#Visa
ናይጀሪያ ወደ አገሯ ለሚጓዙ ኹሉም የአፍሪካ አገራት ዜጎች የመዳረሻ ቪዛ መስጠት ልትጀመር መሆኗን አስታውቃለች። የመዳረሻ ቪዛውም በመጪው ጥር ወር እንደሚጀምር ታውቋል።
@Yenetube @Fikerassefa

የኢትዮጵያ ማሪታይም አካዳሚ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በሜካኒካል እና በኤሌክትሪካል ምህንድስና የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ያገኙ ተማሪዎችን ተቀብሎ በባህር ላይ በመካኒካል እና በኤሌክትሪካል ምህንድስና ኦፊሰርነት ለስድስት እና ለስምንት ወር ተኩል ያሰለጠናቸውን 43 ባለሙያዎች ዛሬ ታህሳስ 2/2012 አስመረቀ፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
@Yenetube @Fikerassefa
የሙዚቀኞች የቅጅ እና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር ማኅበር መቋቋሙን ሸገር ዘግቧል፡፡ ማኅበሩን ማቋቋም ያስፈለገው ለተለያዩ ተዘማጅ ሙያዎች የተቋቋሙ ማኅበራትን በጋራ ለማስተዳደር ነው፡፡ ማኅበሩ ሮያሊቲ ክፍያዎችን ሰብስቦ ለሙያተኞች ያከፋፍላል፡፡ መንግሥት ቀደም ሲል የቅጅ እና ተዛማጅ መብቶች አዋጅን ማውጣቱ ይታወሳል፡፡
Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ቅርስ ጥበቃ እና እንክብካቤ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሻደይ አሸንድየ እና ሶለል የተባሉ በክልሉ በሰፊው የሚከበሩ በዓላትን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ በትጋት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።
@Yenetube @Fikerassefa
@Yenetube @Fikerassefa
የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ አቀባበል እና የራት ግብዣ ስነ ስርዓት በኢዮቤልዩ ቤተመንግስት እየተካሄደ ነው።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የአቅም ግንባታ እና ስልጠና የሚውል 150 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ አፅድቋል::
ምንጭ: የጤና ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
ምንጭ: የጤና ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
የኖቤል የሰላም ሎሬቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ምሽቱን በብሔራዊ ቤተመንግስት በተዘጋጀላቸው አቀባበል እና የእራት ግብዣ ላይ ካስተላለፉት መልዕክት የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች
• በዚያ ፀሀይ ደማቅ አቀባበል ላደረጉልኝ ሁሉ ምሥጋናዬ የላቀ ነው
• ለውጡን ጀምረነዋል እንዲቀጥል እጅ ለእጅ መያያዝ ያስፈልገናል
• ከፍቅር ከመስጠት ከይቅርታ የሚጎድል ነገር የለም
• ክቡር ኢሳያስ አፈወርቂን እና የኤርትራን ህዝብ ማመስገን እፈልጋለሁ
• ትናንት እና ከትናንት ወዲያ የማናውቃትን ኢትዮጵያን ለማወቅ ዕድል አግኝተናል
• ምሁራን ስለ አገራችን ታላቅነት ሲናገሩ ሰምተን አገራችንን በሚገባት ልክ እንደማናውቃት አውቀን ተመልሰናል
• ኢትዮጵያ ድንቅ አገር መሆኗ የሚገባን ከኦስሎ በቀጥታ በረን አዲስ አበባ ስንገባ ነው
• ኖርዌይ ከ5 ሚሊዮን ያልበለጠ ህዝብ ያላት ሀገር ናት፤ በዓመት 9 ወር ጭለማ ነው፣ የኛዋ ኢትዮጵያ ደግሞ የ110 ሚሊዮን ህዝብ ሀገር ናት፤ እንደዚያም ሆኖ ግን እኔ እነርሱን ለመንኳቸው፤ በናንተ ስም እነርሱን መለመኔን ሳልደብቅ ልነግራችሁ እፈልጋለሁ፤ መለመን ያሳፍራል
• ከልመና ወጥተን ወደ ብልፅግና እንድንሄድ ከመላው የአፍሪካና የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ህዝቦች ጋር በትብብር መስራት ይኖርብናል፣ ያኔ ምናልባትም ከ10 ዓመታት በኋላ ከልመና እንወጣለን
• ኢትዮጵያውያን እርስ በርሳችን መናቆርን ትተን ተግተን ብንሰራ የጎደለን ያልተሰጠን ነገር የለም
• ይህን ለማድረግ ሁላችንም ከአሁኑ ሰዓት ጀምረን መስራት ይኖርብናል - እኔም እናንተም፤ አብዝታችሁ አትተኙ፤ የደሃ አገር ህዝብ አብዝቶ መተኛት አይገባውም
• እንደ ኖርዌይ እና ስዊድን ጠንካራ ግንኙነት ያላቸው ብዙ አገራት የሉም፤ ይህ የሆነው አንደኛው ለሌላው በመስጠቱ ነው
• ይህ የእኔ ድል እጅግ ደካማ በሆነ ሰው ላይ ያረፈ ድል ነው፤ ለዚህ ድል ከኔ ይልቅ የተሻለ ዕድል የነበራቸው ብዙ ናቸው፤ ወጣቶች የምታገኟቸውን መልካም አጋጣሚዎች ማባከን አይገባችሁም
• አዳዲስ ድል ማስመዝገብ ጀምረናል፣ በቅርቡ የመጀመሪያውን ሳተላይት እናመጥቃለን
• የፖለቲካ ጨዋታን በቦታው ብቻ በመጫወት፤ በስራ ቦታ በጋራ በመስራት አገራችንን እናበልፅግ፣ ከፍ እናድርግ
via:-EBC

የ2019ን የዓለም የ ሰላም ኖቤል ሽልማታቸውን ወስደው የተመለሱት ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ በብሄራዊ ቤተ መንግስት ከተዘጋጀላቸው የእራት ግብዣ በኋላ ከወራት በፊት የተከሏቸውን ችግኞች ውሃ አጠጥተዋል።
@Yenetube @FikerAssefa
@Yenetube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ መስተዳደር" ገንዘብ የለም" በሚል ምክንያት አዲሱ ደሞዝ ማስተካከያ ሙሉውን ለሰራተኞ አልተከፈለም።
አዲሱ ደሞዝ ማስተካከያ ከሀምሌ ወር ጀምሮ ውዝፍ ክፍያው ቢፈፀምም መስተዳደደሩ "በቂ በጀት" የለውም በሚል ምክንያት በወርሀዊ ደሞዝ ላይ ከ1,500 ብር በላይ ጭማሪ ማድረግ አልቻለም ።ይሄም ማለት ለምሳሌ በአዲሱ ደሞዝ ማስተካከያ ከ 1,300 ብር 3,000 ብር ተጨምሮለት 4,300 ብር የገባ ሰራተኛ አየተከፈው ያለው 2,800 ብር ማለት ነው ።መስተዳደሩ ለቀጣይ አመት ይስተካከላል በማለት ለሰራተኞቹ ገልፇል። እንደ ሰራተኞቹ ገለፃ አዲሱ የደሞዝ ማስተካከያ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ዲግሪን ከሰርተክፌት ያሳነሰ ፣አዲስ ቅጥረኛንም በተመሳሳይ የትምህርት ደረጃ የስራ መስክ ከነባር ሰራተኛ ያሳነሰ ነው በማለት መልክት አድርሰውኛል ሲል ጋዜጠኛ ተስፋዬ ጌትነት በገፁ አስፍራል።
@YeneTube @Fikerassefa

የሐረማያ ዮንቨርስቲ ማስተማር ካቋረጠ ከአንድ ወር በላይ እንደሆነው የዩኒቨርስቲዉ ሠራተኛ እና ተማሪዎች አስታወቁ ።
«ከተመዘገብን አንስቶ እስካሁን በአግባቡ የተማርነው አንድ ሳምንት ቢሆን ነው» የሚለው አንድ የዩንቨርስቲው ተማሪ በዚሁ መስተጓጎል ምክንያት ወደ ቤተሰቦቹ ከተመለሰ አንድ ወር እንደሆነው ገልፆልናል። በስልክ ያነጋገርናቸዉ አንድ ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የዩንቨርስቲው ባልደረባ እንደገለፁልን ደግሞ ትምህርት መልሶ ከተጀመረ 10 ቀን ገደማ ቢሆነውም ክፍል የሚገባው ተማሪ ቁጥር በጣም ውስን ነው። ለዚህም ባልደረባው በምክንያትነት የጠቀሱት አንዳንድ ተማሪዎች በድብቅ በሚያሰራጩት የማስፈራሪያ እና የአድማ ወረቀቶች ምክንያት ነው።
«በሐሮማያ ዩንቨርስቲ ግጭት ከተቀሰቀሰ አንስቶ የከፋ ችግር እንዳይከሰት ለመቆጣጠር ዩኒቨርስቲዉ ቅጥር ግቢ የሰፈረዉ የፌደራል ፖሊስ ቁጥር እንዲጨምር ተደርጓል ፣መከላከያም ገብቷል። የኦሮሚያ አድማ በታኝ እና የዩንቨርስቲው ጥበቃም በግቢው ይገኛሉ» ተብሏል።
በሐረማያ ዮንቨርስቲ ግጭት የተጀመረው ጥቅምት መጨረሻ ወልዲያ ዩንቨርስቲ ሁለት ተማሪዎች ከመገደላቸው ጥቂት ቀናት አስቀድሞ ነው።
የዩንቨርስቲው ተማሪዎች ሰልፍ በመውጣት ወለጋ ላይ የተደነገገዉ የኮማንድ ፖስት አገዛዝ ይነሳ፣ መከላከያ ሠራዊት ከኦሮሚያ ይውጣ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስልጣን ይውረዱ በሚል የፖለቲካ ጥያቄዎች አንስተው መንግሥት በአፋጣኝ ምላሽ ይስጠን ብለው ትምህርት አቁመው እንደነበር የዩንቨርስቲው ባልደረባ ተናግረዋል።
« በካፍቴሪያ ውስጥ ከዚህ ቀደም ከሚመገቡት 13000 ገደማ ተማሪዎች በአሁን ሰዓት 5000 ተማሪዎች ብቻ የሚገኙበት ሁኔታ አለ» ብለዋል የዮንቨርስቲው ባልደረባ።
የተለያዩ የዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች አዲስ አበባ ውስጥ ትናንት እና ዛሬ በጋራ በተለያዩ ዮንቨርስቲዎች የተነሱትን ግጭቶች ተከትሎ በቀጣይ ሂደቱ ላይ በመምከር ላይ እንደሚገኙም ታውቋል።
Via:- DW

ዴንማርክ ቀጣዩን ሃገራዊ ምርጫ ለመደገፍ የሚውል የ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረመች።
የድጋፍ ስምምነቱን በኢትዮጵያ የዴንማርክ አምባሳደር ካሪን ፖልሰን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተወካይ ቱርሃን ሳልህ ተፈራርመውታል።
የዛሬው ስምምነት የዴንማርክ የትብብር ሚኒስትር ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት የዴንማርክ መንግስት በገባው ቃል መሰረት የተደረገ ነው ተብሏል።
@Yenetube @Fikerassefa
የድጋፍ ስምምነቱን በኢትዮጵያ የዴንማርክ አምባሳደር ካሪን ፖልሰን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተወካይ ቱርሃን ሳልህ ተፈራርመውታል።
የዛሬው ስምምነት የዴንማርክ የትብብር ሚኒስትር ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት የዴንማርክ መንግስት በገባው ቃል መሰረት የተደረገ ነው ተብሏል።
@Yenetube @Fikerassefa
ኢ/ር ታከለ ኡማ ከብሄራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላት ጋር ተወያዩ፡፡
የኮሚሽኑ አባላት በሀገሪቱ ብሄራዊ መግባባትን ለማስፈን በሚያከናውኗቸው ተግባራት የከተማ አስተዳደሩ ትብብርና ድጋፍ እንዳይለያቸው ጠይቀዋል፡፡ኢ/ር ታከለ ኡማ ኮሚሽኑ ቁርሾዎችንና ቅራኔዎችን ለመፍታት እያደረገ ያለውን ዝግጅትና ጥረት አድንቀው የከተማ አስተዳደሩ ለኮሚሽኑ ሀሳብ ስኬት ድርሻውን እንደሚወጣ ተናግረዋል፡፡የብሄራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላት ከክልል መስተዳድር አመራሮችና እና ከከተማ መስተዳድር አመራሮች ጋር ትውወቅና ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
Via Mayor Office

ሰበታ ከተማ ለአራት ዓመታት የሚቆይ የ18 ሚሊየን ብር የስፓንሰርሽፕ ስምምነት ከሜታ አቦ ቢራ ጋር ተፈራረመ!
በዘንድሮው ዓመት ከረጅም ጊዜ በኋላ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን የተቀላቀለው ሰበታ ከተማ ለአራት ዓመታት የሚቆይ የ18 ሚሊየን ብር የስፓንሰርሽፕ ስምምነት ከሜታ አቦ ቢራ ጋር ተፈራረመ፡፡የስፓንሰርሽፕ ስምምነቱ በትናትናው ዕለት የክለቡ የበላይ ጠባቂ እና የሰበታ ከተማ ከንቲባ አቶ ብርሃኑ በቀለ እና የክለቡ ፕሬዚደንት አቶ ኡብሳ ለገሰ እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት በትናትናው ዕለት ተፈርሟል፡፡ስምምነቱ የገንዘብ እና የስፖርት ቁሳቁስ ያካተተ ሲሆን በስምምነቱ መሠረት ሰበታ ከተማ በማልያው ላይ የሜታ አቦ ቢራ ምርት ያስተዋውቃል ተብሏል።
Via FBC/Soccer Ethiopia

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከኦስሎ፣ ኖርዌይ ከሰሞኑ የተቀበሉት የሰላም የኖቤል ሽልማት ሜዳልያ እና ዲፕሎማ አዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የተለያዩ ሁለት ሙዚየሞችና በአንድነት ፓርክ ይቀመጣል ተባለ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሸለሙት 3 ሜዳልያና ሦስት ዲፕሎማ መሆኑን ሰምተናል፡፡በሁለቱ ሙዚየሞችና በአንድነት ፓርክ እያንዳንዳቸው አንድ ሜዳልያ እና አንድ ዲፕሎማ ይቀመጣል ተብሏል፡፡ ከአንድነት ፓርክ በተጨማሪ ለሽልማቱ መቀመጫነት የተመረጡት ሁለቱ ሙዚየሞች በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ስር የሚገኘው ኢትኖግራፊክ ሙዚየም እና ብሔራዊ ሙዚየም ናቸው፡፡
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው ሜዳልያና ዲፕሎማውን ነገ ከሰዓት በኋላ ተረክቦ በክብር በሙዚየሙ ውስጥ ያስቀምጣል፡፡የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ደግሞ በመጭው እሁድ ከሰዓት በኋላ ሌላ አንድ ሜዳልያና ዲፕሎማ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ባሉበት ተረክቤ በብሔራዊ ሙዚየም አስቀምጣለሁ ብሏል፡፡በአንድነት ፓርክ ቀሪ አንድ ሜዳልያና አንድ ዲፕሎማ ይቀመጣል የተባለ ሲሆን ሥነ-ሥርዓቱ የሚከናወንበት ቀን ገና አልታወቀም፡፡
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ የተሸለሙት የኖቤል ሽልማት በግላቸው ስለ ሰላም ፈፅመውታል በተባለ ተግባር ቢሆንም ሜዳልያዎቹና ዲፕሎማዎቹ በተጠቀሱት ሙዚየሞች እንዲሁም በአንድነት ፓርክ ተቀምጠው ለህዝብ እይታ ክፍት ይሆናሉ ተብሏል፡፡
Via Sheger

Fake News Alert !! የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር ደብረጽዮን ህይወታቸው አልፏል ብሎ ዋልታ የዘገበው ዜና ከእውነት የራቀ ነው!!
ዋልታ ቴሌቭዥን የውሸት መረጃዎችን ማስተላለፉን ቀጥሏል።
ሆኖም ግን ዋልታ ቴሌቭዥን በስህተት እንደተለቀቀ አምኖ ከተቋሙ እውቅና ውጪ እንደተለቀቀ በFacebook ገፁ አስፍሯል።
@Yenetube @Fikerassefa
ዋልታ ቴሌቭዥን የውሸት መረጃዎችን ማስተላለፉን ቀጥሏል።
ሆኖም ግን ዋልታ ቴሌቭዥን በስህተት እንደተለቀቀ አምኖ ከተቋሙ እውቅና ውጪ እንደተለቀቀ በFacebook ገፁ አስፍሯል።
@Yenetube @Fikerassefa
የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማእከልን እንደሚከስ አስታውቋል!
ሙሉ መግለጫው ⬇️
ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማእከል የተባለ የመገናኛ አውታር የትግራይ ብሄራዊ ክልል መንግስት ም/ርእሰ መሰተዳደር ክቡር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ሂወታቸው አልፈዋል ብሎ በዛሬው እለት ያሰራቸው ነጭ የፈጠራ ወሬ ፈፅሞ ሀሰት መሆኑን ለመላው ህዝባችን ማሳወቅ እንወዳለን፡፡
ዋልታ ኢንፎረሜሽን ማእከል የተባለ የመገናኛ አውታር waltainfo.com በሚል ፌስቡክ ገፁ ላይ ዛሬ ታህሳስ 03/2012 ዓ/ም ከሰአት በኅላ ያሰራጨው ሀሰተኛ የአሉባልታ ወሬ፣ ይህ የመገናኛ አውታር ባለፉት አመታት በትግራይ ህዝብ ላይ የብሄር ተኮር ጥቃት እንዲደርስ ስያካሂደው የነበረ ዘመቻ ኣካል መሆኑን ሊታወቅ ይገባል፡፡
በመጨረሻም የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማእከል የተባለ የመገናኛ አውታር በህግ የሚጠቅይ መሆኑን ይገልፃል፡፡
የትግራይ ክልል ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
መቐለ
ታህሳስ 03/2012

የኢትዮጵያ የባህል ቡድን ወደ ኤርትራ ሊያቀና ነው።
በኢፌዲሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ብዙነሽ መሰረት የሚመራና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ከብሔራዊ ቲያትር፣ ከታዋቂ ደምጻዊያንና የጃኖ ባንድ የተካተቱበት ከ60 በላይ አባላትን የያዘ የኢትዮጵያ የባህል ቡድን ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የሙዚቃ ዝግጅት ለማቅረብ ከሰኞ ታህሳስ 6 ቀን 2012 ዓም ጀምሮ ወደ ኤርትራ ይጓዛል።የባህል በድኑ የኤርትራ ጉዞ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የተፈጠረውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ ነው።የባህል ቡድኑ በኤርትራ ቆይታው በአስመራ፣ ከረን እና ምጽዋ ከተማዎች የተለያዩ የሙዚቃ ዝግጅቶችን እንደሚያቀርብ ይጠበቃል።የኤርትራ የባህል ቡድን በለፈው የካቲት ወር 2011 ዓም በአገራችን በመገኘት ተመሳሳይ ዝግጅቱን በአዲስ አበባ፣ በአዳማ፣ በባህርዳር እና በሀዋሳ ከተማዎች ማቅረቡ ይታወሳል።
ምንጭ: የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ዋልታ ቲቪ የዶ/ር ደ/ ፅዮን የውሸት ሞት ዜና ከየትኛው ኮምፒውተር እንደተፃፈ ኢንሳን ምርመራ አድርግልኝ ብሎ ጠይቋል።
ዋልታ ኢንፎርሜሽን የትግራይ ብሄራዊ ክልል መንግስት ም/ርእሰ መሰተዳደር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ሂወታቸው አልፏል በሚል waltainfo.com ገፁ ላይ ዛሬ ታህሳስ 03/2012 ዓ/ም የለቀቀወን ሰው ለማወቅና ለፍርድ ለማቅረብ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ( ኢንሳ) በኮምፒወተሮቹ ላይ ምርመራ እንዲያርግ ጥያቄ አቅርቧል ሲሉ የውስጥ ምንጮቼ ነግረውኛል።
Via:- ተስፋዬ ጌትነት