YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.89K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ትናንት ምሽት አመታዊው የግራሚ ሽልማት ስነስርዓት ተካሂዷል!

በሙዚቃው ኢንዱስትሪ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠው የአካዳሚ ግራሚ ሽልማት ስነስርዓት ትናንት ምሽት የተካሄደ ሲሆን በትናንትናው እለት በሄሊኮፕተር አደጋ ህይወቱን ያጣውን የቅርጫት ኳስ ኮከብ ኮቤ ብሪያንን በማሰብ የተጀመረው ፕሮግራም ወጣቷ የፖፕ አቀንቃኝ ቤሊ ኤሊሽ ዋና ዋና በሚባሉት ዘርፎች አሸናፊ አርጓታል ።ከዚህ በታች ዋና ዋና በሚባሉት ዘርፎች ያሸነፉትን ዘፋኞች ዝርዝር እንደሚከተለው አቅርበናል:

📌የአመቱ ምርጥ አልበም: ቢሊ ኤሊሽ "When we all fall asleep, Where do we go?"

📌ምርጥ ጀማሪ አርቲስት: ቤሊ ኤሊሽ

📌ምርጥ የራፕ ፔርፎርማንስ: ዲጄ ካሊድ በኒፕሲ ሃስል እና ጆን ሌጀንድ ታጅቦ "Higher"

📌ምርጥ ዘፈን: ቤሊ ኤሊሽ "Bad Guy"

📌ምርጥ የራፕ አልበም: ታይለር ዘ ክሪኤተር "IGOR"

📌ምርጥ ኮሜዲ አልበም: ዴቭ ቻፔል "Sticks and Stones"

📌ምርጥ የጣምራ ፔርፎርማንስ:ዳን እና ሻይ "Speechless"
.
.
.
ስነስርዓቱ በኮቤ ብሪያን ያልተጠበቀ ህልፈት ብዙ ትኩረት ማግኘት ባይችም አሪያና ግራንድ፣ አሸር፣ እንዲሁም ዲጄ ካሊድ ስራቸውን መድረክ ላይ በማቅረብ አድምቀውታል።የመድረክ መሪዋ ደግሞ አሊሻ ኪስ ነበረች።

@YeneTube @FikerAssefa
"የኮሮና ቫይረስ ወደ አገር ውስጥ እንዳይገባ ለመከላከል በቦሌ ዓለምአቀፍ አየር ማረፊያ የተሟላ ምርመራ እየተደረገ ነው " የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ
በቻይና የተከሰተው "የኮሮና" ቫይረስ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ ቀድሞ ለመከላከል የተለየ የምርመራ ክፍል ተዘጋጅቶ በተሟላ የምርመራ መሳሪያ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገለጹ፡፡

በቻይና የተከሰተው "የኮሮና" ቫይረስ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ ለመከላከል በቦሌ ዓለምአቀፍ አየር ማረፊያ ወደ አገር ውስጥ ለሚገቡ ተጓዦች ምርመራ እየተደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የማህበረሰብ ጤና ቁጥጥር ባለስልጣን ከኢትዮጵያ የማህበረሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ጋር በመተባበር ከቻይና እና የበሽታው ምልክት ከታየባቸው አገራት የሚመጡ ተጓዦች ምርመራ የሚደረግበት የተለየ ክፍል ተዘጋጅቶ የተሟላ የምርመራ አገልግሎት እየተከናወነ እንደሚገኝ ምክትል ከንቲባው አመልክተዋል፡፡

ምንጭ:- ከንቲባ ፅ/ቤት
@YeneTube @Fikerassefa
በሀረሪ ክልል በጥምቀት በዓል አከባበር ላይ ተፈጥሮ ከነበረው ሁከት ጋር ተያይዞ የተጠረጠሩ 87 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ።

ከበአሉ አከባበር ጋር የተፈጠረው የፀጥታ ችግር ከሐይማኖትም ሆነ ከብሔር ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው ቢሮ አያይዞ ገልጿል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ናስር ዩያ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት ባሳለፍነው ሳምንት ከጥምቀት በአል አከባበር ጋር ተያይዞ ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ ችግር በሰው እና ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።

ድብቅ የፖለቲካ አላማ ያላቸው አካላት በፈጠሩት የፀጥታ ችግር ምክንያትም የአንድ ሰው ህይወት ማለፉንና ሰባት ሰዎች መቁሰላቸውን ጠቁመዋል።

በተጨማሪም የ11 ህንፃዎች መስታወት የተሰባበረ ሲሆን አንድ የኮካኮላ ማከፋፈያና አንድ ተጨማሪ ህንፃ መቃጠላቸውን ገልጸዋል።

ሁለት መኪኖች እና አራት ባጃጆች ጭምር በሀከቱ መቃጠላቸውን ኃላፊው ተናግረዋል።

Via:- EBC
@YeneTube @FikerAssefa
በአፍጋኒስታን የመንገደኞች አውሮፕላን ተከሰከሰ

በምሥራቅ አፍጋኒስታን አንድ የመንገደኞች አውሮፕላን መከስከሱን ባለስልጣናት ገለጹ።
ከዋና ከተማዋ ካቡል ደቡብ ምዕራብ በምትገኘው የጋዝኒ ግዛት ውስጥ ደህ ያክ በተባለ ቦታ አውሮፕላኑ መከስከሱን የአካባቢው ቃል አቀባይ ተናግረዋል።

ቃል አቀባዩ አክለውም አውሮፕላኑ በቴክኒክ ችግር ምክንያት መከስከሱንና በእሳት መያያዙን ገልጸዋል።

መጀመሪያ ላይ አውሮፕላኑ ዘ አሪያና የተባለው አየር መንገድ ንብረት እንደሆነ ቢነገርም በኋላ የወጡ መረጃዎች ደግሞ አየር መንገዱ አውሮፕላኑ የእኔ አይደለም ማለቱን የሚያትቱ ናቸው።

"የአሪያና አውሮፕላኖች ሁሉም በሰላም ደርሰዋል። ይህ ማለት የተከሰከሰ የአሪያና አውሮፕላን የለም ማለት ነው" ይላል ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በወጡ መረጃዎች።
አውሮፕላኑ በእሳት መያያዙም እየተነገረ ነው። ለጊዜው የተጎጂዎች ማንነትም ሆነ ቁጥር አልተገለጸም።

ምንች:- ቢቢሲ
@YeneTube @Fikerassefa
“የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና የፌደራል መንግስት በታገቱ ሴት ተማሪዎች ዙሪያ ቸልተኝነት አሳይተዋል” የምዕራብ ጎጃም ዞን ዞኑ ከደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲመለሱ በታገቱ ተማሪዎች ዙሪያ ዛሬ ከስዓት መግለጫ ሰጥቷል።

ከታገቱት ተማሪዎች ውስጥ 5ቱ የዞኑ ተወላጆች መሆናቸውን ከወላጆቻቸው ማረጋገጥ መቻሉን ያስታወቀው የምዕ/ጎጃም ዞን፣ የአማራ ክልላዊ መንግስት በፌደራልና በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ላይ ጫና እንዲፈጥር ግፊት እያደረገ እንደሚገኝ ጠቁሟል፡፡

Via:- ELU
@YeneTube @Fikerassefa
የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ደምቢዶሎ ዩንቨርስቲ እየመከሩ ይገኛሉ።

በሰላም ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል የተመራው የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ቡድን ከደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ እና ከአካባቢው ማኅበረሰብ፣ ከጸጥታ አካላት እና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር እየተወያየ መሆኑን አማራ ማስ ሚዲያ ዘግቧል።

ጋዜጠኞችም አብረው እንደተጓዙ ከELU ተመልክተናል።
@YeneTube @Fikerassefa
የታገቱ ተማሪዎችን በተመለከተ 5 በሰብዐዊ መብቶች እንዲሁም በሴቶች ጉዳይ ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች መግለጫ አውጥተዋል።

#Bringbackourhgirls
#Bringbackourhgirls
#Bringbackourhgirls
#Bringbackourhgirls
@YeneTube @Fikerassefa
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በታገቱ ተማሪዎች ጉዳይ ማብራሪያ እንዲሰጡ ዓለም አቀፍ የአማራ ህብረት ጠየቀ።

ዓለም አቀፍ የአማራ ኅብረት የአደረጃጀት ጉዳይ ተጠሪ አቶ ደህናሁን እምሩ እንደገለጹት በፀጥታ ስጋት ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲመለሱ የታገቱ የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጉዳይ እልባት ሊሰጠው እንደሚገባ ጠይቀዋል፡፡ ዓለም አቀፍ የአማራ ኅብረት ድርጊቱን እንደሚያወግዘውም ነው የተናገሩት፡፡ የተማሪ ወላጆችና ሕዝቡ እየተጨነቁ ባሉበት በዚህ ወቅት መንግሥት ዝምታን መምረጡ ተገቢነት የለውም ብሏል ኅብረቱ፡፡

ስለ ጉዳዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ማብራሪያ ሊሰጡ እንደሚገባም ጠይቋል፡፡ መንግሥት ተማሪዎቹ ተለቅቀዋል ብሎ ከዚህ ቀደም መግለጫ ስለሰጠበት ጉዳይም በአደባባይ ለሕዝብ ማሳወቅ እንዳለበት አቶ ደህናሁን ተናግረዋል፡፡ ኅብረቱ በታገቱ ተማሪዎችና እየደረሱ ባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ በዋሽንግተን ዲሲ ትናንት ሲመክር መቆየቱንም አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ:- አብመድ
@YeneTube @Fikerassefa
የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ የነባር ተማሪዎች የ1ኛ ሴሚስተር ማጠቃለያ ፈተና ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን እና የ1ኛ ዓመት ተማሪዎች መደበኛ የመማር ስራ ለጊዜው የተቋረጠ መሆኑን አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮምያ በተለያዩ ዞኖች ቅዳሜና እሁድ ብቻ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ደጋፊዎች የሆኑ ቢያንስ 75 የሚጠጉ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አረጋግጧል፡፡

⬇️⬇️ዘገባውን ይመልከቱ ⬇️⬇️


https://www.amnesty.org/en/latest/news/2020/01/ethiopia-authorities-crack-down-on-opposition-supporters-with-mass-arrest
የተጠራው ሰልፍ ፍቃድ አግኝቷል...

በኦሮምያ ክልል ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች የታገቱን የዩንቨርስቲ ተማሪዎችን ድርጊት ለማውገዝ የተጠራው ሰልፍ ተፈቅዷል።

#ሼር #Share
#Amharapolicecommission
@YeneTube @Fikerassefa
ቄሮ ቢልሱማ ኦሮሞ በኦነግ የፌስቡክ ገጽ ጠጠር ያለ ማስጠንቀቂያ አውጥቷል

"በምዕራብ ኦሮሚያ 4 የወለጋ ዞኖች፣ በደቡብ ኦሮሚያ 2 የጉጂ ዞኖች "የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈጸመ ነው" –በአንድ ቀን 89 ሰዎች ተገድለዋል (ቀኑና ቦታው አልተጠቀሰም)

ቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ "ከመላዉ ኦሮሚያ የህዝባችንን ምርት ጭነዉ ወደ ትላልቅ ከተሞች የሚጓዙ ተሸከርካሪዎች ፍንፍኔን ጨምሮ አቅርቦት ማቅረብ እንዳይችሉ እስከማገድ ደረስ የተለያዩ እርምጃዎችን ለመዉሰድ መዘጋጀት ይኖርብናል" የሚል ጥሪ አቅርቧል።

"በሌላዉ የኦሮሞ ኣከባቢዎች ምንም እዉነተኛነትና ህጋዊ መሰረት ለሌላዉ ምርጫ ምረጡኝ በማለት የህዝቡን ትኩረት የሚበትኑ የፖለቲካ ቡድኖች ሚና የኦሮሞን ህዝብ ከፋፍሎ የማስመታት ዘመቻ ኣካል እንደሆነ እያየን ነዉ" ሲል ቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ ከሷል።

ምንጭ:- Eshete Bekele
@YeneTube @Fikerassefa
አዲስ የተመሰረተው የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ ሊቀ መንበር የነበሩት አበባየሁ ቶራ (ዶ/ር) በኃይለሚካኤል ለማ መተካታቸውን ፓርቲው አስታወቀ።

@YeneTube @Fikerassefa
#ሴታዊነት

አለኝታ ነፃ የስልክ መስመር ፤ ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃት ላይ የስነ-ልቦና ምክር፣ መረጃ እንዲሁም የሪፈራል አገልግሎት በየትኛውም ፆታ እና እድሜ ክልል ውስጥ ላሉ ደዋዮች ይሰጣል፡፡ በፆታዊ ጥቃት ዙርያ መረጃ ወይንም የስነልቦና ድጋፍ የምትፈልግ/የሚፈልግ  ሰው በስራ ሰዓታችን (ከበዓል ቀናት ውጪ) ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡30 እስከ 10፡30 በ 6388 ደውለው አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ።

የአለኝታ ነፃ የስልክ መስመር አገልግሎቱን ከዛሬ ጥር 18,2012 ጀምሮ ስራ ጀምሯል።

#አለኝታ #alegnta #6388

@YeneTube @Fikerassefa
በተማሪዎች ላይ የተፈጸመውን የእገታ ድርጊት የሚያወግዙ ሰላማዊ ሰልፎች በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ከተሞች እየተካሄዱ ነው፡፡

ሰላማዊ ሰልፎቹ በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩና የታገቱ ተማሪዎችን በተመለከተ መንግሥት ግልጽ መረጃ እንዲሰጥ፣ በአጋቾች ላይም እርምጃ በመውሰድ ሕግ የበላይነትን እንዲያረጋገጥ የሚጠይቁ ናቸው፡፡በባሕር ዳር እየተካሄደ በሚገኘው ሰልፍም የእገታ ድርጊቱ ኢ ሰብዓዊ እና ከኢትዮጵያዊነት እሴት ያፈነገጠ ነው ሲሉ ተሳታፊዎቹ ኮንነውታል፡፡መንግሥት የሕግ ጥሰት የፈጸሙ አካላትንም ተጠያቂ እንዲያደርግ ነው እየጠየቁ የሚገኙት፡፡

Via AMMA
Photo: ELU
@YeneTube @FikerAssefa
የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በከፍተኛ ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ ዩናይትድ ስቴትስንና ይህንን ጨምሮ በርካታ ሀገራት ዜጎቻቸውን ከቻይና ለማስወጣት ቻርተር አውሮፕላን እያዘጋጁ እንደሆነ አጃንስ ፍራንስ ፕረስ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa