YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.92K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች ውሃ ማድረስ አለመቻሉን ባለስልጣኑ አስታወቀ!

ከትናንት ጀምሮ በውሃ ግፊት ጣቢያዎች አካባቢ ባጋጠመ የኤሌትሪክ መቋረጥ ምክንያት በአዲስ አበባ በተወሰኑ አካባቢዎች በፈረቃቸው መሰረት ውሃ ማድረስ አልቻልኩም ሲል የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታወቀ። የኤሌትሪክ አገልግሎት መርሀ ግብሩን ሳያሳውቀን መብራት እያጠፋ በመሆኑ በሳምንት አንድ ቀን ውሃ የሚያገኙ ደንበኞቻችን ላይ ከፍተኛ ችግር እየፈጠረ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ኃላፊ ሰርካለም ጌታቸው በተለይ ለኢቲቪ ገልጸዋል።በፈረቃቸው መሰረት ውሃ ያላገኙትም በአራዳ እና ጉለሌ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ የተወሰኑ አካባቢዎች ናቸው ብለዋል።የአዲሰ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ በቀለ ክፍሌ በበኩላቸው፣ በአካባቢው በነበረ የኤሌክትሪክ ፕሮጀክት ስራ አደጋ በመከሰቱ ምክንያት አገልግሎቱ ሊቋርጥ መቻሉን ተናግረዋል።በዚህ ምክንያት የመብራት ኃይል በመቋረጡ በጽዮን ሆቴል አካባቢ ላለው ጉድጓድ የሚሰጠው ኃይል ሊቋረጥ ችሏል ብለዋል።ነገር ግን ችግሩን ለመቅረፍ በአሁኑ ሰዓት አፋጣኝ የጥገና ስራ እየተከናወነ ነው ሲሉ ኃላፊው አክለዋል።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለቻን 2020 ማጣርያ የመልስ ጨዋታቸውን ከሩዋንዳ ጋር ዛሬ ያደርጋል!

ዋልያዎቹ ለስድስተኛ ጊዜ በካሜሮን አስተናጋጅነት ለሚዘጋጀው ቻን 2020 ማጣርያ ከሩዋንዳ ጋር የመልስ ጨዋታቸውን ዛሬ ከቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ የሚያካሂዱ ይሆናል።በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ በሜዳው 1 ለ 0 የተሸነፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ውጤቱን ቀልብሶ ወደ ቀጣይ ዙር ለማለፍ ጥረት እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

@YeneTube @FikerAssefa
ከቃሊቲ ማረሚያ ታራሚዎች አመለጡ!

ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ዞን አንድ ማምለጣቸውን ምንጮች ለዋዜማ ተናገሩ፡፡ በነፍስ ግድያ ጥፈተኛ ተብለው በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የነበሩት 2 ታራሚዎች አሸናፊ መለሰ ፤ሳሙኤል መካ ጥቅምት 2 ቀን 2012 ዓ. ም ከረፋዱ 3 እስከ 4 ባለው ሰአት ውስጥ ከማረሚያ ቤቱ ቅጥር ግቢ ያመለጡ ሲሆን፤ ኤፍሬም ገ/ ጊዩርጊስ የተባለ ሌላ እስረኛ ደግሞ ለህክምና ወደ ሆስፒታል ሲወሰድ ከመኪና ላይ ዘሎ ማምለጡን ምንጮች ተናግረዋል ፡፡ማረሚያ ቤቱ የሁለቱ የታራሚዎቹን ማምለጥ ማታ በቆጠራ ሰአት እንዳወቀ ምንጮች ተናግረዋል፡፡ ይህን ተከትሎ ማረሚያ ቤቱ በእስረኞች ላይ ቁጥጥሩን ማጥበቁ ትተሰምቷል።

“እንደሚያመልጡ ታውቁ ነበር” ፣ “ያያችሁት ነገር አለ” በሚል ታራሚዎች ላይ ከፍተኛ ወከባ እየደረሰ እንደሆነ የታራሚ ቤተሰቦች ተናግረዋል። እስረኞች የጣት ቀለበትና የአንገት ሀብልም እንዲያወልቁ መደረጋቸው አግባብ አይደለም ይላሉ።የእስረኞቹን እንዴት አንዳመለጡ እና አሁንስ በቁጥጥር ስር ውለዋል ወይ? ብለን ተጨማሪ ማብራሪያ ለመጠየቅ ወደ ማረሚያ ቤቶች የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ገረመው አያሌው ስልክ የደወልንላቸው ሲሆን ከጠየቅናቸው በኃላ “የማይመች ቦታ ነኝ መልሼ ልደውል” በማለት የእጅ ስልካቸውን ዘግተውታል ፣ በተደጋጋሚ ብንደውልም ሊሰራልን አልቻለም፡፡

ዘገባው የዋዜማ ሬዲዮ ነው

@YeneTube @FikerAssefa
ዋልያዎቹ ከቻን 2020 ማጣሪያ ውጪ ሆነዋል!

ዋልያዎቹ ዛሬ ከሩዋንዳ አቻቸው ጋር ያደረጉትን የመልስ ጨዋታ በአንድ አቻ ውጤት አጠናቀዋል። 2ለ1 በሆነ የደርሶ መልስ ውጤት ሩዋንዳ የቻን 2020 ተሳታፊ መሆኗን ስታረጋግጥ፤ ኢትዮጵያ ግን ማለፍ ሳትችል ቀርታለች።መስፍን ታፈሰ በ72ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ ሲመራ የነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ83ኛው ደቂቃ የአቻነት ግብ ተቆጥሮበት ነው ከውድድሩ የተሰናበተው።የሩዋንዳን የአቻነት ግብ ያስቆጠረው ኧርነስት ሴጉራ ነው።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
ኬንያውያን በልግስና ከአፍሪካ ቀዳሚ ናቸው ተብሏል!

የማያውቋቸውን የተቸገሩ ሰዎች በመርዳት፣ ለበጎ ምግባር ገንዘብ በመለገስና በበጎ ፈቃድ ስራዎች ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ አላቸው የተባሉት ኬንያውያን፤በልግስና ከአፍሪካ የአንደኛ፣ ከአለም አገራት ደግሞ የ11ኛ ደረጃን መያዛቸውን ሰሞኑን የወጣ አንድ አለማቀፍ ጥናት አመልክቷል፡፡ቻሪቲስ ፋውንዴሽን የተባለ ተቋም በ128 የአለማችን አገራት ላይ የሰራውን ጥናት ጠቅሶ ቢቢሲ እንደዘገበው፣ ከአለማችን አገራት መካከል በልግስና ቀዳሚውን ስፍራ የያዘችው አሜሪካ ስትሆን በርማና ኒውዚላንድ በሁለተኛና በሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡አውስትራሊያ፣ አየርላንድ፣ ካናዳ፣ እንግሊዝ፣ ኔዘርላንድ፣ ሲሪላንካና ኢንዶኔዥያ በተቋሙ የ2019 እጅግ ለጋስ አገራት ዝርዝር ውስጥ እንደ ቅደም ተከተላቸው ከአራተኛ እስከ አስረኛ ያለውን ደረጃ የያዙ የአለማችን አገራት መሆናቸውም ተነግሯል፡፡

በአመቱ ከአለማችን አገራት መካከል በልግስና የመጨረሻውን ደረጃ የያዘችው አገር ቻይና ስትሆን፣ ግሪክና የመን በሁለተኛና በሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡ቻሪቲስ ፋውንዴሽን የተባለው ተቋም፤ ዜጎች የማያውቁትን ሰው በመርዳት፣ ለበጎ ምግባር ገንዘብ በመለገስ ወይም በበጎ ፈቃደኝነት በመሳተፍና ሌሎች መልካም ተግባራትን በመፈጸም ረገድ ያላቸውን ተሳትፎ በመገምገም፣ የአገራቱን የልግስና ደረጃ እንደሚያወጣ ዘገባው ጠቁሟል፡፡ ኢንዶኔዢያ በልግስና ከፍተኛ መሻሻል ያሳየችዋ ቀዳሚዋ የአለማችን አገር ናት ያለው የተቋሙ ሪፖርት፤ ኬንያን በሁለተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል፡፡

Via Addis Admas
@YeneTube @FikerAssefa
Estimated population in 2100. (in million)

India: 1660
China: 1004
Nigeria: 752
US: 450
DR Congo: 389
Pakistan: 364
Tanzania: 299
Indonesia: 242
#Ethiopia : 242
Niger: 209
Uganda: 202
Egypt: 201
Brazil: 200
Bangladesh: 170
Philippines: 169

(United Nations)
@YeneTube @FikerAssefa
⬆️⬆️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በጅቡቲ የኢትዮጵያውያን ኮሚዩኒቲ ዝግጅት ላይ በድንገት በመገኘት ንግግር አሰሙ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የ2019 ኖቤል ሽልማት አሸናፊ መሆናቸውን አስመልክቶ ቅዳሜ ዕለት (ጥቅምት 08፣ 2012ዓ.ም) በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አዘጋጅነት የተሰናዳ የደስታ መግለጫ ፕሮግራም ላይ በድንገት የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በበዓሉ ታዳሚ ለሆኑት ኢትዮጵያውያን ንግግር አሰምተዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ‹‹ይሄ ግጥምጥሞሽ ነው… ዳያስፖራው ዝግጅት አለው ስባል ሰላምታ ለማቅረብ ነው የመጣሁት›› ብለዋል፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ አክለውም ‹‹በጅቡቲ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሚለዩበት አንድ መለያ በሰላም መኖር፣ የአገሪቱን ህግ ማክበር፣ ስራ መውደድ፣ እርስ በእርስ መግባባት፣ የተቸገረን መርዳት ሲሆን ሁሌ የምትመሰገኑበትን ይሄንን መልካም ስማችሁን እንድታቆዩ አደራ እላችኋለሁ›› ብለዋል፡፡

ጅቡቲ ሁለተኛ ቤታችን ነው ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ ጅቡቲያውያኑ እኛን ይወዳሉ፤ እኛም ደግሞ አብዝተን እነሱን እንወዳቸዋለን ብለዋል፡፡ ዶ/ር አብይ መደመር በጅቡቲ እና በኢትዮጵያ በግልጽ መታዩት ጠቅሰው ይሄንን በሁለቱ አገራት መካከል ያለ ጥብቅ ወዳጅነት የምታጠናክሩ ድልድዮች ጀግና ኢትዮጵያውያን ስለሆናችሁ በታማኝነት፣ በጨዋነትና በፍቅር እዚህ ካለው ህዝብ ጋር በመኖር የሁለቱን አገራት ግንኙነት ለማጠናከር እያንዳንዱ ዜጋ እንደ አምባሳደር እንዲሰራ አደራ ብለዋል፡፡ስለ ኖቤል ሽልማቱ ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኖቤል ሽልማቱ በአንድ ሰው ስም መነገር ስላለበት እንጂ ሽልማቱ የሁላችሁም ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በኢኮኖሚ ማሻሻያ ሰፋፊ ስራዎች መጀመሩን፣ በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ታላላቅ ኢኮኖሚ አንዷ እንድትሆን እየሰራ መሆኑን አክለው ገልጸው- የኢትዮጵያ ዕድገትና ብልጽግና የጅቡቲ፣ የሶማሊያ፣ የሱዳን፣ የኤርትራ ብልጽግና መሆኑን አክለው ጠቅሰዋል፡፡ በተጨማሪም በውስጣችንም በአጎራባች አገራት ሰላም እንዲኖር እንሰራለን ብለዋል፡፡በሚቀጥለው ምርጫ ከተመረጥን እንሰራለን ካልተመረጥን አቅፈን በማስረከብ አርዓያ የሆነ ስራ እንሰራለን ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት ተሸንፎ ስልጣንን በስርዓት ማስረከብ ከዚህ ኖቤል የሚበልጥ እንጂ የሚተናነስ አይደለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡በመጨረሻም ስደት እንዲያበቃ ለልጆቻችን የምትበጅ ኢትዮጵያን ሰርተን ማቆየት አለብን በማለት ንግግራቸውን አጠቃለዋል።

በጅቡቲ የኢፌዴሪ ኤምባሲ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉስልጣን አምባሳደር አብዱልአዚዝ መሐመድ በበኩላቸው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ድንገተኛ መገኘት የተሰማቸውን ደስታና ክብር ገልጸው በጅቡቲ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ አምባሳደሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለዚህ ታላቅ ዓለም-አቀፋዊ ሽልማት በመብቃታቸው በጅቡቲ የምንኖር እኛ ኢትዮጵያውያን የተሰማንን ደስታ በዚህ አጋጣሚ ለመግለፅ እንወዳለን፡፡ ሽልማቱ መላው ኢትዮጵያውያንን ያኮራ ከመሆኑም ባሻገር አገራችን በዓለም-አቀፍ መድረኮች ላይ እየተጫወተች ያለውን ሚና የሚያጎላና እውቅናንም የሚሰጥ ነው ብለዋል፡፡በዝግጀቱ የተገኙት ኢትዮጵያውያን የተሰማቸውን ደስታና ክብር ከፍ ያለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

( በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ )
@YeneTube @FikerAssefa
ከ80 በመቶ በላይ የግል ትምህርት ቤቶች ከደረጃ በታች መሆናቸው ተገለፀ።

ከመንግሥት ፖሊሲ ጋር ተናበው ባለመስራታቸው ሰማንያ ነጥብ ሰባት በመቶ የግል ትምህርት ቤቶች ከደረጃ በታች መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ሥልጠና፤ ጥራት ሙያ ብቃትና ምዘና ማረጋገጫ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ባለስልጣኑ ትናንት በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ባካሄደው የውይይት መድረክ ላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሸዊት ሻንካ እንደገለፁት፤ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ብዙ ሥራ ቢሠራም አሁንም በግልና በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ የሆነ ችግር ይስተዋላል፡፡ ከ2009 ዓ.ም እስከ 2011 ዓ.ም በተደረገው የኢንስፔክሽን ሥራ በርካታ የግልና የመንግሥት ተቋሞች ከመንግሥት በወረደ አቅጣጫ ባለመስራታቸው ከደረጃ በታች ናቸው፡፡

ምንጭ:ኢፕድ
@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ 5ተኛ ዙር የ"ማስ" ስፖርት በመስቀል አደባባይ

Photo: Eng. Takele Uma Banti
@YeneTube @FikerAssefa
#FakeLetterAlert

የገቢዎች ሚኒስቴር እንደማንኛዉም ባለበጀት መስሪያ ቤት በጀት ተመድቦለት በበጀት የሚንቀሳቀስ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ነዉ፡፡

ስለዚህ የበጀት ፍሰቱ ቁጥጥር የሚደረግበትና በስርዓት የሚመራ ነዉ፡፡ ከአሰራርና መመሪያ ዉጪ ከተመደበለት በጀት ዉጪ እንደፈለገዉ ለሚዲያም ሆነ ሌሎች አካላት ድጋፍ ማድረግ አይችልም፡፡ በማህበራዊ ሚዲያ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለግል ሚዲያ(ኦኤም ኤን)ድጋፍ አድርጓል ተብሎ የሚናፈሰዉ ወሬ አሉባልታና ሆን ተብሎ ለማደናገሪያነት የተሰራጨ ስለሆነ የፌስ ቡካችን ተከታታዮች በጠየቃችሁን መሰት ወሬዉ ዉሸት መሆኑን እንድታዉቁ እናስታዉቃለን፡፡

በተለይ በዘንድሮዉ ሩብ አመት ያስመዘገብነዉ ዉጤት ሰራተኛና አመራሩን ለተሻለ ዉጤት የሚያነሳሳ እንጂ ለአሉባልታ ቦታ ሰቶ ወደ ኋላ የሚመልስ ስላልሆነ ስኬታማ እንቅስቃሴችንን ለማደናቀፍ የምትጥሩ አካላት ከዚሁ ድርጊታችሁ እንድትታቀቡ እናሳስባለን፡፡ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ ወሬ ተሰራጭቶ ዉሸት መሆኑን ምላሽ የሰጠንበት ሲሆን አሁንም እየተሰራ ያለዉን ስራ ለማጠልሸት ሆን ተብሎ የተሰራጨ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡

-የገቢዎች ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
በቦሌ ክፍለ ከተማ የአማራ ወጣቶች ማኅበር አባላት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ እየተወያዩ ነው፡፡በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ የአማራ ወጣቶች ማኅበር አባላት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር እያደረጉ ነው፡፡በምክክሩም የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ምክክር እንደሚደረግባቸውም ይጠበቃል፡፡

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን አጠናቀቀ።

የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ለሦስት ተከታታይ ቀናት ሲያካሄደው የቆየውን 5ኛ ዘመን 17ኛው መደበኛ ጉባኤ የ2012 በጀት አመት አመታዊ እቅዶችን፣ የተለያዩ አዋጆችን እና አዳዲስ ሹመቶችን በማፅደቅ አጠናቋል፡፡
በበጀት አመቱ ክልሉ በድህነት ቅነሳ፣ የክልሉ ሰላም እና ደህንነትን በማረጋገጥ እንዲሁም የሴቶች እና ወጣቶችን የልማት ተሳታፊነት እና ተጠቃሚነት ላይ በማተኮር በስፋት እንደሚሰራ የክልሉ ም/ርእሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል አስታውቀዋል፡፡የ2011 በጀት አመት ግምገማን ተከትሎ በአመራሩ ለውጥ እንደሚደረግ እና ጥፋት የተገኘበት አመራርም በህግ አግባብ ተጠያቂ እንደሚሆን ምክትል ርእስ መስተዳድሩ ዶ/ር ደብረፂዮን አስምረውበታል፡፡በህብረተሰቡ ለሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስም ያልተማከለ የመንግስት አሰራር ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል።በከተማ እና በገጠር የሚታየውን የስራ አጥነት ችግር ለመፍታት በበጀት አመቱ 258 ሺህ ለሚሆኑ ወገኖች የስራ እድል ለመፍጠር እንደሚሰራም አስታውቀዋል፡፡

ከስድስት ቢልዮን ብር በላይ የብድር አቅርቦት እንዲኖር ማድረግም አንዱ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ዶ/ር ደብረፂዮን አክለው አስረድተዋል። በቅርቡ ተጠሪነቱ ለምክር ቤቱ የሆነው የትግራይ ክልል መልሶ ማቋቋም ድርጅት /ኢፈርት/ በበጀት አመቱ ለሚሰሩ የልማት ተግባራት የሚውል ከ864 ሚልዮን ብር በላይ መመደቡን በቀረበው ሪፖርት ተገልጿል፡፡ምክር ቤቱ የፍርድ ቤቶች አደረጃጀት፣ የዳኝነት የአገልግሎት ክፍያ፣ የዳኞች ጉባኤ ሥልጣን እና ተግባር ለመወሰን ተሻሽለው የወጡ ረቂቅ አዋጆች እና ሌሎች አዋጆችን ጨምሮ 4 የተለያዩ አዋጆችን መርምሮ አፅድቋል፡፡የምክር ቤቱ ምክትል አፈ-ጉባኤ የነበሩ ወ/ሮ የምስራች ብርሃን ለትምህርት በመላካቸው በምትካቸው ወ/ሮ ዘይነብ አብዱልለጢፍን በመሾም ጉባኤውን አጠናቋል፡፡

ምንጭ:ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሚያና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎችን ለሚያገናኘው የአርጆ‐ጉደቱ‐ጅርማ‐ሶጌ መንገድ ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ።

በምስራቅ ወለጋ ዞን በዲጋ ወረዳ የአርጆ ጉደቱ ጅርማ ሶጌ 46 ኪሎ ሜትር የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት መሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ።የመሰረት ድንጋዩን የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሌ ሀሰን እና የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡመድ ኡጁሉ ነው በጋራ የተቀመጠው መንገዱ 392 ሚሊየን ብር የተመደበለት ሲሆን፥ ወጪውን የኦሮሚያ ክልል መንግስት እንደሚሸፍነው ተገልጿል። መንገዱ ሲጠናቀቅ የኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎችን በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ ዘርፎች ይበልጥ ለማስተሳሰር ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል።መንገዱ በአስፋልት ደረጃ እንደሚገነባም ተገልጿል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሚመራ የሰሜን ሸዋ ዞን እና የኦሮሚያ ልዪ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ከተውጣጡ አመራሮችና የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ስለ አካባቢው ሰላምና ጸጥታ ጉዳይ በሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ውይይት በመደረግ ላይ ነው ፡፡

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በውይይቱ መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት አካባቢው በልማት በተለይም ደግሞ በመስኖና በአካባቢ ልማት ጥበቃ የሚታወቅ እንጂ በጸጥታ መደፍረስ የማይታወቅ አካባቢ መሆኑንና የአማራና የኦሮሞ ህዝብ ለዘመናት በወንድማማችነትና በቤተሰብነት በጋራ አብሮ በመኖር ልማትን የሚያለማ እንጂ እርስ በራስ የሚጠፋፋ እንዳልሆነ ገልጸው የሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች አካባቢው ሰላም እንዲሆንና ለዘመናት የቆየውን ወንድማማችነት እንዲቀጥል ኃላፊነት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው እንደገጹት ለዘመናት ተከባብሮና ተቻችሎ የቆየውን ማህበረሰብ ለማለያየትና የፖለቲካ አጀንዳቸውን ለመዘርጋት በሚጥሩ ኃይሎች ተታሎ ለመገዳደል በመድረሱ ማዘናቸውን ገልጸው ይህም ድርጊት የሁለቱን ህዝቦች የማይወክል በመሆኑ ችግሩ እንዲከሰት ያደረጉና የተሳተፉ አካላትን ለህግ አሳልፎ ለመስጠትና የነበረውን ሰላምና በአንድነት ሰርቶ የማደግ ባህል እንዲመለስ የበኩላቸውን እንደሚያደርጉ ገልጸው መንግስትም ለጉዳዪ ልዪ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ምንጭ: ሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር
@YeneTube @FikerAssefa
ግብጽ በኢትዮጵያ ህዳሴ ግድቡ ዙሪያ መውሰድ ስላለባት እርምጃ ለማማከር የተቋቋመው ብሄራዊ ኮሚቴ ዛሬ የመጀመሪያውን ስብሰባ እንደሚያደረግ ይጠበቃል።

ግብጽ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የግብጽን ታሪካዊ የውሃ ድርሻ ይጋፋል በሚል ነበር ከአንድ ሳምንት በፊት ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጣ ብሄራዊ አማካሪ ምክር ቤት ማቋቋሟ የተሰማው።እንደ ግብጹ አልአህራም ዘገባ ከሆነ ይህ አማካሪ ምክር ቤት ከግብጽ ብሄራዊ ደህንነት፣ከህዝብ ተወካዮች፣ከግብርና ሚኒስቴር ፣ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከሌሎች ተቋማት የተውጣጣ ቡድን ተቋቁሟል።

የዚህ ቡድን ዋና አላማ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዳሴው ግድብ የግብጽን ታሪካዊ የውሃ ድርሻ የሚጎዳ በመሆኑ ፕሬዘዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ የግብጽን ጥቅም ለማስበር መውሰድ ስለሚኖርባቸው እርምጃዎች ማማከር መሆኑ ተገልጿል።ይህ ቡድን በተቋቋመ በሳምንቱ ማለትም ዛሬ አመሻሽ እንደሚሰበሰብ ዘገባው አመልክቷል።

ግብጽ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚጋፋ አዲስ አቅድ ይፋ ማድረጓን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሰት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል የግብጽን እቅድ እንደማይቀበል ማስታወቁ ይታወሳል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከግብጹ ፕሬዘዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ጋር ከአንድ ሳምንት በኋላ በሩሲያ ሱቺ ከተማ በሚካሄደው በአፍሪካ-ሩሲያ ጉባኤ ላይ ተገናኝተው በህዳሴው ግድብ ቀጣይ ድርድር ዙሪያ እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa