YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የሀረሪ ጉባኤ ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ አዲስ አፈ-ጉባኤ ሾመ።

የጉባኤው ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ አሚራ አሊ እንደገለፁት ዛሬ የተጠራው አስቸኳይ ስብሰባ የቀድሞው የሀረሪ ጉባኤ አፈ-ጉባኤ አቶ ሙህየዲን አህመድ ያቀረቡትን የስልጣን መልቀቅያ ጥያቄ ተመልክቶ ውሳኔ ለመስጠት ነው።በዚሁ መሰረትም የቀድሞው አፈ-ጉባኤ አቶ ሙህየዲን አህመድ ያቀረቡት የመልቀቂያ ጥያቄ በጉባኤው በሙሉ ድምፅ ፀድቆ አዲስ አፈ-ጉባኤ ተመርጧል።በጉባኤው አዲስ አፈጉባዔ ሆነው የተሾሙት አቶ ኻሊድ አልዋን ቃለ-መሃላ ፈፅመዋል፡፡አዲሱ ተሿሚ አቶ ኻሊድ አልዋን ከሹመታቸው በኋላ ባደረጉት ንግግር ከዚህ ቀደም በጉባኤው የተከናወኑ በርካታ ተግባራት ቢኖሩም የታዩ ክፍተቶችም እንደነበሩ አንስተው ጠንካራ ጎኖችን በማጠናከር ፤ ክፍተት የነበረባቸውን ለመለወጥ በትኩረት እንሰራለን ብለዋል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ጋንታ ካንቻማ ቀበሌ ትናንት ሌሊት የጣለው ዝናብ በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገለፀ፡፡

የጋሞ ዞን ፖሊስ መምርያ አዛዥ ኮማንደር ረታ ተክሉ እንዳሉት ትናንት ከምሽቱ 8 ሰዓት ገደማ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ በ300 አባወራ ቤቶች ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡በጎርፉ 500 ሄክታር የሙዝ ምርት መውደሙን አዛዡ ገልጸው ከዞኑ የተውጣጣ የፖሊስና አመራር አካላት ተጎጂዎችን በመጎብኘትና ወደ ሌላ አካባቢ በማሸጋገር ላይ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡የአደጋው መንስኤ በመንገድ ስራ ወቅት የጎርፍ ማፋሰሻ ትላልቅ ቱቦዎች በመደፈናቸው ምክንያት ነው ብለዋል ኮማንደሩ፡፡በጎርፉ አደጋ የሰው ህይዎት እንዳያልፍ የአካባቢው ህብረተሰብ አስቀድሞ ጥረት ማድረጉን ተናግረው ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይፈጠሩ ተገቢው ጥንቃቄ እንዲደረግ አዛዡ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ምንጭ: ደቡብ ቲቪ
@YeneTube @FikerAssefa
840 ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ አረቢያ ተመለሱ!

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሳውዲ አረቢያ መንግስት ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት ከአምስት እስከ ስምንት አመት ተፈርዶባቸው በሳውዲ እስር ቤቶች ይገኙ የነበሩ 840 ኢትዮጵያውያን በፈቃዳቻው ዛሬ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።

ኢትዮጵያውያኑ ቀይ ባህርን አቋርጠው የሳውዲን ድንበር ሲሻገሩ የተያዙ እና በሳውዲ አረቢያ በጂዳ እና ጂዛን ግዛት በሚገኙ እስር ቤቶች ይኖሩ የነበሩ ሲሆኑ፣ አብዛኛዎቹ ወጣቶች ናቸው። ተመላሾቹ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄነራል የሆኑት አቶ ዮሃንስ ሾዴ ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል። ከዚያ በኋላም ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርድት (IOM) የመጀመሪያ ደረጃ የህክምና እርዳታ አድርጎላቸዋል።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
ጣሊያን ኤርትራዊያን ስደተኞችን ወደ ሊቢያ በግዴታ መመለሷን ሕገ ወጥ ነው- ሲል አንድ የሮም ፍርድ ቤት ወስኗል፡፡ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር እና መከላከያ ሚንስትር 210 ሺህ ዩሮ ካሳ ለተጎጅዎቹ እንዲከፍሉም አዟል ፍርድ ቤቱ፡፡ እኤአ በ2009 ገና ከባሕር የተመለሱት 14ቱ ስደተኞች በጣሊያን ጥገኝነት የመጠየቅ መብት እንዳላቸው እንደተወሰነላቸው ኢንፎ ማይግራንት ድረ ገጽ አስነብቧል፡፡ ፍርዱ አምነስቲ ኢንተርናሽናል መንግሥት ላይ ለመሰረተው ክስ ምላሽ ነው፡፡

Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
ራይድ ታክሲ ምርጥ አገልግሎት ሰጪ በመባል ሽልማት አገኘ። የራይድ ታክሲዎችም ቁጥርም 9,000 አልፏል።

Center for Accelerated Women's Economic Empowerment (CAWEE) የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት የ2019 በኢትዮጵያ ምርጥ አገልግሎት ሰጪ ተቋም በማለት የራይድ ታክሲ ሀሳብ አመንጪና የሀይብሪድ ዲዛይን ባለቤትን ወይዘሪት ሳምራዊት ፍቅሩን በሀያት ሪጀንሲ ሆቴል በተካሄደ ፕሮግራም ላይ ሸልሟል።

-Tesfaye Getnet
@YeneTube @FikerAssefa
💥ማስታወቂያ💥
PUMA (GV SPECIAL)

📎ORIGINAL

Size 40-41-42-43

📌 Made in Vietnam
📌 Price 2200 birr
📌 With delivery
📌 በ 5 አይነት ከለር
📞 0912732493

ቴሌግራም ለማግኘት ሊንኩን ተጭነው ይቀላቀሉን👇👇
@Hkaeg
ኢትዮጵያ 173 ቀን በሚቆየውና 25 ሚልየን ህዝብ በሚጎበኘው በዱባይ 2020 ኤክስፓ ትሳተፋለች።

በዪናይትድ አረብ ኢመሬትሷ ዱባይ በኦክተበር 2020 በሚከፈተው እና 25 ሚልየን ህዝብ ይጉበኘዋል ተብሎ በሚጠበቀው የዱባይ2020 የንግድ ትእይንተና ባዛር ኢትዮጵያ የምትካፈል ሲሆን በመጪው ታህሳስ 2 የንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር እና ከዱባይ የተወከሉ የኤክስፓው አዘጋጆች በጉዳዩ ላይ መግለጫ ይሰጡበታል መባሉን ሰምቻለው።

ኢትዮጰያ ያላትን ምርት፣ባህልና የኢንቨስትመንት አማራጮቿን በኤክስፓ ታቀርባለች።
የዱባይ ኤክስፓ 192 ሀገራት ይሳተፉበታል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በዱባይና በአቡዳቢ ከተሞች መሀከል በተዘጋጀ 438 ሄክታር ላይ ኤክስፓ ይካሄዳል።

Via:- Tesfay Getnet
@Yenetube @Fikerassefa
የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ዴር ሌይን አዲስ አበባ ገብተዋል!
ቦሌ ኤርፖርት በመገኘት አቀባበል ያደረጉላቸው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው ናቸው።

ፎቶ: Ethiopian Airlines | Elias Meseret
@Yenetube @Fikerassefa
ኦባንግ ሜቶ "ለመተማመን እንነጋገር" በሚል ርዕስ በኤልያና ሆቴል ውይይት እያካሄደ ነው።

የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መስራች አቶ ኦባንግ ሜቶ ከተለተያዪ ምሁራንና የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የተሻለ ለውጥ ለማምጣት " ለመተማመን እንነጋገር" በሚል ርዕስ ዛሬ ቅዳሜ ህዳር 27 በኤልያና ሆቴል ወይይት እያካሄደ ነው ።

Via:- Tesfay Getnet
@Yenetube @Fikerassefa
በኦሮሚያ ለሚከሰቱ የጸጥታ መደፍረስ ዋነኛው ምክንያት የስራ አጥነት እንደሆነ የኦሮሚያ ኢኮኖሚስቶች ማህበር አስታወቀ።

የኦሮሚያ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጉቱ ቴሶ እንዳሉት በየቦታዉ ለሚነሱት ግጭቶች የስራ አጥነቱ ሚና ከፍተኛ ነዉ ብለዋል፡፡ከከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመርቀዉ የሚወጡ ተማሪዎች የስራ እድል ባለማግኘታቸዉ በትንሽ ገንዘብ ይታለላሉ ነዉ ያሉት፡፡እነዚህን ወጣቶች ወደ ስራ ማስገባት ችግር ፈጣሪዎች ማስፈፀሚያ እንዳይሆኑ ያደረጋል የሚሉት ዶክተር ጉቱ የስራ አጥነቱን ችግር ለመቀነስ መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

ሥራ የፈታዉ ወጣቱ ትዉልድ መሄጂያ ሲያጣ አማራጭ የሚያደርገዉ ጥፋትን ነዉ ፣ወጣቱ ለሀገሩ ያለዉ አመለካከት በብሄር ተገድቧል፣ ለዚህም የወጣቱን ርዕዮት አለም በማሻሻል የኢኮኖሚ ተጠቃሚነቱን ማረጋገጥ ይገባልም ብለዋል።ወጣቶች ህይወታቸውን በስራ ካልመሩ ድብርት ዉስጥ ይገባሉ፤ በራስ መተማመናቸውም ይነጠቃል ፣ጥርጣሬ፣ ፍራቻ፤ ለአእምሮ ህመም ተጠቂ ከመሆን አልፎ መጨረሻዉ ወደ ዝርፊያ እና አገርን ወደ ማወክ ይሰማራል ብለዋል።

መንግስት በራሱ ለዜጎች የስራ እድል ከመፍጠር ጀምሮ የግል ባለሃብቶችና ከሌሎች ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በተጨማሪ ሃብት መፍጠር የሚያስችሉ እቅዶችንና የኢንቨሰትመንት አማራጮችን መፍጠር ላይ እንዲያተኩር አሳስበዋል። በኢትዮጵያ እድሜያቸው ለስራ ዝግጁ ከሆኑ ዜጎች መካከል ከ11 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ሥራ እንደሌላቸው የፌደራል ስራ እድል ኮሚሽን መረጃ ያስረዳል። ከዚህ ውስጥ የኦሮሚያ ክልል ከሌሎች ክልሎች ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ነው።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ከኦሮሚያ ክልል መቱ ከተማ ወደ ባህርዳር ሲጓዝ በነበረ ተሽከርካሪ ደጀን ከተማ አቅራቢያ በተደረገ ፍተሻ 57ክላሽንኮቭ መሳሪያዎች መያዛቸውን የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ አስታወቀ።

Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
ለኢትዮጵያ የመሮጥ ፍላጎት ኖሮኝ አያውቅም። ኦሮሚያ ነጻ ካልወጣች በቀር" በማለት አትሌት ሲፈን ሃሰን ከቢቢሲ ጋር በነበራት ቆይታ ተናግራለች።ለኔዘርላንድስ የምትሮጠው ሲፈን በአሁኑ ወቅት በዓለም አትሌቲክስ የሴቶች አጠቃላይ የደረጃ ሰንጠረዥ አናት ላይ በአንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

ከቢቢሲ ጋር ያደረገችው ሰፋ ያለ ቆይታ👇👇👇
https://telegra.ph/Sifan-12-07
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ “አንድ ተማሪ ለአንድ ቤተሰብ" ፕሮጀክት በይፋ ተጀመረ

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ “አንድ ተማሪ ለአንድ ቤተሰብ" ፕሮጀክት ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።
ዩኒቨርሲቲው በተያዘው አመት ለማስተማር የተቀበላቸውን 5 ሺህ ተማሪዎች ከጎንደር ከተማ ቤተሰቦቻቸው ጋር ዛሬ አስተዋውቋል።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሯ ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም እንደገለፁት፥ ይህን የኢትዮጵያዊነት ስሜት የሚያጠናክር ተግባር በመውሰድና በማሻሻል ፕሮጀክቱ በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተግባራዊ ይደረጋል።
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር አስራት አፀደወይን ተማሪዎች ከእውቀት ግብይት ባለፈ በማህበራዊ ግንኙነታቸው ውጤታማ እንዲሆኑና ደህንነታቸው እንዲጠበቅ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የጎንደር ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ማስተዋል ስዩም በበኩላቸው፥ እንግዳ ተቀባይነትን ብቻ ሳይሆን ዝምድናን ማጠናከር ባህላችን ነው ብለዋል።
አያይዘውም ይህ የጎንደር የቤተሰብ ፕሮጀክት ውጤታማ እንዲሆን የበኩላችንን እንወጣለንም ነው ያሉት።

የቃል ኪዳን ልጆቻቸውን ለመረከብ በዚህ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት ወላጆችም ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን አጠናቀው እስከሚወጡ ድረስ ከጎናቸው በመሆን እንደሚንከባከቧቸው ተናግረዋል።

ወላጆች አያይዘውም የተረከቧቸውን የቃልኪዳን ልጆች በትምህርታቸው እንዲጠነክሩ ከማገዝ ባሻገር ስለ አብሮነትና አንድነት እንዲሁም የሀገር ፍቅር እንደሚያስተምሩም አውስተዋል።

በፕሮጀክቱ ከጎንደር ቤተሰብ ያገኙ ተማሪዎችም ሁለተኛ ወላጅ በማግኘታቸው ያለፍርሃትና ያለጭንቀት ትምህርታቸውን ተረጋግተው ለመማር እንደሚረዳቸው ገልጸዋል።

Via:- Fana
@Yenetube @Fikerassefa
ከ40 በላይ አለም አቀፍ ብራንድ ሆቴሎች በኢትዮጵያ ሰራ ለመጀመር መስመር ላይ ናቸው።

ከሆቴል አማካሪዎች ባገኘሁት መረጃ አዲስ አበባን ጨምሮ በኢትዮጵያ ባሉ ክልሎች ከ40 በላይ አለም አቀፍ ብራንድ ሆቴሎች አገልግሎታቸውን ለመስጠት ከነባር ሀገር በቀል እና አየተገነቡ ካሉ ሆቴሎች ጋር ድርድር ላይ መሆናቸውን ነግረውኛል።

Via Tesfaye Getnet
@YeneTube @FikerAssefa
“እንደርሳለን” በሚል መሪ ቃል የህዳር ወር የትራፊክ አደጋን የመከላከልና የግንዛቤ ንቅናቄ የባለድርሻ አካላት መድረክ እየተካሄደ ነው።

መድረኩ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ ነው እየተካሄደ የሚገኘው። የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የትራንሰፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስን ጨምሮ ሚኒስትሮችና ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛል።በመድረኩ በ2011 ዓ.ም ብቻ ህይወታቸውን ላጡ 4 ሺህ 597 ሰዎች የህሊና ፀሎት ተደርጓል።

የዛሬው ምክክር የትራንስፖርት ሚኒስቴር በሁሉም ከተሞች እያከናወነው የሚገኘውን የህዳር ወር ሃገር አቀፍ የመንገድ ትራፊክ አደጋ የግንዛቤ ማስጨበጫ አካል ነው ተብሏል። በመንገድ ትራፊክ አደጋ ምክንያት እየጠፋ ያለውን ህይወት፣ ሃገራዊ የንብረት ውድመትና የአካል ጉዳትን መቀነስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት የሚደረግበትና ባለድርሻ አካላት የራሳቸውን የቤት ስራ የሚወስዱበት ነው።በመድረኩ ከዘጠኙም ክልሎች የተገኙ 122 ጠንቃቃ አሽከርካሪዎችና 6 ልዩ ተሸላሚዎች እውቅና እና ሽልማት እንደሚበረከትላቸው የዘገበው ኤፍቢሲ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢፌደሪ መከላከያ ሰራዊት ምክትል ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሀኑ ጁላ በቅርቡ የፀደቀውን የመከላከያ ሰራዊት መተዳደሪያ ደንብ በመተግበር የሰራዊቱን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናገሩ፡፡

ምክትል ኢታማዦር ሹሙ ይህን ያሉት በተሻሻለው የመከላከያ ሰራዊት መተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ለሰራዊቱ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ማጠናቀቂያ መርሀ ግብር ላይ ተገኝተው ነው፡፡

https://telegra.ph/YeneTube-12-07
ጀርመናዊው የጴንጤኮስታል ሰባኪው ሪናርድ ቦንኬ ከዚህ አለም በሞት ተለየ።

ኢትዮጰያን ጨምሮ በብዙ የአፍሪካና የአለም ሀገራት በጴንጤኮስታል ወይንም በፕሮቴስታንት ክርስቲያን እንቅስቃሴ ሰባኪነቱ የሚታወቀውና የክሪስት ኦል ኔሽን መስራቹ ጀርመናዊው ሪናርድ ቦንኬ ዛሬ መሞቱን ቤተሰቦቹ አሳውቀዋል።

የስስት ልጆች አባት የነበረው ቦንኬ በወንጌል ሰበካ አገልግሎት ከ60 አመት በላይ ቆይቷል።

ቤተሰቦቹም በሰባኪው ፌስ ቡክ ገፅ ባሰፈሩት መልእክት " አባታችን ፣አያታችን ፣ሰባኪያችን የነበረውን ሪናርድ ቦንኬ ዛሬ ቅዳሜ ህዳር 27 መሞቱን ስናሳውቃቹ ከባድ ሀዘን እየተሰማን ።ቦንኬ በቤተሰቦቹ እንደተከበበ በሰላም ይቺን አለም ተሰናብቷል" በማለት በፅሁፍ አስፈረዋል።

Via:- ትርጉም - Tesfay Getnet
@Yenetube @Fikerassefa
''Bulchiifni Magaalaa Finfinnee Maaster pilaanii haaraa baasuf, Kutaa magaalaa lakkoofsan baay’isuufi'' jedhamee, midiyaalee Hawaasaa adda addaa irra kan oofamaa jiru, #soba ta’uu Uummatni hubatee, ololli deemaa jiru, dhugummaa akka hin qabne bulchiifni Magaalaa Finfinnee Ni hubachiisa!

- Mayor Office
@YeneTube @FikerAssefa
"የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር የከተማዋን ማስተርፕላን ሊያሻሽል ነው፤ በከተማዋ ያሉት የክፍለ ከተማዎች ቁጥርም ወደ 13 ከፍ ሊል ነው" በሚል በማህበራዊ ድረ ገጾች እየተዘዋወረ ያለው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን የከተማ መስተዳድሩ አሳውቋል። የከተማ አስተዳደሩ ምንም አይነት አዲስ የከተማ አደረጃጀትም ሆነ ማስተርፕላን የመተግበር ሀሳብ የሌለው መሆኑን ገልጿል።

ምንጭ: የከንቲባው ጽ/ቤት
@YeneTube @FikerAssefa