YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የጃዋር መሀመድ ጥበቃዎች መነሳታቸውን ኦቢኤን ዘገበ!

በቅርቡ ኦፌኮን የተቀላቀሉት ጃዋር መሃመድ የፌደራል ፖሊስ ሲያደርግላቸው የነበረውን ጥበቃ ከእሁድ ጥር 17/2012 ጀምሮ ማንሳቱን የኦሮሚያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡ኦቢኤን በምሽት ሁለት ሰአት ዜናው ላይ አንዳስነበበው መንግስት ለማንኛውም ተፎካካሪ ፓርቲ አመራርም ሆነ አባል የግል ጥበቃ ስለማያደርግ እና አሰራሩም ስለማይፈቅድ ጥበቃዎቹ እንደተነሱ የፌደራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ደግሞ አደረኩት ባለው ማጣራት ጃዋር ጠባቂዎቻቸው ወደ መደበኛ ስራቸው እንዲመለሱ እንዲያደርጉ የፌደራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ዘርፍ በፃፈው ደብዳቤ ማስታወቁን አረጋግጫለው ብሏል፡፡የጋዜጣው ኤዲቶሪያል ክፍል ወደ ጃዋር መሃመድ በተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ባደርግም ለግዜው አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል ብሏል፡፡

#Updated
ሁሉ ሰላም ነው ከፌዴራል ፖሊስ ጋር ተወያይተን የተስማማንበት ነው ብሏል ጃዋር መሃመድ

ምንጭ: አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa