YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዚህ በያዝነው የካቲት ወር ዕረፍት ላይ እንሚሆን ተገለጸ፡፡ በዚሁ መሠረት አምስተኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የሰራ ዘመኑ ከየካቲት 1/2012 ዓ.ም እስከ የካቲት 30/2012 ዓ.ም ድረስ በዕረፍት ላይ እንደሚሆን ታውቋል፡፡

ምንጭ:የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
በቅርቡ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ዶ/ር አብርሃም በላይ(በስተግራ ያሉት) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የስራ አመራር ቦርድን እንዲመሩ ተጨማሪ ኃላፊነት ተሰጣቸው፡፡

ምንጭ: አዲስ ስታንዳርድ
@YeneTube @FikerAssefa
አዲስ ዘመን ጋዜጣ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ መረጃ እንዲያሰጠው እንባ ጠባቂን ጠየቀ!

አዲስ ዘመን ጋዜጣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ላለፉት ስምንት ወራት በደብዳቤ፣ በስልክና በአካል በመገኘት መረጃ ቢጠይቀም ለመስጠት ፍቃደኛ ባለመሆኑ የዕንባ ጠባቂ ተቋም መረጃውን በግድ እንዲያሰጠው ይግባኝ ጠየቀ።በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ስር የሚታተመውና በአገሪቱ አንጋፋ የሆነው የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ለዕንባ ጠባቂ ተቋም ዋና እንባ ጠባቂ ያስገባው ይግባኝ እንደሚያመለክተው፤ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባለፉት ስምንት ወራት በቃል፣ በደብዳቤና በአካል ጭምር በመሄድ ስለተቋሙ እንቅስቃሴ፣ በተቋሙ አለ ስለሚባለው የግልጽነትና የአሠራር ችግር፣ የብድር አሰጣጥና አመላለስ፣ የብድር ብልሽትና መንስዔ፣ በተቋሙ ስለተከሰቱ የብድር ብልሽቶችና ተጠያቂነት፣ የቀጣይ ማሻሻያና ሌሎች በርካታ ጉዳዮች ለባንኩ ፕሬዚዳንት ጨምሮ በየደረጃው ላሉ ኃላፊዎች ማብራሪያ እንዲሰጡትና ተቋሙ ላይ ያሉ አሠራሮችና የባንኩ አካሄድ ለባንኩ ባለቤት ለኢትዮጵያ ህዝብ ግልጽ እንዲያደርግ በተደጋጋሚ ቢጠየቅም የተለያዩ ሰበቦችን በመደርደር መረጃውን ለመስጠት ፍቃደኛ ባለመሆኑ ይግባኝ መጻፉን ያመለክታል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚንስትር ዶ/ር ስለሺ በቀለ ዋሽንግተን ዲሲ ገቡ!

በአሜሪካ ዲሲ ለነገ እ.ኤ.አ. ፌብሩዋሪ 12/2020 በተያዘው ቀጠሮ መሰረት የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚንስትር ዶ/ር ስለሺ በቀለ ዋሽንግተን ዲሲ ገብተዋል፡፡በዕለቱም ሳምንቱን ሙሉ ከግብጽ እና ሱዳን ልዑካን ጋር የተደረገውን የህግ ማዕቀፍ ድርድር ውጤት ከኢትዮጵያ ልዑካን ጋር ገምግመዋል፡፡ቡድኑ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ምክክር ያደረገ ቢሆንም ስምምነት ላይ ሊያደርስ የሚችል ሰነድ በጋራ ማዘጋጀት አለመቻሉ በግምገማው ታይቷል፡፡ኢትዮጵያ በፍትሃዊና ምክንያታዊ ተጠቃሚነት እንደምታምን ነገር ግን በአባይ ውሃ የመጠቀም መብቷን አሳልፎ የሚሰጥ ምንም ዓይነት ስምምነት እንደማትፈጽም በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት አረጋግጠዋል፡፡

ምንጭ: ኢቲቪ
@YeneTube @FikerAssefa
የኢፌድሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በቀድሞ የኬንያ ፕሬዚዳንት ዳንኤል ቶሮይቲች አራፕ ቀብር ላይ ለመታደም ናይሮቢ ገብተዋል።

ምንጭ: በናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ
@YeneTube @FikerAssefa
የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት የካቲት 14 በመስቀል አደባባይ ይካሄዳል!

ከደቂቃዎች በፊት የአርቲስቱ ማናጀር አቶ ጌታቸው ማንጉዳይ ከነገረኝ:

"ኮንሰርቱ ቅዳሜ የካቲት 14 ከ10 ሰአት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ ይካሄዳል። ከውጪ የሚገቡትን የድምፅ ሲስተሞች እና መሳርያዎችን ወጪ ለመሸፈን ብቻ በጣም ትንሽ ክፍያ ይኖራል። ኮንሰርቱ ምንም አይነት ስፖንሰር አይኖረውም። አሁን ከማዘጋጃ ጉዳዮችን ጨራርሰን እየወጣን ነው። በሌሎች ከተማዎች ስለታሰበው ኮንሰርት ወደፊት እነግርሀለው።"

-ጋዜጠኛ ኤልያስ መሠረት
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ሰዓት የኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክት ታይቶበት በለይቶ ማቆያ ማእከል የገባ ሰው አለመኖሩ ታወቀ

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ኖቬል ኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ 39 ጥቆማዎች ደርሰውት በሁሉም ጥቆማዎች ላይ ማጣራት ማድረጉን አስታወቀ።

ከተጠቋሚዎች 14ቱ የበሽታውን ምልክት ያሳዩ ስለነበረ፣ ተለይተው ወደ ማቆያ ስፍራ እንዲገቡ ተደርጎ በላብራቶሪ ምርመራ ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸውን ከተረጋገጠ በኋላ ወደ ሕብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል ብሏል።

በትላትናው ዕለት አንድ ሰው በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበረ ሲሆን፣ በኢንስቲትዩቱ የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ውጤቱ ከቫይረሱ ነፃ በመሆኑ ከለይቶ ማቆያ ማእከሉ መውጣቱን አመልክቷል።
በአሁኑ ሰዓት በለይቶ ማቆያ ማእከል ውስጥ የበሽታው ምልክት ታይቶበት የገባ ሰው አለመኖሩን ጠቅሷል።

ስለ በሽታው ግንዛቤ ለመፍጠር ለመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች፣ ለሆቴል ባለሞያዎች እንዲሁም ከክልል እና ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለተውጣጡ ፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድን አባላት ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል ብሏል።
ከቻይና የሚመጡ መንገደኞችን የሙቀት ልየታ እና የበሽታው ምልክት የታየባቸው መንገደኞችን የጤና ሁኔታ የመከታተል ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውንም ጠቅሷል።

በሁሉም የኢንዱስትሪ ፓርክ ባለባቸው ክልሎች ውስጥ የለይቶ ማቆያ ማእከል እና የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ማስተባበሪያ ማእከላትን ለምላሽ ዝግጁ ለማድረግ በተያዘው እቅድ መሠረት ደቡብ ክልል በሀዋሳ ከተማ ድጋፍ ሰጪ የባለሞያዎች ቡድን በመላክ ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር በመሆን የዝግጅት ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝም ገልጿል።

በአጠቃላይ የኖቭል ኮሮና ቫይረስ ዝግጁነት እና ምላሽ እንቅስቃሴ ከተጀመረበት ጊዜ አንሥቶ በሁሉም አቅጣጫ ባሉ የሀገሪቱ መውጫ እና መግቢያ ድንበሮች ላይ ከጥር 14 ቀን 2012 እስከ የካቲት 02 ቀን 2012 ድረስ የኮሮና እና የኢቦላ ቫይረስን ዝግጁነት በጋራ በማጣመር ከ172 ሺህ በላይ መንገደኞች ላይ የሙቀት ልየታ መካሔዱን አስታውቋል።

Via:- የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
@YeneTube @Fikerassefa
የብረታ ብረት እና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) የቢሾፍቱ ባስ መገጣጠሚያ ሠራተኞች የተገባልን የደሞዝ ጭማሪ ይፈፀምልን በሚል ምክንያት ከሦስት ሳምንት በፊት አራት አውቶቡሶችን አቃጠሉ።

ከ 10 ሺሕ በላይ ሠራተኞች ያሉት ድርጅቱ በተደጋጋሚ የደሞዝ ጭማሪ እንደሚያደርግ ለሠራተኞቹ ቃል ቢገባም መፈፀም አልቻለም።

በዚህ ምክንያት ተጀምሮ በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው ፋብሪካው የተነሳ በተቃውሞ ግርግር መካከል ነው፣ መኪኖቹ በእሳት የተያያዙት።
ተገጣጥመው ሊሸጡ የተዘጋጁትን አራት አውቶቡሶች በሚቃጠሉበት ወቅት እሳቱን ለማጥፋት ሠራተኛው መረባረቡን፤ ነገር ግን መኪኖቹ ሙሉ ለሙሉ ከጥቅም ውጪ መሆናቸውን የዐይን እማኞች ገልጸዋል።

የሜቴክ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ መሐመድ እድሪስ ለአዲስ ማለዳ የድርጊቱን መፈጸም አረጋግጠው እስከ አሁን ግን በጉዳዩ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር የዋለ ሰው የለም ብለዋል።

Via:- Addis Maleda
@Yenetube @FikerAssefa
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ ተጠርቷል!

ለየካቲት 5 አስቸኳይ ጉባኤ የጠራው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀረበ ረቂቅ አዋጅን እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል፡፡የሕግ፣ፍትሕና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለውሳኔ የሚያቀርበው ረቂቁ ለትርጉም የተጋለጠ እንዲሁም መንግሥት ተቺዎቹን ሁሉ ሊያሳድድበት የሚችልበት፣ የፀረ ሽብር ሕጉ ግልባጭ እንዳይሆን በሚል ስጋት ፈጥሮ እያከራከረ ይገኛል፡፡ሆኖም ረቂቁ ምን ዕጣ ፈንታ ይገጥመዋል፤ ከዘህ ቀደም የተሰጡ አስተያየቶችንስ በምን መል አካቷቸው ይሆን የሚለው ሐሙስ የሚታይ ይሆናል፡፡

እሁድ የአንድ ወር እረፍታቸውን ጀምረው በ4 ቀናት ልዩነት ለአስቸኳይ ስብሰባ የተጠሩት የሕዝብ ተወካዮች ጉባኤያቸው በ10 አጀንዳዎች ላይ ውሳኔዎችን ያሳልፋሉ፡፡በዚህም የኤክሳይዝ ታክስ፣ የፌደራል የአስተዳደር ሥነ ሥርዓት፣ በውጭ አገራት ለተሰጡ የግልግል ዳኝነት ውሳኔዎች እውቅና የመስጠት እና የመፈጸም ስምምነትን ለማጽደቅ የሚቀርቡ ረቀቅ አዋጆችን ያጸድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን ሕጋዊ ሰውነት ለመስጠት የቀረበ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴም ይመራል፡፡

ምንጭ: አሃዱ ቴሌቪዥን
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ የሚነሱ ግጭቶችን በየሦስት ወሩ መተንተን ሊጀመር ነው።

የኢትዮጵያ ስትራቴጂክ ተቋም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶችን በየሦሰት ወሩ የሚመዘግብ፣ የሚተነትን እና ይፋዊ ሪፖርት የሚያወጣ አዲስ ቡድን አደራጅቶ ወደ ሥራ ሊያስገባ መሆኑን ገለጸ።የመንግሥት ተቋማት፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የተለያዩ የግል ድርጅቶች እንዲሁም የሚዲያ ተወካዮች በዚህ ሥራ የሚሳተፉ ሲሆን፣ በተለያዩ ዘዴዎች የሚሰበሰቡ መረጃዎችን በማረጋገጥ እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም ግጭቶቹ የተከሰቱበት ቦታ ድረስ በመሄድ የሚያረጋግጡበት አንደሆነ ታውቋል። የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ሃሌሉያ ሉሌ ለአዲስ ማለዳ እንደገለፁት፣ የግጭት ትንተናው ዋና ዓላማ መረጃ በቀላሉ እንዲገኝ ለማድረግ እና ስለ ግጭቶች በሚሰጡ የተሳሳቱ መረጃዎች ለከፋ ግጭት እየዳረጉ በመሆኑ ነው። ለዚህም ወቅታዊ እና ትክክለኛውን ሪፖርት ይፋ በማድረግ ግጭቶችን ለፖለቲካ ፍጆታ የማዋል ተግባሮችን ለመከላከል መታሰቡን ገልፀዋል።

ምንጭ: አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
"የዴሞክራሲ ሽግግር በኢትዮጵያ: ተስፋዎቹ እና ተግዳሮቶቹ" በሚል ርእስ በመጪው ሀሙስ በፖለቲካ ሰዎች መሀል ሊደረግ ታስቦ የነበረው ውይይት ተራዝሟል!

አዘጋጁ Institute for Strategic Affairs "ፕሮግራሙ የተራዘመው አንዳንዶቹ ንግግር ያረጋሉ ተብለው የነበሩት ሰዎች ሌላ ስራ ስላጋጠማቸው ነው" ያለ ሲሆን ይህ ፕሮግራም ለግዜው ላልተወሰነ ግዜ ተራዝሟል ብሏል።

Via Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
የመከላከያ ሠራዊት ቀን የፊታችን ቅዳሜ ይከበራል!

የዘንድሮው የመከላከያ ሠራዊት ቀን “የሀገራችንን ሉዓላዊነትና የሕዝባችንን ሠላም በፅናት እንጠብቃለን” በሚል መሪ ሃሳብ የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 7 ቀን 2012 ዓ.ም እንደሚከበር ታውቋል። ሚኒስቴሩ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው በዓሉ ከሕብረተሰቡ ጋር በሚደረጉ ውይይቶች፣ በበጎ አድራጎት ስራዎች፣ በስፖርታዊ ውድድሮች፣ የሠራዊቱን ዝግጁነት በሚያሳዩ ወታደራዊ ሰልፎችና ትርዒቶች ታስቦ ይውላል።ቀኑ እስካሁን ሠራዊቱ የሔደባቸው ጉዞዎች የሚቃኙበት፣ ሕዝባዊ ወገንተኝነቱን በማረጋገጥም እንዳለፉት ጊዜያት ሁሉ ተልዕኮውን በጽናት ለመወጣት ያለውን ዝግጁነት የሚያሳይበት ነው ብሏል መግለጫው። ሠራዊቱ የሕዝቡን ሠላም በጽናት ለመጠበቅ በቁርጠኝነት እንደሚሰራም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
በዋግ ኽምራ ዞን 108 ሺሕ ሰዎች ለምግብ እጥረት ተጋለጡ!

በአማራ ክልል በዋግ ኽምራ ዞን በ2010 የክረምት ወቅት የዝናብ እጥረት በማጋጠሙ በተለይም በዝቋላ፣ በሳሃላ እና በሰቆጣ ወረዳዎች ባጋጠመው ድርቅ ለቀጣይ አምስት ወራት 108 ሺሕ ዜጎች አስቸኳይ የእለት የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ተባለ።ችግሩ በከፋባቸው ቀበሌዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ቤታቸውን ጥለው ውሃ ወዳለባቸው ቀበሌዎች በመሄድ ላይ መሆናቸውን አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። በዞኑ የሚገኙ ከአንድ ነጥብ ሦስት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ እንስሳትም የመኖ እጥረት እንዳጋጠማቸው ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። የሰቆጣ ከተማ ነዋሪ የሆኑት መንግሥቱ ደሳለኝ፣ ከገጠር አካባቢ ወደ ከተማ ገብተዉ የሚማሩ ተማሪዎች ትምህርታቸዉን አቋርጠዉ ወደ ቤተሰቦቻቸዉ እየተመለሱ እንደሆነ መመልከታቸዉን ጠቅሰዋል። አክለውም በአካባቢው ያሉ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የእለት ምግብ ቢሰጡም፣ በቂ ባለመሆኑ ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን እንዲያቋርጡ ምክንያት መሆኑን አክለው ገልጸዋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
አል-በሽር ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተላልፈው ሊሰጡ ነው!

ሱዳን የቀድሞ ፕሬዝደንቷን ኦማር አል-በሽርን ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አሳልፋ ልትሰጥ እንደሆነ ተነገረ።ሱዳን አል-በሽርን አሳልፋ የምትሰጠው በቀረበባቸው የጦር ወንጀል ክሶች ነው።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
LTV የዜና ክፍል ሃላፊ እና ፕሮግራም አዘጋጅ ሆኖ ሲሰራ የቆየ ጋዜጠኛ ተመስገን መንግስቴ በዋልታ ቴሌቭዥን በወቅታዊ ጉዳዮች ክፍል ውስጥ በመሪ አዘጋጅነት መቀጠሩን አረጋግጫለው። #ተስፋዬ_ጌትነት

በማህበራዊ ሚዲያ የተዛባ መረጃ እየተሰራጨ ቢሆንም እውነታው ጋዜጠኛ ተመስገን በደሞዝ ጭማሪ ምክንያት ወደ ዋልታ መግባቱን ታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሶማሌ ላንድ ፕሬዝዳንት እና የሶማልያ ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት አንድ ለአንድ ውይይት ማድረጋቸውን የVOA ምንጮች መግለፃቸውን የVOA ሶማልኛ #ሀረን_ማሩፍ በትዊተር ገፁ አስፍሯል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአንበጣ መንጋ ካሳለፍነው ኅዳር ጀምሮ በምሥራቅና ሰሜን ምሥራቅ ቆላማ አካባቢዎች ተከስቶ በሰብል ላይ ጉዳት ሲያደርስ ቆይቷል።በኅብረተሰቡና በመንግሥት ድጋፍ ጭምር በወቅቱ ፤ መንጋው መወገድ የቻለ ቢሆንም እንደገና ሰሞኑን በአንዳንድ ደጋማ አካባቢዎች መታየቱን የየአካባቢው አርሶ አደሮችና የግብርና ባለሙያዎች አመልክተዋል፡፡

Via:- DW
@YeneTube @Fikerassefa
ትናንት ማምሻውን የተጠናቀቀው 33ኛዉ የአፍሪቃ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ሰሞኑን አዲስ አበባ ላይ በተለያዩ አህጉራዊና ዓለም ዓቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መክሮ ውሳኔ አሳልፏል። ከነዚህም ውስጥ የአህጉሪቱን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅና ከጦር መሳሪያ ድምጽ ነፃ የሆነች አፍሪካን ለመፍጠር የውጭ ኃይሎችን ጣልቃ ገብነት ማስወገድ ተገቢ መሆኑን አመልክቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአንበጣ መንጋ ለመቆጣጠር የሚያስችል ዘመናዊ የድሮን መሳሪያ ሙከራ ላይ ሊውል ነው።
@YeneTube @Fikerassefa
በአማራ ክልል ከብት በመጠበቅ ላይ ያሉ ህጻናትን አግቶ ገንዘብ ለመቀበል የሞከረው ተጠርጣሪ የ25 ዓመት እስራት ተፈረደበት።

ተከሳሽ አገሬ የሗላሸት የተባለ ግለሰብ በአማራ ክልል ጠገዴ ወረዳ የኢፌደሪ የወንጀል ህግ በ1996 ዓ/ም ተደንግጎ የወጣውን አንቀፅ 590 ንዑስ ቁጥር 1/ሀ/ እና 2/ሐ/ በመተላለፍ በሚል ነበር ክስ የተመሰረተበት።

ተከሳሹ
1ኛ. ሁናቸው ማስረሻን ጳጉሜ 4/2011 ዓ/ም አዴት ቀበሌ ከብት በመጠበቅ ላይ እያለ 30 ሽ ብር አምጣ በማለት አግቶ 20 ሽ ብር በመቀበሉ።

2ኛ.የ7 ዓመት ህፃን መልካሙ ጣምያለውን ታህሳስ 7/2012 ዓ/ም አዴት ቀበሌ 75 ሽ ብር አምጡ በማለት ከብት በሚጠብቅበት የጦር መሳሪያ በመያዝ ጭካኔ በተሞላበት 15 ሽ ብር በመቀበል።ከሳምንት በላይ ለርሃብና ለጥም እንዲሁም ለእንግልት በመዳረጉ ዓቃቤ-ህግ ክስ መስርቶበታል።

ተከሳሽም ወንጀሉን ፈፀምክ በተባልኩበት ቀን አዲስ አበባ ነው የነበርኩ በሁለተኛውም መተማ ነው የነበርኩ አልፈፀምኩም በማለት ክዶ ተከራክሯል።

ዓቃቤ-ህግም ተከሳሽ ክዶ ቢቀርብም እንደ ክሱ አመሰራረት ሊያስረዱ የሚችሉ ማስረጃዎችን በማቅረብ ለፍርድ ቤቱ አስደምጧል።

ተከሳሽ እንዲከላከል ቢፈቀድለትም የመከላከያ ማስረጃ የለኝም በዓቃቤ ህግ ማስረጃ ውሳኔ ይሰጠኝ ሲል ለፍርድ ቤቱ አሳስቧል።ፍ/ቤቱም የሁለቱን ወገን መርምሮ ተከሳሽን ጥፋተኛ ብሏል ።የቅጣት ውሳኔ ለማስተላለፉ በፊት የቅጣት ማቅለያና ማክበጃ ጠይቋል። ዓቃቤ-ህግ 3 ማክበጃዎችና 1 ማቅለያ ለፍ/ቤቱ አስይዟል።ተከሳሽ የሁለት ልጆቾ አባት ነኝ ደካማ እናት አለች ይቅለልልኝ ሲል ጠይቋል።ዓቃቤ-ህግ ተቃውሟል ተከሳሽ አዲስ አበባና መተማ ነው የምኖር እያለ በቃል ለፍ/ቤቱ ያሰማ በመሆኑ፣ ቤተሰብ የማይረዳ በመሆኑ ታውቆ ውድቅ ይሁንልን ሲል አሳስቧል።

ፍ/ቤቱም የዓቃቤ ህግን ማክበጃ በመቀበል የተከሳሽን ማቅለያ ውድቅ በማድረግ ተከሳሽ ወንጀሉን የፈፀመው በስግብግብነት ፣በጦር መሳሪያ ፣ በአፍቅሮ ንዋይ የሰው ልጅን ከገንዘብ በማሳነስ እንዲሁም በተደጋጋሚ የተፈፀመና ህፃናትን ለርሃብ ፣ ለጥምና ለእንግልት የዳረገ መሆኑን በማረጋገጥ እሱንም ሆነ ሌሎችን ያስተምራል በማለት በ25 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ እንደተፈረደበት የወረዳው የመንግስት ኮሙንኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa