YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
እስክንድር ነጋ የባልደራስ እውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዝደንት ሆኖ ተመረጠ!

ጠቅላላ ጉባኤው ዛሬ በሶስት ተወዳዳሪ የፓርቲውን ፕሬዝደንት ሚስጥራዊ ምርጫ በማከናወን 60 አባላት ያሉት የብሔራዊ ም/ቤት በምርጫ የተጠናቀቀ ሲሆን የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፕሬዝደንት እስክንድር ነጋ ሆኗል።

Via:- Sintayehu Chekol // ኤልያስ መሰረት
@YeneTube @FikerAssefa
⚠️WARNING ⚠️ *GRAPHIC*

26 ሰዎችን የገደለው አንድ የታይላንድ ወታደር በፖሊስ ተገደለ ፡፡ ቢያንስ 42 የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ጥቃት አድራሹ ግድያውን የጀመረው በሀገሪቱ የሰዓት አቆጣጠር ትናንት ከሰዓት በኋላ ነበር። የ32 ዓመቱ ግለሰብ በመጀመሪያ ኮራት በመባል የሚታወቅ ቦታ የሚገኝ ወታደራዊ ሰፈር ውስጥ አለቃውን እና ሌሎች ሁለት ሰዎች ገድሎ ሸሽቷል።

ከዛም ጠመንጃ እና ጥይቶች ሰርቆ በወታደራዊ መኪና ያመለጠው ይሄው ግለሰብ በዘፈቀደ ሰዎች ላይ እየተኮሰ መግደሉን እና ይህንን ድርጊቱንም በቪዲዮ እየቀረፀ ኢንተርኔት ላይ ይለቅ እንደነበር ተገልጿል።

በመጨረሻም ወደ ገበያ አዳራሽ በመግባት ሰዎች ላይ ሊተኩስ እና በአስራዎቹ የሚቆጠሩ ሰዎችንም ማገቱን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ግለሰቡም ከ 17 ሰዓታት በኋላ በልዩ ኃይል ፖሊስ ሊገደል ችሏል። የድርጊቱ ምክንያት በውል አልታወቀም።

Via:- DW #Photo social media
@YeneTube @Fikerassefa
በኹለት ወር የጤፍ ዋጋ አምስት መቶ ብር ጨመረ

ከኅዳር ወር መጀመሪያ አንስቶ ጭማሪ ማሳየት የጀመረው የጤፍ ዋጋ፣ እስከተገባደደው ሳምንት መጨረሻ ድረስ እስከ 500 ብር የዋጋ ጭማሪ አሳየ። ማኛ ነጭ ጤፍ እስከ 4 ሺሕ 500 ብር ድረስ በመሸጥ ከፍተኛው የዋጋ ንረት የታየበት ሲሆን፣ ቀይ ጤፍ በኩንታል የ300 ብር ጭማሪ እና ሰርገኛ ጤፍም በተመሳሳይ የ300 መቶ ብር ጭማሪ በማሳየት ወደ 3 ሺሕ 400 ብር ከፍ ማለቱን አዲስ ማለዳ በገበያ ላይ ያደረገችው ቅኝት ያሳያል።

ካዛንቺስ አካባቢ የሚገኘው ድል በጌ ገበያ ውስጥ ነጭ ጤፍ በ 4 ሺሕ 500 ብር ሲገዙ አዲስ ማለዳ አግኝታ ያነጋገረቻቸው ሳምሶን ታዬ እንደሚሉት፣ ከኹለት ወራት በፊት በ4 ሺሕ ብር ተመሳሳይ ነጭ ጤፍ መግዛታቸውን ይናገራሉ።

ከአራት ወር በፊት በ3 ሺሕ 300 ብር ሲሸጥ የነበረው ኹለተኛ ደረጃ ነጭ ጤፍ፣ የ 700 ብር ጭማሪ በማሳየት 4 ሺሕ ብር የገባ ሲሆን፣ እምቡር የተሰኘው የነጭ ጤፍ አካባቢ የሚመጣው ጤፍ ሙሉ በሙሉ ከገበያ መጥፋቱን አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው ነጋዴዎች ተናግረዋል።

የጤፍ ምርት የሚሰበሰብበት የመኸር ወቅት ላይ ዘንቦ የነበረው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ እየጨመረ ለመጣው የጤፍ ዋጋ በምክንያትነት የተጠቀሰ ሲሆን፣ በተጨማሪም የሕገወጥ ደላሎች መበራከት የንግድ ሰንሰለቱን እንዳረዘመው እና ይህም ለዋጋ መጨመሩ ምክንያት መሆኑን ነጋዴዎች ገለፀዋል።

የድል በጌ ጤፍ መሸጫና ማስፈጫ ባለቤት የሆኑት ሀያት በረከት እንደሚሉት፣ ከዚሀ በፊት ከገበሬዉ በቀጥታ በመረከብ ለገበያ ያቀርቡ ነበር። አሁን ግን ደላሎች ይህንን ሂደት በመከልከል ተፅእኖ እስከማሳደር መድረሳቸውን ተናግረዋል። ከጊዜ ወደ ጊዜ የደላሎች ቁጥር መብዛት እና በተያዘው ሳምንትም የጤፍ ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉን ደላሎች እንደነገሯቸዉና፣ ከዚህ በላይ አልጨምርም ብለዉ እንዳልገዙ ነግረዉናል። የደላሎች ትስስርም በኹለት ቦታ መሆኑን ሀያት ጨምረዉ ተናግረዋል።

የሰብር ወፍጮ ቤት ሠራተኛ የሆኑት ከሚል አሕመድ እንደሚሉት ደግሞ፣ አንደኛ ደረጃ ጤፍ ዋጋው በመወደዱ ምክንያት ደንበኞቻቸው መግዛት በማቆማቸው እርሳቸውም ጤፍ ማቅረብ ማቆማቸውን ገልፀዋል። ከኹለተኛ እስከ አራተኛ ደረጃ ያለ ነጭ ጤፎ እያንዳንዱ እስከ ሦስት መቶ ብር በኩንታል መጨመሩንም ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

የጤፍ ዋጋ ላይ በስድስት ወር ውስጥ የአንድ ሺሕ ብር ጭማሪ መታየቱን አዲስ ማለዳ በተለያዩ የጤፍ መሸጫ ቦታዎች ተዘዋውራ ያነጋገረቻው ነጋዴዎች አረጋግጠዋል።
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የንግድ ክትትልና ቁጥጥር ኃላፊ ሀብታሙ ጥላዬ፣ የዋጋ ንረቱ እዚህ መድረሱን እንደማያውቁ ተናግረዋል። ከዚህ በፊት የነበረዉ የጤፍ ዋጋ ከ3 ሺሕ 200 እስከ 3 ሺሕ 500 መሆኑንና እየታየ የመጣውን የዋጋ ንረት ለማስተካከልም በጥናት ላይ ተመስርቶ እርምጃ እንደሚወሰድም አስታውቀዋል።
ከዚህ በፊት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሕገ ወጥ ነጋዴዎችንና ደላሎችን ለመቆጣጠር ንብረታቸዉን የመዉረስና በሕግ የማስቀጣት ሥራ እየሠራ መቆየቱና አሁን ያለዉ የሕገ ወጥ ደላሎች ዝዉዉር አዲስ መልክ ይዞ መምጣቱን ሀብታሙ ጠቅሰዋል።

ሀብታሙ እንደሚሉት፣ ወቅቱ የመኸር ወቅት ከመሆኑ አንፃር የገበያ ሁኔታዉ መቀነስ ሲኖርበት፣ ነገር ግን ሊቀንስ ባለመቻሉ ምክንያቱን ለማወቅ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ጥናት እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል። ችግሩን የአድስ አበባ ንግድ ቢሮ ብቻ ሊያስቆመዉ ስለማይችል፣ ሌሎች የሚመለከታቸዉ አካላት ተሳትፎ እንደሚያስፈልግም ለአዲሰ ማለዳ ተናግረዋል።

ምንጭ:- አዲስ ማለዳ
@YeneTube @Fikerassefa
የፍልስጤም ፕሬዚደንት ማህሙድ አባስ የአፍሪካ መንግስታት ለፍልስጤም ትግል ለሚያደርጉት ድጋፍ ምሥጋናቸውን ልከዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት የተጫወቱትን ሚናም አድንቀዋል

ፍልስጤምን ወክለው የቀረቡት
የፍልስጤም ጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ሻተይ በተጨማሪም "ፍልስጤማውያን የሚፈልጉት ርዳታና ዳቦ ሳይሆን ነፃነትና ፍትህ ነው" ሲሉ በ33 ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሩዎች ጉባኤ ላይ ተናገሩ። ለፍልስጤምና ለእስራኤል መስማማት ፕሬዚደንት ትረምፕ ያቀረቡት የሰላም ዕቅድም ተቀባይነት የለውም ብለዋል።

ምንጭ:- አሐዱ ሬዲዮ
@YeneTube @FikerAssefa
ጋምቤላ ክልል በተፈጠረው ከፍተኛ ሙቀት ሳቢያ የስራ ሰዓት ለውጥ ማድረጉን አስታወቀ።

የክልሉ መስተዳድር ጽህፈት ቤት በሙቀት ምክንያት ከየካቲት 1 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ አስከ ሚያዝያ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ለሶሰት ወራት ያክል የስራ ሰዓት ለውጥ ማድረጉን አስታውቋል።በዚህም መሰረት ጧት የስራ ዐት መግቢያ 1 ሰዓት ሲሆን መውጫ 5 :30 እንዲሁም ከሰዓት የስራ ሰዓት መግቢያ 10 ሰዓት ሲሆን መውጫ ደግሞ 12 :30 እንደሆነ ተገልጿል።በአካባቢው ከፍተኛ የሙቀጥ መጠን መፈጠሩ የስራ ሰዓት ለውጥ እንዲደረግ ምክንያት መሆኑን ክልሉ አስታውቋል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
በግብርና ሚኒስቴር ስር ለሚከናወነው ሴፍቲ ኔት ፕሮግራም ማስፈፀሚያ የሚውል 75 ሺሕ ቶን ስንዴ ግዢ ለማከናወን ‹ፕሮሚሲንግ› ከተሰኘ ድርጅት ጋር ከስምምነት ላይ መድረሱን የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት አስታወቀ።

ግዢው የዓለም ባንክ ለግብርና ሚኒስቴር የሴፍትኔት ፕሮግራም ባደረገው 24 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ የሚፈፀም ነው። አቅራቢዎቹን የመለየት ሥራ በመንግሥት ግዢ እና ንብረት ማስወገድ በኩል እንደተከናወነም ለማወቅ ተችሏል።

ምንጭ:- አዲስ ማለዳ
@YeneTube @Fikerassefa
በኮሮና ቫይረስ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ900 በልጧል፡፡

የቻይና ብሔራዊ ጠና ኮሚሽን እንዳረጋገጠው የሟቹ ቁጥር አሁን 908 ድርሷል ፡፡በፊሊፒንስና በሆንግ ሆንግ ከተከሰተው ሞት ጋር ሲደምር ደግሞ የሟቾቹ ቁጥር አሁን 910 መድረሱ ተነግሯል፡፡ሲኤን ኤ እንደዘገበው በአለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙት ሰዎች ቁጥር ወደ 40 ሺህ ያደገ ሲሆን አብዛኛው በቫይረሱ የተጠቁት ሰዎች ቻይናዊን ናቸው፡፡ቻይና ውስጥ በኮሮና የተጠቁ ሰዎች ቁጥር አሁን ከ 37 ሺህ 200 በላይ ደርሷል፡፡እ.ኤ.አ. በ 2002 እና በ 2003 ሳርስ የተባለው ወረርሽኝ የተከሰተ ሲሆን በዓለም ዙሪያ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 774 ነበር።

ይህም እስካሁን ከነበሩ ተመሳሳይ ወረርሽኞች ብዙ ሰዎች የሞቱበት ወረርሽኝ ያደርገዋል ተብሏል።በሌላ ዜና የአለም የጤና ድርጅት ከፍተኛ ባለሙያዎችን ወደ ቻይና ልኳል፡የድርጅቱ ዳሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም በትዊተር ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት በቻይና ለተከሰተው ወረርሽን እገዛ የሚያደርግ የባለሙያ ቡድን መላኩን ተናግረዋል፡፡የቫይረሱ መነሻ ነች በምትባለው ውሃን ግዛት በቀን 97 ሰዎች ህይወታቸውን በአንድ ቀን አጥተዋል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
 “ፓራሳይት” የተሰኘው የደቡብ ኮሪያ ፊልም በዘንድሮው የኦስካር ሽልማት በምርጥ ፊልም ዘርፍ  አሸንፏል።

ፊልሙ በደቡብ ኮሪያ ዋና ከተማ ሴኡል በሚኖሩ እና በተለያየ የኢኮኖሚ ደረጃ በሚኖሩ ሁለት ቤተሰቦች የህይወት ውጣ ውረድ ዙሪያ የሚያጠነጥን መሆኑ ተነግሯል።

በኦስካር ሽልማት ታሪክ በእግሊዘኛ ቋንቋ ያልተሰራ ፊልም  በምርጥ ፊልም  ዘርፍ ሲያሸንፍ ይህ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።

ይህን ተከትሎ ታሪካዊ ፊልም ለመባል የበቃው “ፓራሳይት”  በአጠቃላይ በአራት ዘርፎች የኦስካር ሽልማቶችን መቀዳጀት ችሏል።

የፓራሳይት ፊልም ዳይሬክተር ቦንግ ጁን ሆ  ቢት የኦስካር የዓመቱ ምርጥ ዳይሬክተር በመሆኑ  ተሸልሟል።

በሌላ በኩል ሬኔ ዜልዌገር “ጁዲ” በተሰኘው ፊልም የጁዲ ጋርላንድን ገጽ ባህርይ በመወከል በምርጥ  የሴት ተዋንያን ዘርፍ አሸናፊ ሆናለች።

ጆዋኩን ፊኒክስ  ደግሞ  “ጆከር” በተሰኘው ፊልም በወንዶች ምርጥ ተዋናይ ዘርፍ የኦስካር  ሽልማት አሸናፊ መሆን ችሏል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ/FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የፈተናና ምዘናዎች ኤጀንሲ የዘንድሮውን የትምህርት ዘመን ጊዜያዊ የሀገር አቀፍ የፈተና መስጫ ሰሌዳ ይፋ አድርጓል ።

@YeneTube @FikerAssefa
የገቢዎች ሚኒስቴር ከዚህ ወር ጀምሮ የስራ ሰዓት መግቢያና መውጫ ለውጥ አደረገ!

የገቢዎች ሚኒስቴር ከየካቲት 01/2012 ዓ.ም ጀምሮ የስራ ሰዓት መግበያና መውጫ ያሻሻለ ሲሆን ከሰኞ እስከ አርብ፡

1. ከጠዋቱ 2፡00 - 6፡00 መደበኛ የሥራ ሰዓት፣
2. ከ6፡00 – 7፡00 የምሳ እረፍት፣
3. ዘወትር አርብ ግን የሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡00 – 5፡00 ሲሆን ከ5፡00 -7፡00 የምሳ ሰዓት ሆኖ ከሰዓት በኃላ ደግሞ ከ7፡00 – 11፡00 መደበኛ የሥራ ሰዓት ይሆናል፡፡
4. እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00- 6፡00 ሰዓት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መደበኛ የሥራ ሰዓት መግቢያና መውጫ መሆኑን አውቃችሁ ሁሉም የግብር ከፋይ ደንቤኞቻችንና አገልግሎት ፈላጎዎች በተገለፀው ሰዓት ውስጥ እንዲትጠቀሙ በአክብሮት እንገልጻለን፡፡

ምንጭ:የገቢዎች ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
በኮንታ ልዩ ወረዳ የተከሰተውን የበረሃ አንበጣ መንጋ ለመከላከል በሄሊኮፕተር የማጥፊያ መድሃኒት ርጭት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በአጎራባች መሎ ኮዛ ወረዳ አድርጎ ወደ ልዩ ወረዳው በሁለት መንጋ የገባው ከቆላው ቀበሌያት ወደ ደጋውም እየሰራጨ እንደሚገኝ የልዩ ወረዳው እ/ተ/ሀ/ል/ጽ/ቤት አስታውቋል።አንደኛው መንጋ በጨበራ ጩርጩራ ብሄራዊ ፓርክ ላይ ያረፈ ሲሆን ይህንን ለመከላከል በሄሊኮፕተር/በአውሮፕላን / የማጥፊያ መድሃኒት ርጭት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በተጨማሪም በልዩ ወረዳው በተለያዩ ቀበሌያት የበረሃ አንበጣው ተከስቶ ህብረተሰቡ በተለያዩ ዘዴዎች የመከላከል ስራ በመስራት ላይ ይገኛል። ይህ አንበጣ መንጋ በየትኛውም ዕፅዋትና ሰብል ላይ 100% ውድመት የሚያደርስ ነው።

ስለዚህ ይህ አንበጣ መንጋ በአካባቢው እንዳያርፍ እንዳይቆይ ለማድረግ:-
ጭስ በማጨስና በማፈን፣ የተለያዩ ቆርቆሮ በመምታት ከፍተኛ ድምጽ በማውጣት፣ ጅራፍ በማጮህና በጋራ በመረባረብ ማባረር እንደሚገባ ተገልጿል።

ዘገባው የአስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ነው
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ የነፃ ቪዛ ስምምነት ተፈራረሙ!

ኢትዮጵያ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ ዛሬ የካቲት 2 ቀን 2012 ዓም በአዲስ አበባ ባደረገት የሁለትዮሽ ውይይት በሁለቱ አገሮች መካከል የዲፕሎማቲክ እና የአገልግሎት ፓስ ፖርት ለያዙ ዜጎች ያለ ቪዛ መገባት እንዲችሉ የነፃ ቪዛ ስምምነት ተፈራርመዋል።ስምምነቱን በኢትዮጵያ በኩል የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ የፈረሙ ሲሆን፤ በኢኳቶሪያል ጊኒ በኩል ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ክቡር ሲሞን ኦዮኖ ፈርመዋል።

ሁለቱ ከፍተኛ ባለስልጠናት በዛሬው ውይይታቸው የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቸልባቸው ጉዳዮች እና ከዚህ በፊት የተፈረሙ ስምምነቶች አፈጻጸምን በተመለከተ ተወያይተዋል።ሁለቱ አገሮች ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በቅርቡ በኢኳቶሪያል ጊኒ ባደረጉት ኦፊሴላዊ የስራ ጉብኝት በቱሪዝም እንዲሁም በነዳጅና ፔትሮልየም ዘርፍ በትብብር ለመስራት የሚያስቸል ስምምነት መፈራረማቸው ይታወቃል። በተያያዘ ዜና የአፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ ከካሜሮን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር ሌጅዩን ምባሌ ጋር የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

ምንጭ: የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለኮሮና ቫይረስ መመሪያና መከላከያ መሳሪያዎችን ወደ ሀገር ውስጥ አጓጓዟል።

@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ ክልል የስልጤ ዞን ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ዞኑን በክልል ለማደራጀት ወስኗል። ምክር ቤቱ በክልልነት ለመደራጀት የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ ያጸደቀው በሙሉ ድምጽ መሆኑን የምክር ቤቱ ሕዝብ ግንኙነት ጽሕፈት ቤት በፌስቡክ ገጹ ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል።

Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከካናዳ መንግስት ለተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም የምርጫ ስራ ድጋፍ የተሰጠውን ድጋፍ ዛሬ በጋራ ተፈራርሟል። በፊርማ ስነስርአቱ የቦርዱ አመራር አባላት ብዙወርቅ ከተተ እና አበራ ደገፋ( ዶክተር) ተገኝተዋል።

Via NEBE
@YeneTube @FikerAssefa
የእርሻ ባንክ ለማቋቋም ብሄራዊ ባንክ ጥልቅ ጥናት እንዲቀርብለት ጠየቀ!

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ለእርሻ ባንክ ማቋቋሚያ ይረዳ ዘንድ ጥልቅ ጥናት ይቀርበለት ዘንድ የግብርና ሚኒስቴርን መጠየቁ ታውቋል፡፡የግብርና ዘርፍ ለአገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ግኝት እንዲሁም ለኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ ቢሆንም በፋይናንስ ረገድ እዚህ ግባ የሚባል ጥቅም እያገኘ ባለመሆኑ ባለሞያዎች ለዘርፉ የሚሆን ፋይናንስ በበቂ ሁኔታ ይታሰብበት በማለት ሲወተውቱ ቆይተዋል፡፡

በሳምንቱ አጋማሽ በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት አስተባባሪነት ‘አዲስ ወግ’ በተሰኘው መድረክ ላይ ግብርናውን ለማዘመን በተደረገ ውይይት የለውጥ ማሻሻያ እቅዶችን ያቀረቡት የግብርና ሚኒስትር የፖሊሲ አማካሪ እና የግብርና ማሻሻያ ቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ አንተነህ ግርማ (ፒሄች ዲ) እንደተናገት የግብርናው ዘርፍ ለኢኮኖሚው ሁለንተናዊ ድጋፍ እያደረገ ቢሆንም ከሌሎች ዘርፎች ጋር እኩል ተወዳድሮ ከባንክ ብድር ለማግኘት ተገዷል በማለት ዘርፉ ላይ ያለውን ጫነ አብራርተዋል፡፡ አሁን ላይ ከጠቅላላው ብድር የእርሻው ዘርፍ 10 በመቶ ብቻ እያገኘ መሆኑን ሰነዶች ያሳያሉ፡፡

በመድረኩ አንተነህ እንዳሉት ዘርፉ የራሱ ባንክ ሊኖረው ይገባል ብለዋል፡፡ ከዛም ባለፈ ባንኮች ከብድራቸው እስከ አርባ በመቶ ለግብርናው ሊሰጡ ይገባል ብለዋል፡፡ምንጮች ለካፒታል እንደተናገሩት የግብርና ሚኒስቴር በእርሻ ባንክ ምስረታ ላይ ከብሄራዊ ባንክ ሃላፊዎች ጋር የተነጋገር ሲሆን፡፡ የገንዘብ ተቆጣጣሪው አካል ጥልቅ ጥናት እንዲቀርብለት መጠየቁም ታውቋል፡፡ሃሳቡ በገንዘብ ሚኒስቴር ድጋፍ አግኝቷል የሚሉት ምንጮች ጥናቱ በዚህ አመት ይጠናቀቃል በማለት ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
የካቲት 5!

"የዴሞክራሲ ሽግግር በኢትዮጵያ: ተስፋዎቹ እና ተግዳሮቶቹ" በሚል ርእስ አቶ አንዱለም አራጌ፣ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ፣ አቶ ጌታቸው ረዳ፣ አቶ ጃዋር መሃመድ፣ አቶ ልደቱ አያሌው፣ አቶ አብርሀ ደስታ፣ አቶ ሀሰን ሞአሊን፣ ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ እና ዶ/ር መረራ ጉዲና ንግግር አድርገው ከዛ ውይይት ይደረጋል።

Via:- ኤልያስ መሰረት
@YeneTube @Fikerassefa