YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ባዕድ ነገር ከማር፣ ከቅቤ እና ከጠጅ ጋር ቀምመው ለበዓል ገበያ ሊያቀርቡ የነበሩ 72 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ መጪውን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ ባዕድ ነገር ከቅቤና ከማር ጋር ቀምመው የሚሸጡ 72 ተጠርጣዎችን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቡድን ከኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ጋር ባካሄዱት የጋራ ኦፕሬሽን በዛሬው ዕለት በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር በዋሉበት ሰአት ማር ባለ 50 ኪሎ ግራም 1196 ማዳበሪያ፣ ማር 80 ባልዲ ፣ ለጠጅ የተዘጋጀ 10 በርሜል ማር፣ አንድ ደርዘን ወይም አስር ፍሬ ነጭ ቀለም ያለው የማር መቀመሚያ፣ ግማሽ ማዳበሪ ጨው ፣ ጨው መሰል የውሃ ማጣሪያ ባዕድ ነገር፣ 45 ኪሎ ግራም ስኳር፣እንዲሁም ቅቤ 228 መዳበሪያ ባለ 50 ኪሎ ግራም ፣ አራት ካርቶን ቅቤ ፣ 14 ባልዲ/ አንዱ ባልዲ 24 ኪሎ ግራም የሚይዝ/ 96 ባልዲ ቪክተቢል (የቅቤ መቀመሚያ)፣ 35 ባልዲ ቦቼ የሚረጋ ዘይት እንደተያዘባቸው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በማህበራዊ ሚዲያው ገልጾአል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት በሰበታ ፣ ፉሪ ፣ መርካቶ ይርጋ ኃይሌ አካባቢ፣ አውቶቡስ ተራ ፣ ዳንኤል ሆቴል አካባቢ፣ እህል በረንዳ ፣ ወለጋ ሆቴል አካባቢ፣ አሰፋ ፍለታ ሆቴል አካባቢ፣ ጎጃም በረንዳ አካባቢ፣ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አዲሱ ሚካኤል አካባቢ፣ ጉለሌ ደቻስ ገነሜ ትምህርት ቤት አካባቢ፣ ሲሆን በወንጀል የተጠረጠሩት 72 ግለሶች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል። ያለው ፖሊስ ህብረተሰቡ ለበዓል የሚያስፈልጉትን መጠቀሚያዎች በሚሸምትበት ወቅት ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል፡፡

Via:- ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa
የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና አግባብነት ኤጀንሲ መዋቅሩ ለስራው ማነቆ እንደሆነበት አስታወቀ፡፡ መዋቅሩ እንዲሻሻል ጥያቄ ቢያቀርብም መፍትሄ እንዳላገኘ ጠቅሷል፡፡

በኤጀንሲው የዕውቅና አሰጣጥ ዳይሬክተር አቶ አብይ ደባይ እንደገለፁት፤ የኤጀንሲው መዋቅር ለስራቸው ማነቆ በመሆኑ ይህንኑ ለማስተካከል ባለፉት አራት ዓመታት አጥንተን ማስተካከያ ለማድረግ ለሚመለከታቸው አካላት ተደጋጋሚ ጥያቄ ብናቀርብም መፍትሄ አልተሰጠንም ብለዋል።

በአገሪቱ ላለው የትምህርት ጥራት ችግር በህዝብና በመንግስት መግባባት ተደርሶበታል ያሉት አቶ አብይ፤ ከችግሩ ምክንያቶች መካከል ባለፉት ዓመታት በትምህርት አግባብነትና ጥራት ላይ በሚፈለገው ደረጃ ቁጥጥርና ክትትል አለመደረጉ አንዱ ነው ብለዋል።

Via:- EPA
@YeneTube @Fikerassefa
የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርጎ #አቅጣጫ ማስቀመጡን የፓርቲው ዋና ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

ስራ አስፈፃሚው በሃይማኖትና በትምህርት ተቋማት ጥቃት ዙሪያ እንዲሁም በዘንድሮው ምርጫ ላይ መክሮ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

የፓርቲው ዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ወቅታዊ በሆኑ ጉዳዮች ውይይት ማድረጉን ተከትሎ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት፤ በአገሪቱ የሰላም እና የፀጥታ እንዲሁም በወቅታዊ ጉዳዮች ጥልቅ ውይይት ተደርጓል።

በሃይማኖትና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ በቡድንና በተናጠል በተደራጀ መልኩ ጥቃት የማድረሱ ዘመቻ እየተባባሰ መጥቷል። ይህ እኩይ ተግባር የኅብረተሰቡን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ችግር ውስጥ እንደሚከት ስራ አስፈፃሚው ገምግሟል።

Via:- EPA
@YeneTube @Fikerassefa
ለፖለቲካ ትርፍ የወጣቶች ክቡር ህይወት አይቀጠፍ!

“ወጣቶች ብልጽግናን ከወደዳችሁት ካርዳችሁን ስጡት፤ በልጽግናን ከጠላችሁት በድምጽ ቅጡት። ህይወታችሁን ለእኛም ሆነ ለየትኛውም ፓርቲ አትስጡ፤ ይሄ ትክክል አይደለም። በድምጽ የምትፈልጉትን ምረጡ የማትፈልጉትን ተው እንጂ ህይወታችሁን ፈጽሞ አትገብሩ! እስካሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ልምድ በእናንተ ዕድሜ እንኳ የምታውቁት ከምርጫ ጋር ተያይዞ የሚመጣውን ጦስ ብታዩት ፖለቲከኞች ወንድሞቻቸው፣ ልጆቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው ምንም አልሆኑም፤ የድሃ ልጅ ግን ተቀጠፈ።

ያ የድሃ ልጅ ማንም አያስታውሰውም እናት ናት ያለጧሪ የቀረችው። በቅርቡም ሁልጊዜ የምታዩት ወጣቱን ገፋፍተው የሚወስዱ ኃይሎች ሲሞቱ አይታዩም ሲያጋድሉ እንጂ። የእናንተም ህይወት የእነሱም ህይወት አንድ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ወጣት ስለሆናችሁና ከእነሱም የመሻል ተስፋ ስላላችሁ ለማናችንም ቢሆን ካርዳችሁን እንጂ ህይወታችሁን መስጠት የለባችሁም።”

ይህን እጅግ ወሳኝ፣ ወቅታዊና በተለይም ወጣቱ የኅብረተሰብ ክፍል በልዩ ሁኔታ በአዕምሮው ውስጥ ሊያሰቀምጠው የሚገባውን ንግግር የተናገሩት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶክተር አብይ አህመድ ናቸው።

Via:- EPA
@YeneTube @Fikerassefa
#Breaking

በ440 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ ተወሰደ

በመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተከሰቱ ግጭቶች ውስጥ ተሳትፈዋል በተባሉ 440 ተማሪዎች ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን የሳይንስ ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመሆን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እያጋጠሙ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት አየተከናወኑ ባሉ ስራዎችና ቀጣይ እርምጃዎች ላይ መግለጫ ሰጥቷል።

እርምጃው ከማስጠንቀቂያ ጀምሮ ከትምህርት ገበታቸው እሰከማገድ የሚደርስ ቅጣት የሚደርስ መሆኑም ተመልክቷል።

በዚህ መሰረት እርምጃ ከተወሰደባቸው ተማሪዎች ውሰጥ ከ170 በላይ የሚሆኑት የአንድ ዓመት እገዳና ሙሉ በሙሉ ከተቋማቱ ማባረርን ያካትታል።

ከ270 በላይ ተማሪዎች ደግሞ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ሳሙሄል ክፍሌ ተናግረዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በ10 መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ላይም እርምጃ መወሰዱን ጠቁመዋል።

ባለፈው ጥቅምት ወር በወልዲያ ዩኒቨርስቲ በተማሪዎች መካከል በተከሰተ ግጭት የተማሪዎች መሞትን ተከትሎ በሌሎች የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች አለመረጋጋቶች እየተስተዋሉ መሆኑ ይገለጻል።

ምንጭ፡- ኢዜአ
@YeneTube @Fikeeassefa
በአፍሪካ ከፍተኛ የተሳታፊ ቁጥር የታየበት የማስ ስፖርት በአዲስ አበባ ተካሄደ

ዛሬ ጠዋት የተካሄደው 6ኛው የብዙሃን ስፖርት መርሃ ግብር ብዙ ሰው በማሳተፍ በአፍሪካ የመጀመሪያ የማስ ስፖርት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

የኢፌድሪ ስፖርት ኮሚሽን ከተማዋ በማስ ስፖርት ላስመዘገበችው ድል የእውቅና የምስክር ወረቀት አበርክተዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ አዲስ አበባ ይህን ድል እንድትቀዳጅ ለሰሩ ፣ ላስተባበሩ እና ለተሳተፉ ሁሉ ምስጋናውን እንደሚያቀርብ ከምክትል ከንቲባ ጽ/ ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Via:- EPA
@YeneTube @Fikerassefa
በዩኒቨርስቲዎች በተከሰቱ ግጭቶች የተሳተፉ ከ170 በላይ ተማሪዎች የ1 ዓመት እገዳና እስከ መጨረሻ ከትምህርታቸው እንዲሰናበቱ ተደረገ

በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተከስቶ በነበረው ግጭት እጃቸው አለበት ተብለው በተለዩ ከ450 በላይ በሚሆኑ ተማሪዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱ ተገለፀ፡፡

በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተከስቶ የነበረውን ግጭት እና ሁከት አስመልክቶ የሳይንስ እና ከፍተኛ የትምህር ሚኒስቴር ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመሆን መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

መግለጫውን የሰጡት የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ እና የፌዴራል ፓሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፈንታ ናቸው፡፡

በመግለጫውም ባለፉት 15 ቀናት ብቻ ከ170 በላይ ተማሪዎች ከአንድ አመት እስከ መጨረሻ የሚደርስ የማባረር አስተዳደራዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ተጠቁሟል፡፡
እንዲሁም ከ280 በላይ የሚሆኑት ተማሪዎች ላይ ደግሞ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡

በሁከቱ የደረሰውን ችግር መፍትሄ እንዲያገኝ ለማድረግም ፌዴራል መንግስት እና ክልሎች እንዲሁም ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ከተውጣጡ አካላት ጋር በመሆን ግምገማ ሲደረግ መቆየቱ ነው የተነገረው፡፡

በተደረገው ግምገማም ለሁከቱ እና ለችግሩ ምክንያት ናቸው ተብለው በተለዩ አካላት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲውሰድ ተደርጓል ተብሏል፡፡

በዚህም በወንጀል የተሳተፉትን በህግ ተጠያቂ ማድረግ እንደተጠበቀ ሆኖ የትምህርት ተቋማቱ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዳቸው በመግለጫው ላይ ተነስቷል፡፡

በችግሩ ተሳትፈዋል ተብለው ከተለዩ ተማሪዎች ባለፈም መምህራን እና የትምህርት ተቋማቱ የአስተዳደር ሰራተኞች ተሳታፊ እንደነበሩ መለየት መቻሉ ተጠቁሟል ፡፡
ይህንን ተከትሎ ከአስር በላይ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች የስራ ውላቸው ተሰርዟል ነው የተባለው፡፡

አሁን ላይ የተወሰኑት የትምህር ተቋማት ሙሉ በሙሉ ወደ መደበኛ የመማር ማስተማሩ ሂደታቸው መመለስ መቻላቸውም ተነስቷል፡፡

ቀሪውን የትምህርት ጊዜ ወደነበረበት ሰላማዊ ሁኔታ ለመመለስም ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በመሆን የክትትል ስራ ይሰራል ተብሏል፡፡

አሁን ላይ የሚታዩ ግጭቶች በትምህርት ተቋማቱ ብቻ ተወስነው ሊቀሩ እንደማይችሉ በመገንዘብ ለሚደረገው ሰላምን የማረጋገጥ ስራ ህብረተሰቡም የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል፡፡

Via:- FBC
@YeneTube @Fikerassefa
ህወሓት ከብልፅግና ፓርቲ ጋር እንደማይዋሃድ ታውቋል

ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ/ህወሃት/ ከብልጽግና ፓርቲ ጋር እንደማይዋሃድ አስታወቀ። ድርጅቱ ለሁለት ቀናት ያካሔደውን ጉባኤ ዛሬ ሲያጠናቅቅ ባወጣው የአቋም መግለጫ ከብልጽግና ፓርቲ ጋር የዓላማና የመስመር ልዩነት ስላለው እንደማይዋሃድ አስታውቋል።

ከፌዴራል መንግስት ጋር የሚኖረው ግንኙነትም ህግና ህገ-መንግስትን መሰረት ያደረገ እንደሚሆን ያመለከተው መግለጫው ከዚህ ውጭ የሚኖር እንቅስቃሴ ተቀባይነት እንደማይኖረው አመልክቷል።

ኢህአደግን የመሰረቱ የአራቱ ድርጅቶችን የጋራ ሀብት ህግና ስርአት በተከተለ መንገድ ድርሻውን እንደሚያስመልስም በአቋም መግለጫው አስታውቋል።

የኢህአዴግን መፍረስ ተከትሎ ህወሓት ከሌሎች ፈዴራላዊ ሀይሎች ጋር በፎረም፣ በጥምረትና በግንባር ደረጃ ስትራተጂካዊ ግንኙነት ለመመስረት መወሰኑንም ገልጿል።

Via:- ENA
@YeneTube @Fikerassefa
የክልሎች ግንኙነት ረቂቅ አዋጅ ላይ ለመወያየት የአንድም ክልል ተወካይ አልተገኘም!

በክልሎች ግንኙነት ላይ ያተኮረ ረቂቅ አዋጅ ላይ ለመወያየት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጥሪ ቢያቀርብም የአንድም ክልል ተወካይ አልተገኘም።የፌዴሬሽን ምክር ቤት ክልሎች ከክልሎች ጋር እንዲገናኙ ሲሠራ የሕግ መሠረት አለመኖሩ፤ ፈቃደኛ ያልሆኑ ክልሎችን ማገናኘት እንዳይቻል ማድረጉን የፌዴሬሽን ምክር ቤት ገልጿል።የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፍትህ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢው አቶ አበበ ጉዴቦ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ የክልል መንግሥታት እና ክልሎች ከፌዴራል መንግሥት ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት ላይ ያተኮረ ረቂቅ አዋጅ ለቋሚ ኮሚቴው ከተመራ ስድስት ወራትን አስቆጥሯል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
7 የውጭ ዜጎች ጥራታቸውና ፈዋሽነታቸው ያልተረጋገጡ ምርቶችን በባዛሮች ሲሸጡ በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ስምንት ዓይነት ያህል የባህላዊ መድኃኒቶች ጸጉርን ለማከምና ለማሳጅ ይረዳል በሚል ሲሸጡ በመገኘታቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተጠቁሟል፡፡በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እነዚህ ምርቶች ያልተመዘገቡ፣ የማይታወቁ ፣ጥራትና ደህነንነታቸው ያልተረጋገጠ በመሆኑ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም አሳስቧል፡፡ ባለስልጣኑ በድንገተኛ ቁጥጥሩ ወቅት የያዛቸው እና ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ያሳሰበው ምርቶችም

📌ካስቱሪር ሄርባል ሄር ( KASTURIR HERBALHAIR )
📌ንላንባሪ ካስቱራ ሄርባል ( NEELAMBARI KASTURA HERBAL )
📌ንላምባሪ ሄርባል ኦይል ( NEELAMBARI, HERBAL OIL )
📌ንላምባሪ ሄርባል ( NEELAMBARI, HERBAL)
📌ኤች ኤች አይ ኤን ኬ ኤን አይ ( HHINKNI)
📌ሳንጂቪን ሄርባል አዩስቸር ( SNNSEV,N HYREBALE Ayu)
📌ንላምባሪ ሄርባል ማሳጅ ( NEELAMBARI,HERBAL MASSAGE) መሆናቸውን ገልጾአል፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ቦረና ዞን ያቤሎ ከተማ ገብተዋል!

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቤሎ ሲደርሱ የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎችና ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡በቆይታቸውም ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት የሚያደርጉ ይሆናል፡፡

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
ለዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብና ለወላጆች ጥሪ ቀረበ!

በ170 ተማሪዎች ላይ የአንድ ዓመት ቅጣትና እስከ መጨረሻው ከዩኒቨርሲቲዎች የማባረር እርምጃ ተወስዷል። በኦሮሚያ እና በአማራ ክልል እንዲሁም በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲዎች እየተከሰተ ያለውን ረብሻ ሙሉ ለሙሉ ለማስቆም እና ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሥራን ለማከናወን ለመላው የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብና ለወላጆች ጥሪ ቀርቧል፡፡170 ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዎች የረብሻ ድርጊት ላይ በመሳተፋቸው ለአንድ ዓመት በትምህርት ገበታ ላይ እንዳይሳተፉ ከመቅጣት ጀምሮ እስከ መጨረሻው ከዩኒቨርሲቲዎች የማባረር እርምጃ መወሰዱም ተጠቁሟል፡፡የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን እና የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በጋራ ትናንት መግለጫ በሰጡበት ወቅት፤ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ድኤታው ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ እንደተናገሩት፤ 99 በመቶ የሚሆነው ተማሪ የመማር ፍላጎት አለው።

ምንጭ:EPA
@YeneTube @FikerAssefa
የሰደድ እሳት ባንገበገባት አውስትራሊያ ዝናብ መጣሉ ነዋሪዎችን አስፈንጥዟል!

አውስትራሊያ ሰሞኑን በከባድ የሰደድ እሳት እየታመሰች ትገኛለች፡፡የሀገሪቱ መንግስት እሳቱን ለመቆጣጠር ዘመናዊ የእሳት ማጥፍያ መሳርያዎችን ቢጠቀምም እስካሁን ድረስ እሳቱን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ግን አልቻለም፡፡በሰደድ እሳቱ ሳብያም ከ5 ሚሊየን በላይ እንስሳት የሞቱ ሲሆን በርካቶችን ለስደት ዳርጓቸዋል፡፡ዛሬ ላይ ከወደ አውስትራሊያ የተሰማው ወሬ ዜጎችን እረፍት የሰጠ ነገር ሆኗል፡፡

በሀገሪቱ ባንዳንድ ከተሞች በዋናነትም በሲድኒ እና በሜልቦርን ዝናብ በመጣሉ ምክንያት የሙቀት መጠኑም እንደቀነሰ ነው የተነገረው፡፡ዝናብ መጣሉን ተከትሎ የሀገሪቱ ዜጎች ደስታቸውን ሲገልጹ ተስተውሏል፡፡የሀገሪቱ ባለስልጣናት ግን ሰደድ እሳቱ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ያልተቻለ በመሆኑ አሁንም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሰስቧል፡፡በሀገሪቱ ዝናብ ከጣለ በኃላም ምንም አይነት የእሳት አደጋ የማስጠንቀቂያ ድምጽ እንዳልተሰማ ነው ቢቢሲ ያተተው፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
2020 so far:

- US killing of Qassem Soleimani

- Floods in Indonesia

- Ongoing Australian bushfire crisis

- Conflict in Libya

- Bomb attack in Burkina Faso

- Continued protests in India and Hong Kong

- Knife attack in Paris

- Interpol warrant for Carlos Ghosn
@YeneTube @Fikerassefa
"ኑ የታመሙትን እንጠይቅ ያለንን እንካፈል"

ሮትራክት(አርባ ምንጭ) ፣ አምዩ ቻሪቲ ፣ቀይ መስቀል ማህበር ፣ አርባ ምንጭ ወጣቶች ማህበር እንዲሁም ፒስ ሞዴል ኢቨንት ቤተሰቦች በገና በዓል ዕለት ከጠዋቱ 3:30 ጀምሮ አርባ ምንጭ ሆስፒታል በበዓሉ ዕለት የታመሙትን ይጠይቃሉ ለህፃናቶችም ስጦታን ይለግሳሉ

ከ6:00 ሰዓት ጀምሮ ከአቅም ከሌላቸው ጋር ምሳን ይቋደሳሉ የአልባስትም ድጋፍ ይደረጋል

"ኑ አብረን ወገኖቻችንን እንጠይቅ እርሶም በበዓሉ ዕለት የታመሙ ወገኖቻችንን እንጠይቅ"
በገላን የወንዶች አዳሪ ት/ቤት የ17 አመት ተማሪ ባልታወቀ ምክንያት ከፎቅ ላይ ወድቆ ሞተ ።

ሰዎች ገፍተረውት ወይን እራሱ ወድቆ ይሁን ባልታወቀ ምክያንት በገላን የወንዶች አዳሪ ት/ቤት ዩሀንስ አበራ የተባለ የ17 አመት ተማሪ ባለፈው ሀሙስ ታህሳስ 23 ከፎቅ ላይ ወድቆ የተገኘ ሲሆን በጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል ህክምና ቢደረገለትም ሒወቱ ማትረፍ ሳይቻል ቀርቷል።የቀብር ስነስርአቱም አርብ አዲስ አበባ ውስጥ ተፈፅሟል።
የተማሪው ቤተሰቦች በስልክ እንደነገሩኝ እስከ አሁን የሞቱን መንስኤ እንዳላወቁና ሟቹ ግን ከመሞቱ አንድ ቀን እስቀድሞ ስልክ ደውሎ ቀድሞ ከተማረበት ት/ቤት መሸኛ ስላልወሰደ ቅዳሜ ቤት እንደሚመጣና ጉዳዮን ጨርሶ ወደ ት/ቤት እንደሚመለስ ነግሮን ነበር ብለዋል።
ሟቹ የአስረኛ ከፍል ውጤቱ አራት ነጥብ ያመጣ ሲሆን 11 ክፍል ትምህርቱን በወንድይራድ ት/ቤት እየተከታተለ እያለ መንግስት በዚህ አመት በጀመረው በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን በአንድ የትምህርት ማእከል በሚያስተምረው ፕሮግራም ለመማር ከሶስት ሳምንት በፊት ነበር ወደ ገላን ት/ቤት ገብቶ መማር የጀመረው።

Via:- tsefay Getinet
@YeneTube @Fikerassefa
ፖሊስ ለበዓሉ በቂ ዝግጅት ማድረጉን ገለፀ

የገና በዓል በሰላም እንዲከበር በቂ ዝግጅት ማድረጉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

በኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ሀላፊ ዋና ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ ለጣቢያችን እንደተናገሩት፥ ፖሊስ ኮሚሽኑ ለበዓሉ በቂ ዝግጅት አድርጓል።

የፖሊስ አባላትም ሰዎች በሚበዙባቸው የግብይት ቦታዎች እና የትራፊክ ፍሰት በሚበዛባቸው አካባቢዎች ተሰማርተዋል ነው ያሉት።

በተለይም ስርቆት፣ ቅሚያ፣ ማታለል እና ባዕድ ነገር ከምግብ ጋር ቀላቅሎ መሸጥ በበዓል ግብይት ጊዜ ሊከሰቱ የሚችሉ ወንጀሎች በመሆናቸው ህብረተሰቡ ለግብይት ሲወጣ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል።

@YeneTube @Fikerassefa
እንኳን ደስ አለን❗️

ትናንት በቻይና በተደረገው የዢያሜን ዓለም አቀፍ ማራቶን ኢትዮጵያውያኑ አትሌት መዲና ደሜ እና አትሌት ብርሃን ነበበው አሸንፈዋል።

@YeneTube @Fikerassefa
የአርባምንጭ ቤተሰቦቻችን በዓሉን በበጎ ተግባር ያሳልፉ ዘንድ በክብር ተጠርታችኀል!

ሮትራክት(አርባ ምንጭ) ፣ አምዩ ቻሪቲ ፣ ቀይ-መስቀል ማህበር ፣ የአርባምንጭ ከተማ ወጣቶች ማህበር እና የኔቲዩብ እንዲሁም ፒስ ሞዴል ኢቨንት ቤተሰቦች በገና በዓል ዕለት ከጠዋቱ 3:30 ጀምሮ አርባ ምንጭ ሆስፒታል በበዓሉ ዕለት የታመሙትን ይጠይቃሉ ለህፃናቶችም ስጦታን ይለግሳሉ፡፡ ከ6:00 ሰዓት ጀምሮ ከአቅም ከሌላቸው ጋር ምሳን ይቋደሳሉ የአልባስትም ድጋፍ ይደረጋል

ምሳ ቦታ፦ሲቀላ ቀይ መስቀል ማህበር ግቢ ውስጥ

#share

@YeneTube @Fikerassefa
የእስር ጊዜያቸውን ቢጨርሱም 75 ኢትዮጵያዊያን በታንዛኒያ እስር ቤት ውስጥ እንደሚገኙ ተገለጸ

በተለያዩ ወንጀሎች ተከሰው እና የዕስር ቅጣት ተጥሎባቸው በታንዛኒያ እስር ቤት የሚገኙ 75 ኢትዮጵያዊያን የዕስር ጊዜያቸውን ቢያጠናቅቁም ከእስር አለመፈታታቸው ታወቀ። በታንዛኒያ የማትዋራ ግዛት የቀጠናው ኮሚሽነር ጌላሲስ ባይካናዋ የዕስረኞችን ቅሬታ ባዳመጡበት ወቅት ኹለት ዓመታ ብቻ የዕስር ቅጣት ተጥሎባቸው የነበሩ 75 ኢትዮጵያዊያን የዕስር ጊዜያቸውን ቢያጠናቅቁም አሁንም በዕስር ላይ እንደሚገኙ እንደተገለፀ ጋርዲያን ኮሚሽሩን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

ከዚሁ በተጨማሪም በእስር ላይ የሚገኙት ታራሚዎች ከፈፀሙት ወንጀል በተለየ በሌላ እና ባለፈፀሙት ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸው እንደታሰሩም ቅሬታቸውን ለቀጠናው ኮሚሽር ባቀረቡበት ወቅት ተናግረዋል። ቅሬታ አቅራቢዎች የእስር ጊዜያቸውን ማጠናቀቃቸውን ተናግረው የታንዛኒያ መንግስት ወደ አገራቸው እንዲሸኛቸው ጥያቄያቸውን ማቅረባቸውንም አስታውቀዋል።

Via:- Addis maleda
@YeneTube @Fikerassefa