YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በኢትዮጵያ በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነው የጉዞ እቅድ መተግበሪያ ካርታ (ዲጂታል ማፕ) በይፋ ተመረቀ

በኢትዮጵያ የህዝብ ትራንስፖርት ለማሻሻል ወሳኝ ነው ተብሎ የሚታመነው የጉዞ እቅድ መተግበሪያ (ዲጂታል ማፒንግ) ዛሬ በሂሊተን ሆቴል የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ በተገኙበት በይፋ ተመርቋል።

@Yenetube @Fikerassefa
#HIV

በካፒታል ሆቴል በ HIV ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር ላይ ያተኮረ አውደ ጥናት እየተካሄደ ነው።

በጉባኤው ላይ እንደተነገረው፣ በአሁኑ ወቅት በአመት 23ሺ ኢትዮጵያዊያን በቫይረሱ ይያዛሉ ተብሏል። 11 ሺ 049 በየአመቱ ይሞታሉ። ቫይረሱ እየተስፋፋ ነው። ጦርነት መክፈት ያለብን HIV እንዳይስፋፋ ነው።

via:-Tibebu Belete
@Yenetube @Fikerassefa
በደሴ በአዳማ በወልዲያ በአርሲ ነገሌ በአፋር በደንቢዶሎ በመርሳ በመካነሰላም በሀርቡ በበዴሌ በጅማ በደጋን በሥልጤ በባኮ ትቤ ባሌ ጊንዲር ባቲ መደወላቡ ደጋን እስክካሁን ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደባቸው የሚገኙ አከባቢዎች ናቸው::

@Yenetube @Fikerassefa
በሰላማዊ ሰልፎቹ ላይ የተሰሙ ድምፆች...

* "መንግሥት በእምነት ተቋማት ላይ ጥቃት የሚያደርሱ አካላት ላይ አፋጠኝ እርምጃ ሊወስድ ይገባል!

* የሚዲያዎች የሃይማኖት አድሎ ይቁም!

* መንግሥት ለተቃጠሉ የእምነት ተቋማትና ንብረታቸው ለወደመባቸው ግለሰቦች ተገቢውን ካሳ ሊከፍል ይገባል!

* በሃይማኖትም ሆነ በፖለቲካ ጽንፈኛ አካላትን መንግሥት እንዲያሰተካክል" የሚሉ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።

#ኢትዮጵያ_የሁሉም_እምነቶች_ደሴት_ነት
@Yenetube @Fikerassefa
VACANCY - Fortune

We, at INMP, publisher of the largest English weekly in #Ethiopia, are searching for hardcore programmers who are passionate about breaking things and hacking solutions into microservices out of complex specifications in an effective, iterative manner.

@Yenetube @Fikerassefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ክብር ለኢትዮጵያ
ክብር ለሴቶች
ሰላም ለኢትዮጵያ

ከፍሬወይኒ 🎬BBC
@Yenetube @Fikerassefa
የክልል ልዩ ኃይል አደረጃጀት ላይ ማሻሻያ ለማድረግ ታስቧል

በአገሪቱ የተለያዩ ክልሎች ያለው የደህነነት እና ፖሊስ ሰራዊት አደረጃጀት ላይ ለውጥ የማድረግ ውጥን መኖሩ ተገለጸ፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ድኤታ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ ‹‹የፀጥታ ተቋማት በፖለቲካ ሽግግር ውስጥ›› በሚል ርዕስ ደህንነትና የፀጥታ አካላት አሠራርና ማሻሻያን አስመልክቶ በተደረገ ውይይት ላይ እንደተናገሩት፤ አሁን ባለው ሁኔታ የደህንት መዋቅር ለውጦች መደረግ እንዳለባቸው የታመነ ሲሆን የክልል ልዩ ኃይልና ፖሊስ አካላትም በዚሁ ታሳቢ ተደርገዋል፡፡

እነዚህ ኃይሎች የሚጠቀሙት መሳሪያን ጨምሮ ዩኒፎርማቸውም ታሳባቢ እየተደረገ ነው፡፡ በክልል ያለው ልዩ ኃይል ሆነ ሌላ አደረጃጀት መፍትሄ እንደሚሰጠውም ሚኒስተር ድኤታው አረጋግጠዋል።

Via:- EPA
@Yenetube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የቀድሞ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የነበሩት አዜብ አስናቀ ክስ ተመሰረተባቸው።

ክሱ የተመሰረተባቸው ለታላቁ የኅዳሴ ግድብ ግንባታ በተካሄደ የደን ምንጣሮ ሥራ ጥፋት ፈጽመዋል በሚል ነው።

የኅዳሴ ግድቡ ግንባታ አሰሪ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መሆኑ ይታወቃል። ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ ነሐሴ 2010 ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ይታወሳል። በክስ መዝገቡ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሜቴክ የቀድሞ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኮሎኔል ሙሉ ወልደገብርኤልን ጨምሮ 50 ሰዎች እንደሚገኙበት የኢዜአ መረጃ አመልክቷል።

መንግሥት ለኅዳሴ ግድብ ደን ምንጣሮ የከፈለው ገንዘብ ከተመነጠረው ወይም ከተሰራው በላይ መሆኑ እየተነሳ ሲወቀስ ነበር።
በአንፃሩ የግድቡ ግንባታና የውኃ መያዝ ሥራ በመዘግየቱ በርካታ ቢሊዮን ብር እንደተከፈለበት የሚገለፀው የደን ምንጣሮ ሥራ መልሶ ማቆጥቆጡን አሐዱ ቴሌቪዥን የግድቡን ምክትል ሥራ አስኪያጅ ጠቅሶ ከዚህ ቀደም መዘገቡ ይታወሳል።

Via:- Ahadu
@Yenetube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
- Engineering Art -

የወዳጅ ዘመድዎን ፎቶዎች ከፈለጉት ፅሁፎች እና የተለያዩ ዲዛይኖች ጋር፣ ሳቢና ማራኪ በሆነ የእንጨት ስራ ቀርፀው ያስቀሩ።

ለሚኖሮዎት ጥያቄ @marsengraving ብለው ቴሌግራም ላይ ያግኙን።


ብዙ የተሰሩ ሥራዎች አሉ ቻናላችንን ይቀላቀሉ ⬇️
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFXiDfCeA__IVLJ7PA
Forwarded from YeneTube
እንኳን አደረሳችሁ

በ አዲስ አበባ የተለያዩ እቃዎች አስመጪ
ብራንድ የወንድና የሴት ሰዓቶች
የሴት ቦራሳዎች
የመዋቢያ እቃዎች
አልባሳት

የምናስመጣቸው እቃዎች ጥራት እና በቀላሉ ገበያ ላይ አለመገኘት እንዲሁም ወደ ክልል ከተሞች መላክ መቻላችን ለየት ያደርገናል ።

ቦሌ መዳንአለም ሞል
+251993014846

ከታች ባለው ሊንክ ገብተው ይጎብኙን ይምረጡ ይዘዙን

👇👇👇👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAENXyUTam6WMV6_hmg
Forwarded from YeneTube
🎄🎄ታላቅ ቅናሽ 🎄🎄
እንኳን አደረሳቹሁ በአሉን አስመልክቶ ታላቅ ቅናሽ በየቲ ኮስሞቲክስ እንዳያመልጣችሁ አሁኑኑ ሊንኩን በመጫን ቻናላችን ጆይን ያድርጉ

https://tttttt.me/yeticosmo

Yeticosmotics is glad to announce its #holiday discount

1. Apple cider with only 850 br

2. Zara perfume with only 1200 br

2. Tresemme shampoo and
conditioner 1100

3. 1 literJohnson wash and shampoo with only 650 br and we have discount for so many products

Join our telegram channel using

https://tttttt.me/yeticosmo
https://tttttt.me/yeticosmo
ኦነግ ከሌሎች የኦሮሞ ፓለቲካ ድርጅቶች ጋር ቅንጅት እንደሚፈጥር ቃል አቀባይ ቶሌራ አደባ መናገራቸው ከአዲስ ስታንዳርድ ትዊተር ገጽ ተመልክተናል።

የታሰበው ቅንጅት ቀጣዩን ሀገራዊ ምርጫ ታሳቢ ያደረገ ነው። ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር እየተካሄዱ ያሉት ውይይቶች እስከ ውህደት ሊዘልቁ ይችላሉ።

Via:- wazema
@Yenetube @Fikerassefa
ከወላይታ ዞን የተውጣጣ አንድ ኮሚቴ ለፌደሬሽን ምክር ቤት ይግባኝ ብሏል- ይላሉ ከዞኑ የተሰራጩ መረጃዎች። እቤቱታው በዞኑ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ተፈርሞ የወጣ ደብዳቤ ሲሆን፣ የደቡብ ክልል የወላይታ ክልልነት ጥያቄን ችላ በማለቱ ይከሳል፤ እናም ፌደሬሽን ምክር ቤት ከምርጫ ቦርድ ጋር ተነጋግሮ የክልልነት ሕዝበ ውሳኔ እንዲያደራጅ ይጠይቃል። በኮሚቴው አፈ ጉባዔዋ እና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተካተውበታል።

@Yenetube @Fikerassefa
የጉራጌ ዞን በክልል የመደራጀት ጥያቄ ⬆️
@Yenetube @Fikeeassefa
እንግሊዛዊው አቀንቃኝ ኤዲ ሼረን ላልተወሰነ ግዜ ከሙዚቃ እረፍት እንደሚያደርግ አስታወቀ።

በቅርቡ በእንግሊዝ የ10 ዓመት ምርጥ አቀንቃኝ ተብሎ የተመረጠው ኤዲ ሼረን እረፍት በማድረግ ዓለም ላይ አሉ የተባሉ ድንቅ ድንቅ መስህብ ያላቸው ቦታዎችን መጎብኘት እንደሚፈልግ ከቢቢሲ ጋር ባደረገው ቆይታ አስታውቋል።

በእንግሊዝ ሙዚቃ ስኬታማ የሆኑ 13 ዓመታትን ያሳለፈው ወጣቱ ኤዲ ሼረን በእረፍት ግዜው የተለያዩ አገራትን ከመጎብኘት ባለፈ የተለያዩ መፅሀፍቶችን በማንበብና ግጥሞችን በመፃፍ እንደሚያሳልፍ አስታውቋል።

Via:- EBS Addis Neger
@Yenetube @Fikerassefa
የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክርቤት (ባልደራስ) ፣ መንግስት በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የአፄ ሚኒሊክ ሀውልት ጎን የተሰራውን ቆርቆሮ ቤት በሚቀጥሉት ሶስት ቀናት ውስጥ የማያፈርስ ከሆነ ህዝቡን አስተባብሮ እንዲፈርስ እንደሚጠይቅ ትላንትና አስታውቋል።

በእስክንድር ነጋ የሚመራው ባልደራስ እንዳስታወቀው ከዚህ በፊት በጉዳዩ ላይ የሰጠውን ማሳሰቢያ መንግስት ተግባራዊ ባለማድረጉ፣ ዛሬ ወደ አዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በመሄደ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ገልጿል።

@Yenetube @Fikerassefa
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ከማደሪያ ክፍላቸው ውጪ የሚኖራቸው ቆይታ ከምሽቱ አራት ሰዓት እንዳያልፍ ይህም በተቆታጣሪዎች (ፕሮክተሮች) በየዕለቱ ክትትል እንዲደረግ መገለፁ ተሰምቷል።

እንዲሁም ዩኒቨርስቲዎቹ ተማሪዎች ከንጋት 12:00 ሠዓት በፊትና ከምሽት 1:00 ሰዓት በኋላ ከግቢ ውጪ እንዳይገኙ የተወሰነ ሲሆን፤ ይህንንም በግቢዎቹ ጥበቃ የፈረቃ ኃላፊዎች፣ የፌደራል እና የክልል ፀጥታ አካላት በዚህ ላይ መረጃ ተሰጥቷቸው እንዲያስፈፅሙ መወሰኑን በትናንትናው ዕለት የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቀወል።

በሚኒስቴሩ የኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ደቻሳ ጉርሙ ይህ ውሳኔ "ጊዜያዊ ነው" በማለት ችግር ያጋጠማቸው የትምህርት ተቋማት ሰላም ከተረጋጋ እንደሚነሳ ለቢቢሲ ተናግረዋል:: ሚኒስቴሩ ያስቀመጠው የሰዓት ገደብ ለጥንቃቄ የተደረገ ነው ያሉት አቶ ደቻሳ ጉርሙ፤ በደብረ ብርሃንና በወለጋ ዩኒቨርስቲዎች የተገደሉ ሁለት ተማሪዎች ከዩኒቨርስቲዎቹ ቅጽር ግቢ ውጪ መሆኑን ያስታውሳሉ።

ወለጋ ዩኒቨርስቲ ሞቶ የተገኘው ተማሪ የተገደለው አሳቻ ሰዓት መሆኑን በመጥቀስ፤ ጥፋተኛ ተብለው ከዩኒቨርስቲው የሚታገዱ ወይም የሚባረሩ ተማሪዎች ሌሎች አማራጮችን እንዳይጠቀሙ በሚቻለው አቅም ሁሉ ለተማሪዎቹ ሕይወት ሙሉ ጥንቃቄ ለማድረግ በሚል የተወሰነ መሆኑን ለቢቢሲ አብራርተዋል። በዚህ ዓመት በዩኒቨርስቲ ውስጥ በተነሳ ግጭት ከሞቱት ተማሪዎች መካከል አብዛኞቹ በግቢው ውስጥ እንዲሁም በማደሪያ ክፍላቸው አካባቢ መሆኑን የተጠየቁት አቶ ደቻሳ "ግቢ ውስጥ ያሉ ችግሮችን ለማሻሻል የፀጥታውን ሁኔታ አጠናክረናል፤ ውጪ ደግሞ እንዳይከሰት የተሻለ ጥንቃቄ ለማድረግ ይህ ውሳኔ ተወስኗል" ሲሉ መልሰዋል።

በዩኒቨረስቲ ግቢ ውስጥ የተሻለ ጥበቃ አለ የሚሉት አቶ ደቻሳ የዩኒቨርስቲዎችን ሰላም ለማረጋገጥ በዩኒቨርስቲዎች በፌደራል ፖሊስ የሚካሄደው ጥበቃ ለውጥ እያመጣ ነው በማለት ለዚህም በአስረጅነት አዳዲስ ግጭቶች እየተነሱ አለመሆኑን ይጠቅሳሉ።

በአማራና በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎችን ሰላም ለማጠናከር የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የሚያስተባብረው የዩኒቨርስቲ የቦርድ አመራሮችና ባለስልጣናት ከአካባቢ ኃላፊዎችና የአገር ሽማግሌዎች የተካተቱበት ኮሚቴ ተዋቅሮ ሁሉንም የሚመለከታቸውን አካላት በማወያየት በዩኒቨርስቲዎች ዘላቂ ሰላም ማምጣት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል።

ከዚህ ጎን ለጎን ሰላሙን ማስጠበቅና ጸጥታውን አስተማማኝ በማድረግ ተማሪዎችም ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ በሚል የፌደራል ፖሊስ ወደ ዩኒቨርስቲዎች መግባቱን አስታውሰው አሁን ያለው ሁኔታ ጥሩ መሆኑን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

"ግቢ ውስጥ ያለውን የፀጥታ ሂደት ስናጠናክር ከግቢ ውጪ እንዳይከሰትና የተኘው ሰላም እንዳይደፈርስ ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው" ብለዋል።

በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ በየትኛውም ደረጃ ያለ ግለሰብ የፀጥታ ችግርና ተጠያቂ የሚሆን ከሆነ ተጠያቂ እናደርጋለን ያሉት አቶ ደቻሳ፤ ሰላማዊ የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ አባላት ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ከዩኒቨርስቲ ለቅቀው ወደቀያቸው የሄዱ ተማሪዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ነበሩባቸው ተቋማት እንዲመለሱ እንፈልጋለን ሲሉ ገልፀዋል።

አክለውም ተማሪዎች ተመልሰው ትምህርታቸውን እንዲጀምሩ ጥሪ ቀርቧል ያሉት አቶ ደቻሳ፣ በሚኖሩበት አካባቢ በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ረብሻ ለማነሳሳት መሞከር ወንጀል ነው ሲሉም ተናግረዋል።

የፀጥታ ችግር የታየባቸው 22 ዩኒቨርስቲዎች ተለይተው እየተሰራ ነው ያሉት አቶ ደቻሳ በእነዚህ ዩኒቨርስቲዎች የተወሰዱ የማስተካከያዎች እርምጃዎችን በተመከለተ የተጠቃለለ መረጃ እጃቸው ላይ እንደገባ እንደሚያስታውቁ ተናግረዋል።

በተያያዘ ዜናም በግጭቶች ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ትምህርት በሁሉም የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከሚቀጥለው ሳምንት አንስቶ ይጀመራል ተባሏል።

በሚኒስትሩ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ደቻሳ ጉርሙ ከግጭቶች ጋር ትምህርት ተቋርጦባቸው ከነበሩት ዩኒቨርስቲዎች አብዛኞቹ ትምህርት ጀምረዋል፤ ቀሪዎቹ ደግሞ ከሚቀጥለው ሳምንት አንስቶ ሙሉ በሙሉ ወደመደበኛ ትምህርት ይመለሳሉ ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

Via:- BBC
@Yenetube @FikerAssefa