የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ፣ ‹‹የደንብ ልብሱን ለምን መቀየር አስፈለገ?›› ለሚለው ጥያቄ፣ ‹‹ነባሩ የፖሊስ የደንብ ልብስ አልተቀየረም፡፡ ወደፊት እንደ አስፈላጊነቱ በተጨማሪነት ሊሰጥ ይችላል፡፡ አዲሱ የደንብ ልብስ የተዘጋጀው በሌሎች ክልሎችም እንዳለው ሁሉ፣ ከመደበኛ ፖሊስ በተለየ በከተማው ውስጥ ሁከት ሲፈጠርና ከመደበኛው ፖሊስ አቅም በላይ ሲሆን፣ ያንን #ለሚቆጣጠር ቋሚና ተወርዋሪ ኃይል የተዘጋጀ ነው፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹ቋሚና ተወርዋሪ›› ኃይሉ በዋና ዳይሬክተር የሚመራና ሙሉ ትጥቅ ያለው ኃይል ሲሆን፣ ለከተማ አስተዳደሩ ጥበቃ የተዘጋጀ የ‹‹ክብር ዘብ›› መሆኑንም ዳይሬክተሩ አክለዋል፡፡
ተጨማሪ ለማንበብ ⬇️
https://telegra.ph/YeneTube-10-06
ተጨማሪ ለማንበብ ⬇️
https://telegra.ph/YeneTube-10-06