YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የሶሪያ ሠራዊት 70 አስከሬኖችን የያዘ የጅምላ መቃብር በደማስቆ አቅራቢያ በሚገኝ ቀደም ሲል በአማፅያኑ ተይዞ በነበረ አካባቢ ማግኘቱን የሀገሪቱን የዜና ወኪል ጠቅሶ የዘገበው አጃንስ ፍራንስ ፕረስ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
ከ123 ሄክታር መሬት በላይ የማልማት አቅም ያለው የመስኖ ፕሮጀክት ተመርቆ ሥራ ጀመረ፡፡በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ በግብርና ዕድገት ፕሮግራም በ2010 ዓ.ም የግንባታ ሥራው የተጀመረው የመስኖ ፕሮጀክት ዛሬ ተመርቋል፡፡

ምንጭ:አብመድ
@YeneTube @FikerAssefa
የፊታችን እሁድ ሊካሄድ የነበረው ፍቅር ያሸንፋል የኢትዮጲያ ሩጫ እና ፌስቲቫል ተራዘመ፡፡

ለፍቅር እንሩጥ ጥላቻን እናምልጥ በሚል መሪ ሀሳብ የፊታች እሁድ የካቲት 15 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል ተብሎ ቀጠሮ የተያዘለት ፍቅር ያሸንፋል የኢትዮጲያ ሩጫ እና ፌስቲቫል መራዘሙን ሰምተናል፡፡

የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች እና የመንግስት ሀላፊዎች ያስጀምሩታል ተብሎ ይጠበቅ የነበረው ፌስቲቫል እና ሩጫው ወደ ሌላ ጊዜ የተላለፈበት ምክንያት የካቲት 14 ምሽት ላይ ከሚካሄደው #የድምፃዊ_ቴድሮስ_ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ኮንሰርት ጋር የመርሀግብር መቀራረብ በመከሰቱ መሆኑን አዘጋጆቹ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ውድድሩ መራዘሙን እንጂ ትክክለኛ የሚካሄድበትን የውድድር ቀን ገና አልወሰንም ምክንያቱም የአትሌቲክስ ፌዴሪሽን ፕሮግራሞችን ማጣራት ስለሚኖርብንም ብለዋል አዘጋጆቹ፡፡

ከከንቲባ ጽህፈት ቤት እና ከፀጥታ ሀይሎች ጋርም ተነጋግረነን የፕሮግራም ሂደቱን ማመቻት ስለሚያፈልግ ቲሸርቶች የገዙ ተሳታፊዎች ትክክለኛውን ቀን ይፋ እስከምናደርግ በትዕግስት ጠብቁን ብለዋል፡፡በተቀያሪው የጊዜ ሰሌዳ አይመቸንም የምትሉ ታሳታፉዎች ካላችሁ ቲሸርቶቹን በመመለስ ገንዘባቹን ማግኘት ትችላላቹ ተብላቹሀል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የዱባይ ዐለም ዐቀፍ ወደቦች ኩባንያ የኤርትራ ወደቦችን ለማስፋፋት እንደተስማማ ብሉምበርግ ዘግቧል፡፡ ኩባንያው ለወደቦቹ አዳዲስ የሎጅስቲክ መሳሪያዎችን ይገጥማል፤ የወደቦቹን አገልግሎት አቅም ያሳድጋል፡፡ ኤርትራ ስለ ስምምነቱ ያለችው ነገር የለም፡፡ በሌላ ዜና፣ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ለ3 ቀናት የሥራ ጉብኝት ዛሬ ሪያድ እንደገቡ ቃል አቀባያቸው የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

Via:- ዋዜማ ራዲዮ
@YeneTube @Fikerassefa
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ከሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሞሐመድ ፎርማጆ ጋር በሐርጌሳ ጉብኝት ለማድረግ ያቀረቡትን ጥያቄ የሱማሌላንድ ራስ ገዝ ውድቅ እንዳደረገው ሆርን ዲፕሎማት ዘግቧል፡፡ የጋራ ጉብኝቱን ሃሳብ ለሐርጌሳ ያቀረቡት ዐቢይ ናቸው፡፡

Via:- Horn Diplomat / Wazema
@Yenetube @Fikerassefa
ለመንግስት ሠራተኞች የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ሊሰጥ ነው

ከመጭው ሚያዝያ ወር ጀምሮ በመንግስታዊ መዋቅር ውስጥ ለሚገኙ ሠራተኞች የብቃት ማረጋገጫ ፈተና እንደሚሰጥ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የሲቪል ሰርቪስ ብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ ፕሮጀክት መጀመርን አስመልክቶ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የተዘጋጀ የምክክር መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው።

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ብርሃኑ ፈይሳ እንደገለጹት÷ የብቃት ማረጋገጫ ፈተናው የሚሰጠው ከሀገራዊ ለውጡ ጋር የተቃኘ የመንግስት ሰራተኛ እንዲኖርና የወቅቱን የህዝብ ጥያቄ የሚመልስ ኃይል ለመፍጠር በሚያስችል መልኩ ነው።

https://telegra.ph/yenetube-02-17
መካሄድ የሚጀምረው የጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባኤ በህግ የበላይነትና የክልሉ የጸጥታ ሁኔታ ላይ በትኩረት እንደሚመክር ተገለጸ።

የጨፌው አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ ጨፌው ባካሄደው 10ኛ መደበኛ ጉባኤ ለጸጥታ ጉዳይ ቅድሚያ ሰጥቶ እንደነበር በማስታወስ፥ ይህንንም ተከትሎ በአብዛኛው የክልሉ አካባቢዎች ሰላማዊ ሁኔታ እንዳለ ተናግረዋል።

@YeneTube @Fikerassefa
የጉምሩክ ኮሚሽን በጥር ወር ከ152 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ ዕቃ እና ሕገ ወጥ ገንዘብ መያዙን አሰታወቀ።

ይህም ከገቢ 121 ሚሊዮን ብር ሲሆን፣ ከወጪ ደግሞ 31 ሚሊዮን ብር በአጠቃላይ 152 ሚሊዮን ብር እንደሆነ ተገልጿል።

በቁጥጥር ስር የዋለው የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴው በመጠን ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 75 በመቶ ብልጫ እንዳለው ታውቋል።
@YeneTube @Fikerassefa
የኮሮና ተህዋሲን ለመቆጣጠር የሚደረግ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ የኮሮና ተህዋሲን አስቀድሞ ለመከላከል በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ጊዜያዊ የማቆያ ጣቢያዎች መቋቋማቸውን የአገሪቱ የማኅበረሰብ ጤና ተቋም አስታወቀ። ሰሞኑን ከውጭ የገቡ 14 ቻይናውያን በአሁኑ ወቅት በሀዋሳ በተቋቋመው ጊዜያዊ ማቆያ ጣቢያ ውስጥ እንዲቆዩ ተደርጎአል።

በኢትዮጵያ የኮሮና ተህዋስን አስቀድሞ ለመከላከል በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ጊዜያዊ የማቆያ ጣቢያዎች መቋቋማቸውን የአገሪቱ የማሕበረሰብ ጤና ተቋም አስታወቀ። 

ተቋሙ እንዳስታወቀው የኮሮና ተህዋስን አስቀድሞ ለመከላከል ከውጪ ሀገር የሚመጡ የተለያዩ አገራት ዜጎች ከበሽታው ነጻ መሆናቸው እስኪታወቅ ድረስ ክትትል ለማድረግ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ታሳቢ ያደረጉ ጊዜያዊ የማቆያ ስፍራዎች ተቋቁመው ወደ ስራ ተገብቷል። 

በጊዜያዊ የማቆያ ስፍራዎቹ የክትትል ሥራው እየተከናወነ የሚገኘው ከየክልሎቹ የጤና ቢሮዎችና ከከተማ አስተዳደር የጤና ጽሕፈት ቤቶች ጋር በመተባበር መሆኑን በተቋሙ የዓለም አቀፍ የጤና ደንብ የኢትዮጵያ ተወካይ ዶክተር ፈይሳ ረጋሳ ለዶቼ ቨለ ( DW )ገልጸዋል። 

በደቡብ ክልል ጤና ቢሮ የጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዋና የሥራ ሂደት ባለቤት አቶ እንዳሻው ሽብሩ በበኩላቸው ሰሞኑን ከውጭ የገቡ አስራ አራት ቻይናውያን በአሁኑወቅት በሀዋሳ በተቋቋመው ጊዜያዊ ማቆያ ጣቢያ ውስጥ እንዲቆዩ መደረጉን ገልፀዋል።

አቶ እንዳሻው አያይዘውም «ከውጭ የገቡ ቻይናውያን በጊዜያዊ ማቆያ ውስጥ ከገቡ ዛሬ ስምንተኛ ቀናቸውን አስቆጥረዋል። እስከአሁንም ምንም አይነት ምልክት አልታየባቸውም ።  በአስራ አራት ቀናት ውስጥ የተለየ ምልክት ካልታየ ወደ ስራ ገበታቸው እንዲቀላቀሉ ይደረጋል» ብለዋል። 

የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ፍፁም ከተማ ፓርኩ ቻይናውያንና ሌሎች የውጭ ሀገራት ዜጎችን ጨምሮ ከሰላሳ አራት ሺህ በላይ የሰው ሀይል ያለበት በመሆኑ የኮሮና ተህዋስን አስቀድሞ ለመከላከል አስፈላጊው የቅድመ ጥንቃቄ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።

የፓርኩ ማህበረሰብ በተህዋሱ ባህሪና በሚያስከተለው በሽታ ምልክቶች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በመከናወን ላይ እንደሚገኙም ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል።

Via:- DW
@YeneTube @Fikerassefa
YeneTube
የኮሮና ተህዋሲን ለመቆጣጠር የሚደረግ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ በኢትዮጵያ የኮሮና ተህዋሲን አስቀድሞ ለመከላከል በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ጊዜያዊ የማቆያ ጣቢያዎች መቋቋማቸውን የአገሪቱ የማኅበረሰብ ጤና ተቋም አስታወቀ። ሰሞኑን ከውጭ የገቡ 14 ቻይናውያን በአሁኑ ወቅት በሀዋሳ በተቋቋመው ጊዜያዊ ማቆያ ጣቢያ ውስጥ እንዲቆዩ ተደርጎአል። በኢትዮጵያ የኮሮና ተህዋስን አስቀድሞ ለመከላከል…
ደቡብ ክልል በጊዜያዊነት ማቆያ አዘጋጅተናል ያሉት ከእውነት የራቀ ነው።

ከ14 ቻይናዊ 13 ቻይናዊያን እኔ የምሰራበት መስሪያ ቤት ሰራተኞች ናቸው። ቤቱን ተከራይተው ያስቀመጠው ድርጅቱ ነው። #ክልሉም ሆነ #ፓርኩ ያደረገው ነገር የለም መረጃውን ያደረሰን ለጉዳዩ መረጃ ያለው ወዳጃችን ነው።

እንዲሁም በፓርኩ ውስጥ ካሉ አንዱ ፋብሪካ ነው ለይቶ ማቆያ ቦታውን ያዘጋጀ ነው።
ከተማ ውስጥ ሌላ ቦታም አለ። ፓርኩ ውስጥ በልየታ የተቀመጡ ሌሎችም አሉ።

@YeneTube @Fikerassefa
#COVID-2019_update

የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር ከሰባ ሺህ ያለፈ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ደግሞ 1776 ደርሷል።

Via AFP
@YeneTube @FikerAssefa
በዛሬው እለት ጠ/ሚ አብይ በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው ላይ "ብልፅግና ለሀገራችን- ነፃነት ለህዝባችን" ከሚል መልዕክት ጋር የለጠፉት ካርታ ጀዋር መሃመድን ጨምሮ ከተለያዩ ፖለቲከኞች ትችትን አስተናግዷል። "ካርታው ኢትዮጵያን አሃዳዊ የሆነች ሀገር አድርጎ ነው ሚያሳየው፣ የብሄር ብሄረሰቦች ስብስብ ፣ፌዴሬሽን መሆኗን የዘነጋ ነው፣ ይህም ከዚህ በፊት በነበሩ መንግስታት(አገዛዞች) ተሞክሮ የከሸፈና አደገኛ አካሄድ ነው" ብለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር ማይክ ፖምፒዮ ዛሬ የካቲት 9 ቀን 2012 ዓም ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል።
ሚኒስትሩ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ማይክ ፖምፒዮ በነገው እለት ከክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጋር የሁለቱን አገሮች የሁለትዮሽ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉ።በተጨማሪም ከኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

Via Spokesperson Office
@YeneTube @FikerAssefa
የቀድሞው የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጁነዲን ሳዶ ‹ሸገር› የተሰኘ አዲስ ባንክ ከሌሎች አጋሮቻቸው ጋር በመሆን በማቋቋም ላይ መሆናቸውን አስታወቁ።

የባንኩ መሥራች ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ጁነዲን ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት፣ ድርሻ የመሸጥ ፈቃድ ከብሔራዊ ባንክ አግኝተው ከየካቲት ሰባት ጀምሮ በይፋ አክስዮን መሸጥ ይጀምራሉ። የባንኩ የምሥረታ አስተባባሪ ኮሚቴ በአጠቃላይ 150 ግለሰቦች ያሉበት ሲሆን፣ ከአገር ውስጥ እንዲሁም ከዳያስፖራው ሀብት በማሰባሰብ ካፒታሉን እንደሚያሟላም ጁነዲን ተናግረዋል።

https://telegra.ph/YeneTube-02-18-2
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤውን እያካሄደ ሲሆን ሹም ሽሮች እንደሚኖሩም ይጠበቃል፡፡
@YeneTube @Fikerassefa
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የስነ-ምግባር ጉድለት በተገኘባቸው 29 ሰራተኞች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በበጀት ዓመቱ አጋማሽ የስነ-ምግባር ጉድለት በተገኘባቸው 29 ሰራተኞች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።

ከግብር ከፋዩ የሚመጡ ጥቆማዎችን እና መረጃዎችን ትክክለኛነት በማጥራት የስነ-ምግባር ጉድለት የተገኘባቸው ባለሙዎች እና አመራሮች ላይ እርምጃ መወሰዱን ገልፀዋል።

በዚህም፣ በዘንድሮው በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ የስነ-ምግባር ጉድለት በተገኘባቸው 29 ባለሙያዎች ላይ ከከባድ የዲሲፕሊን ጥፋት ቅጣት ከስራ እስከማሰናበት የደረሰ እርምጃ መወሰዱን የቢሮው ኃላፊ አቶ ሺሰማ ገብረስላሴ ተናግረዋል።

የቢሮው የስድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም 94 ነጥብ 46 በመቶ ሲሆን በበጀት አጠቃቀም ደግሞ 93 በመቶ ማሳካቱን ገልጿል።
ቢሮው፣ የመጀመሪያ ስድስት ወር ዕቅድ አፈፃፀሙን አስመልክቶ ከክፍለ ከተማ የገቢዎች ጽህፈት ቤቶች ከተውጣጡ አመራሮች እና ባለሙያዎች ጋር ተወያይቷል።

ምንጭ:- ኢዜአ
@YeneTube @Fikerassefa
ጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

ጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባኤውን በዛሬው እለት ማካሄድ ጀምሯል።

በዛሬው እለት መካሄድ በተጀመረው ጉባዔ ላይ የክልሉ መንግስት የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት በክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት አስታውቀዋል።

በተጨማሪም የተለያዩ ረቂቅ አዋጆች እና ሹመቶችም ቀርበው ውይይት ከተደረገባቸው በኋላ ይፀድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

እንዲሁም ጨፌው በመደበኛ ጉባዔው በህግ የበላይነትና የክልሉ የጸጥታ ሁኔታ ላይ በትኩረት እንደሚመክርም ተገልጿል።

Via:- FBC
@YeneTube @Fikerassefa
በጥር ወር ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በማስወገድ ከ8 ሚሊዮን ብር በላይ ተገኝቷል!

የአስራ አምስት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ንብረት የሆኑ 30 ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በማስወገድ ከስምንት ሚሊዮን ብር በላይ መገኘቱን የመንግሥት ንብረት፣ ግዢ እና ማስወገድ አገልግሎት አስታወቀ።ለሽያጭ ከቀረቡት 30 ተሽከርካሪዎች ንብረትነታቸው የ10 ፌዴራል ተቋማት የሆኑ 21 ተሸከርካሪዎች፣ ከመነሻ ዋጋ በላይ ላቀረቡባቸው 13 ተጫራቾች እንዲሁም ተወዳዳሪዎች ከፍተኛውን ዋጋ የሰጡባቸው 9 ተሽከርካሪዎችን ሽያጭ ጨምሮ በድምሩ 8 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ተገኝቷል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮ በምክትል ርእሰ መስተዳድርነት በእጩነት ቀርበዋል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን አስቸኳይ ጉባኤ በምክር ቤቱ አዳራሽ ተጀምሯል፡፡የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ የዕጩ ተሿማዎች ዝርዝር ግለ ታሪክና የሹመቱን አስፈላጊነት ለምክር ቤቱ አባላት አስረድተዋል፡፡ ወቅቱን የዋጀ በዕውቀት ላይ የተመሠረተ አመራር ለመስጠትና ኃላፊነትን በአግባቡ ለመወጣት የሚጠይቅ ወቅት ላይ በመሆናቸው ሹመቱ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር ላቀ አያሌው፣ የአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ቧያለው፣ በርእሰ መስተዳድር ደረጃ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ መላኩ አለበል እና የከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋንታ ደጀን በፌዴራል መንግሥት ደረጃ ኃላፊነት ስለተሰጣቸው በምትካቸው አዳዲስ ሹመት መስጠት እንዳስፈለገ ነው ርእሰ መስተዳድር የተናገሩት፡፡በመሆኑም ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮ በምክትል ርእሰ መስተዳድርነት በእጩነት ቀርበዋል፡፡ የምክር ቤት አባላትም በእጩ ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ ዙሪያ ሐሳብ እየሰጡ ነው፡፡

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa