራይ ሕዝብ እንኳን ለ45ኛው የካቲት 11 በዓልህ በሰላም አደረስህ።ውድ የትግራይ ህዝብ እና የትግሉ ሰማእታት ቤተሰብ እና የትግሉ ሰለባዎች በሙሉ

ከ45 ዓመታት በፊት ይደርስብህ የነበረው የዘመናት ጭቆና...

ሙሉው መግለጫ👇👇👇

https://telegra.ph/anniversary-02-19
በቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ውስጥ ተረፈ ምርት ተገኘ!

የቦይንግ 737 ማክስ ጀትላይነር አውሮፕላኖች የነዳጅ ቱቦ ውስጥ አላስፈላጊ ተረፈ ምርት መገኘቱ ተገለጸ። ግኝቱ የአውሮፕላኖቹ አስተማማኝነት ላይ ጥያቄ አስነስቷል።የቦይንግ 737 ዋና ኃላፊ "ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ነው" ሲሉ ለሠራተኞቻቸው የተናገሩ ሲሆን፤ የቦይንግ ቃል አቀባይ በበኩላቸው የተረፈ ምርቱ መገኘት አውሮፕላኑን ከበረራ አያዘገየውም ብለዋል። 737 ማክስ በያዝነው ዓመት አጋማሽ ላይ ወደ ሥራ ይመለሳል መባሉ ይታወሳል።የተረፈ ምርቱ መገኘት ይፋ ከመደረጉ በፊት የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች በረራ እንዲያቋርጡ መወሰኑ ይታወሳል። ይህም በኢትዮጵያና በኢንዶኔዥያ አውሮፕላኖቹ ተከስክሰው የብዙዎች ሕይወት መጥፋቱን ተከትሎ የተላለፈ ውሳኔ ነበር።

ለአየር መንገዶች ያልተላለፉ ብዙ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ክንፍ ላይ በሚገኙ የነዳጅ ቱቦዎች ውስጥ አላስፈላጊ ተረፈ ምርቶች ተትተው መገኘታቸውን ድርጅቱ አሳውቋል።የቦይንግ ቃል አቀባይ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ተረፈ ምርቶች (በእንግሊዘኛ Foreign Object Debris (FOD) የሚባሉት) የተገኙት መጋዘን ውስጥ የሚገኙ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ላይ የጥገና ፍተሻ ሲደረግ ነበር።"ተረፈ ምርቱ መገኘቱን ተከትሎ ምርመራ አድርገናል፤ ማስተካከያም አድርገናል" ብለዋል ቃል አቀባዩ።ፌደራል አቪየሽን አድሚንስትሬሽን (ኤፍኤኤ)፤ ቦይንግ ስለ ተረፈ ምርቶቹ ጥልቅ ምርመራ እያደረገ መሆኑን እንደሚያውቅ ለቢቢሲ ተናግሯል።ተረፈ ምርቶች ስንል አውሮፕላኑ በሚገጣጠምበት ወቅት ሠራተኞች የረሷቸው የብረት ቁርጥራጮች ወይም ሌላ አላስፈላጊ ቁሶችን የሚያካትት ሲሆን፤ በአንድ ወቅት በከፍተኛ ሁኔታ ይሸጥ የነበረው 737 ማክስ ባለፉት ጊዜያት የገጠሙት እክሎች ላይ የሚደመር መሰናክል ነው።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
አንበሳ ጋራዥ በ2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ወደ ዴፖ ሊቀየር ነው!

ከሃምሳ ዓመት በላይ የአንበሳ አውቶቡስ ማቆሚያ እና የጥገና ቦታ ሆኖ ያገለገለው ዋናው መሥሪያ ቤት፣ በአንድ ጊዜ ከ850 በላይ አውቶቡሶችን ማስተናገድ እንችልና የተለያዩ አገልግሎቶችን እንዲሰጥ ‹‹የካ ዴፖ›› በሚል ግንባታ ሊከናወንለት ነው።በሦሰት ወራት ውስጥ የሚጀመረው ይህ ግንባታ፣ ኹለት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር ወጪ ይጠይቃል። በተለምዶ ገርጂ መብራት ኃይል ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ በሚገኘው የአንበሳ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት፣ በአስር ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ ነው።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ስልጤ ዞን ወራቤ ገቡ!

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስልጤ ዞን ከተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ለመወያየት ነው ወራቤ የገቡት፡፡ከሁሉም የዞኑ ወረዳዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት ውይይቱ ለማድረግ በቂ ዝግጅት ተደርጓል፡፡በውይይቱም የልማትና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ትኩረት ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የአማዞን ባለቤት ጄፍ ቤዞስ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ትግል ለማገዝ 10 ቢሊየን ዶላር ለመስጠት ቃል ገቡ።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
ህወሓት የተመሠረተበት 45ኛ ዓመት እየተከበረ ነው!

ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) የተመሠረተበት 45ኛ ዓመት በመቀሌ ከተማ በመከበር ላይ ነው።በዓሉ የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር)፣ የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ ነባር ታጋዮች፣ የሰማዕታት ቤተሰቦች በተገኙበት በሰማዕታት ሐውልት የአበባ ጉንጉን በማስቀመጥ ተጀምሯል።በበዓሉ ላይ ከአክሱም ሥልጣኔ ጀምሮ ክልሉን አሁን እስካለበት ጊዜ የሚያሳዩ ልዩ፣ ልዩ ትርኢቶች ቀርበዋል።የክልሉ ልዩ ኃይል እና ፖሊስ ሠራዊት ያካተተ ወታደራዊ ሰልፍም ተካሒዷል።በዓሉን ለመታደም የሱዳን መንግሥት ተወካዮች፣ የፌዴራል ኃይሎች አባላት፣ ከክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ተወካዮች እየተሳተፉ ነው።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
ኮድ ሁለት ዶልፊን መኪኖች እየተያዘ ነው!

በአብዛኛው (ዶልፊን ኮድ 2) መኪኖችን አዲስ አበባ ላይ እየተያዙ መሆኑን መረጃዎች እየደረሱን ይገኛሉ።

ለምን የሚለውን ጥያቄ ለመኪና ባለቤቶቹን ጠይቀን የተሰጠን ምላሽ

መልስ :- ኮድ 2 በቢኒባስ በህዝብ እንጂ ለቤት አገልግሎት አይውልም በሚል እንደታሰረባቸው ነው የነገሩን።

ነገር ግን የመኪኖቹ ሊብሬ ላይ የህዝብ እና የእቃ በሚል ነው የተሰጠቸው መኪኖቹ ከ5 ሰው ብላይ መጫን አይችልም እንዲሁም ከ6 ኩንታል በላይ መጫን እንደማይችሉ ይገልፃል።

@YeneTube @Fikerassefa
የገንዘብ ሚንስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ለይፋዊ ጉብኝት ወደ ሀርጌሳ ሱማሌ ላንድ ማቅናቱን ሰምተናል።

#Hargeisa #Somaliland
@YeneTube @Fikerassefa
በደቡብ ኦሞ የኮሌራን ወረርሽኝ ለመቆጣጠር የኬሚካል እጥረት አጋጥሟል!

በደቡብ ኦሞ ዞን አራት ወረዳዎች ከታኅሳስ 15/2012 ጀምሮ የተከሰተውን የኮሌራ ወረርሽኝ ለመቆጣጠር ውሃን ለማከም የሚያገለግሉ ኬሚካሎችን ለማግኘት እና የትራንስፖርት አቅርቦት ላይ ችግር እንደገጠመው ዞኑ አስታወቀ።ወረርሽኙ በዞኑ ማሌ፣ ሀመር፣ ሰላማቦ እና ፀማይ በተሰኙ ወረዳዎች ላይ ከተከሰተ ከአንድ ወር 15 ቀን በላይ ሆኖታል። በበሽታው ከ 1ሺሕ 500 በላይ ሰዎች ተይዘው ሕክምና እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን፣ የ20 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ከዞኑ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
ትናንት አመሻሽ ላይ ለተከሰተው የኢንተርኔት እና የሞባይል ድምፅ አገልግሎት መቋረጥ ኢትዮ ቴሌኮም ይቅርታ ጠይቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
መኪናችንን ያለ አግባብ መንግስት አስሮብናል ያሉ ግለሰቦች ለምክትል ከንቲባው ቅሬታቸውን አሰሙ

( Fidelpost.com)
በመንግስት የፀጥታ ሀይሎች በመንገድ ላይ እንድንቆም እየተደረገ መኪናቹ በህገወጥ መልኩ በሌላ አገለግሎት ተሰማርቷል ተብለን አስከ 800,000 ብር ደረስ ቀረጥ ተጠይቀናል ያሉ ግለሰቦች ዛሬ ምክንትል ከንቲባ ታከለ በሚገኙበት የከተማው መስተዳደር ደጃፍ ዛሬ ጠዋት በመግኘት ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

ቅሬታ አሰሚዎቹ ለፊደል ፓስት እንደተናገሩት 600 የሚጠጉ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በአዲሰ አበባ እና በደቡብ ክልል በ2 ቁጥር ታርጋ የተሰጣቸው D4D እና ዳማስ መኪኖቻቸው እንደታሰሩባቸው ገልፀዋል።

መኪናቸው ከተወሰደባቸው መሀል ሰዒድ ጠሀ እንዲህ በማለት ስለተፈጠረው ድርጊት ያስረዳል ” ከትናንት በስቲያ መሳርያ የያዙ ፓሊሶች መንገድ ላይ አስቆሙኝ ።ምን ተፈጠረ ስላቸው ትፈለጋለክ ብለው ወደ ጉሙሩክ ፅህፈት ቤት ወሰዱኝ። እዛም መኪናክ ለህዝብ አገልግሎት ወስደክ ለግልክ ስራ በማዋልክ 700, 000 ብር ቀረጥ ክፈል አሉኝ።

በጣም ግራ የገባኝ መኪናዬን በ2 ቁጥር ታርጋ ሳወጣ ፍቃድ የሰጠኝ የመንግስት አካል ነው።

ይሄ ስህተት ከሆነ መጠየቅ ያለበት እራሱ መንግስት እንጂ እኔ አይደለሁም” በማለት ቅሬታውን ገልፇል።

በጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ቃሊቲ ጎሙሩክ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የበተነው ሰርኩርላር ደብዳቤ እንደሚያሳየው መኪኖቹ በህዝብ አገልግሎት ሰበብገብተው በግል አገልግሎት ሲሰሩ በመገኘታቸው ነው ለግል አገልግሎት በሚቀረጥ የቀረጥ ሂሳብ እንዲከፍሉ የተገደዱት ያሉት ብሏል።

ምንጭ:- Fidelpost.com
@Yenetube @Fikerassefa
"ትግራይ ራስዋን የቻለች አገር ናት ብላችሁ አውጁ" ዶ/ር ደብረፅዮን

በኢትዮጵያ እየተከሰተ ያለው ጣልቃ ገብነት እንዲሁም በትግራይ ላይ ያለው ጥላቻ የማይስተካከል ከሆነ "ትግራይ ራስዋን የቻለች አገር ናት ብላችሁ ልታውጁ ይገባል" ሲሉ ለተወካዮች ምክር ቤት ምክር ቤት አባላት ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል መልእክት አስተላልፈዋል።ይህንን መልዕክት ያስተላለፉት ህወሓት የተመሰረተበትን 45ኛውን አመት አስመልክቶ በዛሬው እለት በመቀሌ ስታዲየም ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።

የትግራይ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ባስተላለፉት መልእክት "የስልጣን ጊዜያችሁ እያለቀ ስለሚገኝ ከመበታተናችሁ በፊት ታሪክ ስሩ። በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ጣልቃ ገብነት በተለይም ትግራይን በተመለከተ በመሪዎች ደረጃ የተሰጡት የጥላቻና የፀረ ህዝብ ንግግሮች ችን በይፋ ኮንኑ" ብለዋል።አክለውም "ይህ የማይሆን ከሆነ ትግራይ ራሷን የቻለች አገር መሆኗን ወስኑ፤ አውጁ" ብለዋል።

"አገር በመበተን ሂደት ነበሩ ተብላችሁ በታሪክ እንዳትወቀሱ፤ ግዳጃችሁን ተወጡም" በማለት መልእክታቸውን ለተሰበሰበው ህዝብ አስተላልፈዋል።ዶ/ር ደብረፅዮን ከዚህም በተጨማሪ በትግራይና በኤርትራ መካከል ያለውን ታሪካዊ ዳራም እንዲሁም አሁንም ስላለው ግንኙነት ምክር አዘል መልእክት አስተላልፈዋል።

ህወሓት በትጥቅ ትግል በነበረበት ወቅት "የደርግን ስርዓት ለመጣል የትግራይ እና የኤርትራ ልጆች አንድ ጉድጓድ ላይ ተቀብረዋል" ያሉት ዶ/ር ደብረጽዮን ከኤርትራ ነጻነት በኋላም ቢሆን የትግራይ ህዝብ እና ህወሓት በኤርትራ ህዝብ የነጻነት ጥያቄ የማያወላዳ አቋም በመያዛቸው ብዙ ፖለቲካዊ ተቃውሞ ቢገጥመውም ከአቋሙ ውልፍት እንዳላለ ተናግረዋል።በሁለቱ ሃገራት ከተካሄደው ጦርነት በኋላ ሰላም ከመምጣቱ በፊትም የኤርትራ ተፈናቃዮችን "አቅፎ ጥላ" በመሆን ለኤርትራ ህዝብ ወዳጅ መሆኑን አስመሰክረዋል ብለዋል።

በየካቲት 11 በዓል ደግሞ የነበሩ ቅራኔዎችን ለመፍታት ዝግጁ መሆናቸውን የገለፁት ዶ/ር ደብረፅዮን የህዝብን ቀጣይነት አስምረውታል። "መንግሥታት ፈራሾች ናቸው እና ሰላማችንን ለማስቀጠል በህዝቦች መሀከል ውይይት እንዲጀመር እንፈልጋለን።" በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።በትግራይና ኤርትራ ህዝቦች መካከል ያለውን የቋንቋ እና ባህል ተመሳሳይነት፣ የጋራ ታሪክ እንዲሁም በደም የተሳሰሩ ከመሆናቸው አንፃር ለጦርነት የሚፈላለጉ ህዝቦች አለመሆናቸውን አፅንኦት በመስጠት ተናግረዋል።

ለዚህም የተለያዩ ኃይሎች ጣልቃ ገብነትን በወነጀሉበት ንግግራቸው ህዝቡን የፖለቲካ አጀንዳ መደበቂያ አድርገውታልም ብለዋል።"የትግራይ እና ኤርትራ ህዝቦችን ወደ ጦርነት ሊማግዱት የሚያስቡ ኃይሎች አሉ፤ የተጀመረውን የሰላም ሂደት ተቋማዊ በሆነ መንገድ ከመፍታት ይልቅ ለፖለቲካ አጀንዳ መደበቅያ እያደረጉት ይገኛሉ" ብለዋል።የትግራይ ህዝብ እህትማማች ከሆነው የኤርትራ ህዝብ ጋር ግጭት የመግባት ምንም አይነት አላማ የለውም የሚሉት ዶ/ር ደብረፅዮን ሁለቱን ሃገራት ወደ ጦርነት ለመክተት የሚደረጉ ሴራዎች እንዳሉም አልደበቁም።

ሁለቱን ሃገራት የሚያገናኙ መንገዶች መዘጋት እንዲሁም በኢትዮጵያ የሚገኙ የኤርትራውያን የስደተኞች መጠለያ እንዲዘጉ እና አዳዲስ ስደተኞች እንዳይቀበሉ የማድረግ ስራ "በኢትዮጵያና በኤርትራ መንግሥት የተደረገ ሴራ ነው" ብለዋል።አክለውም "የኤርትራ ህዝብ ችግር ችግራችን ስለሆነ ለእናንተ የሚዘጋ በር የለንም። ትግራይ አገራችሁ ነው፤ የኤርትራ ሠራዊት ትግራይ አገርህ ነው። እየታለመ ያለው የፖለቲካ ሴራ አብረን እናክሽፈው" በማለት ንግግራቸውን አድርገዋል።በአገሪትዋ የተለያዩ አከባቢዎች እየተካሄደ ስላለው የሠራዊት ስምሪት እና እሱን ተከትሎ ስለተከሰተው ጉዳት ተጠያቂ ሊኖር ይገባል ያሉት ዶ/ር ደብረፅዮን የትኛውን እንደሆነ ዝርዝር ከመስጠት ተቆጥበዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
ሳውድ አረቢያ ከሰሞኑ ሕጋዊ ሆነው በምድሯ እየኖሩ ያልተፈቀደላቸውን ሥራ የሚሠሩ የተለያዩ ሃገራት ዜጎች ማሠር መጀመሯ ተሰማ።

በሕጉ መሠረት አንድ የውጭ ዜጋ ወደሳውዲ ሲገባ እንዲሠራ በተፈረደለትን የሥራ መስክ የማይሠራ ከሆነ እንደ ሕገወጥ ይቆጠራል።

በዚሁም መሠረት ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ አንድ ሺህ ገደማ የሚሆኑ የሌሎች ሃገራት ዜጎች ሕጋዊ ሆነው ሳለ ፈቃድ ከተሰጣቸው የሥራ መስክ ውጭ በመሠማራታቸው በሁለት ሳምንት ውስጥ መታሠራቸውን ከጅዳ ነብዩ ሲራክ የላከልን ዜና ያመለክታል።

ይህን አስመልክቶም በጅዳ ቆንስል ጀነራል አቶ አብዱ ያሲን እንደገለጹት በዚህ የሳውዲ መንግሥት ርምጃ 11 ኢትዮጵያውያን ተይዘዋል።

Via:- የጀርመን ድምፅ ራዲዮ
@YeneTube @Fikerassefa
🇹🇷#Study_in_Turkey!🇹🇷

ያለምንም ፈተና ቱርክ ሀገር ሄደው መማር ይፈልጋሉ?
90% ስኮላርሺኘ አግኝተው መማርስ?
#Sky_Education_Consultancy ይህን መልካም አጋጣሚ አመቻቸሎት!

Deadline: 22 Feb 2020

👉 Medicine & Health sciences
👉 Engineering
👉 Psychology
👉 Pharmacy
👉 Law
👉 Business Administration
👉 Computer science and IT
👉 Architecture
👉 Finance & banking.. and more

#Education_visa_Guaranteed
#Guaranteed_acceptance_letter

#ዛሬውኑ_ያናግሩን!! LIMITED SEATS
#Sky_Education_Consultancy
0977202020
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሳውድ አረቢያ መንግሥት ከሰሞኑ በመውሰድ ላይ ያለውን ርምጃ አስመልክቶ በጅዳ ቆንስል ጀነራል አቶ አብዱ ያሲን የሰጡን ማብራሪያ ያድምጡ።

ቪዲዮ ነቢዩ ሲራክ ከጄዳ (DW)
@YeneTube @Fikerassefa