"እንኳን የኢትዮጵያዊነት ቀን ለሆነው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል አደረሳችሁ፡፡ ይህን በዓል ስናከብር ወደ ቀደመው አሐዳዊነትም ሆነ ወደ እጅ አዙር አሐዳዊነት ዳግም እንደማንመለስ እያረጋገጥን ነው፡፡ ከፊታችን ያለው ዘመን መንፈሳዊ፣ አእምሯዊና ቁሳዊ ብልጽግናችን የሚረጋገጥበት ዘመን ይሆናል፡፡ ባህሎቻችን፣ ቋንቋዎቻችን፣ ዕሴቶቻችን፣ የሚበለጽጉበት ዘመን ይሆናል፡፡ አንድነታችን፣ አብሮነታችን፣ ወንድማማችነታችን የሚበለጽግበት ዘመን ይሆናል፤ በዕውቀትና በሀብት የምንበለጽግበት ዘመን ይሆናል፡፡ በፍትሕ፣ በሰላም፣ በጋራ ደኅንነት፣ የምንበለጽግበት ዘመን ይሆናል፡፡ ካሳለፍናቸው ዘመናት ይልቅ ወደፊት የምናሳልፋቸው ዘመናት ብዙ ናቸው፡፡"
ጠ/ሚ አብይ አህመድ በነገው ዕለት ለሚከበረው የብሄሮችና ብሄረሰቦች ቀን አስመልክተው ካስተላለፉት
@YeneTube @FikerAssefa

#ቡና_ኢንተርናሽናል ባንክ አስረኛ የምስረታ በዓሉን በሚሌኒየም አዳራሽ እያከበረ ይገኛል።በፕሮግራሙ ላይ የባንኩ አመራሮች እንዲሁም ባለአክሲዮኖች ተገኝተዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
@Yenetube @Fikerassefa
#በቢራና #በሲጋራ ዋጋ ላይ 30 እና 40 በመቶ ኤክሳይዝ ታክስ ይጣላል!
በዚህ መሠረት በቢራ ላይ የሚጣለው ኤክሳይዝ ታክስ በጠርሙስ 40 በመቶ ወይም በሊትር 11 ብር እንዲከፈል በረቂቅ ድንጋጌነት ቀርቧል፡፡ ሃያ ፍሬዎችን በሚይዝ አንድ ፓኬት ሲጋራ መሸጫ ዋጋ ላይ 30 በመቶና ተጨማሪ አምስት ብር እንዲሰላ በድንጋጌው ተመልክቷል፡፡በእያንዳንዱ የቢራና የሲጋራ ምርት ላይ ኤክሳይዝ ታክስ የተከፈለበት መሆኑን የሚያመለክት ቴምብር መለጠፍ እንደሚኖርበት በአስገዳጅነት ተቀምጧል፡፡ከዚህ በተጨማሪም ኤክስይዝ ታክስ የሚከፈልበትን ምርት ለማምረትም ሆነ ለማስመጣት፣ እንዲሁም አገልግሎት ለመስጠት ከገቢዎች ሚኒስቴር ልዩ ፈቃድ መያዝ በአስገዳጅነት ተካቷል፡፡ በቢራ አምራችነት ፈቃድ ከተሰጣቸው ኩባንያዎች ውጪ በባር ወይ በምግብ ቤቶች አነስተኛ ቢራ ጠመቃ ለማካሄድ ተጨማሪ ፈቃድ ማግኘትም አስገዳጅ ሆኖ በረቂቁ ተካቷል፡፡
በሥራ ላይ ያለው አዋጅ በቢራ ምርቶች የማምረቻ ዋጋ ላይ የሚጥለው ኤክሳይዝ ታክስ 50 በመቶ ሲሆን፣ በትምባሆ ምርት የማምረቻ ዋጋ ላይ ደግሞ 75 በመቶ ይጥላል።በመሆኑም የማኅበረሰብ ጤናን በከፍተኛ ደረጃ ያቃውሳሉ የተባሉት በሁለቱ ምርቶች ላይ እንዲጣል የቀረበው አዲስ የኤክሳይዝ ታክስ፣ እጅግ ዝቅተኛና የማኅበረሰብ ጤናን ያላገናዘበ መሆኑን ባለሙያዎች ያስረዳሉ።
በተለይ በትምባሆ ምርት ላይ የዓለም የጤና ድርጅት የሚያስቀምጠው የታክስ ምጣኔ 70 በመቶ መሆኑን የሚናገሩት ባለሙያዎቹ፣ አሁን የተረቀቀው ኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ በዓለም የጤና ድርጅት ከተቀመጠውም ሆነ ከሰሃራ በታች የሚገኙ አገሮች በሲጋራ ላይ ከሚጥሉት ኤክሳይዝ ታክስ በእጅጉ እንደሚያንስ ይገልጻሉ።የኢትዮጵያ ፓርላማ ትምባሆን ለመቆጣጠር ባወጣው ጥብቅ ሕግ በዓለም ጤና ድርጅት ባለፈው ዓመት መሸለሙን የሚያስታውሱት ባለሙያዎቹ፣ አዲሱ ኤክሳይዝ ታክስ በሲጋራ ላይ ለመጣል ያቀደው የታክስ ምጣኔ የኅብረተሰብ ጤናን ለመጠበቅ ታስቦ የፀደቀውን የትምባሆ ቁጥጥር አዋጅ ዓላማ የሚቃረን በመሆኑ መንግሥት በድጋሚ ሊያጤነው ይገባል ብለዋል።
በዘንድሮው የበጀት አዋጅ መሠረት 4.2 ቢሊዮን ብር በአገር ውስጥ በሚመረቱ ቢራ መጠጦች ላይ ከሚጣል ኤክሳይዝ ታክስ ለመሰብሰብ፣ እንዲሁም 1.1 ቢሊዮን ብር ከሲጋራ ወይም ከትምባሆ ምርቶች ኤክሳይዝ ታክስ እንዲሰበስብ ለገቢዎች ሚኒስቴር ኃላፊነት ተሰጥቶታል።
በሥራ ላይ በሚገኘው አዋጅ ኤክሳይዝ ታክስ ካልተጣለባቸው ምርቶች በረቂቁ እንዲካተቱ ከተደረጉት መካከል አንዱ ሰው ሠራሽ ፀጉር ወይም “ሂዩማን ሄር” ሲሆን፣ 100 በመቶ ኤክሳይዝ ታክስ እንዲጣልበት በረቂቁ ተካቷል፡፡
Via:- ሪፖርተር

ዜና እረፍት !
በተጫዋችን እንዲሁም ኢትዮ ኤሌክትሪክን ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን፣ ኢትዮጵያ መድን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በተለያዮ የዕድሜ እርከኖች በአሰልጣኝ የነበሩት አንጋፋው አሰልጣኝ ወንድማገኝ ከበደ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን በአሰልጣኝ ወንድማገኝ ከበደ ዜና ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለወዳጅ ዘመዶቹ እና ቤተሰቦቹ መፅናናትን ተመኝቷል።

በቂሊንጦ ማርሚያ ቤት በታራሚዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ስድስት ታራሚዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሰባቸው፡፡
ዛሬ ሕዳር 28 ቀን 2012 ዓ.ም ረፋድ ላይ በአዲስ አበባ በሚገኘው በቂሊንጦ ማረምያ ቤት በእስረኞች መካከል በተፈጠረ ግጭት በስድስት ታራሚዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስታውቋል፡፡ጉዳት የደረሰባቸው ታራሚዎችም ወደ ፌደራል ማረሚያ ቤቶች ሆስፒታል እንደተወሰዱ የፌደራል ማረምያ ቤቶች የቀጠሮ ማረፊያ ቤት ዋና አስተዳዳሪ ኮማንደር ጫላ ጸጋ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
ግጭቱ በታራሚዎች መካከል ከሆነ ፖሊስ ለምን ብዛት ያለው ጥይት ተኮሰ በሚል ለተነሳላቸው ጥያቄም ፖሊስ ጥይት የተኮሰው እስር ቤቱ ጣራ ላይ የተቀመጡትን ታራሚዎች እንዲወርዱ ለማድረግ በማሰብ ነው ብለውናል ኮማንድር ጫላ፡፡በግጭቱ ሳብያም እስካሁን የሞተ እንድም ታራሚ አለመኖሩን ኮማንደሩ ተናግረዋል፡፡በጊዜው የደረሰው ግጭት ወዲያውኑ እንደተቆጣጠሩት እና አሁን ላይም ማረሚያ ቤቱ መረጋጋቱን ኮማንደር ጫላ ተናግረዋል፡፡
Via Ethio FM

በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተመራው የልዑካን ቡድን ዋሽንግተን ገባ!
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ከግብጽና ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር በሚደረገው ውይይት ለመሳተፍ ወደ አሜሪካ ያቀናውና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተመራው የልዑካን ቡድን ዛሬ ህዳር 28 ቀን 2012 ዓ.ም ዋሽንግተን ገብቷል።የልዑካን ቡድኑ ዋሽንግተን ዳላስ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በአምባሳደር ፍጹም አረጋና በኤምባሲው ዲፕሎማቶች አቀባበል ተደርጎለታል።በህዳሴው ግድብ ዙሪያ በሚካሄደው በዚህ ምክክር በቅርቡ በአዲስ አበባ እና በካይሮ ከተደረጉት የግድቡ የውሀ ሙሌትና ሌሎች ባልተቋጩ ነጥቦች ላይ እንደሚያተኩር ይጠበቃል።የአሜሪካ እና የአለም ባንክ ተወካዮች በስብሰባው በታዛቢነት ይሳተፋሉ።
ምንጭ: የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

🐴ፈረስ የታክሲ አገልግሎት🐴
ኮድ 1 ወይም 3 መኪና ካሎት ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት አሁኑኑ በነፃ መኪናዎን ያስመዝግቡ።
🎯ቦታችን ጌቱ ኮሜርሻል ህንፃ አንደኛ ፎቅ ላይ እንገኛለን።
ይህንን ያውቃሉ? ፈረሰ ኮምሽን የሚወስደው 5% ብቻ ነው፣ ይህም ተመራጭ አድርጎታል።
ለበለጠ መረጃ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@feresapps

ፍትህ መፅሄት ህዳር ወር ዕትም ቁጥር 57 ለማ በገበያ በሚል ርዕስ ይዞት ከወጣውን መፅሄት ላይ ዓለማየሁ ገላጋይ "ከድፍን ሀገር ቁራሽ ለትንሽ" በሚል ርዕስ ያስነበበውም በድምፅ ሰርተንላችዋል።
አድምጡት ⬇️
https://youtu.be/G5Oi51BuRBo
አድምጡት ⬇️
https://youtu.be/G5Oi51BuRBo
ኢትዮጵያዊቷ ፍሬወይኒ መብርሃቱ የCNN የአመቱ ጀግና(CNN Hero of The Year) በመባል ተመርጣለች!
እንኳን ደስ አለሽ!
እንኳን ደስ አለን!
@YeneTube @FikerAssefa
እንኳን ደስ አለሽ!
እንኳን ደስ አለን!
@YeneTube @FikerAssefa
ፍረወይኒ ለዛሬ አጥቢያ የ "CNN የአመቱ ጀግና" ተብላ የተመረጠችው ለፍፃሜ ከቀረቡት አስር ሰዎች እና ድርጅቶች መሀል ነው። የኬሚካል ኢንጂነሪንግ ትምህርት በአሜሪካ ያጠናችው ፍረወይኒ ተመልሶ ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ ምርት ዲዛይን አድርጋ እና ለመጠቀሚያ ያቀረበችው የዛሬ 14 አመት ገደማ ነበር።
ከዛን ግዜ ጀምሮ 750,000 ገደማ የሚሆን ይህ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰራ ምርት ለተጠቃሚዎች የተከፋፈለ ሲሆን 800,000 ሺህ ገደማ ሴቶች ከፍረወይኒ ስራ ተጠቃሚ ሆነዋል። ዛሬ ይህንን ሽልማት በማሸነፏም ስራዋን ለማስፋፋት እንዲያግዛት የ100,000 ዶላር ሽልማት ተቀብላለች።
Via ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት
@YeneTube @FikerAssefa
ከዛን ግዜ ጀምሮ 750,000 ገደማ የሚሆን ይህ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰራ ምርት ለተጠቃሚዎች የተከፋፈለ ሲሆን 800,000 ሺህ ገደማ ሴቶች ከፍረወይኒ ስራ ተጠቃሚ ሆነዋል። ዛሬ ይህንን ሽልማት በማሸነፏም ስራዋን ለማስፋፋት እንዲያግዛት የ100,000 ዶላር ሽልማት ተቀብላለች።
Via ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት
@YeneTube @FikerAssefa
🐴ፈረስ የታክሲ አገልግሎት🐴
ኮድ 1 ወይም 3 መኪና ካሎት ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት አሁኑኑ በነፃ መኪናዎን ያስመዝግቡ።
🎯ቦታችን ጌቱ ኮሜርሻል ህንፃ አንደኛ ፎቅ ላይ እንገኛለን።
ይህንን ያውቃሉ? ፈረሰ ኮምሽን የሚወስደው 5% ብቻ ነው፣ ይህም ተመራጭ አድርጎታል።
ለበለጠ መረጃ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@feresapps
ኮድ 1 ወይም 3 መኪና ካሎት ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት አሁኑኑ በነፃ መኪናዎን ያስመዝግቡ።
🎯ቦታችን ጌቱ ኮሜርሻል ህንፃ አንደኛ ፎቅ ላይ እንገኛለን።
ይህንን ያውቃሉ? ፈረሰ ኮምሽን የሚወስደው 5% ብቻ ነው፣ ይህም ተመራጭ አድርጎታል።
ለበለጠ መረጃ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@feresapps
14ኛ የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በአዲስ አበባ ስታዲየም በድምቀት እየተከበረ ነው!
በኦሮሚያ ክልል አስተናጋጅነት 14ኛው የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በአዲስ አበባ ስታዲየም በድምቀት እየተከበረ ነው።በበዓሉ ላይ ከመላው ሀገሪቱ የተውጣጡ የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች እየተሳተፉ ነው።በሺዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችም በበዓሉ ላይ ተገኝተዋል።በዚሁ በዓል ላይ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የተለያዩ ትእይንቶችን እንደሚያቀርቡ ከኤፍቢሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ለኤልያስ መልካ መታሰብያ እንዲሆን "የሙዚቃ መንደር" ግንባታ እንዲካሄድ ለከንቲባ ታከለ ኡማ ጥናቱ የተጠናቀቀ ሰነድ ሊቀርብላቸው መሆኑን የሙዚቃ ሃያሲ እና የአ.አ ኪነጥበብ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ም/ሃለፊ ሰርፀፍሬ ስብሀት ለሁሉ አዲስ ተናገሩ ።እየተገነባ በሚገኘው የአድዋ ሙዚየም ላይ እንዲገነባ ታስቦ የነበረ ቢሆንም የሙዚቀኞች ማህበራት ህብረት አልተቀበለውም።በአዲስ ስፍራ መገንባት አለበት ማለቱን ለማረጋገጥ ችለናል።
Via HuluAddis on Bisrat FM
@YeneTube @FikerAssefa
Via HuluAddis on Bisrat FM
@YeneTube @FikerAssefa
በጎንደር ዩኒቨርስቲ የአንድ ተማሪ ህይወት ማለፉ ተገለፀ!
በጎንደር ዩኒቨርስቲ ትናንት ኅዳር 28/2012 አንድ የኹለተኛ ዓመት ተማሪ ህይወት ማለፉን የጎንደር ዩኒቨርስቲ አስታውቋል።ትናንት ንጋት ላይ በዩኒቨርስተው የቬተርናሪ ፋርማሲ የሁለተኛ ዓመት ተማሪ የሆነው ማሾ ዑመር በደረሰበት ጉዳት ሕክምና ሲደረግለት የቆየ ቢሆንም አመሻሽ ላይ ህይወቱ ማለፉን ዩኒቨርስቲው ባውጣው የሀዘን መግለጫ ላይ ተጠቅሷል።ጉዳቱን በማድረስ የተጠረጠሩት ከሟች የመኝታ ክፍል ፊት ለፊት የሚገኙ ተማሪዎች ሲሆኑ ፖሊስ ሌሊቱን ሙሉ ምርመራ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን የምርመራ ውጤቱም እንደ ተጠናቀቀ ዩኒቨርስቲ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።ጎንደር ዩኒቨርስቲ እና የዩኒቨርስቲው ማኅበረሰብ በተማሪ ማሾ ዑመር ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገልጿል። ለሟች ቤተሰብም መጽናናቱን እንደሚመኝ አስታውቋል። ጎንደር ዩኒቨርስቲ ከቀናት በፊት በግቢው ውስጥ ብሔርን መሰረት ያደረጉ የጥላቻ ጽሑፎች ሲሰራጩ በቁጥጥር ስር ማዋሉን እና ብጥብጥ ሊያስነሱ ነበር ያላቸውን ኹለት ተማሪዎችንም እጅ ከፍንጅ በግቢው ጥበቃ አባላትና በክልሉ ልዩ ኃይል ማዋሉ የሚታወስ ነው።
Via Addis Maleda

የትግራይ ዴሞክስያዊ ትብብር (ትዴት) ለሁለት ቀናት ባካሄደው የመጀመርያ ጉባኤው ዶ/ር አረጋዊ በርሃን ሊቀ መንበር አድርጎ የሾመ ሲሆን ሌሎች የማእከላይ ኮሚቴ አባላትም መርጧል፡፡
ፓርቲው መስራች ጉባኤው ያካሄደው በአዲስአበባ ነው፡፡
Via Million H/Selassie
@YeneTube @FikerAssefa
ፓርቲው መስራች ጉባኤው ያካሄደው በአዲስአበባ ነው፡፡
Via Million H/Selassie
@YeneTube @FikerAssefa
ባህርዳርን ጨምሮ በምዕራብ አማራ ክልል በሚገኙ ከተሞች የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ከማለዳው ጀምሮ ተቋርጧል። አገልግሎቱ የተቋረጠው በክልሉ አዲስ የወጣ የትራፊክ ደንብን በመቃወም አሽከርካሪዎች አድማ በመምታታቸው ነው።
Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa