YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ታግተው የነበሩ #21 የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መንግስት ባደረገው ጥረት መለቀቃቸውን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት አስታወቀ!

በደንቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ግጭት መከሰቱን ተከትሎ ወደ ቤተሰቦቻቸው በመሄድ ላይ የነበሩ ተማሪዎች ጫካ ውስጥ ታግተው መቆየታቸውን የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ለኢቲቪ ተናግረዋል።

በእገታ ላይ የነበሩትን ተማሪዎች በሰላማዊ መንገድ ያለምንም ጉዳት ለማስለቀቅ መንግስት ከአካባቢው የአገር ሽማግሌዎች ፣ ከወጣቶችና ከመከላከያ ሰራዊትና የፀጥታ መዋቅሮች ጋር ሲሰራ መቆቱን ኃላፊው አስታውቀዋል።

የሰላም ጥረቱ ፍሬ በማፍርቱ ታግተው ከነበሩ ተማሪዎች ውስጥ 13 ሴትና 8 ወንድ በድምሩ 21 ተማሪዎች በሰላማዊ ሁኔታ መለቀቃቸውን አቶ ንጉሱ አስታውቀዋል።

ይሁን እንጂ አሁንም ቀሪ #6_ተማሪዎች_በእገታ ላይ መሆናቸውን በአካባቢው የተሰማራው የፀጥታ ኃይል መረጃ መስጠቱን ተናግረዋል።

ታግተው ያሉ ቀሪ ተማሪዎችን ያለምንም ጉዳት እንዲለቀቁ ለማድረግ መንግስት ከአገር ሽማግሌዎችና የሐይማኖት አባቶች ጋር በመተባበር በአካባቢው ወግና ስርዓት ለማስለቀቅ እየሰራ መሆኑንም አቶ ንጉሱ ጥላሁን ለኢቲቪ ገልፀዋል።

መንግስትም በተከታታይ ከእገታ ያልወጡ 6 ተማሪዎችን ለማስለቀቅ እየተደረገ ያለውን ጥረት በየጊዜው ለህዝብ መረጃ እንደሚያደርስም አመልክተዋል።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa