YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ህወሓት አስቸኳይ ድርጅታዊ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አስቸኳይ ድርጅታዊ ጉባኤውን በመቐለ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል።በጉባኤው ከህወሓት መሰረታዊ ድርጅቶች የተወከሉ አባላት፣ ምሁራን፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።ድርጅቱ እያካሄደ በሚገኘው አስቸኳይ ጉባኤ የኢህአዴግን ውህደት በሚመለከት ተወያይቶ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
532 የረዳት ተማሪ ትራፊክ ፖሊስ አስተናባሪዎች ተመረቁ!

አዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ 532 የረዳት ተማሪ ትራፊክ ፖሊስ አስተናባሪዎችን ዛሬ አስመርቋል።የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ነው ስልጠናውን የሰጠው።የረዳት ተማሪ ትራፊክ ፖሊስ አስተናባሪዎቹ መመረቅ በተለይ በትምህርት ቤቶች አካባቢ የሚደርሰውን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ ድርሻው የላቀ መሆኑን በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
ዜና ሹመት!

ዶ/ር መሐሪ ታደሰ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሆነው ተሾሙ፡፡

ዶ/ር መሐሪ ታደሰ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በአሜሪካው ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ኖርዝ ቴክሳስ ተከታትለዋል፡፡ በ‹ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ቴክሳስ አት ኦስተን› እና በሌሎችም በተመራማሪነት ማገልገላቸውም ታውቋል፡፡ የተለያዩ የምርምር ሥራዎችን በአሜሪካና ካናዳ ማቅረባቸውም በግለ ታሪካቸው ተብራርቷል፡፡ዶ/ር መሐሪ የተለያዩ ዓለማቀፍ የሙያ ማኅበራት አባል መሆናቸውም ነው የተገለጸው፡፡ የአሜሪካ የስታትስቲክስ ማኅበር፣ የአሜሪካ የትምህርት ጥናት ማኅበር፣ የተቋማዊ ጥናት ማኅበር፣ የከፍተኛ ትምህርት ጥናት ማኅበር፣ የደቡብ ምዕራብ የትምህርት ጥናት ማኅበርና የቴክሳስ የትምህር ጥናት ማኅበር አባል እንደሆኑም ነው የተገለጸው፡፡ከ13 ዓመታት የአሜሪካ ቆይታ በኋላ ባለፉት አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ በተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በምርምርና የተለያዩ ትምህርቶችን በማስተማር እንደቆዩም ተገልጿል፤ በተለያዩ የመንግሥት ተቋማት በኃላፊነት ደረጃ ማገልገላቸውም ነው የተነገረው፡፡ ዶክተር መሐሪ ታደሰን ልምዳቸውንና የአመራር ብቃታቸውን ግምት ውስት በማስገባት የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ዛሬ ማካሄድ በጀመረው መደበኛ ጉባኤው የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አድርጎ ሾሟቸዋል፡፡

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
በሞጣ ጉዳት ለደረሰባቸው የእምነት ተቋማት 5.4 ሚሊዮን ብር ተሰበሰበ!

በምሥራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ ጉዳት የደረሰባቸውን የእምነት ተቋማት ለመገንባት በተደረገ የገንዘብ ማሰባሰብ አምስት ነጥብ አራት ሚሊዮን ብር በጥሬ ገንዘብ የተገኘ ሲሆን 725 ሺህ ብር ቃል ተገብቷል።ገንዘቡ የተገኘው ከባለሀብቶች፣ ከግለሰቦች፣ ከመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ ከተለያዩ ማህበራት እና ከእምነት ተቋማት ነው።የሞጣ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት የህዝብና ሚዲያ ግንኙነት ኃላፊ አቶ መንግስቱ አለማየሁ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ አቶ ወርቁ አይተነው የተባሉት ባለሀብት ቃል የገቡትን አምስት ሚሊዮን ብር በተከፈተው የባንክ ሒሳብ አስገብተዋል።

የሞጣ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽሕፈት ቤት 100 ሺህ ብር፣ የሁለት እጁነሴ ወረዳ አስተዳደር 500 ሺህ ብር፣ የማቻከል ወረዳ አስተዳደር 50 ሺህ ብር ቃል የገቡ ሲሆን ከአዋበል ወረዳ የተውጣጡ ዕድሮች 42 ሺህ 200 ብር በጥሬ ገንዘብ ገቢ አድርገዋል።በሌላ በኩል የአዋበል ወረዳ ቤተ ክህነት 10 ሺህ ብር ለመስጠት ቃል የገባ ሲሆን በሞጣ ከተማ ውስጥ የሚገኝ አንድ ወጣትም 65 ሺህ ብር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብቷል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
መልካም ወጣት ለዎላይታ በረከት በሚል መሪ ርዕስ በዎላይታ ሶዶ ከተማ በሚካሄደው የመልካም ወጣት ማስተባበሪያ ማዕከል ግንባታ መሠረተ ድንጋይ የሚቀመጥበትን ልዩ ዝግጅት አስመልክቶ በከተማዋ የተለያዩ ፕሮግራሞች እየተከናዎኑ ይገኛሉ፡፡ የሩጫ፤ ችግኝ ተከላ እና ሌሎች በመልካም ወጣት የታጀቡ ትዕይንቶች ተከናውነዋል።

-የዎላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ህዝብ ግንኙነት ዩኒት
@YeneTube @FikerAssefa
ኢ/ር ታከለ ኡማ በመሃል አዲስ አበባ ጎተራ አከባቢ የሚገነባውን የአሚባራ መንደር ግንባታ በዛሬው ዕለት አስጀምረዋል፡፡

ይህ ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር በአፋር ባለሃብቶችና በከተማ አስተዳደሩ በጋራ የሚገነባ ሲሆን የ35ሺ ካሬ ሜትር ነባር ይዞታቸው ላይ የከተማ አስተዳደሩ 15ሺ ካሬሜትር ይዞታ በመጨመር በድምሩ በ50 ሺ ካሬሜትር መሬት ላይ የሚገነባ ይሆናል፡፡ዘመናዊ የመኖሪያ መንደሩ በውስጡ ከ450 በላይ የመኖሪያ አፓርትመንቶችን ጨምሮ የገበያ ማዕከላት፣ ሆቴል፣ ተመራጭ የመዝናኛና የንግድ ማዕከል ፣ ኣረንጓዴ ስፍራዎች እና የአፋር ባህል ማዕከልን ያካተተ ነው፡፡ግንባታው በ11 ቢሊዮን ብር የሚከናወን ሲሆን ከ10 ሺ በላይ ለሚሆኑ የከተማችን ወጣቶች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ ዕድል የሚፈጥር ይሆናል።

ምንጭ: የከንቲባ ጽ/ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ "የሀላባ ብሄረሰብ ዘመን መለወጫ ሴራ በዓል" በደማቅ ስነ-ስረዓት ተከበረ።

@YeneTube @FikerAssefa
ብልፅግና ፓርቲ ምርጫው በዚህ አመት እንዲካሄድ ጠንካራ አቋም አለው - አቶ ብናልፍ አንዷለም

የብልፅግና ፓርቲ የ2012 ብሄራዊ ምርጫ በያዝነው አመት እንዲካሄድ ጠንካራ አቋም መያዙን አስታውቋል። የፓርቲው የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ትናንት በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ እና በሀገራዊ ምርጫው ዙሪያ ተወያይቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን ማሳለፉንም ነው የፓርቲው ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ የጠቆሙት።ብልፅግና ፓርቲ በምርጫው ዙሪያ የአቋም ለውጥ አላደረገም ያሉት ሀላፊው፤ ፓርቲው ምርጫው በዚህ አመት መካሄድ አለበት የሚል እምነት እንዳለው አብራርተዋል።

ይህ ማለት ግን ፈታኝ ነገሮች የሉም ማለት አይደለም፤ ስራ አስፈፃሚው በስብሰባው የምርጫው ስጋቶች እና መልካም እድሎች ዙሪያ በስፋት መክሮ የመፍትሄ ውሳኔዎችን ማሳለፉን ነው አቶ ብናልፍ ያነሱት።ብልፅግና ፓርቲ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሆነ ህብረተሰቡ ከምርጫው መካሄድ ጋር ተያይዞ የሚያነሷቸው ስጋቶችን እንደተወያየባቸው የጠቀሱት ሀላፊው፤ የምርጫው መካሄድ አልያም መራዘም የሚያስገኛቸው ጥቅሞች እና ጉዳቶች ላይ በስፋት መምከሩን ተናግረዋል። “ምርጫው ወቅቱን ጠብቆ የሀገሪቱን የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ እውን ለማድረግ ያግዛል፤ ህብረተሰቡ የመረጥኩት መንግስት ነው የሚያስተዳድረኝ የሚል እምነት እንዲኖረውም ያደርጋል” ነው ያሉት አቶ ብናልፍ በመግለጫቸው።

በብዙ መለኪያዎች ምርጫው ቢካሄድ የተሻለ መሆኑን በስራ አስፋፃሚው ስብሰባ ገምግመናል ያሉት ሃላፊው፤ በሀገሪቱ አሁን ላይ የሚታዩ ችግሮችን ግን በቀላሉ አናያቸውም ብለዋል። ብልፅግና ፓርቲ የቀደመ አቋሙን ያፀናው ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ከተወጣ ችግሮቹን መፍታት እንችላለን ከሚል መነሻ እንጂ ችግር የለም ከሚል አይደለም ሲሉም ተናግረዋል።የፀጥታ ችግሮቹን ለመፍታት የፀጥታ እና የፍትህ ተቋማት ሀላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል፤ ህብረተሰቡም አጥፊዎችን በማጋለጥ የሰላም ቀናኢነቱን አሁንም አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ነው ያሉት ሀላፊው።

ተፎካካሪ ፓርቲዎችም አባላት እና ደጋፊዎቻቸውን ሰላምን ከሚያውኩ ተግባራት እንዲያርቁ የበኩላቸውን ሀላፊነት እንዲወጡ ጠይቀዋል።ህዝቡ የሚወከልባቸው ፓርቲዎች ሀላፊነታቸውን ካልተወጡ ምርጫው ቢራዘምም ችግሩ የመቀጠል እድሉ ሰፊ መሆኑን ነው ያብራሩት።የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በትናንትናው ስብሰባው የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ ሀገሪቱን ወደ ተሟላ መረጋጋት ለመመለስ በየደረጃው ያሉ የፀጥታ መዋቅሮች ፀጥታ የማስከበር ሀላፊነታቸውን በሚገባ እንዲወጡ አቅጣጫ አስቀምጧል።ስራ አስፈፃሚው በብልፅግና ፓርቲ የ10 አመት እቅድ ላይም ዝርዝር ውይይት አካሂዶ አፅድቆታል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ትምህርት ሚኒስቴር የሥርዓተ-ትምህርት ዝግጅትና ትግበራን ከሙከራ እስከ ትግበራ ድረስ ያሉትን ሂደቶች በተሳካ ሁኔታ ለመፈጸም እንዲቻልኝ ይህንን መርሃ-ግብር አዘጋጅቻለው ብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
1443 ኢትዮጵያውያንን ከታንዛኒያ እስር ቤቶች በማስፈታት ወደ አገር ቤት ለመመለስ ዝግጅቱ ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ የማግጓጓዝ ስራው ይጀመራል ። ይህ በእንዲህ እንዳለ በታንዛኒያ መንግሥት በአስቸኳይ ከታንዛኒያ እንዲወጡ የታዘዙ 20 ዜጎቻችን ቅድሚያ በመስጠት ዛሬ ጠዋት ከዳሬሰላም ተነስተው አዲስ አበባ እንዲገቡ ተደርጓል ።

ምንጭ: በዳሬሰላም የኢትዮጵያ ኤምባሲ
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ በየቀኑ 65 ሰዎች በኤች አይ ቪ ቫይረስ እየተያዙ ነው ተባለ።

የፌደራል የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር ፅ/ቤት ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ ከጤና ሚንስትር የስራ ሀላፊዎች እና በህመሙ ዙሪያ ከሚሰሩ ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል።በመድረኩ እንደተነገረውም በሀገሪቷ በቀን ቢያንስ 65 ሰዎች በኤች አይ ቪ ቫይረስ የሚያዙ ሲሆን 30 ያህል ወገኖች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ይሞታሉ።የፅህፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ፅጌረዳ ክፍሌ እንዳሉት በ2030 በኤች አይ ቪ ዙሪያ ለማሳካት እቅድ ከተያዙ ጉዳዮች መካከል ከእናት ወደ ልጅ ያለውን የስርጭት መጠን ዜሮ ማድረስ ዋነኛው ነው።

ከእናት ወደ ልጅ የሚስተዋለው የስርጭት መጠን መቀነስ ይቅርና እየጨመረ መሆኑን ተናግረው አሁን ላይ ያለው ከእናት ወደ ልጅ የቫይረሱ የስርጭት መጠን ከ60 በመቶ ወደ 71 በመቶ ማደጉን ተናግረውል።ዳይሬክተሯ የቫይረሱን የስርጭት መጠን በሴቶች ላይ 1ነጥብ 2 በመቶ በወንዶች ደግሞ 0ነጥብ 6 በመቶ መሆኑም ተናግረዋል። የቫይረሱ አጠቃላይ ስርጭት ደግሞ በከተሞች 2 ነጥብ 9 ሲሆን በገጠር 0 ነጥብ 5 በመቶ መሆኑንም ሃላፊዋ ተናግረዋል።በቀጣይ የስርጭት መጠኑ በስፋት የሚታይባቸው ቦታዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበትም ጠቁመዋል።

ምንጭ: ደቡብ ቲቪ
@YeneTube @FikerAssefa
የኤሊክትሮኒክስ አንድ መስኮት አገልግሎት ሥርዓት ዛሬ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት ተመርቆ ወደስራ ገብቷል፡፡

ፕሮግራሙ ተመርቆ በይፋ ስራ በጀመረበት ወቅት ንግግር ያደረጉት የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፤ የኤሊስትሮኒስ አንድ መስኮት አገልግሎት ሥርዓት በዓለም አቀፍ ንግድ አገልግሎት ረገድ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ተግባራዊ እየተደረገ ያለ ፕሮጀክቶ ሲሆን በዘርፉ ተሳታፊ የሆኑ ተቋማትን የአሠራር ሂደቶች በማቃለልና በማቀናጀት በአንድ የኤሌከትሮኒክ ማዕቀፍ ለተገግልጋዮች የሚያቀርብ ሥርዓት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ትናንት ምሽት ወደ መቀለ ለመጓዝ ወደ ቦሌ ኤርፖርት ቢያመራም በመንግስት ጉዞ እንዳያደርግ መከልከሉንና ለሰዐታት መታሰሩን ተናግሯል።

Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
6ኛው የብዙሃን ስፖርት በአዲስ አበባ
ነገ ጠዋት መስቀል አደባባይ ይካሄዳል።

@YeneTube @FikerAssefa
"አዲሱ ኤክሳይዝ ታክስ ታስቦ የተዘጋጀ ነው ።አሮጌ መኪና ማከማቻ አይደለንም " ጠ/ሚ አብይ።

ዛሬ ከባለሀብቶች በቢሯቸው የተገናኙት ጠ/ሚ አብይ አህመድ አዲስ የተዘጋጀው ኤክሳይዝ ታክስ "የሀገራቷን ነባራዊ ችግር ያገናዘበ ነው ።አሮጌ መኪና እያስገባን በጭስ ምንበከልበት ፣ሲጃራ በገፍ እያስገባን ከመድሀኒት እኩል ለዶላር ወረፋ የምንጋፋበት ምክንያት የለም ብለዋል።ሀገሪቷ ኢኮኖሚ በጤናማ መልኩ ለማስኬድ አዲሱ የታክስ መመርያ እገዛ ያደርጋል" ብለዋል።

Via Tesfaye Getinet
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግረስ በዚህ አመት ይካሔዳል ተብሎ በሚጠበቀው ምርጫ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትን ሥልጣን ለመያዝ እንዳቀደ ሊቀ-መንበሩ መረራ ጉዲና ተናገሩ።

ፓርቲው በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ አዲሱን ፅህፈት ቤቱን ሲያስመርቅ ባደረጉት ንግግር ፕሮፌሰር መረራ ከተሳካ ኦፌኮ ብቻውን አሊያም ከሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ሥልጣን በመጋራት የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የማቋቋም ዕቅድ እንዳለው ተናግረዋል። «ኦፌኮ ከሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እያዘጋጀን ያለንው ስትራቴጂ ቢያንስ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ሥልጣንን መጋራት፤ ከተሳካልን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትን ማቋቋም ነው። ነገ እና ከነገ ወዲያ ሕዝባችንን ሲያስሩ እና ሲያሰቃዩ የነበሩትን በክብር ወደ ቦታቸው እንዲመለሱ ማድረግ ይኖርብናል።

ከሕዝባችን ጋር ወደ ጀመርንው ትግል መግባት እንፈልጋለን ለሚሉ ደግሞ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንደመሆናችን መጠን እና የብሔራችን አካል በመሆናቸው ጥሪ እናደርግላቸዋለን። ንስሀ ገብተው መመለስ ከፈለጉ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለን እንቀበላቸዋለን። ከሀዲዎች ለነበሩት እና ዛሬም ከሀዲነታቸውን መቀጠል ለሚፈልጉ ሕዝባችንን አሳልፈው ለመስጠት መሬታችንን ለመሸጥ፤ ለማዘረፍ እና ለመዝረፍ ለሚፈልጉ የኦሮሞ አምላክ ይፋረዳችሁ እንላለን» ብለዋል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
ቻይና የኢራንን ጦር አዛዥ የገደለችው አሜሪካ ኃይሏን ያለ አግባብ መጠቀም እንድታቆም አሳሰበች።

የቻይናው ውጭ ጉዳይ ምኒስትር ዋንግ ይ ከኢራኑ አቻቸው ባደረጉት የስልክ ውይይት የአሜሪካ ጦር እርምጃ የዓለም አቀፍ ግንኙነት መሠረታዊ ባህልን የሚጣረስ፤ የመካከለኛው ምሥራቅን ውጥረት የሚያባብስ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በዕለተ አርብ ማለዳ አሜሪካ በሰው አልባ አውሮፕላን ከፈጸመችው ግድያ በኋላ በመካከለኛው ምሥራቅ የሰፈነው ውጥረት ያሳሰባቸው የጀርመን፤ የቻይናና እና የፈረንሳይ ውጭ ጉዳይ ምኒስትሮች ውይይት አድርገዋል።

ኢራን እንደዛተችው የበቀል እርምጃ እንደምትወስድ የሚያምኑ ተንታኞች እና ፖለቲከኞች የሁለቱ አገሮች ፍጥጫ ከመካከለኛው ምሥራቅ ተሻግሮ ዳፋው ለዓለም እንደሚተርፍ አስግቷቸዋል።

Via:- DW
@YeneTube @Fikerassefa
መልካም ዕለተ ሰንበት ይሁንላችሁ።
#ሀረር_ግንብ
እንደተለመደው መረጃዎችን እውነተኛነታችውን እንደተጠበቀ ሳይበርዱ በትኩሱ እናደርሳችዋለን።

ለጓደኛዎ t.me/yenetube ማጋበዝ አይዘንጉ!!
Don't forget to subscriber

https://youtu.be/W0tFAfbklt8