YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) በቅርቡ በአባልነት የመዘገበው ጃዋር መሐመድ ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ ነው ሲል ፓርቲው ተናገረ። #Ethiopia
@YeneTube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በ2012 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት 338,253 ሜትሪክ ቶን ምርቶችን በ17.52 ቢሊዮን ብር አገበያየ፡፡

አጠቃላይ የግብይቱ መጠን ከእቅዱ አምስት በመቶ፣ ካለፈው በጀት ዓመት በ28 በመቶ ብልጫ አለው፡፡ የግብይቱ ዋጋም ከእቅዱ 13 በመቶ፣ ከቀደመው በጀት ዓመት በ22 በመቶ ከፍ ብሏል፡፡ በእነዚህ ወራት ከተገበያየው ምርት መጠን ውስጥ ቡና 45 በመቶ፣ ሰሊጥ 31 በመቶ፣ አኩሪ አተር 10 በመቶ፣ አረንጓዴ ማሾ 8 በመቶ፣ ነጭ ቦሎቄ 5 በመቶ ድርሻ አላቸው፡፡

ከዚህ ግብይት ውስጥ ባለፈው ዓመት ሥራ በጀመሩት በሀዋሳ ኤሌክትሮኒክ የግብይት ማዕከል ብር 45 ሚሊየን ግምት ያለው ቡና እንዲሁም በሁመራ ኤሌክትሮኒክ የግብይት ማዕከል ደግሞ ብር 124 ሚሊየን ግምት ያለው ሰሊጥ ግብይት ተፈጽሟል፡፡

Via ECX
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የፊታችን ሰኞ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ ይሰጣሉ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህዝብ ግንኙነት እንዳስታወቀው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፊታችን ሰኞ ጥር 25 ቀን 2012 ዓ.ም ከሰዓት ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ በምክርቤቱ በመገኘት ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ፡፡በመድረኩም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመንግስት ስራዎች አፈጻጸም፣ወቅታዊ ጉዳዮች እና ሌሎች አጀንዳዎች ዙሪያ ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሏል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ተቋማዊ ነጻነታቸውና ገለልተኝነታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ በቅርቡ የሚካሄደውን ሃገር አቀፍ ምርጫ አስመልክቶ ቅድመ ዝግጅት ለማድረግና በዓዋጁ ድንጋጌዎች ላይ የጠራ ግንዛቤ ለመያዝ የጋራ ውይይት አደረጉ፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ወ/ሮ ብርቱካን ሚደቅሳ ከዚህ ቀደም በፍትህ ስርዓቱ ካሳለፉት ታርክ አኳያ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ በመሆን በፍርድ ቤቱ መገኘታቸው ልዩ ስሜት እንዳሳደረባቸው ገልጸው ስብሰባውን ጀምረዋል፡፡
ሁለቱ ተቋማት በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ አዳራሽ ያካሄዱት የጋራ ውይይት በምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ ቁጥር 1162/2011 ይዘትና አፈጻጸም፤ ወደ ፍርድ ቤት ሊቀርቡ በሚችሉ ጉዳዮች ዓይነትና ባህሪያት፤ የምርጫና ተያያዥ ጉዳዮችን የሚመለከቱ ችሎቶች ስለሚደራጁባቸው አግባብ እና የዳኞች ስልጠና ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ፍርድ ቤቶች ከምርጫ ጋር ተያይዞ ለሚቀርቡላቸው አቤቱታዎች የሚሰጧቸው ውሳኔዎች የህዝብ አመኔታ እንዲኖራቸው፤ በተለይም ከምርጫ ድምጽ ቆጠራና ውጤት ጋር ተያይዞ ወደ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚቀርቡ አቤቱታዎች በአጭር ጊዜ ውሳኔ ስለሚያገኙበትና የምርጫውን ሂደት ፍትሃዊነት የሚያረጋግጡ እንዲሆኑ ሊወሰድ ስለሚገባ ጥንቃቄ በሰፈው ተወያይተዋል፡፡በመጨረሻም በምርጫ አፈጻጸምና ጉዳዮች ላይ ሰፊና የተሻለ ልምድ ካላቸው የአፍሪካ ሃገራት ዳኞችና የምርጫ አስፈጻሚዎቸ ከፍርድ ቤት ሚና አንጻር መልካም ተሞክሮ የሚቀስሙበት ሁኔታ እንዲመቻች አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቃል፡፡

ምንጭ:የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
@YeneTube @FikerAssefa
"በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ በዋሽንግተን ዲ.ሲ. ከማክሰኞ ጥር 19 ጀምሮ በመካሄድ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ: የግብጽና የሱዳን ውይይት ዛሬም ለ4ኛ ቀን ቀጥሏል:: ስብሰባው ባለመጠናቀቁ ከማክስኞ ወዲህ የወጣ ምንም አይነት የጋራ መግለጫ የለም!

ኢትዮጵያ በውሃው የመጠቀም መብቷን አሳልፎ የሚሰጥ ምንም አይነት ስምምነት አትፈጽምም:: "

-አምባሳደር ፍፁም አረጋ
@YeneTube @FikerAssefa
ቡሌ ሆራ ዩንቨርስቲ በአስራት ቴሌቭዥን የተሳሳተ ዘገባ ተሰርቶብኛል አለ!

<<አስራት ቴሌቪዥን ጥር 21/2012 ዕለት ከሰራቸዉ ዘገባዎች ዉስጥ "የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ" ከሚል ርዕሰ አንቀፅ ጋር የተቋሙን ሎጎ በመለጠፍ "በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የአማራ ተማሪዎች አድራሻ መጥፋት" የሚል ንዑስ አንቀፅ በማከል
"ስድስት የአማራ ተወላጅ ተማሪዎች አድራሻ መጥፋቱ ተገልጿል" በማለት የዘገበ ሲሆን፤ ለመረጃ ምንጭነት የተጠቀመው አንድ ተማሪ መሆኑ ያልተረጋገጠ ነገር ግን እንደ ተማሪ በስልክ ያነጋገረው አካልን ሆኖ ስለ መረጃዉ ተአማኒነት ብሎም እንደ አንድ የሚዲያ ተቋምነቱ ሚዛናዊ የሆነ መረጃ ለህዝቡ ለማድረስ የሚመለከታቸውን አካላት አግኝቶ ሳያናግር፤ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ አሁን ካለበት ነባራዊ ሁኔታ አንፃር በምንም አይነት መሥፈርት ተቀባይነት የሌለውን የተበላ ዕቁብ አይነት የሀሰት ዘገባ አሰራጭቷል።

በተጨማሪም የዚህ ዘገባ የዉሸት ዘገባ መሆኑ ማሳያ በእህት የደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ታገቱ ከተባለዉ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ትላንት ማታ በመንግሥት በኩል በሦስትዮሽ ጥምረት በተሰጠዉ መግለጫ ማግስት መሆኑ፤ ያ እቅድ የከሸፈ ይመስላል።ጉዞዉ በሀሰተኛ እና የእዉነት መሠረት በሌለዉ ብሎም ሚዛናዊነቱን ባልጠበቀ መልኩ በመዘገብ እና በማሰራጨት ኢ-ፍትሃዊ የሆነ ስራቸዉን ለማየት መንቀሳቀስ ሆነ። በመሆኑም በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ ዘገባ ጋር ተያይዞ ምንም ዓይነት ክስተት እንደሌለ ለማስገንዘብ እንወዳለን።

እኛም እየሰራን ነዉ!
ተማሪዎቻችንም ትምህርታቸውን እየተማሩ ነዉ! ቤተሰቦችም ስጋት አይግባችሁ!

ከዚያ ባለፈ ግን ህዝብንና ሀገርን በዉሸት ዘገባ ሰላምና እረፍት በሚነሱ የሚዲያ ተቋማት ላይ በህግ የማስጠየቅ እና የህግ የበላይነትን በማክበር የሚዲያ ሃላፊትን ተላብሰዉ እንዲሰሩ የምንሰራ መሆኑን በመግለፅ ጭምር ነዉ።መንግሥት በነዚህ አይነቶች እና ሃላፊነት በጎደለዉ መልኩ የሀሰት እና ሚዛናዊነት የጎደለዉ መረጃ በሚያሰራጩ ሚዲያዎች ላይ አትኩሮት በመስጠት ሀይ ሊላቸዉ እንደሚገባ እንጠይቃለን ።>>

-ቡሌ ሆራ ዩንቨርስቲ
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) በቅርቡ በአባልነት የመዘገበው ጃዋር መሐመድ ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ ነው ሲል ፓርቲው ተናገረ። #Ethiopia @YeneTube @Fikerassefa
አቶ ጃዋር መሐመድ የኢትዮጵያ ዜግነት ማግኘታቸውን አስታወቁ!

በታኅሳስ ወር የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስን መቀላቀላቸውን ያስታወቁት ጃዋር መሐመድ ረቡዕ ጥር 13/2012 ለኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና የወሳኝ ኩነት የሚጠበቅባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት የኢትዮጵያ ዜጋ መሆናቸውን ጠበቃቸው ለአዲስ ማለዳ ተናገሩ። የጃዋር መሐመድ ጠበቃ የሆኑት ገመቹ ጉተማ፤ ጃዋር በዜግነት አዋጁ የሚጠበቅባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላታቸውን እና በዚህም መሰረት ለሚመለከተው አካል ማስገባታቸውን ገልፀዋል። ‹‹በሕጉ መሰረት ዜግነትን መልሶ ለማግኘት የምንጠብቀው ምንም ዓይነት መልስ የለም። አስፈላጊ ሰነዶችን ግን አስገብተናል›› ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
የኮሮና ቫይረስ መነሻ በሆነችው በቻይናዋ ውሐን ግዛት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን መንግሥት ወደ ሀገራቸው እንዲመልሳቸው እንደጠየቁ አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡ በግዛቲቷ ትምህርት ላይ ያሉ 300 ኢትዮጵያዊያን በማኅበራቸው በኩል ጥያቄውን ያቀረቡት ቻይና ላለው ኢምባሲ ነው፡፡ ተማሪዎቹ የምግብ ዕጥረት ስጋትም አለባቸው፡፡ ሆኖም እስካሁን በቫይረሱ የተያዘ ኢትዮጵያዊ የለም፡፡
@YeneTube @Fikerassefa
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በወንዶ ገነት ካምፓስ የጄኔራል ፎረስትሪ ት/ክፍል 3ኛ ዓመት ተማሪ የሆነው በርዬ አወቀ አበበ በድንገተኛ ሕመም ሕይወቱ ማለፉን ዩኒቨርሲቲው ገልጾ ለቤተሰቡ፣ ለዘመዶቹ እና ለጓደኞቹ መጽናናትን ተመኝቷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በኮሮና ቫይረስ የሙቱ ሰዎች ቁጥር 213 የደረሰ ሲሆን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 10,000 ተጠግቷል።

ምንጭ: አጃንስ ፍራንስ ፕረስ
@YeneTube @FikerAssefa
በጋሞ ዞን በደረሰ የመሬት ናዳ የአራት ሰዎች ህይወት አለፈ!

በደቡብ ክልል ጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ ልዩ ስሙ ጋፀ ቀበሌ ዛሬ በደረሰ የመሬት ናዳ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን የዞኑ ፖሊስ አስታወቀ።የጋሞ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ሬታ ተክሉ እንደገለጹት፣ አደጋው የተከሰተው በአካባቢው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ መጣሉን ተከትሎ የመሬት ናዳ በመድረሱ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት መረጃ ያመለክታል።
በአደጋው ህይወታቸውን ካጡት በተጨማሪ ሁለት ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

እንዲሁም 12 የቤት እንስሳት ሲሞቱ በ13 አባወራ የሚገኙ 69 የቤተሰብ አባላትም ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን የገለጹት የዞኑ ፖሊስ አዛዥ በ30 ሄክታር መሬት ላይ የሚገኝ የመኸር ሰብልም ከጥቅም ውጭ መሆኑን አስረድተዋል።በአደጋው የተፈናቀሉ ሰዎች በቀበሌው በሚገኝ ትምህርት ቤት ተጠልለዋል።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
በሞጣ ለተጎዱ ሙስሊሞች ድጋፍ ማሰባሰቢያ ባንክ ቁጥር ለጠየቃችሁን የቻናላችን ቤተሰቦች እኚን አካውንቶች መጠቀም ትችላላችሁ።

@YeneTube @Fikeeassefa
Just In!

ብሪታንያ በይፋ ከአውሮፓ ህብረት መውጣቷን ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን አረጋግጠዋል።ሀገሪቱ ላለፉት 47 አመታት የህብረቱ አባል ሆና ቆይታ ነበር።

@YeneTube @FikerAssefa
#Update ኮሮና ቫይረስ

- 259 ሰው በቫይረሱ ተጠቅተው ሞተዋል

- 1800 ሰዎች በከባድ ሁኔታ ላይ ናቸው።

- ወደ 12,000 የሚጠጉ በቫይረሱ ተጠቅተዋል።
@YeneTube @Fikerassefa
Reports that the Embassy is is not doing any thing is untrue. From the very beginning of the declaration of the nCOV, the 4 Ethiopian missions in China are working with student bodies in Wuhan and other universities.The government is also following the matter very closely.

Via:- Ambassador Teshome Toga
@YeneTube @Fikerassefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የታላቁ ህዳሴ ግድብን እየጎበኙ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው የግድቡ የሲቪል ምህንድስናም ሆነ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራው ያለበትን ሁኔታ የሚቃኙ ይሆናል::

Via:- ኢ.ዜ.አ
@YeneTube @Fikerassefa
በሞጣ ለተጎዱ ሙስሊሞች ድጋፍ ማሰባሰቢያ ባንክ ቁጥር ለጠየቃችሁን የቻናላችን ቤተሰቦች እኚን አካውንቶች መጠቀም ትችላላችሁ።

@YeneTube @Fikeeassefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ግብጽ በአሁኑ አቋሟ የምትቀጥል ከሆነ የታላቁ ህዳሴን ግድብ አሞላል እና አጠቃቀምን በተመለከተ ስምምነት ላይ ለመድረስ ረጅም ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል በዮናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ አምባሳደር ጠቆሙ። አምባሳደር ፍጹም አረጋ ይሄን የገለጹት ለሶስት ቀናት የፈጀው እና ሶስቱ ሀገራት በሚኒስትር ደረጃ ሲያደርጉት የነበረው ድርድር ማብቃቱን አስመልክቶ ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ ነው።

የሀገራቱ ድርድር የመጨረሻ የስምምነት ሰነድ እንዲዘጋጅ ለቴክኒክ እና ህግ ባለሙያዎች ትዕዛዝ መሰጠቱ ይፋ በሆነበት በአሁኑ ሰዓት አምባሳደሩ ግብጽ ፈጣን ስምምነት ላይ እንዲደረስ ፍላጎት እንዳላት ብታሳይም፣በዝርዝር ጉዳዮች ላይ ያላት አቋም ግን የሚፈለገውን ስምምነት እንዳያዘገየው እንደሚሰጉም ጠቁመዋል።አምባሳደር ፍጹም አረጋ ከVOA ጋር ያደረጉትን አጭር ቆይታ እንስማ።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
የሠንሻይን ኮንስትራክሽን መስራች እና ባለቤት አቶ ሳሙኤል ታፈሰ ከአንጋፋው የአሜሪካ ሊንከን ዪንቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ተሰጣቸው።

ዩንቨርሲቲው ለአቶ ሣሙኤል የክብር ዶክትሬት ድግሪ የሰጠው በኮንስትራክሽን እና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋፅዖ ነው።ከ30 አመት በፊት የመሠረቱት ድርጅታቸው የአሜሪካው ሊንከን ዪንቨርሲቲ በካሊፎርኒያ ኦክላንድ የሚገኝ ሲሆን ከተመሠረተ 100 አመቱ ነው። በኢትዮጵያም ዌስተረን ዪንቨርሲቲ ከተሰኘ ኮሌጅ ጋር በኢትዮጵያ በተለያዪ የትምህርት መስኮች በማስተማር ላይ ይገኛል።ድርጅታቸው ከ6ሺህ በላይ ዜጎች የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን በርካታ ወገኖችንም በተለይ ወለጅ ያጡ ህፃናትን ትምህርት እንዲያገኙ ድጋፍ በማድረግ ይታወቃል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ከፈረንሳይ ፓርክ እስከ ፈረንሳይ አቦ ድረስ ያለው መንገድ ግንባታ ተጀመረ።

ኢ/ር ታከለ ኡማ የመንገዱን ግንባታ ተመልክተዋል።የመንገዱ ግንባታ የረጅም አመታት የአካባቢው ነዋሪዎች ጥያቄ የነበረ ነው።መንገዱ 1.2 ኪ.ሜትር የሚረዝም ሲሆን 15 ሜትር የጎን ስፋት እንዲኖር ተደርጎ የሚገነባ ይሆናል።ኢ/ር ታከለ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር የተወያዩ ሲሆን የተለያዩ የመሰረልማት ጥያቄዎች እና ከመንገዱ ግንባታ ጋር በተያዘዘ የወሰን ማስከበር ጥያቄዎች ተነስተውላቸዋል።

የተነሱ የውሀና የመብራት ጥያቄዎች አፋጣኝ መፍትሄ እንደሚያገኙ እንዲሁም የወሰን ማስከበር ጥያቄዎችም ተገቢው ምላሽ እንደሚሰጥ ኢ/ር ታከለ ኡማ ተናግረዋል።የአካባቢው ነዋሪዎች ኢ/ር ታከለ ከቀናት በፊት ቃል በገቡት መሰረት የመንገዱ ግንባታ በፍጥነት በመጀመሩ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው የከተማ አስተዳደሩ ችግሮችን ለመፍታት እያሳየ ላለው ጥረት አመስግነዋል።

Via Mayor Office
@YeneTube @FikerAssefa