YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.92K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በአፋርና በሱማሌ ክልል ህዝቦች መካከል የሚከሰቱ ግጭቶችን በዘላቂነት ለመፍታት መስማማታቸውን የሁለቱም ክልሎች አመራሮች ተናገሩ!

በአፋርና በሱማሌ ክልል ህዝቦች መካከል የሚከሰቱ ግጭቶችን በዘላቂነት ለመፍታት ከፌደራል የፀጥታ ሀይል ጋር በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን የሁለቱም ክልሎች አመራሮች በሰጡት የጋራ መግለጫ ተናግረዋል፡፡
ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከአፋርና ሱማሌ ክልል አመራሮች ጋር የመከላከያና የሰላም ሚኒስቴር አመራሮች በተገኙበት በፀጥታ ጉዳይ ውይይት አድርገዋል፡፡የሱማሌ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሀሰን እና የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ በጋራ በሰጡት መግለጫ የተከሰተውን ግጭት ለመፍታት የአመራሩ ቁርጠኝነት እንዳለ ተናግረዋል፡፡ችግሩን በህግ አግባብ እንዲፈታ በሀላፊነት ስሜት እንደሚንቀሳቀሱም የሁለቱም ክልሎች አመራሮች አስታውቀዋል፡፡

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ በአሜሪካ የኢኮኖሚ፣ የልማትና የኢነርጂ ምክትል ጸሃፊ ጋር ተወያዩ።

ክቡር የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ በአሜሪካ የኢኮኖሚ፣ የልማት፣ የአካባቢና የኢነርጂ ዘርፍ ምክትል ጸሃፊ ኬት ክራች (Keith Krach) ጋር ዛሬ መስከረም 7 ቀን 2012 ዓ.ም ተወያይተዋል።ኢትዮጵያ እያካሄድ ያለውን ወቅታዊ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ የለውጥ እርምጃዎች አስመልክቶ ክቡር ሚነስትሩ ማብራሪያ ሰጥተዋል።በአገር በቀል የኢኮኖሚ መርሆዎች በመነሳት የአሜሪካን ጨምሮ የውጭ ባለሃብቶችን ለመሳብ ሰፊ ስራዎች እየተካናወኑ መሆኑን ክቡር ሚኒስትሩ ገልጸዋል።ምክትል ጸሃፊ ኬት ክራች በበኩላቸው ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለውን ለውጥ እንደሚያደንቅ በመግለጽ የሁለቱ አገራት ግንኙነት የበለጠ እንዲጎለብት የአገራቸው ፍላጎት መሆኑን ተናግረዋል።

ምንጭ: በዋሽንግተን የኢትዮጵያ ኤምባሲ
@YeneTube @FikerAssefa
Brand New Samsung A10 (2019)
32GB
2GB RAM
Fast Face Unlock
FOR MORE INFORMATION GO TO 👉 https://m.dalibr.com/ProductDetailM.php?proid=10
Forwarded from YeneTube
ማስታወቂያ 💥

BLUE Brand Solutions

Blue Brand Solutions brought you the latest
📌Technologies(smartphones,Laptops)

📌 Men's and women's clothing👔

📌 Human hair 🙆‍♀

📌Musical instruments

📌Mens and Women's Perfume

Contact; @sherlockseller @Nah22
Call us
+251947896322&+251945421100

ቻናላቸውን ተቀላቅለሁ ይመልከቱ⬇️
https://tttttt.me/blueelec
Forwarded from YeneTube
ማስታወቂያ💥

Buy and Order Quality clothes we will bring any orders from USA 🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸 in 8 to 15 days
for more info: @order_us1_inbox
0911073577 (abrsh)
👉tops 👚
👉Demin👖
👉Dress 👗
👉underwear 👙
👉T- shirt 👕
For more 👇🏾👇🏾👇🏾join the chanal
👉🏻 https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFeEeXHsZxR6KmWVxA

🏠location: medihanialem mall, 3rd floor , 306
Forwarded from YeneTube
Macbook Pro😍 15.4" 256GB SSD Intel Core i7 9th Gen 2.60 GHz 16GB Touch Bar - Space
Call now🏃‍♂+251912894363
Or via ZenachBrands1
Join our channel 😍😍@ZenachBrands for more items
ሲጠበቅ የነበረው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ 'መደመር' መጽሀፍ በዛሬዉ ዕለት ጥቅምት 8 ቀን 2012 በሚሊኒየም አዳራሽ ስምንት ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት ይመረቃል:: እንዲሁም ከ30 በላይ ከተሞች ላይ ይመረቃል:: ይህ መጽሀፍ ኢትዮጵያ በቀጣይ የምትከተለውን የኢኮኖሚ: ፖለቲካዊ እና የውጭ ግንኙነት አቅጣጫ የሚተነትንና ፋኖተ ካርታ የሚያስቀምጥ ነው።

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
አዳዲስ መኪኖች ላይ የቀረጥ ቅናሽ ተደረገ።አለምአቀፉ የጉሙሩክ ድርጅት በየ5 አመቱ የሚያሻሽለውን መጽሐፍ መሠረት በማድረግ ከሁለት አመት በፊት ተከልሶ መጠናቀቅ ይገባው የነበረው የታሪፍ መጽሐፍ በማዘጋጀት ያፀደቀው የገንዘብ ሚኒስቴር በአዳዲስ መኪኖች ላይ የ5% ቅናሽ አድርጓል።

ምንጭ: አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
አሳዛኝ ዜና!!

በአዊ ብሔ/አስተዳደር በባንጃ ወረዳ ዘንገና ሀይቅ አከባቢ ዛሬ በቀን 8/2/2012/ዓ/ም በደረሰ የትራፊክ አደጋ በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ። አደጋው ከጥዋቱ 12:00 ላይ ኮደ 3 አማ 13673 የህዝብ ሀይሩፍ ከቲሊሊ ወደ እንጅባራ እና ከባህርዳር ወደ አዲስ አበባ ይጓዝ የነበረው የህዝብ አውቶብስ ኮድ 3 ኢ ት A 02863 በመጋጨት የ10 ሰዎች ህይወት ወዲያዉኑ ሲያልፍ ቀሪዎቹም እንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛሉ ።

ምንጭ: የአዊ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን
@YeneTube @FikerAssefa
20 ዓመታት ያስቆጠረው የጥቁር አባይ ቆዳ ፋብሪካ ተዘጋ።

ባለፉት 20 ዓመታት የቆዳ ምርቶችን በማምረት ወደ ውጭ በመላክ የሚታወቀው እና በደብረብርሃን ከተማ ከቀዳሚዎቹ ፋብሪካዎች ውስጥ የሚጠቀሰው የጥቁር አባይ ቆዳ ፋብሪካ የአካባቢ ብክለት በማስከተሉ መዘጋቱ ተገለፀ፡፡የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ደስታ አንዳርጌ በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል እንደገለፁት፣ ከሁለት አሥርት ዓመታት በላይ ያቋረጠው ፋብሪካ በአካባቢ ብክለት ምክንያት ከነዋሪዎች በተነሳ ተደጋጋሚ ቅሬታ እንዲዘጋ መደረጉን አረጋግጠዋል፡፡ፋብሪካው ቀደም ሲል ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል የፈጠረና በአመሰራረቱም ከቀዳሚዎቹ ውስጥ የሚጠቀስ ነበር፡፡ ይሁንና ከከተማው መስፋት ጋር ፋብሪካው ያለበት ስፍራ ዋና የመኖሪያ ማዕከል ሆኗል፡፡

ምንጭ: ኢፕድ
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያዊው አትሌት በዶፒንግ ምርመራ እገዳ ተጣለበት!

አሶሺዬትድ ፕሬስ ከሞናኮ እንደዘገበው - በመላው አፍሪካ ውድድሮች በ10,000 ሜትር አሸናፊ የነበረው እና ከሁለት ሳምንት በፊት ኬንያዊው አትሌት ጄፍሪ ካዎሮንሮ የግማሽ ማራቶን የዓለምን ሪከርድ በሰበረበት ውድድር በሶስተኛ ያጠናቀቀው እንዲሁም በIAAF የረጅም ርቀት አትሌቶችየደረጃ ሰንጠረዥ በ5ኛነት የሚገኘው ብርሃኑ ፀጋ አሁን እገዳ ተጥሎበታል።የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የፀረ-አበረታች ክፍል እናዳስታወቀው በEPO የታገደ እና የተከለከለ የጡንቻ እድገትን የሚጨምር ሆርሞን የዶፕተንት ምርመራ ውጤቱ ላይ በመገኘቱ አትሌት ብርሃኑ ፀጋ ከአለም አቀፍ ውድድሮች መታገዱን ዘገባው ያመለክታል።

Via Ethio Kickoff
@YeneTube @FikerAssefa
13 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ 200 የባቡር ፉርጎዎች እስካሁን ወደ አገር ውስጥ አልገቡም

በቻይና ሀገር የተመረቱና 13 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ሁለት መቶ የባቡር ፉርጎዎች እስካሁን ድረስ ወደ አገር ውስጥ እንዳልገቡ የኢትዮ ጂቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር አስታወቀ።የአክሲዮን ማህበሩ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ጥላሁን ሰርካ ሰሞኑን ከአዲስ ዘመን ጋር በነበራቸው ቆይታ የባቡር ፉርጎዎቹን ከቻይናውያኑ ለመግዛት ሲታሰብ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማምጣት ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንደነበር ገልፀዋል።ከዚሁ የባቡር ግዢ ውስጥ ከ30 አስከ 35 በመቶ የሚሆነውን በአገር ውስጥ በማምረት ለመሸፈን በመንግሥት በኩል አቅጣጫ መያዙንም ጠቅሰዋል።

ምንጭ: አዲስ ማለዳ/ኢፕድ
@YeneTube @FikerAssefa
የደቡብ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ የ148 ዳኞችን ሹመት በማጽደቅ ተጠናቀቀ!

ከጥቅምት 4 እስከ 7/2012 ዓ.ም ድረስ ሲካሄድ የቆየው የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት ጉባኤ የ148 ዳኞችን ሹመትና የአንድ ዳኛ ስንብት በማድረግ ተጠናቋል፡፡የዳኞችን ሹመት ለምክር ቤቱ ያቀረቡት የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት አቶ ሙሉጌታ አጎ ናቸው፡፡የፍርድ ቤቱ ፕሬዘዳንት ባቀረበት መሰረት አንድ የወረዳ ዳኞ በፈፀሙት የስነ ምግባር ግድፈትና ወንጀል የዳኞች ጉባኤ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት የዳኛውን ስንብት ከመረመረ በኋላ ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ ተቀብሎ አጽድቋል፡፡

ከዳኞች ሹመት ውስጥ የሴቶች ቁጥር አነስተኛ መሆኑን የምክር ቤቱ አባላት ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት ጥያቄ የቀረበላቸው ሲሆን የሴቶች ቁጥር ሊያንስ የቻለበት ዋንኛ ምክንያት ሴቶች በህግ ትምህርት ያላቸው ተሳትፎ ማነሱ መሆኑን አንስተው ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር የሴቶች የህግ ትምህርት ተሳትፎ እንዲጨምሩ መስራት ተገቢ እንደሆነ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት አቶ ሙሉጌታ ገልጸዋል፡፡ምክር ቤት የ148 ዕጩ ዳኞችን ሹመት በሙሉ ድምጽ ካፀደቀ በኋላ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ ደምሴ ዶልቻ ዕጩ ዳኞችን ቃለ መሀላ በማስገባት የምክር ቤቱ ጉባኤ ተቋጭቷል፡፡

Via SRTA
@YeneTube @FikerAssefa
የዓዲ ግራት ዩኒቨርስቲ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን እየተቀበለ ይገኛል።ሰሞኑን የዩኒቨርስቲው አመራር ከዓዲ ግራት ህዝብ ጋር አዲስ ገቢ ተማሪዎችን በደመቀ መልኩ መቀበል የሚያስችል ውይይት እና ቅድመ ዝግጅት ሲያደርጉ መቆየታቸውን ድምፂ ወያኔ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
መደመር፣ የዶክተር አብይ መጽሃፍ ዛሬ አዲስ አበባን ጨምሮ በ20 ከተሞች በምረቃ ላይ ነው፡፡በሶስት ቋንቋዎች (በአማርኛ፣ ኦሮምኛና እንግሊዝኛ) የተጻፈው መጽሃፍ በቀጣይ በውጭ ሃገራት ይመረቃል፡፡የመደመር እሳቤ የሃገራችን ቀጣይ የለውጥ ጉዞ ላይ መሻገሪያ እሳቤ ሆኖ ሃገራዊ አንድነትን፣ የዜጎች ክብርን እና ብልጽግናን የማሳት ግብ አለው ተብሏል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር በአዲስ አበባ ውይይት እያካሄደ ነው፡፡

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) በኢትዮጵያ የመጣውን ለውጥና በትግራይ ሕዝብ ላይ ያለውን የወደፊት አንድምታ እንዲሁም በለውጡ የራሱን ሚና አስመልክቶ በአዲስ አበባ ውይይት እያደረገ ነው፡፡በውይይቱ ትዴት ዓላማና ፕሮግራሙን አስመልክቶ ግንዛቤ እያስጨበጠም ነው፡፡ በአዲስ አበባ ሀገር ፍቅር ቲያትር አዳራሽ የትዴት አባላት፣ ደጋፊዎች፣ የተፎካካሪ ፓርቲዎችና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት ውይይት ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

‹‹ካልተሰባሰበ ትልቅ ሀገር ይልቅ የተሰባሰበች ትንሽ ሀገር ቁም ነገር ትሠራለች›› ያሉት የትዴት ሊቀ መንበር አረጋዊ በርሄ (ዶክተር) አንድነት በኢትዮጵያ እንዲጠነክር በየቦታዉ የሚነሱ ጥያቄዎችን በትብብር መፍታት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡ ‹‹የትህነግ አመራር የትግራይ ሕዝብን የመልካም አስተዳደር ችግር እና ፍትሕና ዴሞክራሲ ሳያስከብር ፓርቲዉንና ሕዝቡን ‹አንድ ነው› ብሎ መናገሩ ተገቢ አይደለም፡፡ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ የሆኑትም ጥቂት ግለሰቦች ናቸው፤ ሕዝቡ ላይ የሚፈጥረውን ውዝግብ ማቆም አለበት፤ ይህንንም ለመታገል ትዴት የፖለቲካ ምኅዳሩ እንዲሰፋ ይሠራል›› ብለዋል ዶክተር አረጋዊ በንግግራቸው፡፡

ምንጭ: አብመድ
@YeneTube @FikerAssefa
''መደመር'' መፅሀፍ ተመረቀ!

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተፃፈው መደመር መፅሀፍ በሚሊኒየም አዳራሽ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አርቲስቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል።በምረቃ ስነስርዐቱ ላይ የጥበብ ባለሙያዎች ከመፅሀፉ ምዕራፎች ጥቂቱን ያነበቡ ሲሆን የመፅሀፍ ዳሰሳም ቀርቧል።የእለቱ የክብር እንግዶች ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፣ ቀዳማይ እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ እና የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ የተዘጋጀውን ኬክ ከቆረሱ በኋላ መፅሀፉን ለተተኪ ተማሪዎች በስጦታነት አበርክተዋል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
#Shot_Fired !

📌 ''ውስኪ ጠጭ ኢህአዴጎች ውሀ የሚጠጣ ህዝብ እንዳለ አትርሱ''

📌 ''በአምስት ሺህ ብር ደመወዝ ሆቴል እየተቀለባችሁ (ምንጩን ፈጣሪ ይወቀው) ዳቦ የራበውን ህዝብ ላንተ ቆሜልሀለሁ ማለት ዘበት ነው።''

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኢህአዴግን ውህደት አስመልክተው እየወጡ ያሉ የተሳሳቱ መግለጫዎችን መሠረት አድርገው ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ ካደረጉት ንግግር የተወሰደ

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
አምስተኛው የማስ ስፖርት መርሃ-ግብር እሁድ ይካሄዳል፡፡

የአበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ40ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ32ኛ ጊዜ “ቱሪዝም ለሥራ እድል ፈጠራና ለተሻለ ህይወት” በሚል መሪ ቃል በከተማ ደረጃ እየተከበረ ያለውን የአለም ቱሪዝም ቀን ምክንያት በማድረግ ከአዲስ አበባ ስፖርት ኮምሽን ጋር በጋራ በመሆን ከ100ሺ ሰው በላይ ተሳታፊ የሚሆንበት አምስተኛው ከተማ አቀፍ የማስ ስፖርት መርሃ-ግብር እሁድ (ጥቅምት 9 ቀን 2012 ዓ.ም) ከማለዳው 12:30 ጀምሮ በመስቀል አደባባይ ይካሄዳል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ በመቀሌ ሊካሄድ የነበረ ሠላማዊ ሰልፍ በፖሊስ ተበተነ!

'ህድሪ ሰብ' በተባለ ማህበር ዛሬ ቅዳሜ መቀሌ ከተማ ውስጥ ሊካሄድ ተጠርቶ የነበረው ሠላማዊ ሰልፍ ህጋዊ አይደለም ተብሎ በፖሊስ ተበተነ።ይህ ሠላማዊ ሰልፍ የተጠራው የትግራይ ክልል የከፍተኛ የትምህርት ተቋም ተማሪዎች ችግር ያጋጥማቸዋል ወደተባሉ ቦታዎች እንዲሄዱ እንዳይደረግ በክልሉ መንግሥት ላይ ግፊት ለማድረግ እንደነበረ ተነግሯል።ሠላማዊ ሰልፉን የጠራው ማህበር ሊቀ መንበር መሃሪ ዮሐንስ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ስለሰልፉ ለማሳወቅ ለመቀሌ ከተማ ከንቲባ ጸሐፊ ደብዳቤ ማስገባታቸውንና ግልባጩንም ለዞኑ ፖሊስ ለማስገባት ሙከራ ባደረጉበት ወቅት አንቀበልም መባላቸውን ተናግረዋል።

ሊቀ መንበሩ በተጨማሪ ሠላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ መንግሥት ሁኔታዎችን እንዲያመቻች ማሳወቅ እንጂ የመፍቀድና የመከልከል ህጋዊ መብት የለውም ብለዋል።ዛሬ ጠዋት ሠላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ሮማናት ተብሎ በሚጠራው የመቀሌ ከተማ አደባባይ መሰባሰብ በጀመሩበት ጊዜ ፖሊሶች ወደ ስፍራው መጥተው ሰልፉ ህጋዊ ስላልሆነ በመግለጽ እንዲያስቆሙ መታዘዛቸውን በመግለጽ ሰልፈኞቹ እንዲበተኑ ማድረጋቸውን የሰልፉ አስተባባሪዎች ተናግረዋል።አስተባባሪዎቹም ከፖሊስ ጋር ግብግብ መፍጠር ተገቢ ባለመሆኑ ሰልፉን ለማካሄድ ለሁለተኛ ጊዜ ለፖሊስ የማሳወቂያ ደብዳቤ እንደሚያስገቡ ተናግረዋል።

የመቀሌ ከተማ ምክትል ከንቲባ ስለተከለከለው ሠላማዊ ሰልፍ ተጠይቀው "ሰልፉ ሊከለከል አይገባም። ቢሆንም የጸጥታውን ሥራ በተመለከተ ማን ተጠይቆ ምን መልስ ተሰጠ? የሚሉትን ጥያቄዎች መመለስ ይገባል" ብለዋል።የሠላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ደብዳቤውን ተቀብሎ ወደሚመለከተው አካል ያላቀረበ ግለሰብ ካለ እንቀጣለን" ያሉት አቶ አቶ ብርሐነ፤ ለፖሊስ ቀርቦ ነበር የሚለው ቅሬታን ተከትሎ ፖሊስ የመከልከል መብት ስለሌለው ተቀባይነት እንደሌለው ገልጸዋል።ሠላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ተጠይቆ ሲከለከል በዚህ ሳምንት ውስጥ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን፤ ከቀናት በፊት በሴቶች ላይ የሚፈጸም ጾታዊ ጥቃትን ለማውገዝ በተመሳሳይ መቀሌ ውስጥ ሠላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ጥያቄ ቀርቦ እንደተከለከለ መዘገባችን ይታወሳል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa