በአጣዬ 8 ሰዎች ተገደሉ ተባለ።
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ ከተማና አካባቢዉ ከትናንት በስቲያ በተቀሰቀሰዉ ግጭት የ5 ሰላማዊ ዜጎች እና ሕይወት ማለፉ ተገለፀ። በግጭቱ ከመንግሥት ወገን 3 የፀጥታ ኃይላት መሞታቸውንና 5 መቁሰላቸውም ተገልጧል።
ተጨማሪ ለማንበብ ⬇️
https://telegra.ph/Ataye-10-07
@YeneTube @Fikerassefa

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የመክፈቻ ንግግር ለሁለቱ ምክር ቤቶች እያቀረቡ ነው!
የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 5ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን በይፋ ተከፍቷል።ይህንንም ተከትሎ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የመክፈቻ ንግግር በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።
በንግግራቸውም፦👇👇👇👇👇
https://telegra.ph/joint-opening-session-10-07
Via EBC/FBC
@YeneTube @FikerAssefa

የሂልተን ሆቴል ይዞታ 70 በመቶ ወደ ግል ሊዘዋወር ነው!
የመንግስት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ በ 2012 በጀት ዓመት ሂልተን ሆቴልን 70 በመቶ ድርሻ ወደ ግል ይዞታ ለማዘዋወር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን፣ የሆቴሉ የሀብት ግመታ ጥናት እንደተረጋገጠም በሚወጣ ጨረታ ድርሻው እንደሚዘዋወር የኤጀንሲው ዳይሬክተር ጄነራል በየነ ገ/መስቀል ባሳለፍነው ሳምንት በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።በዓለም አቀፉ የሂልተን ባለቅርንጫፍ ሆቴሎች አስተዳደር ስር የሆነውና ንብረትነቱ በኢትዮጵያ መንግስት ባለቤትነት የተያዘው ሂልተን ሆቴል ለገበያ እንደሚቀርብ ለአመታት ቢነገርም ቀን ግን ሳይቆረጥለት ቆይቷል።
ከዚህ በተጨማሪም በፍል ውሃ አገልግሎት ድርጅት ስር ላንጋኖ የሚገኘው ሆቴል እንዲሁም ሶስት የማኑፋክቸሪንግና ስድስት የስኳር ፋብሪካዎች በዚህ ዓመት ወደ ግል ይዞታ እንደሚተላለፉ ዳይሬክተሩ ጨምረው አስታውቀዋል።በ2011 እንደ አዲስ የተዋቀረው የመንግስት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ አሁን በስሩ 23 የልማት ድርጅቶችን የያዘ ሲሆን፣ በዚህ ዓመትም አዶላ ወርቅና የመንግስት ነዳጅና ባዮፊዩል ኮርፖሬሽን ተዋህደው ቁጥሩ ወደ 21 ዝቅ እንደሚል ተገልፃል።
Via Addis Maleda

በአጣዬና አካባቢው ያለውን አለመረጋት ለመቀነስ እየተሠራ መሆኑን የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተፈራ ወንድማገኝ ተናግረዋል፡፡
‹‹የተኩስ ልውውጡ አሁን ላይ የቆመ ሲሆን በደረሰዉ ጥቃት እስካሁን የአምስት ሰዎች ሕይወት አልፏል›› ብለዋል፡፡ ሌሎች ስምንት ሰዎች ቆስለዉ ክትል እየተደረገላቸዉ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡ በአንዳንድ የመገናኛ ብዙኃን ዘንድ የሟቾች ቁጥር ስምንት ተብሎ መዘገቡ የተሳሳተ መሆኑም ተገልጿል፡፡ተጨማሪ የሰዉ ሕይወት እንዳይጠፋና ጉዳት እንዳይደርስ ከሀገር መከላከያ ሠራዊትና ከልዩ ኃይል ጋር በጋራ እየተሠራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ዛሬ ከአጣዬ ውጭ በማጀቴ አካባቢ ጥቃት ለማድረስ የተሞከረ መሆኑን የተናገሩት ዋና አስተዳዳሪዉ የፀጥታዉን ጉዳይ በቁጥጥር ስር ለማዋል ሰፊ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ‹‹የታጠቁ ኃይሎችን በቁጥጥር ስር ለማዋልም ከአጎራባች ዞኖች ጋር እየሠራን ነው›› ያሉት አቶ ተፈራ ኅብረተሰቡ እገዛ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ከዚህ በፊት በአካባቢዉ በተቀሰቀሰዉ ግጭት እጃቸዉ አለበት ተብለዉ የሚጠረጠሩ አካላትን በቁጥጥር ስር በማዋል ለኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን መሰጠታቸውንም ዋና አስተዳዳሪው አስታውቀዋል፡፡ ‹‹ሕግ የማስከበር ሥራዎችን ሥንሠራ ከብሔር ጋር ማያያዝ ተገቢነት የለውም የማደኛ ትዕዛዛ የወጣባቸዉ ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን ነዉ የያዝነዉ›› ብለዋል፡፡በአጣዬና አካባቢዉ ያለዉ አለመረጋጋት አሁን ላይ በአመዛኙ የተሻለ መሆኑን ያመለከቱት ዋና አስተዳዳሪው ኅብረተሰቡ በንቃት አካባቢዉን መጠበቅ እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡ የመከላከያና የልዩ ኃይል በቅንጅት አካባቢዉን ወደ ሠላም ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉእንደሚገኙም አመልክተዋል፡፡
Via AMMA

የሙዚቃ አቀናባሪው የኤልያስ መልካ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈጸመ።
በቀብር ስነ ስርዓቱ ላይ አንጋፋ እና ወጣት የጥበብ ባለሙያዎች፣ ቤተሰቡ፣ የሙዚቃ አፍቃሪያን እንዲሁም በያሬድ ትምህርት ቤት ያስተማሩት መምህራን እና ሌሎችም በርካታ ሰዎች ተገኝተዋል። የአርቲስቱ ስርዓተ ቀብር ወዳጅ ዘመዶቹና አድናቂዎቹ በተገኙበት ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ በጴጥሮስ ወ-ጳውሎስ ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።ሙዚቀኛ ኤልያስ መልካ ባሳለፍነው ቅዳሜ ረፋድ መስከረም 24 ቀን 2012 ዓ.ም በስኳርና በኩላሊት ህመም ምክንያት ነበር ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው።የሙዚቃ አቀናባሪ፣ ገጣሚ፣ የዜማ ደራሲ እና ጊታሪስት የሆነው ኤልያስ መልካ በዘመናዊ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ ጉልህ አሻራ ያኖረ አርቲስት ነው።
Via Ethio FM

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2012 የትምህርት ዘመን #በመደበኛ የዲግሪ ትምህርት መርሃ-ግብር በትምህርት ሚ/ር መስፈርት መሠረት #አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ #ጥቅምት_01 ቀን እና #ጥቅምት_02 ቀን 2012 ዓ.ም በተመደባችሁበት የዩኒቨርስቲው ካምፓስ ሪፖርት እንድታደርጉ አሳውቋል፡፡
ተማሪዎችም ለምዝገባ ስትመጡ፣
➡️ ብርድልብስና አንሶላ፣
➡️ የአስራ ሁለተኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ፣
➡️ ስምንት ጉርድ ፎቶግራፍ ይዛችሁ መምጣት እንዳለባችሁ ያስታውቃል፡፡
➡️ የስፖርት ትጥቅ
📌 በተጠቀሱት ቀናት ከአዲስ አበባ ውጪ ለሚመጡት ተማሪዎች በመርካቶ አውቶብስ ተራ፣ በአቃቂ እና በአስኮ የመኪና መናኸሪያዎች በመገኘት ዩኒቨርስቲው የትራንስፖርት አገልግሎት ያቀርባል፡፡ ፡
📌 ከተገለጸው ቀን በፊት ለሚመጡ ተማሪዎች ምንም ዓይነት አገልግሎት ዩኒቨርስቲው አይሰጥም፡፡
📌 ለተጨማሪ መረጃ የዩኒቨርስቲን ድረገጽ https://
portal.aau.edu.et/ ወይም www.aau.edu.et ማየት የሚቻል ሲሆን
📌 ነዋሪነታችሁ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሆኖ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት የምታደርጉትና ስለ ዩኒቨርስቲው ገለጻ የምታገኙት ጥቅምት 03 ቀን 2012 ዓ.ም መሆኑን ያሳውቃል፡፡
📌 ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትመጡ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው ውስጥ የመኝታ አገልግሎት ለማግኘት የተመደበላችሁን የመኝታ ክፍል 12ኛ ክፍል በተፈተናችሁበት ቁጥር በመጠቀም ከ portal.aau.edu.et ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ያሳውቃል፡፡
📌 ተማሪዎች ከወላጆቻቸውና በአካባቢያቸው ከሚገኙ ወረዳዎች ጋር ውል ተፈራርመው የማረጋገጫ ወረቀት ካላመጡ ዩኒቨርስቲው የማይቀበል መሆኑን በጥብቅ ያሳስባል፡፡
📌 በተጨማሪም ባለፈው ስርዓተ ትምህርት መሠረት በመጀመሪያ ዓመት 1ኛ እና 2ኛ ሴሚስተር በተለያየ ምክንያት አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ ውጤታችሁ የሚያበቃችሁ ተማሪዎች ከዘድሮ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች ጋር በመቅረብ በ2012 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሴሚስተር መልሶ ቅበላ እንድታመለክቱ እናሳውቃለን፡፡እንዲሁም መደበኛ የድህረ ምረቃ አዲስ ተማሪዎች ምዝገባ ጥቅምት 06 2012 ዓ.ም ሲሆን ትምህርት የሚጀመረው ጥቅምት 10 ቀን 2012 ዓ.ም መሆኑን እንገልጻለን፡፡
Via አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

በኢጋድ አባል አገራት በአጠቃላይ ከ9 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ የውስጥ መፈናቀል መከሰቱን በ12ተኛው የኢጋድ አባል አገራትጉባዔ ላይ ተገልጿል። የኢጋድ አባል አገራት የፈረሙትና ኢትዮጵያ የሌለችበት የካምፓላ ስምምነት በደቡብ ሱዳን ተግባራዊ ተደርጎ ለውጥ በማምጣት ላይ መሆኑ ታዉቋል። ጉባዔው ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን የሚፈናቀሉ ሰዎችን ወደ ቀዬአቸው በመመለስ ለዘለቄታው ማቋቋም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እየመከረ ነው።
(ኢቢሲ)
@YeneTube @FikerAssefa
(ኢቢሲ)
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
🤩🤩🤩🤩የምስራች 🤩🤩🤩
በአ.አ በቀላሉ የማይገኙ ፤ ወደ12ሺ ሰዓቶች እና ቦርሣዎች ለትዛዝ ፤ ከ 1ሺ በላይ እቃዎች በ እጃችን መርጠው ይዘዙን ወደ ክልልም እንልካለን
ከታች ባለው ሊንክ ይጎብኙን
👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAENXyUTam6WMV6_hmg

የኅዳሩ የሲዳማ ሕዝበ ውሳኔ በምርጫ ሕግጋቱ መሠረት እንደሚደረግ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡ ለሕዝበ ውሳኔ የተዘጋጀ ሌላ ሕግ ሀገሪቱ የላትም፡፡ የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ለኢቢሲ እንደተናገሩት፣ ከክልሉ አልቀው መምጣት ያለባቸው የአስተዳደር እና ሕግ ማዕቀፎ ሰነዶች እስካሁን ለቦርዱ አለቀረቡም፡፡ ቀነ ገደቡ ከመስከረም 12 ወደ 30 ተራዝሟል፡፡ በእነዚህ ጉዳዮች ዞኑና ክልሉ ካልተስማሙ፣ ቦርዱ የሕዝበ ውሳኔውን ሂደት ሰላማዊነት ለማረጋገጥ ይቸገራል፡፡
Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
በአዊ ብሔ/አስ/ በደረሰ #የትራፊክ_አደጋ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ ፡፡
ከእንጅባራ ከተማ ወጣ ብሎ በአካይታ ቀበሌ በቀን 26/1/2012 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ስዓት አካባቢ ከእንጅባራ አምበላ ተሳፋሪ ጭኖ ይጓዝ የነበረ ኮድ 3-13645 አማ ታርጋ የሆነ አይሱዙ የህዝብ ማመላለሻ ከአዲስ አበባ ወደ እንጅባራ አቅጣጫ ከሚመጣ ሎቤድ ኮድ 3-84604 ኢት ጋር በመጋጨቱ ወዲያውኑ የ1 ሰው ህይወት ሲያልፍ ሌሎቹ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን በእንጅባራ አጠቃላይ ሆስፒታል እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሆነ የባንጃ ወረዳ የትራፊክ ክፍል ኃላፊ ኢ/ር አስማረ ገብረኪዳን ተናግረው እንዲሁም በንብረት ላይ ውድመት መድረሱን ገልፀዋል፡፡ በቀጣይም ሌሎች መረጃዎችን ተከታትለን የምናደረስ ይሆናል ብሏል የዞኑ ኮሙኒኬሽን ቢሮ፡፡

በድሬደዋ ዳግም ግጭት ተቀሰቀሰ።
ግጭቱን በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ #ተደርጓል።
በድሬዳዋ ከተማ በተለምዶ ገንደ ጋራ ፣ደቻቱና አምስተኛ ተብለዉ በሚጠሩ ቦታዎች ትናንት ረፋድ ጀምሮ በአካባቢዉ ነዋሪዎች መካከል ማንነት ላይ ያነጣጠረ ግጭት ተቀስቅሷል።
ይህንን በመቃወምም በደቻቱ አካባቢ የሚኖሩ ሴቶች «መንግስት መፍትሄ ይስጠን» ሲሉ የከተማዋን አስተዳደር በሰላማዊ ሰልፍ ጠይቀዋል።
ከሰልፈኞቹ መካከል ተመርጠው ከአስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ያካሄዱት ነዋሪዎች "ብሄርና ማነትታችንን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች እየደረሱብን ነው። አስተዳደሩ አፋጣኝ ምላሽ እና መፍትሄ ሊሰጠን ይገባል ብለዋል።
ነዋሪዎቹ "የአካባቢ /መንደር ግጭትን መፍታት ለመንግስት እንዴት አንደተሳነው አልገባንም? ምላሽ ይሰጠን ?"ሲሉም ጠይቀዋል።እንደ ሰላማዊ ሰልፈኞቹ "ከአስተዳደሩ አመራር አካላት ጭምር ችግሩን በየጊዜው የሚያባብስ አካል አለ ፤ አስተዳደሩም ሆነ የፀጥታ ኃይሉ ሰላማችንን እና ደህንነታችንን በተገቢው መንገድ ሊያስጠብቅ ባለመቻሉ የፌደራል መንግስት ጣልቃ ሊገባና ለችግራችን አንድ መፍትሄ ሊሰጠን ይገባል» ብለዋል።
በድሬደዋ ከአዲስ አመት ዋዜማ ጀምሮ የተቀሰቀሰው የደቻቱ አምስተኛ፣ ገንደጋራ እና አዲስ ከተማ አካባቢዎች ግጭት ሞቅ ቀዝቀዝ እያለ የቀጠለ ሲሆን በግጭቱ ለበርካታ ሰዎች ህይወት መጥፋት፣ ለአካል መጉደል እንዲሁም ለንብረት ዉድመትና ዝርፊያ ምክንያት ሆኗል። የእነዚህ አካባቢዎች ትልቁ የገበያ ማዕከል ቀፊራም ተገቢውን የንግድ እንቅስቃሴ ማካሄድ ተስኖታል።
ዛሬ ለአቤቱታና ተቃውሞ አደባባይ የወጡ ነዋሪዎችን ያነጋገሩት የአስተዳደ የድርጅት እና መንግስት ስራ ኃላፊዎች በበኩላቸዉ አስተዳደሩ በአካባቢው እየተፈጠሩ የሚገኙ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ፣የችግሩ ጠንሳሽ እና አባባሽ ያላቸውን አካላት ወንጀል በማጣራና በቁጥጥር በማዋል ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ እየሰራን ነው ብለዋል ።
በሌላ በኩል ከህዝቡ ጋር ወርዶ በመወያየት ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት እንደሚሰሩም ጠቁመዋል።
Via:-DW

በአማራ ክልል ኤፍራታና ግድም ወረዳ አጣዬ ከተማ ላይ ባልታወቁ ሰዎች ተፈጥሮ የነበረው ግጭት መረጋጋቱን የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳዳር አስታወቀ።
የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ተፈራ ወንድምአገኘሁ ዛሬ በሰጠት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከቱት የተፈጠረውን አለመረጋጋት በዘላቂነት ወደ ነበረበት ሰላማዊ ሁኔታ ለመመለስ የሚያስችሉ ስራዎች በቅንጅት እየተከናወኑ ነው።
በክልሉ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን አዋሳኝ ቦታዎች አካባቢ የተከሰተው ግጭት በጸረ-ሰላም ኃይሎች ምክንያት እንጂ በህዝቦች መካከል የተነሳ እንዳልሆነም አስረድተዋል።
ከአራት ወራት በፊት በነዚህ አካባቢዎች በተመሳሳይ መልኩ በተከሰተ ግጭት የአጣየና አካባቢው ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን አውስተዋል።
“ከዛ ጊዜ ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ የሚወስደው የአስፓልት መንገድ ግራና ቀኝ አምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መቀሳቀስ ክልክል መሆኑ በኮማንድ ፖስት ታውጆ ነበር” ብለዋል።
ይሁን እንጂ ሰሞኑን የጦር መሳሪያ የታጠቁ ሁለት ግለሰቦች አጣየ ከተማ ገበያ ሊገቡ ሲሉ በአካባቢው በጥበቃ ላይ በነበሩ የክልሉ ልዩ ሀይል አባላት ሊያዙ ሲሉ ተኩስ በመክፈታቸው ግጭት መፈጠሩን ተናግረዋል።
በእለቱም ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቁ ሀይሎች የአጣየን ከተማ ለመውረርና ግጭቱን ወደ ሌሎች አካባቢዎች ለማስፋት ያደረጉት ሙከራ በክልሉ ልዩ ሃይል፣ በፌደራል ፖሊስና በመከላከያ ሰራዊት በተደረገ ጥረት መክሸፉን ገልጸዋል።
ይሔንን ተከትሎ በነበረው የተኩስ ልውውጥም አምስት ሰዎች ሲሞቱ አራት መቁሰላቸውን ገልጸው ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የሁለቱም ዞኖች አመራሮች፣ ህዝቡና የሚመለከታቸው አካላት በጋራ እየሰሩ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
#ENA

ማስተካከያ!
ዛሬ የአሜሪካ Ambassador Micheal Raynor በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የነበራቸው አጭር ቆይታ ዋና አጀንዳ በኢትዮ ኤርትራ የሰላም ስምምነት ሂደት ዙርያ ያሉትን ተግዳሮቶች በሚመለከት የባለሙያዎች እይታን ለመስማት ነበር። ፕሮፌሰር ክንደያ እና የፖለቲካ ምሁሩ መረሳ ፀሃየ በጉዳዩ ለአምባሳደሩ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። ከአምባሳደሩ ጋር በተገኙት የፖለቲካ አማካሪያቸው ጥሪ አቶ ጌታቸው ረዳ ስብሰባው ላይ ተገኝተው በጉዳዩ ዙርያ የትግራይ መንግስት እና ህዝብ ሃሳብ ገልፀዋል፣ ለጥያቄዎቹም መልስ ሰጥተዋል! ከዚህ ስብሰባ ጋር በተያያዘ በተለያዩ ሚድያዎች እየተዘገቡ ያሉት ሌሎች ዜናዎች ስህተት መሆናቸውን እንገልፃለን!
-Mekele University

ከሐረር ወደ ጅግጅጋ የሚወስደው መንገድ ድልድይ ከአገልግሎት ውጪ ሆኗል
ከሐረር ወደ ጅግጅጋ የሚወስደው የመኪና መንገድ ኤረር ቀበሌ ገበሬ ማህበር ላይ የሚገኘው ድልድይ በመሰንጠቁ አገልግሎት መስጠት በማቋረጡ አሽከርካሪዎችና ተገልጋዮች እየተቸገሩ መሆኑን ተናገሩ።
ከድሬዳዋ ወደ ጎዴ አልሚ የእርዳታ እህል ጭኖ እየተጓዘ ሳለ በመንገዱ መበላሸት ምክንያት በአካባቢው ቆሞ ያገኘነው የከባድ መኪና አሽከርካሪ አቶ ደረጀ የማነህ እንደሚገልጸው አደጋ የደረሰበት ድልድይ በወቅቱ ባለመጠገኑ ለሰባት ቀናት የጫነው እቃ ሳናራግፍ በስፍራው ለመቆየት ተገደናል።
በአካባቢውም የተደራጀ ጥበቃ ባለሞኖሩ ንብረቱ ለስርቆት እየተዳረገ ነው፤ ተሽከርካሪም ለማለፍ ሲሉ ለትራፊክ አደጋ እየተዳረግን ነው ፡፡
ባካባቢው የምግብና ውሃ አቅርቦት ባለመኖሩም እየተቸገሩ መሆናቸውን ገልጾ ለዚህ ሁሉ ችግሩ መንገዱ በወቅቱ አለመሰራተሩና ተሽከርካሪዎች በስፍራው ላይ መበራከት በመሆኑ መፍትሄ ሊሰጥበት ይገባል ሲል ተሯል።
የነዳጅ ቦቴ አሽከርካሪው አቶ መኮንን ቦጋለ እንደተነገሩት ተለዋጭ መንገዱን ባግባቡ ሰርቶ የሚያሳልፈን አካል በማጣታችን የያዝነውን ጭነት ሳናራግፍ ለእንግልት ተደርገናል ሲሉ ተነግረዋል ፡፡
ግማሽ ኪሎ ሜትር የማይሞላ ተወለዋጭ መንገድን በአንድ ቀን መስራት ሲቻል ከጅቡቲ ድረስ ተጉዘን ለህዝብ ማድረስ የሚገባንን ንብረት ሳናደርስና የተሽከርካሪው ባለንብረትና መንግስት ከዘርፉ ሊያገኝ የሚችለውን ገቢ እያጡ ነው።
Harari Government communication Office

በአማራ ክልል ዋግኽምራ ዞን የአበርገሌ ወረዳ አራት አመራሮች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተሰማ። ባለሥልጣናቱ ትናንት ለስብሰባ ሰቆጣ ላይ በተገኙበት ነው የታሠሩት። የእስራቸው ምክንያት ያልታወቀው ባለሥልጣናት ካልተለቀቁ በሚል የአካባቢው ኅብረተሰብ የመንግሥት ሠራተኞች ወደሥራ እንዳይገቡ እንዳገደ የወረዳው የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ባለሙያ ለዶቼ ቬለ DW ተናግረዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
263 ኢትዮጵያን ከሊባኖስ ወደአገራቸው ተመለሱ!
ባለፉት 3 ተከታታይ ቀናት በአጠቃላይ 263 ህጋዊ ሰነድ የሌላቸው ኢትዮጵያውያን ከልጆቻቸው ጋር ወደ አገራቸው መመለሳቸውን በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄነራል ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡
Via EBC