YeneTube
120K subscribers
31.2K photos
482 videos
79 files
3.83K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ሰዓት የኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክት ታይቶበት በለይቶ ማቆያ ማእከል የገባ ሰው አለመኖሩ ታወቀ

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ኖቬል ኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ 39 ጥቆማዎች ደርሰውት በሁሉም ጥቆማዎች ላይ ማጣራት ማድረጉን አስታወቀ።

ከተጠቋሚዎች 14ቱ የበሽታውን ምልክት ያሳዩ ስለነበረ፣ ተለይተው ወደ ማቆያ ስፍራ እንዲገቡ ተደርጎ በላብራቶሪ ምርመራ ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸውን ከተረጋገጠ በኋላ ወደ ሕብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል ብሏል።

በትላትናው ዕለት አንድ ሰው በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበረ ሲሆን፣ በኢንስቲትዩቱ የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ውጤቱ ከቫይረሱ ነፃ በመሆኑ ከለይቶ ማቆያ ማእከሉ መውጣቱን አመልክቷል።
በአሁኑ ሰዓት በለይቶ ማቆያ ማእከል ውስጥ የበሽታው ምልክት ታይቶበት የገባ ሰው አለመኖሩን ጠቅሷል።

ስለ በሽታው ግንዛቤ ለመፍጠር ለመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች፣ ለሆቴል ባለሞያዎች እንዲሁም ከክልል እና ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለተውጣጡ ፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድን አባላት ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል ብሏል።
ከቻይና የሚመጡ መንገደኞችን የሙቀት ልየታ እና የበሽታው ምልክት የታየባቸው መንገደኞችን የጤና ሁኔታ የመከታተል ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውንም ጠቅሷል።

በሁሉም የኢንዱስትሪ ፓርክ ባለባቸው ክልሎች ውስጥ የለይቶ ማቆያ ማእከል እና የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ማስተባበሪያ ማእከላትን ለምላሽ ዝግጁ ለማድረግ በተያዘው እቅድ መሠረት ደቡብ ክልል በሀዋሳ ከተማ ድጋፍ ሰጪ የባለሞያዎች ቡድን በመላክ ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር በመሆን የዝግጅት ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝም ገልጿል።

በአጠቃላይ የኖቭል ኮሮና ቫይረስ ዝግጁነት እና ምላሽ እንቅስቃሴ ከተጀመረበት ጊዜ አንሥቶ በሁሉም አቅጣጫ ባሉ የሀገሪቱ መውጫ እና መግቢያ ድንበሮች ላይ ከጥር 14 ቀን 2012 እስከ የካቲት 02 ቀን 2012 ድረስ የኮሮና እና የኢቦላ ቫይረስን ዝግጁነት በጋራ በማጣመር ከ172 ሺህ በላይ መንገደኞች ላይ የሙቀት ልየታ መካሔዱን አስታውቋል።

Via:- የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
@YeneTube @Fikerassefa
የብረታ ብረት እና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) የቢሾፍቱ ባስ መገጣጠሚያ ሠራተኞች የተገባልን የደሞዝ ጭማሪ ይፈፀምልን በሚል ምክንያት ከሦስት ሳምንት በፊት አራት አውቶቡሶችን አቃጠሉ።

ከ 10 ሺሕ በላይ ሠራተኞች ያሉት ድርጅቱ በተደጋጋሚ የደሞዝ ጭማሪ እንደሚያደርግ ለሠራተኞቹ ቃል ቢገባም መፈፀም አልቻለም።

በዚህ ምክንያት ተጀምሮ በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው ፋብሪካው የተነሳ በተቃውሞ ግርግር መካከል ነው፣ መኪኖቹ በእሳት የተያያዙት።
ተገጣጥመው ሊሸጡ የተዘጋጁትን አራት አውቶቡሶች በሚቃጠሉበት ወቅት እሳቱን ለማጥፋት ሠራተኛው መረባረቡን፤ ነገር ግን መኪኖቹ ሙሉ ለሙሉ ከጥቅም ውጪ መሆናቸውን የዐይን እማኞች ገልጸዋል።

የሜቴክ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ መሐመድ እድሪስ ለአዲስ ማለዳ የድርጊቱን መፈጸም አረጋግጠው እስከ አሁን ግን በጉዳዩ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር የዋለ ሰው የለም ብለዋል።

Via:- Addis Maleda
@Yenetube @FikerAssefa
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ ተጠርቷል!

ለየካቲት 5 አስቸኳይ ጉባኤ የጠራው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀረበ ረቂቅ አዋጅን እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል፡፡የሕግ፣ፍትሕና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለውሳኔ የሚያቀርበው ረቂቁ ለትርጉም የተጋለጠ እንዲሁም መንግሥት ተቺዎቹን ሁሉ ሊያሳድድበት የሚችልበት፣ የፀረ ሽብር ሕጉ ግልባጭ እንዳይሆን በሚል ስጋት ፈጥሮ እያከራከረ ይገኛል፡፡ሆኖም ረቂቁ ምን ዕጣ ፈንታ ይገጥመዋል፤ ከዘህ ቀደም የተሰጡ አስተያየቶችንስ በምን መል አካቷቸው ይሆን የሚለው ሐሙስ የሚታይ ይሆናል፡፡

እሁድ የአንድ ወር እረፍታቸውን ጀምረው በ4 ቀናት ልዩነት ለአስቸኳይ ስብሰባ የተጠሩት የሕዝብ ተወካዮች ጉባኤያቸው በ10 አጀንዳዎች ላይ ውሳኔዎችን ያሳልፋሉ፡፡በዚህም የኤክሳይዝ ታክስ፣ የፌደራል የአስተዳደር ሥነ ሥርዓት፣ በውጭ አገራት ለተሰጡ የግልግል ዳኝነት ውሳኔዎች እውቅና የመስጠት እና የመፈጸም ስምምነትን ለማጽደቅ የሚቀርቡ ረቀቅ አዋጆችን ያጸድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን ሕጋዊ ሰውነት ለመስጠት የቀረበ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴም ይመራል፡፡

ምንጭ: አሃዱ ቴሌቪዥን
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ የሚነሱ ግጭቶችን በየሦስት ወሩ መተንተን ሊጀመር ነው።

የኢትዮጵያ ስትራቴጂክ ተቋም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶችን በየሦሰት ወሩ የሚመዘግብ፣ የሚተነትን እና ይፋዊ ሪፖርት የሚያወጣ አዲስ ቡድን አደራጅቶ ወደ ሥራ ሊያስገባ መሆኑን ገለጸ።የመንግሥት ተቋማት፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የተለያዩ የግል ድርጅቶች እንዲሁም የሚዲያ ተወካዮች በዚህ ሥራ የሚሳተፉ ሲሆን፣ በተለያዩ ዘዴዎች የሚሰበሰቡ መረጃዎችን በማረጋገጥ እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም ግጭቶቹ የተከሰቱበት ቦታ ድረስ በመሄድ የሚያረጋግጡበት አንደሆነ ታውቋል። የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ሃሌሉያ ሉሌ ለአዲስ ማለዳ እንደገለፁት፣ የግጭት ትንተናው ዋና ዓላማ መረጃ በቀላሉ እንዲገኝ ለማድረግ እና ስለ ግጭቶች በሚሰጡ የተሳሳቱ መረጃዎች ለከፋ ግጭት እየዳረጉ በመሆኑ ነው። ለዚህም ወቅታዊ እና ትክክለኛውን ሪፖርት ይፋ በማድረግ ግጭቶችን ለፖለቲካ ፍጆታ የማዋል ተግባሮችን ለመከላከል መታሰቡን ገልፀዋል።

ምንጭ: አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
"የዴሞክራሲ ሽግግር በኢትዮጵያ: ተስፋዎቹ እና ተግዳሮቶቹ" በሚል ርእስ በመጪው ሀሙስ በፖለቲካ ሰዎች መሀል ሊደረግ ታስቦ የነበረው ውይይት ተራዝሟል!

አዘጋጁ Institute for Strategic Affairs "ፕሮግራሙ የተራዘመው አንዳንዶቹ ንግግር ያረጋሉ ተብለው የነበሩት ሰዎች ሌላ ስራ ስላጋጠማቸው ነው" ያለ ሲሆን ይህ ፕሮግራም ለግዜው ላልተወሰነ ግዜ ተራዝሟል ብሏል።

Via Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
የመከላከያ ሠራዊት ቀን የፊታችን ቅዳሜ ይከበራል!

የዘንድሮው የመከላከያ ሠራዊት ቀን “የሀገራችንን ሉዓላዊነትና የሕዝባችንን ሠላም በፅናት እንጠብቃለን” በሚል መሪ ሃሳብ የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 7 ቀን 2012 ዓ.ም እንደሚከበር ታውቋል። ሚኒስቴሩ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው በዓሉ ከሕብረተሰቡ ጋር በሚደረጉ ውይይቶች፣ በበጎ አድራጎት ስራዎች፣ በስፖርታዊ ውድድሮች፣ የሠራዊቱን ዝግጁነት በሚያሳዩ ወታደራዊ ሰልፎችና ትርዒቶች ታስቦ ይውላል።ቀኑ እስካሁን ሠራዊቱ የሔደባቸው ጉዞዎች የሚቃኙበት፣ ሕዝባዊ ወገንተኝነቱን በማረጋገጥም እንዳለፉት ጊዜያት ሁሉ ተልዕኮውን በጽናት ለመወጣት ያለውን ዝግጁነት የሚያሳይበት ነው ብሏል መግለጫው። ሠራዊቱ የሕዝቡን ሠላም በጽናት ለመጠበቅ በቁርጠኝነት እንደሚሰራም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
በዋግ ኽምራ ዞን 108 ሺሕ ሰዎች ለምግብ እጥረት ተጋለጡ!

በአማራ ክልል በዋግ ኽምራ ዞን በ2010 የክረምት ወቅት የዝናብ እጥረት በማጋጠሙ በተለይም በዝቋላ፣ በሳሃላ እና በሰቆጣ ወረዳዎች ባጋጠመው ድርቅ ለቀጣይ አምስት ወራት 108 ሺሕ ዜጎች አስቸኳይ የእለት የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ተባለ።ችግሩ በከፋባቸው ቀበሌዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ቤታቸውን ጥለው ውሃ ወዳለባቸው ቀበሌዎች በመሄድ ላይ መሆናቸውን አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። በዞኑ የሚገኙ ከአንድ ነጥብ ሦስት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ እንስሳትም የመኖ እጥረት እንዳጋጠማቸው ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። የሰቆጣ ከተማ ነዋሪ የሆኑት መንግሥቱ ደሳለኝ፣ ከገጠር አካባቢ ወደ ከተማ ገብተዉ የሚማሩ ተማሪዎች ትምህርታቸዉን አቋርጠዉ ወደ ቤተሰቦቻቸዉ እየተመለሱ እንደሆነ መመልከታቸዉን ጠቅሰዋል። አክለውም በአካባቢው ያሉ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የእለት ምግብ ቢሰጡም፣ በቂ ባለመሆኑ ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን እንዲያቋርጡ ምክንያት መሆኑን አክለው ገልጸዋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
አል-በሽር ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተላልፈው ሊሰጡ ነው!

ሱዳን የቀድሞ ፕሬዝደንቷን ኦማር አል-በሽርን ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አሳልፋ ልትሰጥ እንደሆነ ተነገረ።ሱዳን አል-በሽርን አሳልፋ የምትሰጠው በቀረበባቸው የጦር ወንጀል ክሶች ነው።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
LTV የዜና ክፍል ሃላፊ እና ፕሮግራም አዘጋጅ ሆኖ ሲሰራ የቆየ ጋዜጠኛ ተመስገን መንግስቴ በዋልታ ቴሌቭዥን በወቅታዊ ጉዳዮች ክፍል ውስጥ በመሪ አዘጋጅነት መቀጠሩን አረጋግጫለው። #ተስፋዬ_ጌትነት

በማህበራዊ ሚዲያ የተዛባ መረጃ እየተሰራጨ ቢሆንም እውነታው ጋዜጠኛ ተመስገን በደሞዝ ጭማሪ ምክንያት ወደ ዋልታ መግባቱን ታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሶማሌ ላንድ ፕሬዝዳንት እና የሶማልያ ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት አንድ ለአንድ ውይይት ማድረጋቸውን የVOA ምንጮች መግለፃቸውን የVOA ሶማልኛ #ሀረን_ማሩፍ በትዊተር ገፁ አስፍሯል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአንበጣ መንጋ ካሳለፍነው ኅዳር ጀምሮ በምሥራቅና ሰሜን ምሥራቅ ቆላማ አካባቢዎች ተከስቶ በሰብል ላይ ጉዳት ሲያደርስ ቆይቷል።በኅብረተሰቡና በመንግሥት ድጋፍ ጭምር በወቅቱ ፤ መንጋው መወገድ የቻለ ቢሆንም እንደገና ሰሞኑን በአንዳንድ ደጋማ አካባቢዎች መታየቱን የየአካባቢው አርሶ አደሮችና የግብርና ባለሙያዎች አመልክተዋል፡፡

Via:- DW
@YeneTube @Fikerassefa
ትናንት ማምሻውን የተጠናቀቀው 33ኛዉ የአፍሪቃ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ሰሞኑን አዲስ አበባ ላይ በተለያዩ አህጉራዊና ዓለም ዓቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መክሮ ውሳኔ አሳልፏል። ከነዚህም ውስጥ የአህጉሪቱን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅና ከጦር መሳሪያ ድምጽ ነፃ የሆነች አፍሪካን ለመፍጠር የውጭ ኃይሎችን ጣልቃ ገብነት ማስወገድ ተገቢ መሆኑን አመልክቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአንበጣ መንጋ ለመቆጣጠር የሚያስችል ዘመናዊ የድሮን መሳሪያ ሙከራ ላይ ሊውል ነው።
@YeneTube @Fikerassefa
በአማራ ክልል ከብት በመጠበቅ ላይ ያሉ ህጻናትን አግቶ ገንዘብ ለመቀበል የሞከረው ተጠርጣሪ የ25 ዓመት እስራት ተፈረደበት።

ተከሳሽ አገሬ የሗላሸት የተባለ ግለሰብ በአማራ ክልል ጠገዴ ወረዳ የኢፌደሪ የወንጀል ህግ በ1996 ዓ/ም ተደንግጎ የወጣውን አንቀፅ 590 ንዑስ ቁጥር 1/ሀ/ እና 2/ሐ/ በመተላለፍ በሚል ነበር ክስ የተመሰረተበት።

ተከሳሹ
1ኛ. ሁናቸው ማስረሻን ጳጉሜ 4/2011 ዓ/ም አዴት ቀበሌ ከብት በመጠበቅ ላይ እያለ 30 ሽ ብር አምጣ በማለት አግቶ 20 ሽ ብር በመቀበሉ።

2ኛ.የ7 ዓመት ህፃን መልካሙ ጣምያለውን ታህሳስ 7/2012 ዓ/ም አዴት ቀበሌ 75 ሽ ብር አምጡ በማለት ከብት በሚጠብቅበት የጦር መሳሪያ በመያዝ ጭካኔ በተሞላበት 15 ሽ ብር በመቀበል።ከሳምንት በላይ ለርሃብና ለጥም እንዲሁም ለእንግልት በመዳረጉ ዓቃቤ-ህግ ክስ መስርቶበታል።

ተከሳሽም ወንጀሉን ፈፀምክ በተባልኩበት ቀን አዲስ አበባ ነው የነበርኩ በሁለተኛውም መተማ ነው የነበርኩ አልፈፀምኩም በማለት ክዶ ተከራክሯል።

ዓቃቤ-ህግም ተከሳሽ ክዶ ቢቀርብም እንደ ክሱ አመሰራረት ሊያስረዱ የሚችሉ ማስረጃዎችን በማቅረብ ለፍርድ ቤቱ አስደምጧል።

ተከሳሽ እንዲከላከል ቢፈቀድለትም የመከላከያ ማስረጃ የለኝም በዓቃቤ ህግ ማስረጃ ውሳኔ ይሰጠኝ ሲል ለፍርድ ቤቱ አሳስቧል።ፍ/ቤቱም የሁለቱን ወገን መርምሮ ተከሳሽን ጥፋተኛ ብሏል ።የቅጣት ውሳኔ ለማስተላለፉ በፊት የቅጣት ማቅለያና ማክበጃ ጠይቋል። ዓቃቤ-ህግ 3 ማክበጃዎችና 1 ማቅለያ ለፍ/ቤቱ አስይዟል።ተከሳሽ የሁለት ልጆቾ አባት ነኝ ደካማ እናት አለች ይቅለልልኝ ሲል ጠይቋል።ዓቃቤ-ህግ ተቃውሟል ተከሳሽ አዲስ አበባና መተማ ነው የምኖር እያለ በቃል ለፍ/ቤቱ ያሰማ በመሆኑ፣ ቤተሰብ የማይረዳ በመሆኑ ታውቆ ውድቅ ይሁንልን ሲል አሳስቧል።

ፍ/ቤቱም የዓቃቤ ህግን ማክበጃ በመቀበል የተከሳሽን ማቅለያ ውድቅ በማድረግ ተከሳሽ ወንጀሉን የፈፀመው በስግብግብነት ፣በጦር መሳሪያ ፣ በአፍቅሮ ንዋይ የሰው ልጅን ከገንዘብ በማሳነስ እንዲሁም በተደጋጋሚ የተፈፀመና ህፃናትን ለርሃብ ፣ ለጥምና ለእንግልት የዳረገ መሆኑን በማረጋገጥ እሱንም ሆነ ሌሎችን ያስተምራል በማለት በ25 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ እንደተፈረደበት የወረዳው የመንግስት ኮሙንኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ከማዕድን ሀብት ገቢ 50 በመቶው ለራሱ ክልል እንዲውል መወሰኑ ተገለፀ!

ከማዕድንና ነዳጅ ተፈጥሮ ሀብቶች ከሚገኝው ገቢ ውስጥ 50 በመቶው ሀብቱ ለመነጨበት ክልል እንዲውል መወሰኑን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር አስታወቀ።ሚኒስቴሩ የመጀመሪያውን መንፈቅ ዓመት የሥራ አፈፃፀም አስመልክቶ ሰሞኑን በሰጠው መግለጫ ላይ በሚኒስቴሩ የሕግ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ ባምላክ አለማየሁ በፌዴራልና በክልል መንግሥታት መካከል ያለውን የማዕድን ሕግ ጉዳዮችን አስመልከተው እንደገለፁት፤ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በቅርቡ በወሰነው መሰረት ከሐምሌ አንድ ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ከማዕድንና ነዳጅ ተፈጥሮ ሀብቶች ከሚገኝው ገቢ ውስጥ 50 በመቶው ሀብቱ ለመነጨበት ክልል ልማት እንዲውል ተወስኗል።

ክልሎች ከማዕድንና ነዳጅ ተፈጥሮ ሀብታቸው ማግኝት የሚገባቸውን ጥቅም ምክርቤቱ በቅርቡ የወሰነውን ውሳኔ ዳይሬክተሩ እንዳብራሩት፤ ከማዕድንና ነዳጅ ተፈጥሮ ሀብቶች ከሚገኝው ገቢ ውስጥ 50 በመቶው ማዕድኑ ወይም ነዳጁ ለተገኝበት ክልል፤ ከ50 በመቶው ውስጥ 10 በመቶው ማዕድኑ ወይም ነዳጁ ለተገኝበት ስፍራ ወይም ኩባንያው ፍቃድ ለወሰደበት ወረዳ ይውላል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
ምርጫ ቦርድ አቶ ጃዋር መሃመድ ኢትዮጵያዊ ዜግነት መልሶ ማግኘቱን የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንዲሰጠው ኢሚግሬሽን፣ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲን ጠየቀ፡፡

የኢትዮጵያ የምርጫ፣የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ-ምግባር አዋጅ የሀገር አቀፍም ሆነ የክልል ፓርቲ አባል መሆን የሚችለዉ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለዉ ሰዉ ብቻ መሆኑን ያስቀምጣል፡፡ከዚህ አንጻር የአቶ ጃዋር መሃመድ የኢትዮጵያዊነት ዜግነትን ማግኘት ጉዳይ ማስረጃ ይሰጠኝ ሲል ለኢሚግሬሽን፣ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ጥያቄ አቅርቧል፡፡ቦርዱ፣ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረንስ (ኦፌኮ) አቶ ጃዋር መሃመድ የኢትዮጵያ ዜግነታቸዉን መልሰዉ በማግኘት ሂደት ላይ ነኝ እያሉ ፓርቲዉ ግን ኢትዮጵያዊ የሚል የአባልነት መታወቂያ ሰጥቷቸዋል ብሏል፡፡

አሁን በስራ ላይ ባለዉ የዜግነት አዋጅ መሰረት ግለሰቡ የኢትዮጵያ ዜግነት መልሰዉ አግኝተዉ ከሆነ ይህን የሚያስረዳ ሰነድ ከደህንነት፣ኢሚግሬሽንና ስደተኞች ጉዳይ ባለስልጣን አቅርብ የተባለዉ ፓርቲዉ፣ይዘዉት የነበረዉን ሌላ ሀገር ዜግነት ስለተዉና ስልጣን ላለዉ አካል ስላመለከቱ ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸዉን አግኝተዋል፤ኢትዮጵያዊም ሆነዋል ሲልም ፓርቲዉ ቀደም ሲል ምላሽ ሰጥቷል፡፡ከዚህ በተጨማሪም በሰነድ እንዳስረዳ ምርጫ ቦርድ መጠየቁ ተገቢ አይደለም ሲልም አክሏል ፓርቲው፡፡በመሆኑም በዚህ ጉዳይ ላይ የኢሚግሬሽን፣ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ማብራሪያ እንዲሰጠዉ ምርጫ ቦርድ ጠይቋል፡፡

ማብራሪያዉም አንድ የሌላ ሀገር ዜግነት ያለዉ ትዉልደ ኢትዮጵያዊ፣የሌላ ሀገር ዜግነቱን ትቶ ኢትዮጵያ መኖር ከጀመረና ኢትዮጵያዊ ዜግነቱ እንዲመለስለት ካመለከተ ያለ ኤጀንሲዉ ዉሳኔ ወዲያዉ ሊያገኝ ይችላል ወይ የሚለዉን የሚያጠራ እንዲሆን ጠይቋል፡፡ኤጀንሲዉም እስከ የካቲት 09 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ለዚህ ጉዳይ ማብራሪያ ይስጠኝ ሲል ነዉ ምርጫ ቦርድ ጥያቄዉን በደብዳቤ ያቀረበዉ፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የስፖርት ውድድር ቤቲንግ በሚል ስም በአገሪቱ የሚስተዋለው ቁማር እንዲቆም ከስምምነት መድረሱን የሴቶች ህፃናት ወጣቶች ሚኒስቴር ሲገልፅ፤ የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር አሁንም በተለየ አቋሙ ፀንቷል።

የሚኒስትሩ የወጣቶች ስብዕና ልማት ዳይሬክተር አቶ አለሙ ሰኢድ የስፖርት ውድድር ቁማር እንዲቆም መወሰኑን ገልፀዋል።26 አባላት ያቀፈ የፌደራል የአሉታዊ መጤ ልማዶችና አደንዛዥ ዕፆች ግብረ ኃይልና ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት ተሳተፊ የሆኑበት መድረክ በማዘጋጀት የስፖርት ውድድር ቁማር በዜጎች ስነልቦና፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊና አጠቃላይ የሚያደርሰውን ችግር መፈተሹንም ጠቁመዋል።በጥር ወር ውስጥ ለስፖርት ውድድር በሚል ይሰጥ የነበረው ፍቃድ የቆመ ሲሆን፤ ስራ ላይ የሚገኙ አቋማሪ ድርጅቶች የውላቸው ጊዜ እስኪጠናቀቅ ብቻ ሊቆዩ እንደሚችሉ ዳይራክተሩ ተናግረዋል።

ምንጭ: አዲስ ዘመን/አሃዱ
@YeneTube @FikerAssefa
የዲያስፖራ ትረስት ፈንድ ለአምስት ፕሮጀክቶች የመጀመሪያውን ድጋፍ አደረገ!

ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አህመድ በቀን አንድ ዶላር ከዲያስፖራው ህብረተሰብ በጠየቁት መሰት የተሰበሰበ ገንዘብን የልማት ስራዎች ለማዋል በቀረበ ጥሪ መሰረት ተወዳድረው ላሸነፉ አምስት ፕሮጀክቶች የመጀመሪያውን ገንዘብ ለቀቀ።ከዚህ ቀደም ትረስት ፈንዱን ከሚስተዳድረው ቦርድ በወጣ ማስታወቂያ መሠረት 466 ፕሮጀክቶች ንደፈ ሀሳብ ያቀረቡ ሲሆን ሌሎች ቀሪ ፕሮጀክቶችም ወደፊት በሚደረግ ማጣራት ወደ ስራ እንደሚባቡ ገልጿል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
በአንዳንድ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የኃይል አቅርቦት ለተወሰነ ሰዓት ይቋረጣል ተባለ!

ከነገ ጀምሮ በአንዳንድ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የኃይል አቅርቦት ለተወሰነ ሰዓት እንደሚቋረጥ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

በዚሁ መሠረት ሐሙስ የካቲት 05 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 5:00 ሰዓት ድረስ

➡️ በኮልፌ፣ በፈጥኖ ደራሽ፣ በኮፕረኸንሲቭ ት/ቤት፣ በደጉ ሆቴል፣ በታይዋን ገበያ፣ በኢትዮ- ጠቢብ ሆስፒታል፣ በካርል አደባባይ፣ በሜክሲኮ፣ በትንባሆ ሞኖፖል እና አካባቢዎቻቸው፤

ዓርብ የካቲት 06 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 9:00 ሰዓት ድረስ፣

➡️ በፈረንሳይ ኤምባሲ፣ በጉራራ፣ በፊልም ማእከል፣ በራስ ካሣ ክሊኒክ፣ በአቦ ቤተክርስቲያን፣ በእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን፣ በለቡ ጆሞ አንድ በከፊል፣ በቻይና ቱቦ፣ በቆሼ ፊት ለፊት፣ በረጲ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን፣ በፋና ራዲዮ እና አካባቢዎቻቸው፤

በተጨማም በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ

➡️ በጎላጎል፣ በቦሌ ሚሌኒየም እና አካባቢው በከፍተኛ የኤሌክትሪክ መስመር ላይ ማሻሻያ ሥራን ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥ በመሆኑ ደንበኞች አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የኮሮና ቫይረስ ስያሜ #COVID -2019 የተባለበት አግባብ ።⬆️⬆️

ምንጭ: የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
@YeneTube @FikerAssefa