YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በጀርመኗ ፍራንክፈርት ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የመስጊዶችን መቃጠል በመቃወም በዛሬው ዕለት አደባባይ መውጣታቸውን ከጅርመን ድምፅ ራዲዮ ተመልክተናል።

@YeneTube @Fikerassefa
ታግተው የነበሩ #21 የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መንግስት ባደረገው ጥረት መለቀቃቸውን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት አስታወቀ!

በደንቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ግጭት መከሰቱን ተከትሎ ወደ ቤተሰቦቻቸው በመሄድ ላይ የነበሩ ተማሪዎች ጫካ ውስጥ ታግተው መቆየታቸውን የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ለኢቲቪ ተናግረዋል።

በእገታ ላይ የነበሩትን ተማሪዎች በሰላማዊ መንገድ ያለምንም ጉዳት ለማስለቀቅ መንግስት ከአካባቢው የአገር ሽማግሌዎች ፣ ከወጣቶችና ከመከላከያ ሰራዊትና የፀጥታ መዋቅሮች ጋር ሲሰራ መቆቱን ኃላፊው አስታውቀዋል።

የሰላም ጥረቱ ፍሬ በማፍርቱ ታግተው ከነበሩ ተማሪዎች ውስጥ 13 ሴትና 8 ወንድ በድምሩ 21 ተማሪዎች በሰላማዊ ሁኔታ መለቀቃቸውን አቶ ንጉሱ አስታውቀዋል።

ይሁን እንጂ አሁንም ቀሪ #6_ተማሪዎች_በእገታ ላይ መሆናቸውን በአካባቢው የተሰማራው የፀጥታ ኃይል መረጃ መስጠቱን ተናግረዋል።

ታግተው ያሉ ቀሪ ተማሪዎችን ያለምንም ጉዳት እንዲለቀቁ ለማድረግ መንግስት ከአገር ሽማግሌዎችና የሐይማኖት አባቶች ጋር በመተባበር በአካባቢው ወግና ስርዓት ለማስለቀቅ እየሰራ መሆኑንም አቶ ንጉሱ ጥላሁን ለኢቲቪ ገልፀዋል።

መንግስትም በተከታታይ ከእገታ ያልወጡ 6 ተማሪዎችን ለማስለቀቅ እየተደረገ ያለውን ጥረት በየጊዜው ለህዝብ መረጃ እንደሚያደርስም አመልክተዋል።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEO_AwEACCqYXy4L9A. 👈🏾👈🏾👈👈👈 🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄
የተከበራችሁ የ SHOPIA®️ ቤተሰቦች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዐል በሰላም አደረሳችሁ ❤️ እያልን በዐሉን ምክንያት በማድረግ ከ 25/04/12(ቅዳሜ) ጀምሮ ለ 3 ተከታታይ ቀናት በቻናላችን በኩል በሚሸጡ ሁሉም ዕቃዎች ላይ 5-15%⬇️ ቅናሽ አድርገናል።🤗
🎉🛍 ይግዙ በዕድሉ ተጠቃሚ ይሁኑ ቅናሹ የሚቆየው እስከ በዐሉ ዋዜማ ድረስ ብቻ ነው🎁🛒

🎅🎄🎅🎄🎅🎄🎅🎄🎅🎄🎅
⭐️ መልካም የገና በዐል ⭐️
⭐️ SHOPIA ⭐️
🎅🎄🎅🎄🎅🎄🎅🎄🎅🎄🎅👇👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEO_AwEACCqYXy4L9A
BRANDED Items 👇👇👇👇👇

BOOK NOW🔥🔥🔥
Contact @kiru04
0931607806
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEPkyxEP1snCoAkFGw
💥ማስታወቂያ💥
School of American English

📌ቻይንኛ
📌ፈረንሳይኛ
📌ጀርመንኛ
📌ጣልያንኛ
📌አፋን ኦሮሞ
📌አረብኛ

አንቱታን ባተፈሩ መምህራን እናስተምራለን

አድራሻዎቻችን ⬇️
ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ +251919913021
ፒያሳ ፒያሳ ገበያ ማዕከል +251919913023
22 ጎላጎል ህንፃ 6ተኛ ፎቅ +251919913022


💥💥💥10% Discount 💥💥💥💥

ቅናሹን ለመጠቀም
ይህንን ፓስት screenshot አድርገው መያዝና ስመጡ ማሣየት ይኖርብዎታል

T.me/SCHOOLOFAMERICAN
ከአዲስ አበባ 270 KM የምትርቀው ሀዋሳ
ፎቶ ፍቅር ሀይቅ

-----መልካም ቀን ይሁንሎ-----
ስብሰባ ተከልክለን ደጅ ቆመናል ~ ስንታየሁ ቸኮል

የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክርቤት በፓርቲዎች ማቋቋሚያ አዋጅ 11/62 ለምርጫ ቦርድ ቅድመ ምስረታ የጠራዉ ጉባኤ በመንግስት ትህዛዝ ተከለከለ።

ዛሬ ጥር 3 2012ዓም በኢንተር ኮንትኔታል የስብሰባ ዝግጅት ቢኖረም ከላይ በመጣ ትህዛዝ በሚል በቅድመ ስምምነት የተከፈለ አዳራሽ ከህግ አግባብ ዉጪ በመንግስት ጥብቅ መመሪያ ተሰብሳቢዉ በመግቢያ በር ላይ ለመሰብሰብ ተገዷል።

Via:- ስንታየሁ ቸኮል
@YeneTube @Fikerassefa
"ምርጫው ላይ በሰላማዊ መንገድ እንሳተፋለን! አሁንም በሰላም ወደየቤታችን እንሂድ!" እስክንድር ነጋ

ኢንተር-ኮንቲኔንታል በር ላይ የነበረው ፕሮግራም ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠት ተጠናቋል።

Via:- ኤልያስ መሰረት
@YeneTube @Fikerassefa
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን፣ ጭልጋ ቁጥር አንድ ወረዳ ከቀናት በፊት ታግቶ የነበረ አንድ የ14 ዓመት ታዳጊ በአጋቾቹ ተገደለ። ታዳጊው ታህሳስ 27 ቀን ከአይከል ከተማ በታጣቂዎች የተወሰደ ሲሆን፣ ለማስለቀቂያ 100ሺህ ብር ተጠይቆበት ነበር።

ምንጭ:- ኢትዮጵያን ላይቭ አፕዴት
@YeneTube @Fikerassefa
SELL/BUY/ORDER/RENT EVERYTHING
SOFTWARE/WEB/GRAPHICS DESIGN
IT SUPPORT
STUDENT SCHOLARSHIPS/VISA's
Work with us GET PAID
📩 @CloudMultiTrading 📩
+1(617)580-0402 0944182119 +971586233799
📩 @CloudMultiTrading2 📩

Join our Channel⬇️
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEPkQuyukYp1DOpZEw
የታጋች ተማሪዎች ቤተሰቦች መረጃ እንዲሰጣቸው እየጠየቁ ይገኛሉ

የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሪተሪ ሃላፊ የሆኑት ንጉሱ ጥላሁን በምዕራብ ኦሮሚያ ታግተው ካሉ 27 ተማሪዎች መካከል 21ዱ ተለቀዋል ቢሉም የተማሪዎች ቤተሰቦች ግን ምንም አይነት መረጃ እንዳላገኙ ተናገሩ፡፡

አዲስ ማለዳ ካነጋገረቻቸው ቤተሰቦች መካከልም የተማሪ ግርማነሽ የኔነው አባት በሰሙት ዜና ደስተኛ ቢሆኑም ደስታቸው ግን አሁንም በብዙ ስጋት ውስጥ እንደሆነ ለአዲስ ማለዳ ተናገረዋል፡፡

‹‹የተለቀቁትን ልጆች ስም ዝርዝር ቢያሳዩ፣ አሊያም በፎቶ ቢያሳዩን ይሻል ነበር፡፡ የኛ ልጅ ከቀሩት መካከል ብትሆን በምን እናውቃለን?›› ሲሉ ስጋታቸውን ያጋራሉ፡፡ ከአዲስ ማለዳ ጋር በስልክ ቃለመጠይቅ ባደረጉበት ወቅትም ሊጠይቋቸው ለሚመጡ ጎረቤቶቻቸው ‹‹ተለቀዋል ፈጣሪ ይመስገን›› ሲሉ ሰምተናል፡፡ ‹‹በስልክ እንኳን ድምጿን አልሰማንም፤ እንደእናተው በቴሌቪዥን ነው ተለቀዋል ሲባል የሰማነው›› በማለት ጥርጣሬአቸውን ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም ሌሎች ሶስት ቤተሰቦችን በስልክ ያነጋገረችው አዲስ ማለዳ የልጆቻቸው ስልክ አሁንም እንደማይሰራ እና ምንም አይነት አዲስ መረጃ እንዳልደረሳቸው ተናግረዋል፡፡

በአራቱም የወለጋ ዞኖች ፀጥታ የማስከበር ስራውን እያከናወነ የሚገኘውንና የታገቱትንም ልጆች የማስለቀቅ ስራ እየሰራ ያለው የመከላከያ ሰራዊት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የመከላከያ ሚኒስቴር የኢንዶክትሬኔሽን እና የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ሜጀር ጄነራል መሃመድ ተሰማን በስልክ አነጋግራለች፡፡ መረጃ በተማከለ መልኩ እንዲሰጥ በመንግሰት ስልተወሰነ የጠቅለይ ሚኒቴሩን ጽህፈት ቤት አነጋግሩ ብለዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሪታሪ ሀላፊ ንጉሱ ጥላሁንን ለማግኘት ለሁለት ቀናት በተከታታይ ብንሞክርም ማነጋገር እንደማይችሉ ለአዲስ ማለዳ ነግረዋታል፡፡

የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) በበኩላቸው ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተሉት እንደሆነ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡ አክለውም መረጃዎች አሁንም በእገታ ላይ ያሉ ልጆቸን አደጋ ላይ በሚጥል መልኩ እንዳይሰራጩ ጥንቃቄ ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን መንግስትም ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት እየሰራ ነው ብለው እንደሚያምኑ ገልፀዋል፡፡

‹‹ይሄ ጉዳይ ከሰብአዊ መብት ጉዳይነት በላይ የፀጥታ እና የደህንነት ጉዳይ በመሆኑ ከእኛ ይልቅ ሌሎች ተቋማትን የሚመለከት ቢሆንም፤ አሁንም በቅርበት መከታተላችንን እንቀጥላለን›› ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ:- አዲስ ማለዳ
@YeneTube @Fikerassefa
⬆️
ከኢንተር-ኮንቲኔንታል ሆቴል እና ከእስክንድር ነጋ ተጨማሪ መረጃ!

"የሙዚቃ መሳርያ ያለበት የዩኒቨርሲቲ ምርቃት ፕሮግራም እንዲሁም የእነ እስክንድር ፕሮግራም አጠገብ ለአጠገብ ባሉ የአዳራሽ ክፍሎች ተገጣጥሞብን ነበር። የዩኒቨርሲቲው ፕሮግራም ቀደም ብሎ የተያዘ የነበረ ሲሆን ይሄኛው ግን በሁዋላ ላይ የተያዘ ነበር፣ እርግጥ ሁለቱንም አንድ ላይ መቀበል አልነበረብንም። ትናንት ማታ ደውለን ሌላ ቀን በፈለጋችሁበት ቀን አድርጉት፣ አለበለዛ የሙዚቃ መሳርያ ያለበት ፕሮግራም አጠገባችሁ ያለ አዳራሽ ውስጥ ስላለ ትረበሻላችሁ አልን። እነርሱ ግን አልተስማሙም። አሁንም በፈለጉበት ሌላ ቀን መጥተው ፕሮግራማቸውን ማካሄድ ይችላሉ። ፖሊስ ግን ጫናም አላደረገብንም።"--- የኢንተር-ኮንቲኔንታል ሆቴል ስራ አስኪያጅ አቶ ወገኔ ማቴዎስ

"ሂልተን ሆቴልም፣ ራስ ሆቴልም፣ ኢትዮጵያ ሆቴልም ሲሉ የነበረው እኛ አልከለከልንም ነበር። አሁን ይሄ ለአራተኛ ግዜ መደገሙ ነው። ሆቴሎቹ ማለት ያለባቸውን ብለዋል። ከዚህ ውጪም አልጠበቅንም። ለእኛ ግን በውስጥ የሚነግሩን ሌላ ነገር ነው፣ ይሄ ከእኛ አቅም ውጪ ነው ይሉናል። ብዙ ግዜ ገንዘብ ከፍለን ከዛ ስለ ስብሰባችን በሚድያ ስናሳውቅ ነው ይሄ ክልከላ እየመጣ ያለው። ምክንያቱ ይሄ ከሆነ ገንዘብ ለምን ተቀበሉን? ብዙ ጥያቄዎች ሊነሱ ይችላሉ።"

የሁለቱንም ወገን ድምፅ ለማቅረብ ሞክሬአለሁ። የራሳችሁን ድምዳሜ መውሰድ የናንተ ድርሻ ይሆናል።

Via:- Elias Meseret
@YeneTube @Fikerassefa
የሐረማያ ዩኒቨርስቲ ያሰለጠናቸውን ሁለት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ የህክምና ዶክተሮች አስመረቀ።

በኹከት ውስጥ የሰነነበተው የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በተቋሙ ስር ሀረር ባለው የህክምና ፋክልቲ የህክምና ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ተማሪዎቹን ነው ለምረቃ ያበቃው ።

በቅርብ ቀናት ዩኒቨርሲቲው ባካሄደው የፕሬዝዳንት ውድድር አሸናፊ ሆነው የተሾሙት ዶ/ር ጀማል ዩሱፍ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ መልዕክት አስተላልፈዋል ።

በስነ ስርዓቱ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ዑርዲን በድሪን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ በዩኒቨርሲቲው እየታየ ያለውን የሰላም መደፍረስ ተማሪዎች በመወያየት መፍታት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል ።

ዩኒቨርስቲው የመማር ማስተማር ስራውን በተለያየ መልኩ ሰላማዊ እንዳይሆን እንቅስቃሴ አድርገዋል ባላቸው ሰባ ሰባት ተማሪዎች እና ሁለት መምህራን ላይ እርምጃ መውሰዱ የሚታወስ ነው።

Via :- DW
@YeneTube @Fikerassefa
በዚህ አመት ይካሔዳል ተብሎ በሚጠበቀው የኢትዮጵያ ምርጫ የአገሪቱ ሰላም እና መረጋጋት ፈተና ሊሆኑ እንደሚችሉ ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ። ምርጫው በመጪው ግንቦት አሊያም ሰኔ ወር ሊካሔድ እንደሚችል ጠቁመዋል።

ምንጭ:- DW
@YeneTube @Fikerassefa
Forwarded from YeneTube
💥ማስታወቂያ💥
School of American English

📌ቻይንኛ
📌ፈረንሳይኛ
📌ጀርመንኛ
📌ጣልያንኛ
📌አፋን ኦሮሞ
📌አረብኛ

አንቱታን ባተፈሩ መምህራን እናስተምራለን

አድራሻዎቻችን ⬇️
ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ +251919913021
ፒያሳ ፒያሳ ገበያ ማዕከል +251919913023
22 ጎላጎል ህንፃ 6ተኛ ፎቅ +251919913022


💥💥💥10% Discount 💥💥💥💥

ቅናሹን ለመጠቀም
ይህንን ፓስት screenshot አድርገው መያዝና ስመጡ ማሣየት ይኖርብዎታል

T.me/SCHOOLOFAMERICAN
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በጅቡቲ ቅርንጫፍ ከፈተ

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የጅቡቲው ፕሬዝዳንት እስማኤል ጉሌህ በትላንትናው ዕለት የባንኩን ስራ መጀመር ይፋ አድርገዋል፡ ፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ባጫ ጊናና በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኢምባሲ አምባሳደር አብዱልአዚዝ ሙሐመድም በስነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአገር ውጭ ቅርንጫፉ ከጅቡቲው ባሻገር በደቡብ ሱዳንም ከፍቶ በስራ ላይ ይገኛል፡፡

ምንጭ ፡- ጅቡቲ ፕሬስና ሶማሌላንድሰን
@YeneTube @Fikerassefa
ባለደራ

የባልደራስ ቃለጉባኤ ለምርጫ ቦርድ
ቦርዱ ያመጣችሁት ከበቂ በላይ ነው ብሏል።
ባልደራስ ለእዉነተኛ ዲሞክራሲ ትላንት ጥር 3/ 2012 ዓም በኢንተር ኮንትኔታል ሜዳ ላይ የተመሰረተበት ቃለጉባኤ እና የምስረታ አባላት ፊርማ የያዘ ፎርም ዛሬ ጥር 4/2012ዓም ለምርጫ ቦርድ አቅርቧል።

ምንጭ:- ስንታየሁ ቸኮል
@YeneTube @Fikerassefa
ብሔራዊ ሎተሪ ለስፖርት አወራራጅ ድርጅቶች ለጊዜው ፍቃድ መስጠት ማቆሙን ገለፀ።

የብሔራዊ ሎተሪ የህግ ባለሙያ አቶ አመሀ ደሳለኝ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ስፖርት ውርርድ ጥናትና የህግ ማዕቀፍ ላይ ተመስርቶ የተጀመረ መሆኑን ተናግረዋል።

ይሁንና ህብረተሰቡ ላይ እየተፈጠረ ያለውን ብዥታ ለመገምገምና ለማጥራት ለጊዜው አዲስ ፍቃድ ለሚጠይቁ አወራራጆች ፍቃድ መስጠት ማቆማቸውን ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ እስካሁን 21 የስፖርት ውርርድ ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች አሉ ተብሏል።

ለህዝቡ ግንዛቤ ለመስጠትና የተፈጠረውን ብዥታ ለማጥራት በብሄራዊ ሎተሪና ስፖርት ውርርድ ላይ በሚሰሩ ድርጅቶች አማካይነት በጎልደን ቱሊፕ ሆቴል መግለጫ እየተሰጠ ነው።

የስፖርት ውርርድ ላይ ብሄራዊ ሎቶሪ ፍቃድ እንዲሰጥ በአዋጅ ቁጥር 535/1999 ቢፈቀድለተም በተግባር ፍቃድ መስጠት የጀመረው ግን ከ 2011 ዓ.ም ግማሽ በኋላ ነው።

ከዚያም በ2001 ሌላ የተሻሻለ አዋጅ እንደወጣለት ተነግሯል።

ምንጭ:- Ethio FM
@YeneTube @Fikerassefa
ካለፈው ሳምንት ወዲህ አሜሪካና ኢራን አንድ ሁለት ተባብለው ፍጥጫቸው አይሏል፡፡አሜሪካ በኢራን ላይ ተጨማሪ ማዕቀብም ጥላለች፡፡ 176 ንጹሀን የተቀጠፉበት አውሮፕላን ጉዳይም በኢራን ላይ ጫናዎች እንዲበረቱ አድርጓል፡፡

ምንጭ:- Al ain
@YeneTube @Fikerassefa
በህገ ወጥ መንገድ ወደ አዲስ አበባ ሊገባ የነበረ የጦር መሳሪያ ተያዘ

በህገ ወጥ መንገድ ወደ አዲስ አበባ ከተማ ሊገባ የነበረ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ በሰበታ ከተማ ተያዘ።

የሰበታ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት መረጃ እንደሚያመለክተው፥ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያው የተያዘው ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ ነው።

የሰበታ ከተማ የፀጥታ አካላት ባደረጉት ክትትል በአይሱዙ የጭነት ማመላለሻ ተሽከርካሪ ተጭኖ ከቦንጋ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ 52 ክላሽንኮቭ የጦር መሳሪያ መያዙንም ቢሮው አስታውቋል።

ተሽከርካሪው በረቀቀ መንገድ በድብቅ በተዘጋጀ ስፍራ መሳሪያዎችን ጭኖ ሲጓዝ እንደነበር የሰበታ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል።

የከተማ አስተዳደሩ የፀጥታ አካላት ባደረጉት ፍተሻ የጦር መሳሪያዎቹ መያዛቸውን ጠቅሶ፥ አሁን ላይም በጉዳዩ ላይ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን አስረድቷል።

ፀረ ሰላም ሀይሎች የህዝቡን ሰላም ለማወክ ሌት ተቀን የሚሰሩትን ስራ ለመቆጣጠር የህብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ ነው ያለው ፖሊስ መምሪያው፤ ህብረተሰቡ አጠራጣሪ ነገሮችን ሲመለከት በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታ አካላት እንዲያሳውቅም ጥሪውን አቅርቧል።

ምንጭ:- ኤፍ.ቢ.ሲ
@Yenetube @Fikerassefa