YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
አዋሽ ባንክ ከወለድ ነፃ አገልግሎት የሚሰጥባቸውን ቅርንጫፎች በአዲስ አበባ ነገ ጥር 5/2012 ሊከፍት ነው

አዋሽ ባንክ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ አገልግሎት የሚሰጥባቸው ሦስት ቅርንጫፎችን ነገ ጥር 5/2012 በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚከፍት አስታወቀ።

ባንኩ ቅርንጫፎቹን በመርካቶ ኹለት ቅርንጫፍ እና በቦሌ ሚካኤል አንድ ቅርንጫፍ እንደሚከፍት አስታውቋል።

Via:- Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
አቶ ኃይለማርያም ደሣለኝ መጥሪያ ስላልደረሳቸው ፍርድ ቤት አልተገኙም

አቶ ኃይለማርም ደሣለኝ፣ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና አቶ ደመቀ መኮንን ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ። የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በእነበረከት ስምኦን መዝገብ ላይ የመከላከያ ምስክር ለመስማት ነበር ለዛሬ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው።
የተከሳሽ ጠበቃ፤ መጥሪያ ለምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና ለውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው መሰጠቱን ገልጸው የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለማርያም ደሣለኝን ማግኘት ባለመቻላቸው መጥሪያ መስጠት አለመቻላቸውን ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል።

በፋክስ በደረሰው መረጃ መሠረት አቶ ደመቀ እና አቶ ገዱ በሥራ ምክንያት መቅረብ አለመቻላቸውን መግለጻቸውን ፍርድ ቤቱ አስታውቋል። አንድ ሌላ ምስክርም በዛሬው ችሎት ላይ ሳይቀርቡ ቀርተዋል። ተከሳሾች የተሰከሳሽነት ቃላቸውን ለፍርድ ቤቱ በመስጠት ላይ ናቸው። የፍርድ ሂደቱ ከሰዓት በኋላም እንደሚቀጥል ቢቢሲ አስነብቧል በFacebook ገፁ።

Via:- BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበበ ከተማ ፖሊስን ደመወዝ ከመክፈል ውጪ ከተማ አስተዳደሩ እንደማያስተዳረው ኢንጂነር ታከለ ኡማ ተናገሩ፡፡

ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና ካቢኔያቸው ከሕዝብ ተወካዩች ምክር ቤት አባላት ጋር ዛሬ ረፋድ ውይይት አካሂደዋል።

የምክር ቤቱ አባላት በከተማዋ የሚሰተዋለውን የተደራጀ ወንጀልና ዘረፋ ህብረተሰቡ ኑሮ ላይ ጫና እያሳደረ ነው ከተማዋ አስተዳድር ምን እየሰራ ነው የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸዋል።

ኢንጅነር ታከለ ለተነሳላቸው ጥያቄ የአዲስ አበባ ፖሊስ እኛ ደመወዝ ከመክፈል ውጪ ሌላ ሃላፊነት የለንም የከተማዋን ፖሊስ የሚመራው ፌደራል ፖሊስ ነው ብለዋል፡፡

የከተማዋን ፖሊስን መምራት ባንችልም የከተማው ጸጥታ ስለሚመለከተን ወጣትና ነዋሪውን የአካባቢውን ፀጥታ እንዲያስከብርና እንዲጠብቅ እንደገና እንዲደራጁ አድርገናል ብለዋል፡፡

የከተማዋን ፖሊስ ለማስተዳደር ሙሉ በሙሉ ሃላፊነት ባይሰጠን እንኳን የፌደራል ፖሊስን ውክልና ስጡን እና እንምራ ብለን ጥያቄ ብናቀርብም አልሰጡንም ችግሩን ለመፍታት የፓርላማውም ድጋፍ ያስፈልገናል ብለዋል ኢንጅነር ታከለ፡፡

Via:- ETHIO FM
@YeneTube @Fikerassefa
ባህር ዳር ዩንቨርስቲ ተማሪዎች በሙሉ ⬆️
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የብድር አሰጣጥ እና አመላለስ ስርዓቱን በማስተካከል በ 2012 በጀት ዓመት አምስት ወራት ከ 3 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር በላይ የተበላሸ ብድር ማስመለስ መቻሉን አስታወቀ።

ልማት ባንኩ በ 2010 እና 2011 የሰጣቸው የተበላሹ ብድሮች መጠን ባንኩን ኪሳራ ውስጥ ከተውት የቆየ ሲሆን፣ በወቅቱም ከ 40 ቢሊዮን ብር በላይ ከሚሆን ገንዘብ ውስጥ እስከ 18 ቢሊዮን የሚደርሰው የተበላሸ እንደነበር ይታወሳል።

Via:- Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
በምዕ/ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ የመከላከያ ሰራዊት ልብስ በመልበስ ኬላ ዘርግተው ሲፈትሹ በነበሩ ታጣቂዎች፣ አንድ አሽከርካሪን ጨምሮ 6 ሰዎች ታግተው ተወስደዋል። ዕገታው የተፈጸመው ከ4 ቀን በፊት ሲሆን፣ አጋቾቹ በሰው ከ150ሺህ-250ሺህ ብር ጠይቀዋል።

Via Ethiopia Live Updates
@Yenetube @Fikerassefa
በወለጋ ለበርካታ ቀናት ታግተው የቆዩ 13 ወንድ እና 8 ሴት ተማሪዎች እንደተለቀቁ መንግሥት ለመገናኛ ብዙኻን ቢያሳውቅም፣ ተማሪዎቹ አሁን ያሉበት ሁኔታ እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ስለመገናኘታቸው ግን እስካሁን የጠራ መረጃ አልወጣም፡፡ ባጠቃላይ በአካባቢው ስንት ታጋች ተማሪዎች እንዳሉ እና ስለ አጋቾች ማንነትም የተብራራ መረጃ አልተሰጠም።

Via Wazema
@YeneTube @Fikerassefa
Forwarded from YeneTube
💥ማስታወቂያ💥
School of American English

📌ቻይንኛ
📌ፈረንሳይኛ
📌ጀርመንኛ
📌ጣልያንኛ
📌አፋን ኦሮሞ
📌አረብኛ

አንቱታን ባተፈሩ መምህራን እናስተምራለን

አድራሻዎቻችን ⬇️
ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ +251919913021
ፒያሳ ፒያሳ ገበያ ማዕከል +251919913023
22 ጎላጎል ህንፃ 6ተኛ ፎቅ +251919913022


💥💥💥10% Discount 💥💥💥💥

ቅናሹን ለመጠቀም
ይህንን ፓስት screenshot አድርገው መያዝና ስመጡ ማሣየት ይኖርብዎታል

T.me/SCHOOLOFAMERICAN
Forwarded from YeneTube
SELL/BUY/ORDER/RENT EVERYTHING
SOFTWARE/WEB/GRAPHICS DESIGN
IT SUPPORT
STUDENT SCHOLARSHIPS/VISA's
Work with us GET PAID
📩 @CloudMultiTrading 📩
+1(617)580-0402 0944182119 +971586233799
📩 @CloudMultiTrading2 📩

Join our Channel⬇️
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEPkQuyukYp1DOpZEw
‹‹የሲዳማ ክልል የሚመራበት ህገ መንግስት በረቂቅ ደረጃ ተጠናቋል›› ሲሉ የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደስታ ሌዳሞ ገለፁ።

ተቋማትን የመገንባት ስራ ከዚሁ ጎን ለጎን እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።ዋና አስተዳዳሪው አቶ ደስታ ሌዳሞ ሰሞኑን ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት፤ በአሁኑ ወቅት አዲሱ የሲዳማ ክልል የሚመራበት የራሱ ህገ መንግስት በረቂቅ ደረጃ ተጠናቋል።

ህገ መንግስቱን የማርቀቅ ስራ ቀደም ሲል የተጀመረ ሲሆን፣ ከተረቀቀም አንድ ዓመት ያህል ሆኖታል።ረቂቅ ህገ መንግስቱ ላይ የሲዳማ ህዝብ አንድ ጊዜ እንዲወያይበት መደረጉን የተናገሩት አቶ ደስታ፤ በህዝቡ መተቸቱና ማስተቸቱ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ክልል የምግብ ዋጋ ግሽበት 23 በመቶ ደረሰ!

የትግራይ ክልል የምግብ ዋጋ ግሽበት ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፃር እስከ አስር በመቶ የሚደረስ ጭማሪ ማስመዝገቡን የብሔራዊ ባንክ ዓመታዊ ዘገባ አመላከተ።ለምግብ ፍጆታ የሚውሉ ግብዓቶች ላይ በክልሉ የተስተዋለው የግሽበት መጠን በ2011 ከነበረበት የ 13 በመቶ የአስር በመቶ ጭማሪ በማድረግ አሁን 23 ከመቶ ላይ እንደሚገኝ የባንኩ ዓመታዊ ዘገባ ያስረዳል። አጠቃላይ የዋጋ ግሽበቱ በትግራይ ክልል ባለፈው ዓመት 13.9 በመቶ ላይ የነበረ ሲሆን፣ አሁን 19.8 በመቶ ላይ ደርሶ ይገኛል።

ምንጭ: አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በህዳሴ ግድብ ዙሪያ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ከትናንት ጀምሮ እየተወያዩ ነው።

ከዚህ ቀደም ሀገራቱ በደረሱት ስምምነት መሰረት ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ተገናኝተው በመወያየት ላይ የሚገኙት።በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ አተኩሮ እየተካሄደ ባለው ስብሰባ ላይ የሀገራቱ የውሃ ሚኒስትሮችም እየተካፈሉ ሲሆን፥ የአሜሪካ መንግስት እና የዓለም ባንክ ተወካዮችም በታዛቢነት ተገኝተዋል። ሚኒስትሮቹ በስብሰባቸው በውሃ ሚኒስትሮች ደረጃ በተለያዩ ዙሮች የህዳሴ ግድብን በተመለከተ ያደረጓቸውን ድርድሮች ውጤት ይመለከታሉ።ባሳለፍነው ሳምንት ኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በአዲስ አበባ ሲያካሂዱት የቆዩት አራተኛና የመጨረሻው የቴክኒክ ውይይት ያለስምምነት መጠናቀቁ ይታወሳል።

ውይይቱ ያለስምምነት የተጠናቀቀው ግብፅ የግድቡን የውሃ ሙሌት በተመለከተ አዲስ ሃሳብ ይዛ በመቅረቧ መሆኑንም የኢፌዴሪ የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ግብፅ ግድቡ ከ12 እስከ 21 ዓመት እንዲሞላ የሚል አዲስ ሀሳብ ማቅረቧ እና ኢትዮጵያ በበኩሏ ይህን ሃሳብ በማንኛውም መልኩ እንደማትቀበል መግለጿን ነው ሚኒስትሩ በወቅቱ የተናገሩት።ሶስቱ ሀገራት ከዚህ በፊት የህዳሴው ግድብ በ7 ዓመት ውስጥ እንዲሞላ ስምምነት ላይ ደረሰው የነበረ መሆኑ ይታወሳል።

ሶስቱ አገራት በዋሺንግተን ዲሲ በደረሱት ስምምነት አማካኝነት ስምምነት ላይ ካልደረሱ የህዳሴ ግድቡን አስመልክቶ በካርቱም የተፈረመው ስምምነት አንቀጽ 10 ተግባራዊ እንዲሆን ይደረጋል።የካርቱም ስምምነት አንቀጽ 10 “ሶስቱ አገራት በመርሆዎች ስምምነቱ አተረጓጎምና ተግባራዊነት የተነሱ አለመግባባቶችን በውይይት ወይም በድርድር ይፈታሉ፤ ይህንን ማድረግ ካልቻሉ ግን አደራዳሪ ሊጠይቁ ወይም ለአገራቸው መሪዎች ሊያሳውቁ ይችላሉ” ይላል።ይህንንም የሚያደርጉት የሶስቱም ሀገራት ስምምነት ሲኖር እንደሆነም አስቀምጧል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
 ሁሉንም ሰብስቦ በአንድ ላይ የያዘ የግብይት ድረገፅ
 በድረ ገፁ ላይ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት ዕቃዎቹን ወይም አገልግሎቱን መሸጥ ይችላል።
 ከ2700 በላይ ዕቃዎችና አገልግሎቶች
@SebsibieEthiopia
www.sebsibie.com
 0953707070
የቲቦር ናዢ የኢትዮጵያ ጉብኝት

የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚንስትር ቲቦር ናዢ ኢትዮጵያን ጨምሮ 5 የአፍሪካ አገራትን ሊጎበኙ ነው፡፡

ረዳት ሚንስትሩ ከጥር 6 እስከ 20/2012 በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሱዳን የሥራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ነው የተገለጸው፡፡
በሁለት ሳምንት ቆይታቸውም ከየአገራቱ ከፍተኛ አመራሮችና ዓለም ዐቀፍ የዋሽንግተን አጋር ተቋማት ኃላፊዎች ጋር ይመክራሉ ተብሏል፡፡

ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን ማጠናከር፣ አካባቢያዊ ፀጥታን ማጎልበት፣ ሙስናን መዋጋት እና የንግድና የመዋዕለ ነዋይ ፍሰትን ማበረታታት የታቦር ናዢ ጉብኝት ዓላማ መሆናቸውን የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ገልጿል፡፡

ምንጭ:- አሀዱ ቴሌቪዥን
@YeneTube @Fikerassefa
የትግራይ ቲቪ ጋዜጠኞች አሶሳ ላይ መታሰር እና የክልልሉ መልስ!

የትግራይ ቲቪ የአዲስ አበባ ቢሮ አስተባባሪ አቶ አክሊሉ ደባልቀው በስልክ ከነገረኝ:
"የትግራይ ቲቪ ጋዜጠኛ የሆነው ዳዊት ከበደ እና የካሜራ ባለሙያው በሀይሉ ውቤ ትናንት ምሽት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ሶስት ሰአት ገደማ ታስረዋል። ከቅዳሜ ጀምሮ የተለያዩ ቀረፃዎችን ሲያካሂዱ ቆይተው ትናንት እስካሁን ምክንያቱ ምን እንደሆነ ባልታወቀ ምክንያት ታስረዋል። እዛ ሆነው የሰሩት እና በቲቪ የተላለፈ ፕሮግራም እንኳን አልነበረም።"

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቃል አቀባይ አቶ መለሰ በየነ የሰጠኝ መልስ:
"እኔ ለስራ ሌላ ቦታ ነኝ ነገር ግን ስልክ በመደወል ለመረዳት እንደቻልኩት ጋዜጠኞቹ የነበረንን አሰራር ተከትለው አልመጡም። ይህ ማለት ወደ ክልሉ ለዘገባ እንደሚመጡ ለክልሉ ኮሚኒኬሽን አላሳወቁም። ምን መስራት እንደሚፈልጉ ነግረውን፣ እኛም ባለሙያ እና አስፈላጊም ከሆነ የፀጥታ አካላት መድበን መሆን ነበረበት። ለምሳሌ እኔ እንደ ክልሉ ኮሚኒኬሽን ሀላፊ ስለመምጣታቸው የማውቀው ነገር የለም። ታሰሩ ሲባል እንደሌላው ሰው ነው የሰማሁት። አሁን ግን የታሰሩበት ምክንያት ምን እንደሆነ በትክክል አጣርተን እናሳውቃለን።"

ምንጭ:- ኤልያስ መሰረት
@YeneTube @Fikeeassefa
ግብፅ ከአሜሪካ ባደረገችው የተናጠል ውይይት ታላቁ የኅዳሴ ግድብ ውኃ የሚሞላበትና የሚተዳደርበት ሕግጋት እና አሰራር ምን መሆን እንዳለበት አገራቸው ማስረዳቷን የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አሕመድ ሐፌዝ ገልጸዋል።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
የሰሜን ሸዋ ዞን ገቢዎች መምሪያ አዲሱ የመሬት ልኬታ/ካዳስተር/ በተካሄደባቸው አካባቢዎች የእርሻ መሬት ግብር ክፍያ የተቀየረና የተጨመረ ተደርጎ የሚነሳው ስህተት መሆኑን ገለፀ፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን ገጠር መሬት አጠቃቀምና አስተዳደር መምሪያና የሰሜን ሸዋ ዞን ገቢዎች መምሪያ በጋራ በመሆን የአርሶ አደሩ የገጠር መሬት ይዞታ አዲስ የመሬት ልኬት /ካዳስተር/ከተሰራ በኋላ የገጠር መሬት መጠቀሚያና የእርሻ ስራ ግብር ላይ ያለውን ሁኔታ በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡የሰሜን ሸዋ ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ንጉሴ እንደገለፁት ፤የገጠር መሬት መጠቀሚያና የእርሻ ስራ ስራ ገቢ ግብር በክልሉ ምክር ቤት አዋጅ ህዳር 2001 ዓ.ም በጸደቀው መሰረት በአርሶ አደሩ መሬት ልክ እንዲከፍል ተደርጎ እየተሰራበት ቆይቷል፡፡

የአርሶ አደሮች የገጠር መሬት ይዞታ የግብር ክፍያ በምግብ ዋስትና የተያዙና ያልተያዙት በስተቀር ልዩነት እንደሌለው ገልጸው ፤በጥማድ 30 እና 40 ብር እንዲከፍሉ ሲደረግ ቆይቷል፤ አሁንም ይህ አሰራር እንደቀጠለ ያለና ያልተቀየረ ሲሆን ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት በአንዳንድ አካባቢዎች ከግንዛቤ ማነስ ሊሆን በሚችል የአርሶ አደሩ የመሬት መጠቀሚያ ግብር የተቀየረና የተጨመረ ተደርጎ የሚነሳው ስህተትና ልዩነት አለመደረጉን ገልፀዋል፡፡

ምንጭ: የሰሜን ሸዋ ዞን ኮሚኒኬሽን መምሪያ
@YeneTube @FikerAssefa
የቤኒሻንጉል ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ‹‹ቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ›› የተሰኘ አዲስ ፓርቲ ለመመሥረት በዝግጅት ላይ የነበሩ 10 ግለሰቦች ላይ የእስር ማዘዣ በማውጣት ሰብሳቢውን ጨምሮ አራት ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አዋለ። የፓርቲዉ ምክትል ሰብሳቢ ጌታሁን መርጋ፣ የሕግ ባለሙያ የሆኑት ጌታቸዉ ወድሻ፣ የድርጅት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ጉዮ ፈረደን (ዶ/ር) ሐሙስ ታኅሳስ 30/2012 መታሰራቸውን የቦሮ ፓርቲ የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ ዮሐንስ ተሰማ ተናግረዋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
"ጋዜጠኞቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ደብዳቤ ይዘው ስላልተገኙ ነው" የአሶሳ ፖሊስ

ዋና ኢንስፔክተር እስማኤል፤ ሁለቱ ጋዜጠኞች የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይትን ለመዘገብ ከኤጀንሲው አዲስ አበባ ቅርንጫፍ መላካቸውን እንደነገሯቸው ጠቅሰው፤ ጋዜጠኞቹ ወደ አሶሳ ሲመጡ ደብዳቤ ባለመያዛቸው እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስለ ሁለቱ ጋዜጠኞች ወደ ክልሉ መምጣት የሚያውቀው ነገር ባለመኖሩ መታሰራቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮ-ቴሌኮም ንብረት የሆኑ በርካታ የስልክ ገመዶችን ከነ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገፀ፡፡

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ እንዳስታወቀው ጥር 15 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ መርካቶ ጋዝ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለበርካታ ኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች አገልግሎት የሚሰጡ እና ከመሬት ውስጥ ተቆፍረው የወጡ የስልክ ገመዶችን አከማችተው የተገኙ 2 ተጠርታሪዎች በፖሊስ አባላት ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በተመሳሳይ በክ/ከተማው መርካቶ ኢትዮጵያ ዳቦ ቤት ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ አንድ ተጠርጣሪ በመሬት ውስጥ የተቀበሩ ንብረትነቱ የኢትዮ ቴሌኮም የሆኑ የስልክ ገመዶችን ቆፍሮ እያወጣና እየቆረጠ ሰርቆ ለመውሰድ ሲሞክር በፖሊስ አጋዥ ሃይሎች እጅ ከፈንጅ ሊያዝ መቻሉን የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ወንጀሉን ሲፈፅሙ የነበረው በሌሊቱ ክፍለ ጊዜ መሆኑን ያስታወሰው ፖሊስ መምሪያው በአሁኑ ወቅት ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡የመሰረተ ልማት አውታሮች የህብረተሰቡን የዕለት ተዕለት መረጃ ግንኙነት ያቀላሉ፡ ለሀገራች የኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ ሚና ያላቸው የህዝብ ሀብት ስለሆኑ ፖሊስ ወንጀሉን ለመከላከል የሚያደርገው ጥረት ህብረተሰቡ በነቃ ተሳትፎ እንዲያግዝ ኮሚሽኑ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

Via Addis Ababa Police Commission
@YeneTube @FikerAssefa