YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ለመጪው ምርጫ ወደ 300 ሺህ ገደማ የምርጫ አስፈጻሚዎች እንደሚመለመሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አባል ብዙወርቅ ከተተ ተናግረዋል።ቦርዱ የምርጫ አስፈጻሚዎችን ለመመልመል እና ለማሰልጠን ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ ለፋና ገልጸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ልዩ ሀይል በኦሮሞ ልዩ ዞን እንደገና ሊሰማራ በሚችልበት ሁኔታ ላይ ዛሬ በከሚሴ ከተማ ውይይት ተካሄደ። በውይይቱም ልዩ ሀይሉ ወደ ዞኑ ተመልሶ እንዲገባ ስምምነት ላይ ተደርሷል።በውይይቱ የዞኑ አስተዳዳሪዎች፣ የልዩ ሀይሉ ሀላፊዎችና አባላት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የመከላከያ ሰራዊት፣ የፌድራል ፖሊስ፣ እና ሌሎችም ተሳትፈዋል።

Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሥራን ባደናቀፉ 10 ተማሪዎች ላይ አሰተዳደራዊ ዕርምጃ ወስጃለሁ ብሏል። ዕርምጃ የተወሰደባቸው ተማሪዎች ሌሎች ሰላማዊ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዳይከታተሉ በሃይል አስገድደዋል፤ ደኅንነት ሰጋትም ፈጥረዋል። ቅጣቱ እስከ 2 ዐመት ከትምህርት ማገድ ጀምሮ ጨርሶ እስከማሰናበት የዘለቀ መሆኑን ኢዜአ ዩኒቨርስቲውን ጠቅሶ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ ክልል ጎፋ ዞን በ«ኮሌራ መሰል አጣዳፊ የተቅማጥና ትውከት በሽታ» አራት ሰዎች መሞታቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ እና የጎፋ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቁ።

በሽታው የታየው በዞኑ ኡባ ደብረ ፀሐይ እና ዛላ በተባሉ ወረዳዎች ነው። ሕይወታቸው ካለፉት አራት ሰዎች በተጨማሪ አንድ መቶ ሃያ አንድ ታማሚዎች በሕክምና ላይ እንደሚገኙ በክልሉ ጤና ቢሮ የጤና እና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዋና የሥራ ሂደት ባለቤት አቶ እንዳሻው ሽበሩ ተናግረዋል። አቶ እንዳሻው «ነገሩ የተከሰተው ከእሁድ ጀምሮ ነው። በመጀመሪያው ቀን አራት ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል። አሁን እስካለንበት ሰዓት ድረስ አገልግሎት ያገኙ በሽተኞች 121 ደርሰዋል። ሕሙማኑ ከሁለቱም ወረዳ ነው እየመጡ ያሉት። አጣዳፊ ተቅማጥ እና ትውከት ብዙ መንስኤዎች አሉት። አንዱ ኮሌራ ነው። ኮሌራ መሆኑን የሚረጋግጥልን ከሐዋሳ ነገ ማታ የሚመጣው የላብራቶሪ ውጤት ነው» ብለዋል።ኃላፊው እንዳሉት ሕሙማኑ ከክልሉ ጤና ቢሮ እና ከጎፋ ዞን በተውጣጡ ባለሙያዎች ሕክምና እየተደረገላቸው ነው። ኮሌራ መሰል የተባለው አጣዳፊ የተቅማጥና የትውከት በሽታ ወደ ሌሎች አጎራባች ወረዳዎች እንዳይዛመት የቅኝትና የክትትል ሥራዎች በመከናወን ላይ እንደሚገኙ አቶ እንዳሻው መናገራቸውን ዶይቸ ቨሌ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
ደላሎች ባዘጋጁት መጋዝኖች ተዘግቶባቸው የነበሩ 84 ኢትዮጵያዊያን ከሱዳን ወደ አገራቸው ተመለሱ፡፡

በሱዳን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ኤምባሲ ከዓለምአቀፉ የፍልሰት ድርጅት ( I.O.M) ጋር በመተባበር በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባ የሆኑ 84 ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።ተመላሾቹ በሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች አማካይነት በሱዳን በኩል ወደ መካከለኛው ምስራቅ አገራት ለመሄድደላሎች ባዘጋጁት መጋዝኖች ተዘግቶባቸው የነበሩ መሆኑ ተገልጿል። ኤምባሲው ከሱዳን የሰዎች ሕገ-ወጥ ዝውውር ቁጥጥር መስሪያ ቤት ጋር በቅርበት በመስራት ከአደጋ በማዳን በካርቱም የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ማቆያ ማዕከል ድጋፍ ሲደረግላቸው የቆዩ መሆናቸው ነው የተጠቀሰው።


ተመላሾቹ በካርቱም የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ማቆያ ማዕከል በቆዩባቸው ጊዜያት ኮሚዩኒቲው የምግብ፣ ህክምና፣ የንጽህና፣ ምክር አገልግሎትና እንክብካቤ ሲደረግላቸው ቆይቷል።በሱዳን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ኤምባሲ ከዚህ ቀደም ከሦስት መቶ በላይ የሚሆኑ የሕገወጥ ሰዎች ዝውውር ሰለባ የሆኑ እና በእስር ላይ የነበሩ ዜጎችን ከሱዳን ባለሥልጣን መስሪያ ቤቶችና የተለያዩ ዓለምአቀፍ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ና በቅርበት በመስራት ወደ አገራቸው እንዲመለሱ መደረጉ ይታወሳል።

ምንጭ: ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
በሞጣ የደረሰውን የቤተ እምነቶች ውድመት ለማውገዝ በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች ሠላማዊ ሰልፎች እንደሚደረጉ እየተገለፀ ይገኛል፡፡ የትና መቼ እንደሚካሄድ በግልፅ ለኮሚሽኑ የደረሰ መረጃ አለመኖሩንና ከማኅበረሰቡ ግን በተለያዩ አካባቢዎች ሰልፍ እንደሚኖር እንደሚወራ ተናግረዋል፡፡ በጥንቃቄ ኅብረተሰቡ እንዲመለከተውም የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ አሳስበዋል።

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
ዘመን ባንክ ከታክስ በፊት 636 ሚሊዮን ብር አተረፈ!

ዘመን ባንክ በ2011 የሒሳብ ዓመት ከታክስ በፊት ያገኘው የ636 ሚሊዮን ብር ትርፍ ከባለፈው ዓመት ትርፉ 86 በመቶ ዕድገት ያለውን መሆኑን ገለጸ፡፡ባንኩ የ2011 የሒሳብ ዓመት አፈጻጸሙን ይፋ ባደረገበት ሪፖርቱ፣ በሒሳብ ዓመቱ ከታክስ በፊት ያገኘው ትርፍ ከባለፈው ባንኩ በሒሳብ ዓመቱ አገኘዋለሁ ብሎ በዕቅድ ከያዘው አንፃርም በ55 በመቶ ብልጫ ያለው መሆኑን ይጠቀሳል፡፡ በሒሳብ ዓመቱ ከታክስ በፊት ያገኘው ትርፍ ከባለፈው ዓመት የ293.5 ሚሊዮን ብር ብልጫ ያለው ሲሆን፣ ከታክስ በኋላ ያገኘው ትርፍ ደግሞ 483.7 ሚሊዮን ብር ነው፡፡ ይህ የትርፍ መጠን ዘመን ባንክ ባለፉት 12 ዓመታት ውስጥ በአንድ ዓመት ውስጥ ዓመታዊ ትርፉን በ86 በመቶ ያሳደገበት ወቅት ያልነበረ በመሆኑ፣ የ2011 የሒሳብ ዓመቱ የትርፍ ምጣኔው በባንኩ ታሪክ በከፍተኛነቱ የሚጠቀስ ነው፡፡

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከተማ 11 ሽጉጦች እና ከ1 ሺ 600 በላይ ጥይቶች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ የለቡ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ከህገ ወጥ የጦር ማሳሪያ ዝውውር ጋር በተያያዘ ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ መሰረት አስፈላጊውን ጥናትና ክትትል በማድረግ በክፍለ ከተማው ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ሀይሌ ጋርመንት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በአንድ ግለስብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ተደብቀው የተገኙ 10 ቱርክ ሰራሽ እና 1 ኮልት ሽጉጦችን እንዲሁም 1ሺ 663 የሹጉጥ ጥይቶችን ከሶስት ተጠርጣሪዎች ጋር ታህሳስ 11 ቀን 2012 ዓ.ም በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር የሚያስከትለውን ጉዳት የአካባቢው ህብረተሰብ በመገንዘብ ላበረከተው ቀና አስተዋፅኦ ፖሊስ ኮሚሽኑ ላቅ ያለ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

ምንጭ: የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን
@YeneTube @FikerAssefa
የ45 የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ከንጋት 12 ሰዓት በፊትና ከምሽቱ 1 ሰዓት በኋላ ከቅጥር ግቢዎቻቸው ውጪ እንዳይገኙ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር መመሪያ አሳለፈ። ከምሽቱ 4 ሰዓት በኋላ ከመኝታ ክፍሎቻቸው ውጪ መቆየት አይችሉም።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
ሼር ይደረግ !!

የነገው የሀረርጌ ሰልፍ ወደ ሚቀጥለው ማክሰኞ ተዛውሯል! - አህመዲን ጀበል - #Share

የክርስትና እምነት ተከታዮች የሚያከብሩትን ዓመታዊ የቁሉቢ ገብርኤል በዓልን አስታከው የሃይማኖት ግጭት ለመፍጠር ጸረ ሰላም ኃይላት እንቅስቃሴ እያደረጉ እንዳሉ ምክልክቶች በመታየታቸው እና የክርስትና እምነት ተከታዮች በዓላቸውን በሰላም አሳልፈው እስኪያጠናቅቁ ድረስ በሰላም ለማሳለፍ ሲባል በሀረርጌ በሚከተሉት ከተሞች የነገው ሰልፍ ወደ ማክሰኞ ተዛውሯል። የነገው ሰልፍ የተዛወሩባቸው ከተሞች በሀረር ከተማ፣ አወዳይ ከተማ፣ ሀረማያ፣ ደንገጎ፣ ቀርሳ፣ ላንጌ፣ ቁሉቢ፣ ጨለንቆና ቆቦ ናቸው። በመሆኑም ከላይ በተጠቀሱት ከተሞች ምንም አይነት ሰላማዊ ሰልፍ አለመኖሩ ይታወቅ። ሌሎች አከባቢዎችም ሰላማችሁን በንቃት ጠብቁ።


Hirriirri Harargee bori gara sulasaiitti dabarfateera!

Hirriirri mormi Harargee magaaloota Harar, Awaday, Haramaayaa, dhangaggoo, Qarsaa, Laangee, Qullubbii, Calanqoo fi Qobboo gara kibxata (sulasaa'iiti) Dabarfateera. Sababni isaammoo ayyaana waggaa amantaa kirstaanaa Qullubbi Gabrieliin walqabatee qamoonni jeequmsa amantaa kaasuuf qophaahan sochirra akka jiran mallattoon mulachu hubachuudhan marii godhameen ayyaanni amantaa kiristaana nagaadhaan akka kabajamu fi warraa

Via:- አህመዲን ጀበል
@YeneTube @Fikerassefa
የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ የተሰጠ መግለጫ
@YeneTube @Fikerassefa
መልካም ቀን ይሁንላችሁ
#ጁመዐ
#BCAA
#ሰበር_ዜና

98 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አውሮፕላን ካዛኪስታን ውስጥ ተከሰከሰ ንብረትነቱ የቤክ ኤይር አየር መንገድ የሆነው ፎከር 100 የተሰኘው አውሮፕላን ካዛኪስታን አልማቲ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ ተከስክሶ እስካሁን በትንሹ 14 ሰዎች ሞተዋል።

ባለሁለት ወለለል ህንጻ ላይ በተከሰከሰው አውሮፕላን ውስጥ ከነበሩት ውስጥ 93 መንገደኞች እና አምስት የበረራ ሰራተኞች መሆናቸውም ታውቋል።

የአውሮፕላን ማረፊያው ባለስልጣናት እንዳሉት አውሮፕላኑ ከአልማቲ ወደ ኑር ሱልጣን ከተማ ለመጓዝ በረራ እንደጀመረ በጥቂት ደቂቃዎች ልዩነት ነው የተከሰከሰው።
ህጻናትን ጨምሮ ጉዳት የደረሰባቸው ከ60 የማያንሱ ሰዎች ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።
የአውሮፕላን አደጋው ምክንያት እስካሁን አልታወቀም።

Via:- BBC
@yenetube @Fikerassefa
በሞጣ ከተማ የደረሰውን የመስጂዶችና ንብረት ቃጠሎ የደሴ ከተማ ነዋሪዎች አወገዙ።

በምሥራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ አስተዳደር ታኅሣሥ 10 ቀን 2012ዓ.ም በመስጅዶችና ንብረት ላይ የደረሰውን ቃጠሎ የደሴ ከተማ አስተዳደር ሙስሊሞች በሠላማዊ ሰልፍ አወገዙ፡፡ ነዋሪዎቹ ከጠዋቱ 12፡00 ጀምሮ በደሴ ከተማ ሠላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ ነው፡፡

Via:- አብመድ
@Yenetube @FikerAssefa
የሀዋሳ ከነማ እግር ኳስ የደጋፊዎች ማኅበር አባላትየሀዋሳ ከተማን አጸዱ

የሀዋሳ ከነማ እግር ኳስ የደጋፊዎች ማኅበር አባላት በዛሬው ዕለት የሀዋሳ ከተማን አጽድተዋል፡፡

የማኅበሩ አባላት የጽዳት ሥራውን ያከናወኑት የፊታችን እሑድ የሚከበረውን የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል አስመልክቶ መሆኑንም ነው ያስታወቁት፡፡

በጽዳት ዘመቻው የክለቡ ደጋፊዎች እና የከተማዋ ኅብረተሰብ መሳተፉን ክለቡ በፌስቡክ ገጹ አስነብቧል፡፡

ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ በተካሄደው የጽዳት ዘመቻ ላይ የሀዋሳ ከተማ ወደ ቀደመው ሰላሟ መመለሷ እንግዶቿን ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኗን ደጋፊዎቹ አስታውቀዋል፡፡

በመጪው እሑድ ለሚከበረው በዓል ሁሉም ሃይማኖት ሳይገድበው ሀዋሳ ለእንግዶች ጽዱ ከተማ ሆና እንድትታይ በማለት ከተማዋን እንዳጸዱ ተገልጿል፡፡

Via:- EBC
@Yenetube @Fikerassefa
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ኮርፖሬሽን የቀላል ባቡር ጥገናና እድሳት ማዕከል ለመገንባት ከቻይና መንግስት ጋር መስማማቱን ገለፀ፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሙሉቀን አሰፋ በተለይ እንደገለፁት በከተማዋ ቀደም ሲል ሁለት የጥገና ማዕከላት ቢኖሩም የጥገና አገልግሎት ቀላል ለሆኑ ብልሽቶች ብቻ በመሆኑ ባቡሮች ሲበላሹ ከፍተኛ ወጪ በማውጣት ወደ ቻይና በመላክ ሲያስጠግን ቆይቷል። ይህ ደግሞ በትራንስፖርት አገልግሎቱ ላይ ከሚፈጥረው ጫና ጋር ተዳምሮ ከፍተኛ ችግር ሆኖ ቆይቷል።

አዲስ አበባ ላይ የሚገነባው ጥገናና እድሳት ማዕከል ወደ ቻይና የሚደረገውን ጉዞ ያስቀራል ተብሏል።

ፎቶ :- ፋይል
@Yenetube @Fikerassefa
የኢትዮ ኤርትራ የቴሌኮም ንግድ ልውውጥ

ኢትዮጵያና ኤርትራ እርቅ ማውረዳቸው ተከትሎ በተከፈተው የስልክ ጥሪ አገልግሎት እስካሁን የ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር የንግድ ልውውጥ ማድረጋቸው ተሰማ፡፡
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ጉብኝት ሲያደርጉ ለነበሩት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሽኝት እራት በጋበዙበት ወቅት ነው ይህን ያሉት፡፡

በአየር መንገድ ዘርፍም ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ በረራ መጀመሩን ተከትሎ ከቴሌኮሙ የሚልቅ የንግድ ልውውጥ ተደርጓል ብለዋል፡፡
ለሁለት ቀናት ኢትዮጵያ የነበሩት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር እና ኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የተለያዩ የማምረቻ ማዕከላትን ሲጎበኙ እንደነበር ይታወቃል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ታኅሣሥ 17 ረፋድ ወደ አስመራ ተሸኝተዋል፡፡//

Via:- አሐዱ ቴሌቪዥን
@yenetube @Fikerassefa