የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሥራ ክንውን ሁኔታ ሪፖርት ለጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አሕመድ ቀረበ።
የክንውን ሁኔታውን በመመልከት ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ ሕልምን እውን ለማድረግ ውጤታማ ሥራ የማከናወንን አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥተው አንስተዋል። ከአያያዝ ጉድለት የተነሣ የተከሠተውን የሥራ መጓተት አስታውሰውም፣ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ የሕዳሴው ግድብ የግንባታ ሥራ የገጠመውን ችግር ለመፍታት መንግሥት የወሰዳቸውን ርምጃዎች ዘርዝረዋል። ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ ሁሉም ተቋራጮች ሥራውን ለማፋጠን በኅብረት እንዲሠሩና በቶሎ ኃይል ለማመንጨት የሚያስችሉ ቁልፍ ምዕራፎችን እንዲያጠናቅቁ አበረታተዋል።ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ ለኢትዮጵያውያንም ሆነ አፍሪካውያን የኩራት ምንጭ በሆነው ግድብ ፣ የተፋሰሱን ሀገራት በማይጎዳ ሁኔታ በፍትሐዊነት ለመጠቀም ያላቸውን ቁርጠኝነት አውስተዋል።
#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa

አንድ አፍታ ሚዲያ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ዙሪያ በሰራው ዘገባ ምክንያት በፖሊስ ወከባ እንደተፈጸመበት ገለጸ፡፡
“ህግ እና ስርአትን ባልተከተለ መልኩ የመረጃ ምንጫችን ታስራለች” የተቋሙ ኃላፊ
“ማስረጃ እና መረጃ ይዘን ባቀረብነው ዘገባ ጥፋት ካለ በሚዲያው ህግ መሰረት ልንጠየቅ ይገባል እንጂ ሆን ተብሎ የዕረፍት ቀናትን አስታክኮ በመምጣት የተቋሙን ስራ አሰኪያጅ እንዲሁም አንድ ጋዜጠኛን ወደ ፖሊስ ጣቢያ ለመውሰድ እና እንግልት ለማድረስ የታሰበ እንቅስቃሴ ተደርጓል” ያሉት የተቋሙ ባልደረቦች ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ጉዳይን በተመለከተ ባቀረቡት ዘገባ ተሳታፊ እንደሆነ በተገለጸ ግለሰብ ላይ የተበዳይ ስሞታ እና ማስረጃን ለተመልካቾች በማቅረባቸው ምክንያት ክስ እንደተመሰረተባቸው ከፖሊሶቹ መስማታቸውንም ጠቁመውናል፡፡
በህግ አግባብ መጥሪያ ድርሶት ላልቀረበ ተጠርጣሪ መጥሪያ እንዲደርሰው ማድረግ ተገቢ ሆኖ ሳለ 5 ሆነው በመምጣት በወቅቱ በቢሮው ያልነበሩትን ስራ አስኪያጅ እና ጋዜጠኛ ካላመጣችሁ በሚል ወከባ ተፈፅሞብናል ብለዋል፡፡
ስለ ጉዳዩ የጠየቅናቸው የሚዲያው ኃላፊ በተሰራው ዘገባ ላይ የግል ተበዳይ ነኝ ያሉትን ግለሰብ ማስረጃ እና መረጃ ይዘው ዘገባውን እንዳቀረቡ ጠቁመው “የመረጃ ምንጯ መረጃ ሰጥተሻል በሚል ህግ እና ስርአትን ባልተከተለ መልኩ በቁጥጥር ስር መዋሏን” መስማታቸውን እና ፖሊስ ባቀረበው የስም ማጥፋት ክስ ምርመራ በመጀመሩ ዘገባው ከዩቲዩብ ላይ እንዲወርድ ጥር 22 ቀን ከቦሌ ምድብ ችሎት የተፃፈ ትዕዛዝ በመቅረቡ ቪዲዮው ከእይታ ዛሬ እንዲወርድ መደረጉንም ተናግረዋል፡፡
“ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን በተመለከተ መረጃ እና ማስረጃ በእጃችን ይገኛል ያሉት ኃላፊው በኢንተርፖል ደረጃ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር የሚፈለጉ ተጨማሪ 4 ግለሰቦች እጃቸው እንዳለበት ማስረጃ ደርሶናል፡፡ ይህንንም ሙያው በሚጠይቀው መሰረት አጣርተን ክፍል 1 ዘገባችንን ለህዝብ በማድረሳችን ፖሊስ ነኝ ያለ በኋላም የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ባልደረባ መሆኑን ባረጋገጥነው ግለሰብ በተደጋጋሚ ስልክ እየተደወለ በእኔም ሆነ ፐሮግራሙን ባቀረበው ጋዜጠኛ ላይ ማስፈራሪያ እና ዛቻ ይደርስብን ነበር ” ብለዋል፡፡
ሁኔታው ሚዲያው አንፃራዊ በሚባል መልኩ በነፃነት እየተንቀሳቀሰ ነው በሚባልበት በዚህ ወቅት አሁንም በግሉ መገናኛ ብዙሀን እና አባላቱ ላይ ጫና እና ተግዳሮቱ መቀጠሉን የሚያሳይ ሲሆን ከዚህ ቀደም የአሀዱ ሬዲዮ ባልደረቦች በተመሳሳይ መልኩ ትፈለጋላችሁ በሚል የደንብ ልብስ የለበሱ የፖሊስ አባላት ወደ ጣቢያው በማምራት በጣቢያው ኃላፊዎች እና ጋዜጠኞች ላይ ከፍተኛ ጫና ማድረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡
Via Sheger Times

Forwarded from YeneTube
✅ ሁሉንም ሰብስቦ በአንድ ላይ የያዘ የግብይት ድረገፅ
✅ በድረ ገፁ ላይ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት ዕቃዎቹን መሸጥ ይችላል።
✅ ከ2700 በላይ ዕቃዎች
✅ @SebsibieEthiopia
www.sebsibie.com
📞 0953707070

#Coronavirusupdate
1⃣4⃣3⃣8⃣0⃣ ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል።
3⃣0⃣4⃣ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው ሞተዋል።
1⃣9⃣5⃣4⃣4⃣ ሰዎች ተጠርጥረው ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
በ2⃣5⃣ ሀገራት የቫይረሱ ኬዝ ተረጋግጧል።
@YeneTube @FikerAssefa
1⃣4⃣3⃣8⃣0⃣ ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል።
3⃣0⃣4⃣ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው ሞተዋል።
1⃣9⃣5⃣4⃣4⃣ ሰዎች ተጠርጥረው ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
በ2⃣5⃣ ሀገራት የቫይረሱ ኬዝ ተረጋግጧል።
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
#Coronavirusupdate 1⃣4⃣3⃣8⃣0⃣ ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል። 3⃣0⃣4⃣ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው ሞተዋል። 1⃣9⃣5⃣4⃣4⃣ ሰዎች ተጠርጥረው ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል። በ2⃣5⃣ ሀገራት የቫይረሱ ኬዝ ተረጋግጧል። @YeneTube @FikerAssefa
ከቻይና ውጭ የመጀመርያው ሟች ዛሬ የተመዘገበ ሲሆን በፊሊፒንስ የሚገኝ ቻይናዊ ግለሰብ መሆኑን CGTN ዘግቧል። በትናንትናው እለት ብቻ በውሃን ከተማ የሞቱት ቁጥር ደግሞ 45 መሆኑንም ዘገባው አክሏል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የኢንተርኔት ማቆም፣ መዝጋትና መረጃን አጣርቶ መልቀቅ የሚያስችል ህግ ሊወጣ ነው!
የኢንተርኔት ማቆም፣ መረጃን አጣርቶ ማውጣትና መዝጋት በተመለከተ በአገር ደረጃ የወጣ ህግ ባለመኖሩ ተገቢው መረጃ ለተገቢው አካል እንዳይደርስ ሆኗል። በዚህም ይህንን ለማረም በኮምፒውተር ወንጀሎች አዋጅ ለማካተት ረቂቅ እየተዘጋጀ መሆኑን የብሔራዊ ህግና ፍትህ አማካሪ ምክርቤት አስታወቀ።በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት መምህርና በጠቅላይ አቃቤ ህግ የተቋቋመው የህግና ፍትህ አማካሪ ምክርቤት አባል ረዳት ፕሮፌሰር መሰንበት አሰፋ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ መንግስት ኢንተርኔትን በማቆም፣ በመዝጋትና መረጃ አጣርቶ በማውጣቱ ዙሪያ ሊከተላቸው የሚገቡ ህጎች በአገር ደረጃ አልተቀመጡም። በዚህም በተለያየ መንገድ እነዚህ ክዋኔዎች ተግባራዊ እየሆኑ መጥተዋል። ይህ ደግሞ ተጠቃሚዎችንም ሆነ ህዝቡን መረጃ በትክክል እንዳያገኝ አድርጎታል።በሚዲያ የመረጃ ነጻነትና በኮምፒውተር ወንጀሎች ረቂቅ አዋጅ ዙሪያ አሁን ባለው ደረጃ ምክር ቤቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት ህግ ለማውጣት እየሰራ እንደሆነ የሚገልጹት ረዳት ፕሮፌሰሩ፤ የህጉ መውጣት በህግ አግባብ የተቃኘ መረጃ ለህዝብ እንዲደርስ እድል ይሰጣል ብለዋል። የኢንተርኔት አጠቃቀም ሁኔታውም ሥርዓት እንዲኖረው ያደርጋል።
ምንጭ: ኢ.ፕ.ድ

ኣክሱም ዩኒቨርሲቲ አራተኛ ግቢው አስመረቀ!
አክሱም ዩኒቨርሲቲ አራተኛ ግቢው ዓድዋ ግቢ ትናንት አስመርቋል፡፡ ዓድዋ ግቢ በጠቅላላ እስከ 700 የሚደርሰ ተማሪዎች የመቀበል አቅም ያለው ሲሆን አሁን 400 የሚሆኑ የቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ፋካሊቲ ተማሪዎች ከ 40 መምህራን እና 45 አስተዳደር ሰራተኞች ጋር ወደ ግቢው ገብተዋል፡፡ በ1999 ዓ.ም ኣክሱም ዩኒቨርሲቲ 735 ተማሪዎችን በአምስት ፋካሊቲ በመቀበል በ60 መምህራን እና 150 የአስተዳደር ሰራተኞችን የመማር ማስተማር ሂደቱን የጀመረው በአሁን ጊዜ ኣክሱም ዩኒቨርሲቲ 1800 የሃገር ውስጥ እና የውጭ መምህራን ፣ 3000 ገደማ የአስተዳደር ሰራተኞች እና የጤና ባለሞያዎች እንዲሁም ከ 24,000 በላይ ተማሪዎች አሉት፡፡
ከአዲሱ ግቢ ዓደዋ በተጨማሪ ኣክሱም ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ ፣ ጤና ሳይንስ ግቢ እና ሽረ ግቢ ያሉት ሲሆን በተጨማሪም ሰለኽለኻ የምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ማእከል እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አሉት፡፡ ኣክሱም ዩኒቨርሲቲ በ 11 ዙር የተማሪዎች ምረቃ ከ24,000 በላይ አስመርቋል፡፡የምረቃ ስነስርዓቱ ግቢው በመጎብኘት ፣ ችግኝ በመትከል ፣ በሙዚቃ እና ፋሽን ሾው ያጠቃለለ የነበረ ሲሆን የኣክሱም ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዝዳት ፀሃዬ ኣስመላሽ (ዶ/ር) ፣ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ፣ የዓድዋ ከተማ ምህበረሰብ እና አስተዳደር በምረቃ ስነስርዓቱ መገኘታቸውን ከዩንቨርስቲው የማህበራዊ ሚዲያ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በአማራ ክልል የተለያዩ ከተማ ነዋሪዎች ለታገቱት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣት ድምጻቸውን አሰምተዋል፡፡የታገቱ ተማሪዎች እንዲለቀቁ ለመጠየቅ፣ የእገታ ድርጊቱንና የመንግሥትን ዝምታም ለማውገዝ በጎንደር፣ ደብረ ታቦር፣ ሰቆጣ፣ ኮምቦልቻ እና መተማ ዮሐንስ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሂደዋል።
ምንጭ: አብመድ
@YeneTube @FikerAssefa
ምንጭ: አብመድ
@YeneTube @FikerAssefa
የኮንዶሚኒየም ቤቶችን መገበያየት እንጂ ካርታ ማዘዋወር እንደማይቻል አስተዳደሩ ማገዱ ተሰማ!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጋራ መኖሪያ ቤቶችን መገበያየት (መሸጥና መግዛት) ቢቻልም፣ የባለቤትነት ሰነድ (ካርታ) ስም ማዘዋወር እንዳይቻል ዕግድ መጣሉ ተሰማ፡፡አምስት ዓመታትና ከዚያ በላይ ያስቆጠረ የጋራ መኖሪያ ቤት ባለቤት፣ ቤቱን መሸጥ የሚከለክለው እንደለሌለና መብቱም እንደሆነ፣ ነገር ግን ቤቱን የገዛው አካል የቤት ባለቤትነት መብቱን (ካርታውን) ስም ማዞር ማግኘት እንዳይችል (እንዳይዘዋወርለት) ላልተወሰነ ጊዜ መታገዱን የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ መሬት ልማት አስተዳደር የኮንዶሚኒየም ቤቶች የባለቤትነት ሰነድ ስም ማዘዋወር እንዳይቻል ዕግድ የጣለው፣ የቀበሌ ቤቶች የባለቤትነት ሰነድ (ካርታ) እየተዘጋጀ በመሆኑና እስከሚጠናቀቅ ድረስ በየክፍላተ ከተሞች ባለው የሥራ ጫና መሆኑን ምንጮች ተናግረዋል፡፡ የቀበሌ ቤቶች ካርታ ተሠርቶ እንደተጠናቀቀ መደበኛና ማንኛውም ቤትንና ንብረትን በሚመለከት መከናወን ያለበት ሥራ በመደበኛነት እንደሚቀጥል የተገለጸ ቢሆንም፣ ዕግዱ ሌላ ምክንያት እንዳለውም የሪፖርተር ምንጮች ጠቁመዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ምንጩ ያልታወቀ ከፍተኛ ገንዘብ እየተዘዋወረና በአስተዳደሩም ሆነ በባለሥልጣናት ጥርጣሬ ሳያድር እንዳልቀረ የገመቱት ምንጮች፣ በከተማው ውስጥ በዕጣ የተላለፉና አምስት ዓመታት ያለፋቸውን የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በመግዛት፣ በአንድ የቤት ቁጥር በርከት ያሉ የቀበሌ መታወቂያዎች ይወጣሉ የሚል ሥጋትም እንዳለም ጠቁመዋል፡፡ይህ ደግሞ በቀጣይ በሚካሄደው ምርጫ ላይ የራሱ ተፅዕኖ ስላለው ያንን ለመቆጣጠርና ለመከላከል መሆኑንም ግምታቸውን ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ነባር መታወቂያ ያላቸው ነዋሪዎች ካልሆኑ በስተቀር አዲስ መታወቂያ መስጠት መቆሙ ይታወሳል፡፡ዕግድ ተጥሎበታል ስለተባለው የኮንዶሚኒየም ቤት የባለቤትነት ሰነድ (ካርታ) ስም ማዘዋወር የታገደበት ምክንያት ምን እንደሆነና እስከ መቼ እንደሚቆይ ማብራሪያ ለማግኘት፣ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊዎችን ለማግኘት የተደረገው ጥረት አዲስ ምደባ ላይ እንደሆኑ በመግለጹ ተጨማሪ ማብራሪያ ማግኘት አልተቻም፡፡
Via Reporter

የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር የአፍሪካ ጉብኝታቸውን በሚቀጥለው ሳምንት ከኢትዮጵያ ይጀምራሉ!
የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ የአፍሪካ ጉብኝታቸውን በሚቀጥለው ሳምንት ከኢትዮጵያ ይጀምራሉ። ከፈረንጆቹ የካቲት 6 ጀምረው እስከ የካቲት 14 ቀን 2020 በሚቆየው ጉብኝታቸው ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ወደ ሴኔጋል ያቀናሉ። በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር ይገናኛሉ ተብሎም ይጠበቃል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው ወቅት በአዲስ አበባ በሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባኤ ላይ በመሳተፍ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ጋርም ይወያያሉም ብሏል ፅህፈት ቤቱ። ኢትዮጵያ እና ካናዳ በአውሮፓውያኑ 1965 ዓመተ ምህርት ይፋዊ ዲፒሎማሲያዊ ግንኙነት ጀምረዋል።
Via FBC

ዛሬ በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች የታገቱ የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ይለቀቁ የሚሉ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሄዱ። ሰልፎች ከተካሄዱባቸው ከተሞች መካከል ጎንደር፣ ሰቆጣ፣ ደብረታቦር፣ ኮምቦልቻ፣ ላሊበላና ሌሎችም ይገኙባቸዋል፡፡
Via:- DW
@YeneTube @Fikerassefa
Via:- DW
@YeneTube @Fikerassefa
አዲስ አበባ ወደ ጎን እንዳትሰፋ የሚያደርግ የሕንፃ ከፍታ መጠንና ቁጥጥር ሕግ ሊወጣ ነው!
የአዲስ አበባ ከተማን የጎንዮሽ መስፋፋት ለመግታት ያለመ አስገዳጅ የሕንፃዎች ከፍታ መጠን ሕግና አፈጻጸሙን የሚቆጣጠር ደንብ፣ የከተማዋ አስተዳደር ሊያወጣ መሆኑን ምንጮች ገለጹ፡፡በቀጣዮቹ ጥቂት ሳምንታት ለከተማዋ ካቢኔ ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ይፀድቃል ተብሎ የሚጠበቀው ይኼ ሕግ፣ የአዲስ አበባ ከተማን ወደ ጎን መስፋፋት በመግታት ቀጣይ ዕድገቷ ወደ ላይ እንዲሆን ማድረግን ያለመ እንደሆነ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
ዝርዝር ዘገባው👇👇👇
https://telegra.ph/LatestPlan-02-02

#Coronavirus.
Updated 3hrs ago.
እስካሁን 14,531 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 305 ሰዎች ሞተዋል።
Via AFP
@YeneTube @FikerAssefa
Updated 3hrs ago.
እስካሁን 14,531 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 305 ሰዎች ሞተዋል።
Via AFP
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በቀጣዩ ወር መጀመሪያ ላይ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በዱባይ ሊወያዩ ነው።
በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ፥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከየካቲት 5 እስከ የካቲት 7 ቀን 2012 ዓመተ ምህረት ድረስ ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ከተውጣጡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር የሚወያዩበት መድረክ ተዘጋጅቷል። የመድረኩ ተሳታፊዎች በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ ግንዛቤ የሚያገኙበት ብቻ ሳይሆን ዜጎች በየሚኖሩባቸው ሀገራት መብትና ክብራቸው ተጠብቆ እየኖሩ በሀገራቸው ውስጥ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የለውጥ ሂደትም ተሳታፊ ሊሆኑ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ውይይት እንደሚያደርጉ ኤምባሲው አስታውቋል።
በዚህ መድረክ ላይ ከሳዑዲ አረቢያ፣ ሊባኖስ፣ ኩዌት፣ ኦማን፣ ካታር እና ባህሬን የተውጣጡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ይሳተፋሉም ብሏል።ህዝባዊ መድረኩ ስኬታማ እንዲሆን በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሚገኙ የአቡዳቢ ኤምባሲ እና የዱባይ ቆንስላ ፅህፈት ቤት የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመፍጠር ሰፊ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑ ተመልክቷል።በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተደራጅተው የዝግጅቱ አካል በመሆን እየሰሩ እንደሚገኙ ኤምባሲው ገልጿል።
ምንጭ: ፋና

ያለወቅቱ የምርጫ ቅስቀሳ የሚያደርጉትን በመለየት ስርዓት ለማስያዝ እንደሚሠራ ምርጫ ቦርዱ አስታውቋል፡፡
ከሰሞኑ አብሮነት ለኢትዮጵያ ፌደራላዊ አንድነት ፓርቲ “ምርጫ መካሄድ ያለበት መቼ ነው?” በሚል ባወጣው መግለጫ የምርጫ ጊዜው ከመወሰኑ በፊት መንግስት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ድርድር ማካሄድ እንዳለበት ጠይቋል፡፡ “ድርድሩ ምርጫ ቦርድን የሚመለከት አይደለም” ያሉት የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ ፓርቲዎች መደራደር ያለባቸው ከመንግስት እና ከፓርላማ ጋር እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡
ቦርዱ ተጠሪነቱ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመሆኑ ድርድሩን ተቀብሎ እና አሻሽሎ ካመጣው ምርጫ ቦርድ ተግባራዊ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡ ምርጫ ቦርድ በቅርቡ ያፀደቀውን የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ አዋጅ 1162/2011ን መሠረት አድርጎ የምርጫ ማስፈፀሚያ ደንቦችን እና መመሪያዎችን እያወጣ ነው፡፡ ይህንን ተከትሎም ከ70 በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተቃወሙትን አዋጅ መሠረት አድርጎ ምርጫ ቦርድ የሚያወጣውን የማስፈፀሚያ ደንብና መመሪያ እንዲያቆም ፓርቲዎች ጠይቀዋል፡፡
‹‹አዋጁ የፀደቀበትን ሂደት ከቦርዱ ባልተናነሰ መንገድ ፓርቲዎቹም›› ያውቁታል ያሉት ምክትል ሰብሳቢው ረጅም ጊዜ ተወስዶ እና በርካታ ውይይቶች ተደርገውበት በመጨረሻ በፓርላማ የፀደቀ አዋጅ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ አዋጅ ሆኖ ከወጣ በኋላ በሌላ አዋጅ እስኪሻሻል ድረስ ደግሞ ምርጫ ቦርድ ምርጫውን ለማስፈፀም እና ፓርቲዎችን ለማስተዳደር ይጠቀምበታል፡፡
“የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድም በህግ የተሰጠውን ኃላፊነት እና ግዴታ ለመፈፀም ከማንም ይሁንታ ማግኘት የለበትም” ነው ያሉት አቶ ውብሸት ከአሜሪካ ድምፅ ጋር በነበራቸው ቆይታ፡፡ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን እና የሃገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት የምርጫ ማስፈፀሚያ መርሃ ግብር መዘጋጀቱንም ምክትል ሰብሳቢው አስታውቀዋል፡፡ የጋራ መግባባት እና ስምምነት እንዲኖርም በዚህ ሳምንት ከሁሉም የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ጋር ውይይት ያደርጋል ነው ያሉት፡፡፡
በቀጣይም የመንግስት አካላትን፣ ሲቪክ ማኅበራትን፣ ታዋቂ ግለሰቦችን እና የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ ውይይት እንደሚኖር አቶ ውብሸት አስታውቀዋል፡፡ ያለወቅቱ የሚደረግ የምርጫ ቅስቀሳን በሚመለከት ቦርዱ ያለውን እይታ በተመለከተም ጥያቄ ቀርቦ ነበር፡፡ አቶ ውብሽት ሲመልሱም “በምርጫ ቦርድ ከሚሰጠው ጊዜ ውጭ የሚደረግ ቅስቀሳ መቆም አለበት” ነው ያሉት፡፡
ቦርዱ ጥናት አድርጎ እና ለይቶ ስርዓት ለማስያዝ ይሰራልም ብለዋል፡፡ “የምርጫ ህጉን ማስፈፀም በአዋጅ የተሰጠው ለምርጫ ቦርድ ነው፤ ቦርዱ ፓርቲዎችን ሊያማክር ይችላል፤ ወሳኙ ፓርቲው በመሆኑ ‘የሰጠነው ሃሳብ ሁሉ አልተካተተም’ በሚል በፓርቲዎች የሚቀርብ ቅሬታ ተገቢነት አይኖረውም” ነው ያሉት ምክትል ሰብሳቢው፡፡
Via AMMA

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው እለት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመገኘት ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባውን ዛሬ ከሰዓት ያካሂዳል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።ምክር ቤቱ በስብሰባው የ11ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለጉባኤን መርምሮ እንደሚያጸድቅ ፋና ብሮድካስትንሽ ኮርፖሬት ዘግቧል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
ከኖቭል ኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የተሰጠ ወቅታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ!
የዓለም ጤና ድርጅት የኖቭል ኮሮና ቫይረስ በሽታ ከታሕሳስ 21, 2012 ዓ.ም. ጀምሮ በቻይና ዉሃን (Wuhan) ግዛት የተከሰተ መሆኑን አሳውቋል፡፡ በድርጅቱ ሪፖርት መሰረት ይህ በሽታ ከተከሰተበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥር 24, 2012 ድረስ ከ 23 ሀገራት በጠቅላላ 14, 557 ታካሚዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሪፖርት ያደረጉ ሲሆን ከቻይና ውጪ ያሉ አገራት 146 በቫይረሱ የተጠቁ ታካሚዎችን ሪፖርት አድርገዋል፡፡
ሙሉ መግለጫ👇👇👇
https://telegra.ph/Corona-02-03