YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#በቢራና #በሲጋራ ዋጋ ላይ 30 እና 40 በመቶ ኤክሳይዝ ታክስ ይጣላል!

በዚህ መሠረት በቢራ ላይ የሚጣለው ኤክሳይዝ ታክስ በጠርሙስ 40 በመቶ ወይም በሊትር 11 ብር እንዲከፈል በረቂቅ ድንጋጌነት ቀርቧል፡፡ ሃያ ፍሬዎችን በሚይዝ አንድ ፓኬት ሲጋራ መሸጫ ዋጋ ላይ 30 በመቶና ተጨማሪ አምስት ብር እንዲሰላ በድንጋጌው ተመልክቷል፡፡በእያንዳንዱ የቢራና የሲጋራ ምርት ላይ ኤክሳይዝ ታክስ የተከፈለበት መሆኑን የሚያመለክት ቴምብር መለጠፍ እንደሚኖርበት በአስገዳጅነት ተቀምጧል፡፡ከዚህ በተጨማሪም ኤክስይዝ ታክስ የሚከፈልበትን ምርት ለማምረትም ሆነ ለማስመጣት፣ እንዲሁም አገልግሎት ለመስጠት ከገቢዎች ሚኒስቴር ልዩ ፈቃድ መያዝ በአስገዳጅነት ተካቷል፡፡ በቢራ አምራችነት ፈቃድ ከተሰጣቸው ኩባንያዎች ውጪ በባር ወይ በምግብ ቤቶች አነስተኛ ቢራ ጠመቃ ለማካሄድ ተጨማሪ ፈቃድ ማግኘትም አስገዳጅ ሆኖ በረቂቁ ተካቷል፡፡

በሥራ ላይ ያለው አዋጅ በቢራ ምርቶች የማምረቻ ዋጋ ላይ የሚጥለው ኤክሳይዝ ታክስ 50 በመቶ ሲሆን፣ በትምባሆ ምርት የማምረቻ ዋጋ ላይ ደግሞ 75 በመቶ ይጥላል።በመሆኑም የማኅበረሰብ ጤናን በከፍተኛ ደረጃ ያቃውሳሉ የተባሉት በሁለቱ ምርቶች ላይ እንዲጣል የቀረበው አዲስ የኤክሳይዝ ታክስ፣ እጅግ ዝቅተኛና የማኅበረሰብ ጤናን ያላገናዘበ መሆኑን ባለሙያዎች ያስረዳሉ።

በተለይ በትምባሆ ምርት ላይ የዓለም የጤና ድርጅት የሚያስቀምጠው የታክስ ምጣኔ 70 በመቶ መሆኑን የሚናገሩት ባለሙያዎቹ፣ አሁን የተረቀቀው ኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ በዓለም የጤና ድርጅት ከተቀመጠውም ሆነ ከሰሃራ በታች የሚገኙ አገሮች በሲጋራ ላይ ከሚጥሉት ኤክሳይዝ ታክስ በእጅጉ እንደሚያንስ ይገልጻሉ።የኢትዮጵያ ፓርላማ ትምባሆን ለመቆጣጠር ባወጣው ጥብቅ ሕግ በዓለም ጤና ድርጅት ባለፈው ዓመት መሸለሙን የሚያስታውሱት ባለሙያዎቹ፣ አዲሱ ኤክሳይዝ ታክስ በሲጋራ ላይ ለመጣል ያቀደው የታክስ ምጣኔ የኅብረተሰብ ጤናን ለመጠበቅ ታስቦ የፀደቀውን የትምባሆ ቁጥጥር አዋጅ ዓላማ የሚቃረን በመሆኑ መንግሥት በድጋሚ ሊያጤነው ይገባል ብለዋል።

በዘንድሮው የበጀት አዋጅ መሠረት 4.2 ቢሊዮን ብር በአገር ውስጥ በሚመረቱ ቢራ መጠጦች ላይ ከሚጣል ኤክሳይዝ ታክስ ለመሰብሰብ፣ እንዲሁም 1.1 ቢሊዮን ብር ከሲጋራ ወይም ከትምባሆ ምርቶች ኤክሳይዝ ታክስ እንዲሰበስብ ለገቢዎች ሚኒስቴር ኃላፊነት ተሰጥቶታል።

በሥራ ላይ በሚገኘው አዋጅ ኤክሳይዝ ታክስ ካልተጣለባቸው ምርቶች በረቂቁ እንዲካተቱ ከተደረጉት መካከል አንዱ ሰው ሠራሽ ፀጉር ወይም “ሂዩማን ሄር” ሲሆን፣ 100 በመቶ ኤክሳይዝ ታክስ እንዲጣልበት በረቂቁ ተካቷል፡፡

Via:- ሪፖርተር
@Yenetube @Fikerassefa