YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የአንድነት ፓርክን ጎበኙ።

ቀደም ባሉት ጊዜያት ፓርኩን ደጋግመው የጎበኙት ፕሬዚዳንቷ በዛሬው ጉብኝታቸው በየጊዜው አዳዲስ ነገሮች በፓርኩ እየተጨመሩ መምጣታቸውን መመልከታቸውን ተናግረዋል።

ፓርኩን "አንድ ጊዜ አይቸዋለሁ ተብሎ የሚቀርብበትና ታይቶ የሚጠገብም አይደለም" ያሉት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ፥ በተለይ የኢትዮጵያውያንን ታሪክ ከማሳየትና ለትውልድ ከማስተላለፍ አኳያ ትልቅ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

የአትዮጵያ ከተሞች ተመሳሳይ ዓይነት ታሪካዊ መዝናኛዎች እንደሚያስፈልጋቸው ጠቁመው፥ አንድነት ፓርክ የኢትዮጵያንም ሆነ የአዲስ አበባን መልካም ገፅታ ለዓለም በማስተዋወቅ ትልቅ ሚና እንዳለው ነው ያመለከቱት።

ከፓርኩ በተጨማሪ ታላቁን ብሄራዊ ቤተ መንግስት ጨምሮ የኢትዮጵያን ታሪክ ሊያሳዩ የሚችሉ ስራዎች በቀጣይ እንደሚከናወኑም በዚሁ ወቅት ተናግረዋል።

Via:- FBC
@YeneTube @FikerAssefa
አምባሳደር ፕ/ር አድማሱ ፀጋዬ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለካምቦዲያ ንጉስ አቀረበዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በአርማጭሆ አካባቢ ሕጻናትን፣ ሾፌሮችን እና ግለሰቦችን በማገት ከቤተሰቦቻቸው ገንዘብ በመጠየቅ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ወደ 50 የሚደርሱ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ አስታውቀዋል፡፡

በተያያዘ ዜና በሞጣ ከተማ በሃይማኖት ተቋማት እና በንግድ ተቋማት ላይ በደረሰው ጥቃት እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩ ወደ 80 ያህል ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ አስታወቁ።ከተጠርጣሪዎቹ መካከል 'ሕጋዊ የሆነውን መጅሊስ ለማፍረስ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦች' እንዳሉበት እና በመስጂዶች ቃጠሎ መሳተፋቸውን ገልጸዋል፡፡

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
በኢሚግሬሽን ፣ የዜግነትና ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ የድቡብ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ተገቢውን አገልገሎት ባለመስጠቱ ለከፍተኛ እንግልት እየተዳረግን ነው ሲሉ ተገልጋዮች አማረሩ።

Via:- DW
@YeneTube @FikerAssefa
“ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ እዚህ አገር ፍትህ እንዲመጣ ከፍተኛ መስዋእትነት የከፈሉ ሰው ናቸው፤ ከሁላችን የበለጠ እንጂ ያነሰ ቁርጠኝነት አላቸው ብዬ አላምንም”

~~~~~~ጀዋር መሐመድ~~~~~~
@Yenetube @Fikerassefa
YeneTube
“ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ እዚህ አገር ፍትህ እንዲመጣ ከፍተኛ መስዋእትነት የከፈሉ ሰው ናቸው፤ ከሁላችን የበለጠ እንጂ ያነሰ ቁርጠኝነት አላቸው ብዬ አላምንም” ~~~~~~ጀዋር መሐመድ~~~~~~ @Yenetube @Fikerassefa
ዛሬ አቶ ጅዋር መሀመድ ከቢቢሲ አማርኛ ጋር አጠር ያለ ቆይታ ነበረው በዚህ ቃለ ምልልስ ፓስፓርት ስለ መመለሱ ጋር ለቀረበለት ጥያቄ #ፓስፖርቱን ለአሜሪካ መንግስት መመለሱን አስታውቋል እንዲሁም አሁን በኢትዮጵያ ፓለቲካ ላይ ለመሳተፍ ምንም #እንደማያግደው ተናግራል።

@YeneTube @Fikerassefa
ትናንት ምሽት በአማራ ክልል፣ አገው አዊ ዞን፣ አዮ ጓጉሳ ወረዳ እሁዲት ከተማ ቤተክርስቲያን ለማቃጠል ሙከራ አድርገዋል የተባሉ 3 ግለሰቦችን ለመያዝ የአካባቢው ማህበረሰብና የጸጥታ ሀይሎች ሙከራ ባደረጉበት ወቅት የአንዱ ህይወት አለፈ።

Via:- ElU
@YeneTube @Fikerassefa
አሜሪካዊቷ የፖፕ ሙዚቃ አቀንቃኛ ፒንክ
አውስትራልያ የተከሰተውን የእሳት አደጋ ለመታደግ አምስት መቶ ሺ ዶላር ረዳች።

@YeneTube @FikerAssefa
መልካም ገና በዐል ይሁንላችሁ
ፎቶ:- @leykunadvertising
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የፊታችን ቅዳሜ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሊያቀኑ ነው።

እንደ ፕረስ ላቲና ዘገባ ከሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥር 2 ቀን 2012 ዓ.ም ወደ ደቡብ አፍሪካ ያቀናሉ።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዞ ዓላማም በኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ ቀጣይ ግንኙነት ዙሪያ ከፕሬዘዳንት ሲሪል ራማምፖሳ ጋር መምከር ነው።

በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የአገራቸውን ሁለንተናዊ እድገት እንዴት እንደሚደግፉም ከዳያስፖራዎቹ ጋር እንደሚመክሩ ተገልጿል።

በተጨማሪም የደቡብ አፍሪካ ግዙፍ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት መስኮች እንዲሰማሩ ማግባባት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጨማሪ የጉዞ ዓላማ ነው ተብሏል።

52 ሚሊዬን ህዝብ ያላትና ከአፍሪካ የበለጸገችዋ አገር ደቡብ አፍሪካ በአህጉሩ እና ዓለም አቀፍ ደረጃ ተጽዕኖ ፈጣሪ ኩባንያዎች ባለቤት ስትሆን ከኢትዮጵያ ጋር አንድ ክፍለ ዘመን ያስቆጠረ ወዳጅነት አላት።

ኢትዮጵያ ደቡብ አፍሪካ ገጥሟት ከነበረው የእንግሊዝ አፓርታይድ ቅኝ ግዛት ነጻ እንድትወጣ ወታደራዊ ድጋፍ ከማድረግ አንስቶ በተለያዩ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የዲፕሎማሲ ድጋፍ ማድረጓን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።

Via :- Ethio FM
@Yebetube @FikerAssefa
💥ማስታወቂያ💥
School of American English

📌ቻይንኛ
📌ፈረንሳይኛ
📌ጀርመንኛ
📌ጣልያንኛ
📌አፋን ኦሮሞ
📌አረብኛ

አንቱታን ባተፈሩ መምህራን እናስተምራለን

አድራሻዎቻችን ⬇️
ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ +251919913021
ፒያሳ ፒያሳ ገበያ ማዕከል +251919913023
22 ጎላጎል ህንፃ 6ተኛ ፎቅ +251919913022


💥💥💥10% Discount 💥💥💥💥

ቅናሹን ለመጠቀም
ይህንን ፓስት screenshot አድርገው መያዝና ስመጡ ማሣየት ይኖርብዎታል

T.me/SCHOOLOFAMERICAN
ኢ/ር ታከለ ኡማ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በክረምት በጎፈቃድ መርሃ ግብር ቤታቸው የታደሰላቸው እናቶችን ጎበኙ!

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በክረምት በጎፈቃድ መርሃ ግብር ቤታቸው የታደሰላቸው እናቶች ቤት ቆይታ አድርገዋል። በጉብኝቱ ከምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ በተጨማሪ የተለያዩ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች መገኘታቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።የከተማ አስተዳደሩ ባሳለፍነው የክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ-ግብር በመዲናዋ ውስጥ ለሚገኙ 1ሺህ 573 ለሚሆኑ አረጋዊያን የመኖሪያ ቤት እድሳት ማከናወኑ ይታወሳል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
በአፍሪካ በፈረንጆች 2020 ዓመት ኢትዮጵያን ጨምሮ 22 አገራት ምርጫ ያደርጋሉ።

የአፍሪካ ምርጫ እና ዘላቂ ዲሞክራሲ ኢንስቲትዩት መረጃ እንደሚያሳየው ከሆነ በያዝነው የፈረንጆች 2020 ዓመት በአፍሪካ ብቻ ኢትዮጵያን ጨምሮ 22 አገራት አገራዊ ምርጫ ያካሂዳሉ።

ኢትዮጵያ፣ግብጽ፣ጋና፣ አይቮሪ ኮስት፣ቡርኪና ፋሶ፣ቡሩንዲ፣ ማዕከላዊ አፍሪካ እና ሱዳን በአፍሪካ ተጠባቂ እና አጓጊ ምርጫ ይካሄድባቸዋል ከሚባሉ አገራት መካከል ናቸው።

ይህ ዓመት ሚሊዮን አፍሪካዊያን መሪዎቻቸውን ለመምረጥ ወደ ምርጫ ጣቢያ የሚሄዱበት ዓመት ተብሏል።

ኤርትራ በታሪኳ ምንም ምርጫ ያላካሄደች አገር ስትሆን ባህሬን፣ ኦማን፣ ኩዌት፣ ኳታር፣ ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬት የፖለቲካ ፓርቲዎችን ማቋቋም በህግ የከለከሉ አገራት ናቸው።

ናይጀሪያ፣ደቡብ አፍሪካ፣አልጀሪያ፣ሴኔጋል እና ቦትስዋና በአንጻራዊነት በተጠናቀቀው የፈረንጆች 2019 ዓመት ስኬታማ ምርጫ ያካሄዱ አገራት ናቸው።

ሕንድ ባሳለፍነው ዓመት ያካሄደችው ምርጫ በዓለም የምርጫ ታሪክ 900 ሚሊዮን መራጮች የተሳተፉበት ትልቁን ምርጫ አካሂዳለች።

@YeneTube @Fikerassefa
የአውስትራሊያ የእሳት አደጋ

- 24 ሰው በዚህ ቃጠሎ ምክንያት ሞተዋል

-500 ሚልዮን እንስሳት ሞተዋል

- ከ5.5 ሚልዮን ሄክታር በላይ በቃጠሎ
ምክንያት ወድሟል ( ቤልጅየምን የሚያክል )

-ከ1400 በላይ ቤቶች ተቃጥለዋል

@YeneTube @FikerAssefa
የኢራኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጃቫድ ዛሪፍ በአሜሪካ ቪዛ መከልከላቸውን ተናገሩ።

ዛሪፍ በሚቀጥለው ሳምንት በኒዮርክ ለሚካሄደው የመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታ ጉባኤ ላይ ለመካፈል ወደ ኒዮርክ ለማምራት ቪዛ እንዲሰጠኝ ባመለክትም አሜሪካ ቪዛውን ከልክላኛለች ማለታቸውን አልጀዚያ ዘግቧል።

የመንግስታቱ ድርጅት በ1947 ባወጣው ድንጋጌ የአሜሪካ መንግስት ለማንኛውም አገር መሪ ቪዛ መከልከል አትችልም የሚል ድንጋጌ ቢያስቀምጥም አሜሪካ በተደጋጋሚ ይሄንን ዓለም አቀፍ ህግ ስትጥስ ቆይታለች።

የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጃቫድ ዛሪፍ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ቪዛ ሲከለከሉ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን ከዚህ በፊት የቬንዙዌላ ፕሬዘዳንት ኒኮላስ ማዱሮን እና ሌሎች መሪዎችን ቪዛ ከልክላለች።

ዛሪፍ ወደ ኒዮርክ እንዳልሄድ የተከለከልኩት አሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ እየሰራች ያለውን ግፍ በጉባኤው ላይ እንዳልናገር ነው ብለዋል።

አሜሪካና ኢራን በተለይም ከፕሬዘዳንት ትራምፕ መመረጥ በኋላ እየተካረረ የመጣ ሲሆን ባሳለፍነው ሳምንት የኢራን አብዮታዊ ዘብ ጠባቂ ቡድን መሪ ሱሊማኒን ከገደለች በኋላ በአካባቢው ውጥረቱ ነግሷል።

ዛሪፍ የቪዛ ጥያቄውን ያቀረቡት እና የተከለከሉት ሱሊማኒ ከመገደሉ በፊት መሆኑ ደግሞ አሜሪካ ድርጊቱን ቀደም ብላ ስትዘጋጅበት ማሳያ ነው ተብሏል።

Via:- Ethio FM
@YeneTube @Fikerassefa
የሮታሪ ኢንትርናሽናል አካል የሆነው ሮታራክት ኢትዮጵያ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ጐዳና ላይ ለሚኖሩ ከ1500 ሰዎች በላይ የምሳ ማብላት እና የአልባሳት ድጋፍ በማድረግ የገና በዓልን አከበረ።

Via:- Yenus Shemsu / YeneTube
@YeneTube @Fikerassefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የገና በዓልን ከአረጋውያን፣ ሕጻናት እና አካል ጉዳተኞች ጋር አከበሩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጠዋቱን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል (ገና)ን ከአረጋውያን፣ ሕጻናት እና አካል ጉዳተኞች ጋር በአንድነት ፓርክ አከበሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዝግጅቱ ወቅት አጽንኦት ሰጥተው እንደ ተናገሩት፣ ቁሳዊ ሀብት ብቻውን ባለጸጋ አያደርግም፣ ብልጽግና መስጠት እና መካፈልንም ይጨምራል ብለዋል።

Via:- EBC
@YeneTube @Fikerassefa