YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.89K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ባንኮች የገጠማቸውን የገንዘብ እጥረት ለማቃለል ብሄራዊ ባንክ 5.5 ቢሊየን ብር ሊያበድራቸው ነው፡፡

ዛሬ ለህትመት የበቃችው የእንግሊዘኛዋ ፎርቹን ጋዜጣ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ባንኮች የገጠማቸውን የገንዘብ እጥረት ለማቃለል ብሄራዊ ባንክ 5.5 ቢሊየን ብር በጨረታ ሊያበድራቸው መሆኑን በፊት ገጿ አስነብባለች፡፡ በጉዳዩ ላይ ከሁለት ሳምንት በፊት ካፒታል ጋዜጣ ግዙፉ መንግስታዊ ተቋም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጨምሮ በሁሉም የገንዘብ ተቋማት ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ዕጥረት መከሰቱን እና ያንን ተከትሎ ባንኮቹ ባልተለመደ ሁኔታ የተቀማጭ ሂሳባቸውን ለማሳደግ አቅም አላቸው የተባሉ አካላትን በማግባባት ላይ ናቸው ስትል መዘገቧ የሚታወስ ነው፡፡

ወቅቱ የኮርፖሬት ግብር መክፈያ እንዲሁም ባንኮች ራሳቸው ለባለ አክሲዮኖቻቸው የትርፍ ክፍፍል እና የታክስ ክፍያ የሚፈፅሙበት በመሆኑ እንዲህ አይነት የገንዘብ ዕጥረት ሊከሰት እንደቻለ ጋዜጦቹ ያነጋገሯቸው የባንክ ኃላፊዎች አስረድተዋል፡፡

አሁን ቀረበ የተባለው 5.5 ቢሊየን ብር ይህንን እጥረት የሚያቃልል እንደሚሆን ተስፋ ተደርጓል፡፡

via:- Sheger Times
@Yenetube @Fikerassefa
የአፍሪካ ህብረት በሶማሊያ ለበርካቶች ሞት ምክንያት የሆነውን የሽብር ጥቃት በማውገዝ አገሪቷን ለማረጋጋት የሚያደርገን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል፡፡

ትላንት በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ሰዎች ለስራ በሚሯሯጡበት ማለዳ መኪና ላይ በተጠመደ ቦንብ በደረሰ የሽብር ጥቃት የ76 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከ90 በላይ ሰዎች ትመቁሰላቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

via- EBC
@Yenetube @Fikerassefa
የዓመቱ ታህሳስ 19 ቀን የሚከበረው የቁልቢ ገብርኤል ንግስ በዓል ዛሬ በደማቅ ስነ ስርዓትና በሰላም መከበሩን የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ ገለጸ።

@Yenetube @Fikerassefa
#ኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (#ኢዜማ) ከፍተኛ አመራሮች ሞጣ ከተማ በመገኘት ባለፈው ሳምንት ጥቃት የደረሰባቸውን የእምነት ተቋማት እና የንግድ ቤቶች ጎበኙ።

ጉብኝቱን ያደረጉት የኢዜማ ሊቀመንበር የሺዋስ አሰፋ እና የሴቶች ጉዳይ ተጠሪ ከውሰር እድሪስ ከአካባቢው የኢዜማ አደራጆች ጋር በጋራ በመሆን ነው።

በጉብኝቱ ወቅት አመራሮቹ በእምነት ተቋማት ላይ እና በንጹሃን ዜጎች ንብረት ላይ በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገልፀው ድርጊቱን አውግዘዋል። ከፍተኛ አመራሮቹ ከተማዋን ለማረጋጋት እና የሃይማኖት ተቋማቱን መልሶ ለመገንባት ከተዋቀረው ኮሚቴ ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን በውይይቱ ላይ ተገኝተው የነበሩ የአካባቢው ባለሃብቶች ለመልሶ ግንባታ የሚሆን እገዛ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።

የከተማው ወጣት በወንድማማችነት ሰላሙን እንዲያስከብር፣ ጥቃቱን ያደረሱ ሰዎች ለሕግ እንዲቀርቡ እና የእምነት ተቋማቱን መልሶ ለመገንባት ሁሉም ማኅበረሰብ የተቻለውን እንዲያግዝ ኢዜማ መልዕክት እንዲያስተላለፍ ከኮሚቴው የቀረበውን ጥያቄ አመራሮቹ በሙሉ ልብ ተቀብለዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
ባለሀብቱ አቶ ወርቁ አይተነዉ ጉዳት ለደረሰበት ለሞጣ ቅድስ ጊዮርጊስ 2 ሚሊዮንና ለመስጊዶች ደግሞ 3 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ ዛሬ ቃል ገቡ። ቃል የገቡትን ማክሰኞ እንደሚያስገቡ ተናግረዋል።

Via:- AMMA
@Yenetube @Fikerassefa
"የኢትዮጵያዊያን የሴቶች እግር ኳስ ተጫዋቾች መሰረታዊ መብቶች እንዲከበሩ እየተደረገ ላለው የሶሻል ሚዲያ ካምፔን ሁላችሁንም ላመሰግን ወዳለው"

የተከበራችሁ!,ድምፃችን እንዲሰማ ከጎናችን ሁኑ 🙏

Via:- Loza Abera | ጀግኒት
@Yenetube @Fikerassefa
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ግጭት ለመቀስቀስ ሞክረዋል ያላቸውን ተማሪዎች እስከ ሁለት አመት ከትምህርት ማገዱን አስታወቀ።

አስተዳደራዊ እርምጃ የተወሰደባቸው በዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ በሚገኙ ተማሪዎች መካከል የብሔር ማንነትን መሰረት ያደረገ ግጭት ለመፍጠር ሙከራ ያደረጉ መሆናቸውን የጅንካ ዩኒቨርሲቲ የኮምዩንኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ዘርጋው ማንአርጎ ለዶይቼ ቬለ ገልጸዋል።አቶ ዘርጋው እንዳሉት አምስት ተማሪዎች ለሁለት አመታት፤ ሌሎች ሰባት ተማሪዎች ደግሞ ለአንድ አመት ከትምህርት ታግደዋል።

አቶ ዘርጋው እንደሚሉት ባለፈው ጥቅምት 30 ቀን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ በተማሪዎች መካከል በሙዚቃ ምርጫ ሳቢያ ከተፈጠረ አለመግባባት በኋላ አሁን ቅጣት የተጣለባቸው ተማሪዎች የተቆራረጡ የፌሮ ብረቶችን ወደ ግቢው ይዘው ገብተዋል፤ ለተማሪዎች የተዘጋጁ ምግቦችንም ደፍተዋል። በዩኒቨርሲው ውሳኔ ከትምህርት ከታገዱት መካከል ሁለቱ የሁለተኛ አመት ተማሪዎች ሲሆኑ የተቀሩት የመጀመሪያ አመት ተማሪዎች ናቸው።

በጂንካ ዩኒቨርሲቲ እርምጃ በተወሰደባቸው ተማሪዎች ሁከት ለመፈጠር ሙከራ ቢደረግም ትምህርት አለመቋረጡን አቶ ዘርጋው ጨምረው ገልጸዋል።

Via:- Dw
@Yenetube @Fikerassefa
በምስራቅ ሸዋ ዞን በዱግዳ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ22 ሰዎች ህይወት አለፈ!

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ወረዳ ዛሬ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ22 ሰዎች ህይወት ማለፉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።የመምሪያው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር አስቻለው አለሙ እንደገለፁት፥ ዛሬ ከቀኑ ስምንት ሰዓት ላይ አደጋው የደረሰው።አደጋው ከባቱ ከተማ ወደ መቂ በመጓዝ ላይ የነበረ የታርጋ መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ተሽከርካሪ በተቃራኒው ከሚመጣ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ጋር በመጋጨታቸው ነው የደረሰው።እንደ ኮማንደር አስቻለው ገለፃ፥ በወረዳው ኦቦኖ ቀበሌ ላይ በደረሰው በዚሁ አደጋ ሾፌሩን ጨምሮ በመለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ/ ሚኒባሱ ውስጥ የነበሩ 22 ሰዎች ህይዎት አልፋል። በአደጋው ህይወታቸው ካለፈ ሰዎች መካከልም አምስቱ ህፃናት መሆናቸውም ታውቋል።የአውቶብሱ አሽከርካሪ ለፖሊስ እጁን መስጠቱን የገለፁት ኮማንደር አስቻለው፥ የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑን አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
Christmas 🎄 gift perfumes
100 ml 👇👇👇👇👇👇
ALL AVILABLE NOW🔥🔥🔥
Contact @kiru04
0931607806

Vercace crystal noir - 1100 birr
Versace bright crystal - 1500 birr
Jadore-1100 birr
YSL -1100 birr
Poison girl dior-1500 birr
Ysl manifesto-1100 birr
Miss dior - 1500 birr
Chanel coco -1100 birr
Dolce &gabaana the one- 1100 birr
Ladi millon - 1100 birr
Vercace dylan blue-1100 birr
Black OPIUM- 1500 birr
Lacoste intense pour femme-1100
Lacoste- 1100 birr
Polo blue - 1100 birr
212 men-1100 birr
Bleu de chanel -1500 birr
Calvin klein eternity -1100 birr
Hugo boss -1100 birr
Giorgio armani-1100 birr
Tom ford -1100 birr
Dior homme-1100 birr
Hugo boss-1100 birr
La casona- 1100 birr
Versace for man -1100 birr
Versace pour homme-1100 birr
Gucci flora-1100 birr
La casona-1100 birr
Dunhill-1100 birr
OLmpea-1100 birr
Gucci flora-1100 birr
Invictus -1100 birr

ALL AVILABLE NOW🔥🔥🔥
Contact @kiru04
0931607806
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEPkyxEP1snCoAkFGw
🎄🎄ታላቅ ቅናሽ 🎄🎄
እንኳን አደረሳቹሁ በአሉን አስመልክቶ ታላቅ ቅናሽ በየቲ ኮስሞቲክስ እንዳያመልጣችሁ አሁኑኑ ሊንኩን በመጫን ቻናላችን ጆይን ያድርጉ

https://tttttt.me/yeticosmo

Yeticosmotics is glad to announce its #holiday discount

1. Apple cider with only 850 br

2. Zara perfume with only 1200 br

2. Tresemme shampoo and
conditioner 1100

3. 1 literJohnson wash and shampoo with only 650 br and we have discount for so many products

Join our telegram channel using

https://tttttt.me/yeticosmo
https://tttttt.me/yeticosmo
💥ማስታወቂያ💥
School of American English

📌ቻይንኛ
📌ፈረንሳይኛ
📌ጀርመንኛ
📌ጣልያንኛ
📌አፋን ኦሮሞ
📌አረብኛ

አንቱታን ባተፈሩ መምህራን እናስተምራለን

አድራሻዎቻችን ⬇️
ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ +251919913021
ፒያሳ ፒያሳ ገበያ ማዕከል +251919913023
22 ጎላጎል ህንፃ 6ተኛ ፎቅ +251919913022


💥💥💥10% Discount 💥💥💥💥

ቅናሹን ለመጠቀም
ይህንን ፓስት screenshot አድርገው መያዝና ስመጡ ማሣየት ይኖርብዎታል

T.me/SCHOOLOFAMERICAN
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የአገልግሎት ክፍያ መጠኔን በ3 እጥፍ ላሳድግ ነው አለ።
ተቋሙ እንዳለዉ በየጊዜዉ እየጨመረ የመጣዉ የማምረቻ ዋጋ ጭማሬ በሚሰጠዉ የአገልግሎት ክፍያ ላይ ጭማሬ ለማድረግ እንዳስገደደዉ አስታዉቋል፡፡

የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራዉ ተሊላ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት፣በ1998 የወጣዉና እስከ 2010 ዓ.ም ድረስ ተግባራዊ የተደረገዉ የክፍያ መጠን እጅግ ዝቅተኛ እንደነበር አስታዉሰዉ፣ከ2010 ጀምሮ መጠነኛ ማሻሻያ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ባለፋት 10 ዓመታት የአንድ ኪሎ ዋት ፐር ሃዎር ዋጋ በአማካይ 7 የአሜሪካን ሳንቲም ይሸጥ የነበረ ቢሆንም እኛ ግን አሁንም በ1 ነጥብ 8 የአሜሪካን ሳንቲም ነዉ እያቀረብን ያለነዉ ብለዋል፡፡

በዚህ ሁኔታ የምሰጠዉን አገልግሎት ተደራሽ ማድረግና ጥራት ማሻሻል ስለማልችል አሁን ያለዉን የአገልግሎት ክፍያን በ3 እጥፍ ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ጉዳዩ ለመንግስት ቀርቦ ማሻሻያዉ ቢፈቀድም ጭማሬዉ ግን በአንድ ጊዜ ከሚሆን ይልቅ እስከ 2014 ድረስ እየተጨመረ በ2014 ላይ የአንድ ኪሎ ዋት ፐር ሃዎር ዋጋ 7 የአሜሪካን ሳንቲም እንዲደርስ ይደረጋል ብሏል ተቋሙ፡፡

ይህም ቢሆን በአለም ደረጃ ዝቅተኛ ዋጋ መሆኑን የተናገረዉ ተቋሙ፣ኤሌክትሪክ ለማመንጨትና ለማሰራጨት የሚወጡ ወጭዎችን ለመተካት እንደማያስችለዉ ገልጿል፡፡

በአዲስ አበባ እና በተመረጡ ስድስት ከተሞች የማሻሻያ ስራ እያከናወነ መሆኑን የገለጸዉ ተቋሙ፣በተለይም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያሉ አምራቾች ላይ የአገልግሎት መቆራረጥ እንዳይኖር ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ አስታዉቋል፡፡

የአገልግሎት ክፍያን በተመለከተ ኢትዮጵያ በአንድ ኪሎ ዋት ፐር ሃዎር 1 ነጥብ 8 የአሜሪካን ሳንቲም ስታስከፍል ጎረቤት ሀገር ኬንያ ለተመሳሳይ አገልግሎት ከ15 የአሜሪካን ሳንቲም በላይ ትጠይቃለች፡፡

Via:- Ethio FM
@yenetube @Fikerassefa
በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ሦስት ትምህርት ቤቶችን ለማስገንባት ቃል ገቡ።

በዋሽንግተን ዲሲ በተዘጋጀው የዳስ ትምህርት ቤቶችን ገጽታ መቀየሪያ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ከ 1ነጥብ 5 ሚሊዬን ብር በላይ ተሰብስቧል።የዳስ ትምህርት ቤቶችን ገጽታ ለመቀየር በዋሽንግተን ዲሲ ዛሬ በተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር የአማራ ተወላጅ ግለሰቦች ሦስት ትምህርት ቤቶችን ለማስገንባት ቃል ገብተዋል፤ በዝግጅቱም በጨረታ ብቻ 51 ሺህ 260 ዶላር ወይም 1ሚሊዮን 538 ሽህ የሚደርስ ብር ተሰብስቧል።

በዋሽንግተን ዲሲ የአማራ ማኅበር ከአልማ ጋር በመተባበር አንድ ትምህርት ቤት፣ ርብቃ ኃይሌ ከኒውዮርክ፣ አንድ ትምህርት ቤት፤ የማያ ሪልስቴት ባለቤት አቶ ዓለማየሁ መኮንት፣ አንድ ትምህርት ቤት ለማስገንባት ቃል ገብተዋል።በሌላ በኩል የቲጂ ሲጋር ባለቤት እና ሥራ አስኪያጅ ትዕግስት ተገኘ፣ ለ100 ህጻናት ማሳደጊያና ማስተማሪያ፣ ለ100 አረጋዊያን መጦሪያ በጎንደር ከተማ ለማስገንባት ቃል ገብተዋል።

በሰሜን አሜሪካ ሰባት ግዛቶች ከሰሞኑ በተካሄዱ ሕዝባዊ ውይይቶች የአማራ ተወላጆች 7 የዳስ ትምህርት ቤቶችን ደረጃቸውን ጠብቀው ለማስገንባት ቃል መግባታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
ባሳለፍነው አርብ ተጠርቶ የነበረው ቡሃላም በአሚሮቹ ትዕዛዝ ለክርስትና እምነት ተከታዮች ዓመታዊው የቁሉቢ ገብርአል በዓል ሲባል ለዛሬ የተላለፈው የድሬደዋ ሰልፍ እየተካሄድ ይገኛል።
@Yenetube @Fikerassefa
ግብጽ በኅዳሴው ግድብ ዙሪያ የሚደረጉ ድርድሮች የሦስቱንም ወገን ጥቅም የማስጠበቅ አላማ እንዳላት ተገለፀ!

የግብጹ ፕሬዘዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ባሳለፍነው ዓርብ ታኅሳስ17/2012 ከግብጽ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች ጋር ባደረጉት ስብሰባ አገራቸው በኅዳሴው ግድብ ዙሪያ በሚደረጉ ድርድሮች ላይ የሦስቱንም ተደራዳሪ አገራት ጥቅም የማስጠበቅ አላማዋን እንድምታስቀጥል ተናግረዋል።ዴይሊ ኒውስ እንደዘገበው በቀጣይ በታኅሳስ 30 እና ጥር 1/2012 በአዲ አበባ በሚካሔደው የመጨረሻው ዙር በህዳሴው ግድብ ዙሪያ በሚደረገው ስብሰባ ላይ ግብጽ በዓባይ ውሃ ላይ የሚኖራትን መብት፣ እንዲሁም በግድቡ የውሃ ሙሊት ላይ ስምምነት ላይ እንደሚደረስ እምነት እንዳላቸው ገለጸው በተመሳሳይም የሱዳን እና የኢትዮጵያñ ጥቅምም እንዲጠበቅ እንደሚሰሩ ታውቋል።ዘገባው አያይዞም አልሲሲ በተወሰኑ መገናኛ ብዙኃን ግብጽ በኅዳሴው ግድብ ውሃ ሙሊት ላይ ያቀረበችውን የጊዜ ገደብ አንስታለች ተብሎ የተሰራጨው ወሬ መሰረተ ቢስ ነው ሲሉ ማጣጣላቸውንም አስታውቋል።

ምንጭ: አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
አዋሽ ኢንሹራንስ 160 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ አገኘ
ከተመሠረት 25 ዓመታት የሆነው አዋሽ ኢንሹራንስ 160 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ባለፈው በጀት ዓመት ማትረፉን አስታወቀ። ትርፉ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ሁሉም ኢንሹራንስ ተቋማት ትልቅ ሲሆን፣ በ32 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር የላቀ ነው።

ኢንሹራንስ ኩባንያው ባለፈው በጀት ዓመት ከ797 ሚሊዮን ብር በላይ አረቦን የሰበሰበ ሲሆን፣ ቁጥሩም ከ123 ሚሊዮን ብር ይበልጣል። ከዚህ ውስጥ 75 በመቶ የሚሆነው ከአጠቃላይ ኢንሹራንስ ፖሊሲ የተገኘ ሲሆን፣ ቀሪው ከሕይወት መድን ፖሊሲዎች የተሰበሰበ መሆኑን የኩባንያው ሪፖርት ያመላክታል።

ድርጅቱ ከሰበሰበው አረቦን ውስጥ የሞተር ኢንሹራንስ ፖሊሲ 62 በመቶ ሲሆን የእሳት አደጋ ኢንሹራንስ በ10 በመቶ ይከተላል። የአዋሽ የተከፈለ ካፒታል 425 ሚሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም ከባለፈው በጀት ዓመት በ148 ሚሊየን ብር የላቀ ነው።

የአዋሽ አጠቃላይ ሃብት 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ ባለፈው በጀት ዓመት ለባለ አክሲዮኖች የሚከፍለው ድርሻ ክፍፍል 38 በመቶ ደርሶ ነበር። በኢትዮጵያ 16 የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ሲኖሩ፣ የኢትዮጵያ መድን ድርጀት ከ38 በመቶ በላይ የገበያ ድርሻ አለው።

Via:- Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ህጋዊ ፈቃድ ተሰጥቶት በመንግስት ግብር የሚሰበሰብበት የስፖርት ውርርድ፣ አሁን አሁን የሀገራችንን ወጣቶች ለውርርድ ሱስ እየዳረገ ነው በሚል ውግዘት ተሰንዝሮበታል፡፡
በተለያዩ የስፖርት ውርርዱ ቦታዎች ከ18 ዓመት በታች የሆነ ታዳጊዎች፣ ወጣቶችና ጎልማሶችን ተመልክተናል፡፡
ወጣቶችም ውርርዱ ሱስ እየሆነባቸው መምጣቱን ይናገራሉ፡፡
“ውርርድ” በሚል ቃል መሽሞንሞን አይገባውም ግልፅ የሆነ ቁማር ነው የሚሉት አንድ ባለሞያ በዚሁ ሳቢያ ኬንያ እና ኡጋንዳ የኳስ አቋማሪ ድርጅቶችን መዝጋታቸውን ይጠቅሳሉ፡፡
ባለሞያው አክለውም ጉዳዩ የሥራ ባህልን የሚያዳክም፣ ስንፍናን የሚያስፋፋ እና ባልተገባ መንገድ ገንዘብ ይገኛል የሚል እሳቤን ወጣቶች አእምሮ ውስጥ የሚያኖር ነው ይላሉ፡፡
ነገርየው በጊዜ ሃይ ባይ ካላገኘ በርካታ ማህበራዊ ቀውሶችን ሊያስከትል እንደሚችል ይነገራል፡፡

በአሁኑ ወቅት 20 ድርጅቶች ፍቃድ ወስደው እየሰሩ እንደሆነ ተነግሯል።
Via:- Shager FM
@Yenetube @fikerassefa
ለፖለቲካ ፓርቲዎች በመገናኛ ብዙሃን የአየር ሰዓት ድልድል ለማውጣት ዝግጅት ተደርጓል!

የፖለቲካ ፓርቲዎች ፕሮግራማቸውን እና ዓላማቸውን በመገናኛ ብዙሃን ለህዝቡ እንዲያስተዋውቁ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የአየር ሰዓት ድልድል ለማውጣት መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ገለፀ።በኢትዮጵያ በጠቅላላ ሃገራዊ ምርጫ ወቅት የመገናኛ ብዙሃን የአየር ሰዓት ስርጭታቸውና ከህትመት ገፃቸው ለፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ ያውላሉ።በተያዘው ዓመት ለሚደረገው ጠቅላላ ምርጫም ለፖለቲካ ፓርቲዎች ከሰው ንክኪ በጸዳ መልኩ በሶፍትዌር የታገዘ የአየር ሰዓት ድልድል ለማድረግ መዘጋጀቱን ነው የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የገለፀው።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸው ድንቁ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት፥ የአየር ሰዓት ድልድሉን ለማድረግ የምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመነጋገር የሚያቀርበውን ቀመር እየጠበቀ ነው።ቀመሩ በየምርጫ ዘመኑ የሚቀያየርና ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በሚደረግ ንግግር የምርጫ ቦርድ ከስምምነት የተደረሰበትን የአየር ሰዓት ድልድል ቀመር ለኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ያሳውቃል።በዚህም መሰረት ባለስልጣኑ የተሰጠውን ቀመር ወደ ተዘጋጀው ሶፍትዌር በማስገባት የአየር ሰዓት ድልድሉን የሚያደርግም ይሆናል።

በቅድመ ዝግጅቱ ላይም ከምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን የሚያነሱት ዋና ዳሬክተሩ፥ ሁለቱ ተቋማት በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ የባለሙያዎች ቡድን ኮሚቴ መዋቀሩን ተናግረዋል።የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣንም በምርጫ ዘገባ ላይ ለጋዜጠኞችና ለመገናኛ ብዙሃን የስራ ሃላፊዎች የተለያየ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።ሆኖም ግን አሁንም መገናኛ ብዙሃን አሰራሮቻቸው ስነ ምግባርን ጠብቀው በመስራት የተለየ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል ነው የሚሉት ዶክተር ጌታቸው ድንቁ።የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አባል ወይዘሪት ብዙወርቅ ከተተ በበኩላቸው የሲቪክ ማህበራት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና መራጩን ህዝብ የሚያቅፍ የኮሙዩኒኬሽን ስትራቴጂ እየተዘጋጀ መሆኑ ተናግረዋል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
በተለያዩ የዓለማችን አገራት ውስጥ የሚከሰቱ ግጭቶችን የሚከታተለው ክራይስስ ግሩፕ የተሰኘው ተቋም፣ በቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት 2020 ዓ.ም ግጭት እጅግ ገዝፎ ሊታይባቸው ይችላል ያላቸውን 10 አገራት ይፋ ባደረገበት ሪፖርቱ ኢትዮጵያን ሦስተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል።

Via:- BBC
@YeneTube @Fikerassefa