YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ጋምቤላ ክልል በተፈጠረው ከፍተኛ ሙቀት ሳቢያ የስራ ሰዓት ለውጥ ማድረጉን አስታወቀ።

የክልሉ መስተዳድር ጽህፈት ቤት በሙቀት ምክንያት ከየካቲት 1 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ አስከ ሚያዝያ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ለሶሰት ወራት ያክል የስራ ሰዓት ለውጥ ማድረጉን አስታውቋል።በዚህም መሰረት ጧት የስራ ዐት መግቢያ 1 ሰዓት ሲሆን መውጫ 5 :30 እንዲሁም ከሰዓት የስራ ሰዓት መግቢያ 10 ሰዓት ሲሆን መውጫ ደግሞ 12 :30 እንደሆነ ተገልጿል።በአካባቢው ከፍተኛ የሙቀጥ መጠን መፈጠሩ የስራ ሰዓት ለውጥ እንዲደረግ ምክንያት መሆኑን ክልሉ አስታውቋል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
በግብርና ሚኒስቴር ስር ለሚከናወነው ሴፍቲ ኔት ፕሮግራም ማስፈፀሚያ የሚውል 75 ሺሕ ቶን ስንዴ ግዢ ለማከናወን ‹ፕሮሚሲንግ› ከተሰኘ ድርጅት ጋር ከስምምነት ላይ መድረሱን የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት አስታወቀ።

ግዢው የዓለም ባንክ ለግብርና ሚኒስቴር የሴፍትኔት ፕሮግራም ባደረገው 24 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ የሚፈፀም ነው። አቅራቢዎቹን የመለየት ሥራ በመንግሥት ግዢ እና ንብረት ማስወገድ በኩል እንደተከናወነም ለማወቅ ተችሏል።

ምንጭ:- አዲስ ማለዳ
@YeneTube @Fikerassefa
በኮሮና ቫይረስ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ900 በልጧል፡፡

የቻይና ብሔራዊ ጠና ኮሚሽን እንዳረጋገጠው የሟቹ ቁጥር አሁን 908 ድርሷል ፡፡በፊሊፒንስና በሆንግ ሆንግ ከተከሰተው ሞት ጋር ሲደምር ደግሞ የሟቾቹ ቁጥር አሁን 910 መድረሱ ተነግሯል፡፡ሲኤን ኤ እንደዘገበው በአለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙት ሰዎች ቁጥር ወደ 40 ሺህ ያደገ ሲሆን አብዛኛው በቫይረሱ የተጠቁት ሰዎች ቻይናዊን ናቸው፡፡ቻይና ውስጥ በኮሮና የተጠቁ ሰዎች ቁጥር አሁን ከ 37 ሺህ 200 በላይ ደርሷል፡፡እ.ኤ.አ. በ 2002 እና በ 2003 ሳርስ የተባለው ወረርሽኝ የተከሰተ ሲሆን በዓለም ዙሪያ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 774 ነበር።

ይህም እስካሁን ከነበሩ ተመሳሳይ ወረርሽኞች ብዙ ሰዎች የሞቱበት ወረርሽኝ ያደርገዋል ተብሏል።በሌላ ዜና የአለም የጤና ድርጅት ከፍተኛ ባለሙያዎችን ወደ ቻይና ልኳል፡የድርጅቱ ዳሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም በትዊተር ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት በቻይና ለተከሰተው ወረርሽን እገዛ የሚያደርግ የባለሙያ ቡድን መላኩን ተናግረዋል፡፡የቫይረሱ መነሻ ነች በምትባለው ውሃን ግዛት በቀን 97 ሰዎች ህይወታቸውን በአንድ ቀን አጥተዋል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
 “ፓራሳይት” የተሰኘው የደቡብ ኮሪያ ፊልም በዘንድሮው የኦስካር ሽልማት በምርጥ ፊልም ዘርፍ  አሸንፏል።

ፊልሙ በደቡብ ኮሪያ ዋና ከተማ ሴኡል በሚኖሩ እና በተለያየ የኢኮኖሚ ደረጃ በሚኖሩ ሁለት ቤተሰቦች የህይወት ውጣ ውረድ ዙሪያ የሚያጠነጥን መሆኑ ተነግሯል።

በኦስካር ሽልማት ታሪክ በእግሊዘኛ ቋንቋ ያልተሰራ ፊልም  በምርጥ ፊልም  ዘርፍ ሲያሸንፍ ይህ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።

ይህን ተከትሎ ታሪካዊ ፊልም ለመባል የበቃው “ፓራሳይት”  በአጠቃላይ በአራት ዘርፎች የኦስካር ሽልማቶችን መቀዳጀት ችሏል።

የፓራሳይት ፊልም ዳይሬክተር ቦንግ ጁን ሆ  ቢት የኦስካር የዓመቱ ምርጥ ዳይሬክተር በመሆኑ  ተሸልሟል።

በሌላ በኩል ሬኔ ዜልዌገር “ጁዲ” በተሰኘው ፊልም የጁዲ ጋርላንድን ገጽ ባህርይ በመወከል በምርጥ  የሴት ተዋንያን ዘርፍ አሸናፊ ሆናለች።

ጆዋኩን ፊኒክስ  ደግሞ  “ጆከር” በተሰኘው ፊልም በወንዶች ምርጥ ተዋናይ ዘርፍ የኦስካር  ሽልማት አሸናፊ መሆን ችሏል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ/FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የፈተናና ምዘናዎች ኤጀንሲ የዘንድሮውን የትምህርት ዘመን ጊዜያዊ የሀገር አቀፍ የፈተና መስጫ ሰሌዳ ይፋ አድርጓል ።

@YeneTube @FikerAssefa
የገቢዎች ሚኒስቴር ከዚህ ወር ጀምሮ የስራ ሰዓት መግቢያና መውጫ ለውጥ አደረገ!

የገቢዎች ሚኒስቴር ከየካቲት 01/2012 ዓ.ም ጀምሮ የስራ ሰዓት መግበያና መውጫ ያሻሻለ ሲሆን ከሰኞ እስከ አርብ፡

1. ከጠዋቱ 2፡00 - 6፡00 መደበኛ የሥራ ሰዓት፣
2. ከ6፡00 – 7፡00 የምሳ እረፍት፣
3. ዘወትር አርብ ግን የሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡00 – 5፡00 ሲሆን ከ5፡00 -7፡00 የምሳ ሰዓት ሆኖ ከሰዓት በኃላ ደግሞ ከ7፡00 – 11፡00 መደበኛ የሥራ ሰዓት ይሆናል፡፡
4. እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00- 6፡00 ሰዓት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መደበኛ የሥራ ሰዓት መግቢያና መውጫ መሆኑን አውቃችሁ ሁሉም የግብር ከፋይ ደንቤኞቻችንና አገልግሎት ፈላጎዎች በተገለፀው ሰዓት ውስጥ እንዲትጠቀሙ በአክብሮት እንገልጻለን፡፡

ምንጭ:የገቢዎች ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
በኮንታ ልዩ ወረዳ የተከሰተውን የበረሃ አንበጣ መንጋ ለመከላከል በሄሊኮፕተር የማጥፊያ መድሃኒት ርጭት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በአጎራባች መሎ ኮዛ ወረዳ አድርጎ ወደ ልዩ ወረዳው በሁለት መንጋ የገባው ከቆላው ቀበሌያት ወደ ደጋውም እየሰራጨ እንደሚገኝ የልዩ ወረዳው እ/ተ/ሀ/ል/ጽ/ቤት አስታውቋል።አንደኛው መንጋ በጨበራ ጩርጩራ ብሄራዊ ፓርክ ላይ ያረፈ ሲሆን ይህንን ለመከላከል በሄሊኮፕተር/በአውሮፕላን / የማጥፊያ መድሃኒት ርጭት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በተጨማሪም በልዩ ወረዳው በተለያዩ ቀበሌያት የበረሃ አንበጣው ተከስቶ ህብረተሰቡ በተለያዩ ዘዴዎች የመከላከል ስራ በመስራት ላይ ይገኛል። ይህ አንበጣ መንጋ በየትኛውም ዕፅዋትና ሰብል ላይ 100% ውድመት የሚያደርስ ነው።

ስለዚህ ይህ አንበጣ መንጋ በአካባቢው እንዳያርፍ እንዳይቆይ ለማድረግ:-
ጭስ በማጨስና በማፈን፣ የተለያዩ ቆርቆሮ በመምታት ከፍተኛ ድምጽ በማውጣት፣ ጅራፍ በማጮህና በጋራ በመረባረብ ማባረር እንደሚገባ ተገልጿል።

ዘገባው የአስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ነው
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ የነፃ ቪዛ ስምምነት ተፈራረሙ!

ኢትዮጵያ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ ዛሬ የካቲት 2 ቀን 2012 ዓም በአዲስ አበባ ባደረገት የሁለትዮሽ ውይይት በሁለቱ አገሮች መካከል የዲፕሎማቲክ እና የአገልግሎት ፓስ ፖርት ለያዙ ዜጎች ያለ ቪዛ መገባት እንዲችሉ የነፃ ቪዛ ስምምነት ተፈራርመዋል።ስምምነቱን በኢትዮጵያ በኩል የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ የፈረሙ ሲሆን፤ በኢኳቶሪያል ጊኒ በኩል ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ክቡር ሲሞን ኦዮኖ ፈርመዋል።

ሁለቱ ከፍተኛ ባለስልጠናት በዛሬው ውይይታቸው የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቸልባቸው ጉዳዮች እና ከዚህ በፊት የተፈረሙ ስምምነቶች አፈጻጸምን በተመለከተ ተወያይተዋል።ሁለቱ አገሮች ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በቅርቡ በኢኳቶሪያል ጊኒ ባደረጉት ኦፊሴላዊ የስራ ጉብኝት በቱሪዝም እንዲሁም በነዳጅና ፔትሮልየም ዘርፍ በትብብር ለመስራት የሚያስቸል ስምምነት መፈራረማቸው ይታወቃል። በተያያዘ ዜና የአፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ ከካሜሮን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር ሌጅዩን ምባሌ ጋር የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

ምንጭ: የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለኮሮና ቫይረስ መመሪያና መከላከያ መሳሪያዎችን ወደ ሀገር ውስጥ አጓጓዟል።

@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ ክልል የስልጤ ዞን ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ዞኑን በክልል ለማደራጀት ወስኗል። ምክር ቤቱ በክልልነት ለመደራጀት የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ ያጸደቀው በሙሉ ድምጽ መሆኑን የምክር ቤቱ ሕዝብ ግንኙነት ጽሕፈት ቤት በፌስቡክ ገጹ ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል።

Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከካናዳ መንግስት ለተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም የምርጫ ስራ ድጋፍ የተሰጠውን ድጋፍ ዛሬ በጋራ ተፈራርሟል። በፊርማ ስነስርአቱ የቦርዱ አመራር አባላት ብዙወርቅ ከተተ እና አበራ ደገፋ( ዶክተር) ተገኝተዋል።

Via NEBE
@YeneTube @FikerAssefa
የእርሻ ባንክ ለማቋቋም ብሄራዊ ባንክ ጥልቅ ጥናት እንዲቀርብለት ጠየቀ!

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ለእርሻ ባንክ ማቋቋሚያ ይረዳ ዘንድ ጥልቅ ጥናት ይቀርበለት ዘንድ የግብርና ሚኒስቴርን መጠየቁ ታውቋል፡፡የግብርና ዘርፍ ለአገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ግኝት እንዲሁም ለኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ ቢሆንም በፋይናንስ ረገድ እዚህ ግባ የሚባል ጥቅም እያገኘ ባለመሆኑ ባለሞያዎች ለዘርፉ የሚሆን ፋይናንስ በበቂ ሁኔታ ይታሰብበት በማለት ሲወተውቱ ቆይተዋል፡፡

በሳምንቱ አጋማሽ በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት አስተባባሪነት ‘አዲስ ወግ’ በተሰኘው መድረክ ላይ ግብርናውን ለማዘመን በተደረገ ውይይት የለውጥ ማሻሻያ እቅዶችን ያቀረቡት የግብርና ሚኒስትር የፖሊሲ አማካሪ እና የግብርና ማሻሻያ ቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ አንተነህ ግርማ (ፒሄች ዲ) እንደተናገት የግብርናው ዘርፍ ለኢኮኖሚው ሁለንተናዊ ድጋፍ እያደረገ ቢሆንም ከሌሎች ዘርፎች ጋር እኩል ተወዳድሮ ከባንክ ብድር ለማግኘት ተገዷል በማለት ዘርፉ ላይ ያለውን ጫነ አብራርተዋል፡፡ አሁን ላይ ከጠቅላላው ብድር የእርሻው ዘርፍ 10 በመቶ ብቻ እያገኘ መሆኑን ሰነዶች ያሳያሉ፡፡

በመድረኩ አንተነህ እንዳሉት ዘርፉ የራሱ ባንክ ሊኖረው ይገባል ብለዋል፡፡ ከዛም ባለፈ ባንኮች ከብድራቸው እስከ አርባ በመቶ ለግብርናው ሊሰጡ ይገባል ብለዋል፡፡ምንጮች ለካፒታል እንደተናገሩት የግብርና ሚኒስቴር በእርሻ ባንክ ምስረታ ላይ ከብሄራዊ ባንክ ሃላፊዎች ጋር የተነጋገር ሲሆን፡፡ የገንዘብ ተቆጣጣሪው አካል ጥልቅ ጥናት እንዲቀርብለት መጠየቁም ታውቋል፡፡ሃሳቡ በገንዘብ ሚኒስቴር ድጋፍ አግኝቷል የሚሉት ምንጮች ጥናቱ በዚህ አመት ይጠናቀቃል በማለት ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
የካቲት 5!

"የዴሞክራሲ ሽግግር በኢትዮጵያ: ተስፋዎቹ እና ተግዳሮቶቹ" በሚል ርእስ አቶ አንዱለም አራጌ፣ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ፣ አቶ ጌታቸው ረዳ፣ አቶ ጃዋር መሃመድ፣ አቶ ልደቱ አያሌው፣ አቶ አብርሀ ደስታ፣ አቶ ሀሰን ሞአሊን፣ ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ እና ዶ/ር መረራ ጉዲና ንግግር አድርገው ከዛ ውይይት ይደረጋል።

Via:- ኤልያስ መሰረት
@YeneTube @Fikerassefa
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዚህ በያዝነው የካቲት ወር ዕረፍት ላይ እንሚሆን ተገለጸ፡፡ በዚሁ መሠረት አምስተኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የሰራ ዘመኑ ከየካቲት 1/2012 ዓ.ም እስከ የካቲት 30/2012 ዓ.ም ድረስ በዕረፍት ላይ እንደሚሆን ታውቋል፡፡

ምንጭ:የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
በቅርቡ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ዶ/ር አብርሃም በላይ(በስተግራ ያሉት) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የስራ አመራር ቦርድን እንዲመሩ ተጨማሪ ኃላፊነት ተሰጣቸው፡፡

ምንጭ: አዲስ ስታንዳርድ
@YeneTube @FikerAssefa
አዲስ ዘመን ጋዜጣ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ መረጃ እንዲያሰጠው እንባ ጠባቂን ጠየቀ!

አዲስ ዘመን ጋዜጣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ላለፉት ስምንት ወራት በደብዳቤ፣ በስልክና በአካል በመገኘት መረጃ ቢጠይቀም ለመስጠት ፍቃደኛ ባለመሆኑ የዕንባ ጠባቂ ተቋም መረጃውን በግድ እንዲያሰጠው ይግባኝ ጠየቀ።በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ስር የሚታተመውና በአገሪቱ አንጋፋ የሆነው የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ለዕንባ ጠባቂ ተቋም ዋና እንባ ጠባቂ ያስገባው ይግባኝ እንደሚያመለክተው፤ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባለፉት ስምንት ወራት በቃል፣ በደብዳቤና በአካል ጭምር በመሄድ ስለተቋሙ እንቅስቃሴ፣ በተቋሙ አለ ስለሚባለው የግልጽነትና የአሠራር ችግር፣ የብድር አሰጣጥና አመላለስ፣ የብድር ብልሽትና መንስዔ፣ በተቋሙ ስለተከሰቱ የብድር ብልሽቶችና ተጠያቂነት፣ የቀጣይ ማሻሻያና ሌሎች በርካታ ጉዳዮች ለባንኩ ፕሬዚዳንት ጨምሮ በየደረጃው ላሉ ኃላፊዎች ማብራሪያ እንዲሰጡትና ተቋሙ ላይ ያሉ አሠራሮችና የባንኩ አካሄድ ለባንኩ ባለቤት ለኢትዮጵያ ህዝብ ግልጽ እንዲያደርግ በተደጋጋሚ ቢጠየቅም የተለያዩ ሰበቦችን በመደርደር መረጃውን ለመስጠት ፍቃደኛ ባለመሆኑ ይግባኝ መጻፉን ያመለክታል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚንስትር ዶ/ር ስለሺ በቀለ ዋሽንግተን ዲሲ ገቡ!

በአሜሪካ ዲሲ ለነገ እ.ኤ.አ. ፌብሩዋሪ 12/2020 በተያዘው ቀጠሮ መሰረት የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚንስትር ዶ/ር ስለሺ በቀለ ዋሽንግተን ዲሲ ገብተዋል፡፡በዕለቱም ሳምንቱን ሙሉ ከግብጽ እና ሱዳን ልዑካን ጋር የተደረገውን የህግ ማዕቀፍ ድርድር ውጤት ከኢትዮጵያ ልዑካን ጋር ገምግመዋል፡፡ቡድኑ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ምክክር ያደረገ ቢሆንም ስምምነት ላይ ሊያደርስ የሚችል ሰነድ በጋራ ማዘጋጀት አለመቻሉ በግምገማው ታይቷል፡፡ኢትዮጵያ በፍትሃዊና ምክንያታዊ ተጠቃሚነት እንደምታምን ነገር ግን በአባይ ውሃ የመጠቀም መብቷን አሳልፎ የሚሰጥ ምንም ዓይነት ስምምነት እንደማትፈጽም በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት አረጋግጠዋል፡፡

ምንጭ: ኢቲቪ
@YeneTube @FikerAssefa
የኢፌድሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በቀድሞ የኬንያ ፕሬዚዳንት ዳንኤል ቶሮይቲች አራፕ ቀብር ላይ ለመታደም ናይሮቢ ገብተዋል።

ምንጭ: በናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ
@YeneTube @FikerAssefa
የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት የካቲት 14 በመስቀል አደባባይ ይካሄዳል!

ከደቂቃዎች በፊት የአርቲስቱ ማናጀር አቶ ጌታቸው ማንጉዳይ ከነገረኝ:

"ኮንሰርቱ ቅዳሜ የካቲት 14 ከ10 ሰአት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ ይካሄዳል። ከውጪ የሚገቡትን የድምፅ ሲስተሞች እና መሳርያዎችን ወጪ ለመሸፈን ብቻ በጣም ትንሽ ክፍያ ይኖራል። ኮንሰርቱ ምንም አይነት ስፖንሰር አይኖረውም። አሁን ከማዘጋጃ ጉዳዮችን ጨራርሰን እየወጣን ነው። በሌሎች ከተማዎች ስለታሰበው ኮንሰርት ወደፊት እነግርሀለው።"

-ጋዜጠኛ ኤልያስ መሠረት
@YeneTube @FikerAssefa