YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ኡጋንዳ ካምፓላ ⬆️
ሀረር⬆️
የደመራ ስነስርዓት በሰላም ተጠናቋል።
@YeneTube @Fikerassefa
አርባምንጭ⬆️
የደመራ ስነስርዓት በሰላም ተጠናቋል።
ዱባይ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ⬆️

የደመራ ስነስርዓት በሰላም ተጠናቋል።
@YeneTube @Fikerassefa
ቤንሻንጉል ጉምዝ
የደመራ ስነስርዓት በሰላም ተጠናቋል።

@YeneTube @Fikerassefa
የም ልዩ ወረዳ ደሪ ከተማ የደመራ ስነስርዓት በሰላም ተጠናቋል።

@YeneTube @Fikerassefa
አዲስ አበባ⬆️
የደመራ ስነስርዓት በሰላም ተጠናቋል።
@YeneTube @Fikerassefa
በዛሬው የመስቀል ደመራ በአል አከባበር ላይ 55 የበዓሉ ታዳሚዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ህዝብ ግንኙነት እና ጉዳይ አስፈፃሚ መላከ ሕይወት አባ ወልደየሱስ ሰይፉ ለቢቢሲ ገለፁ።

መላከ ህይወት አባ ወልደየሱስ እንደገለፁት 33ቱ ምእመናን በቁጥጥር ስር የዋሉት ቤተክርስትያኗ ላይ የሚሰነዘር ጥቃት እንዲቆም የሚያወግዝ ፅሁፍ ያለበት ቲሸርት ለብሰው በመገኘታቸው ነበር።ምእመናኑ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ምክንያት የሆኑት ቲሸርቶች 'የቤተክርስትያን ጉዳይ ያገባኛል'፣ የቤተክርስትያን መቃጠልና ጥቃት ይቁም' የሚሉ ፅሁፎች ያለባቸው እንደነበሩ አባ ወልደየሱስ አስረድተዋል።

አራቱ ደግሞ የሌላ ሰው ባጅ አድርገው በመገኘታቸው በቁጥጥር ሲውሉ ቀሪዎቹ 12 የሚሆኑት ደግሞ ስለት ይዘው ተገኝተዋል በሚል በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ያስረዳሉ።

በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች የተወሰዱት ካዛንችዝ ከሚገኘው ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደነበርና በኋላ እሳቸው ወደ ፖሊስ ጣቢያው ሄደው ሃላፊዎች ከነጋገሩ በኋላ 37 በዋስ መለቀቃቸውን መላከሕይወት አባ ወልደየሱስ ተናግረዋል።

ምንጭ:- ቢቢሲ አማርኛ
@YeneTube @Fikerassefa
ትናንት በካታር ዶሃ በተጀመረው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ለግማሽ ፍፅሜ እና ፍፃሜ አልፈዋል።

በ17ኛው የዓለም ሻምፕዮና ለኢትዮጵያ የመጀመርያ በሆነው የሴቶች 800 ሜትር የመጀመሪያ ዙር ድርቤ ወልተጂ በተወዳደረችበት ምድብ አራት 02፡02.71 ደቂቃ በመግባት አምስተኛ ሆና አጠናቃለች። ሆኖም የዓለም ከ20 ዓመት በታች ሻምፕዮኗ ከተሸናፊዎች ፈጣን ሰዓት ባስመዘገበ በሚለው ህግ ነገ መስከረም 17/2012 ዓ.ም ለሚካሄደው ግማሽ ፍፃሜ አልፋለች።

በሴቶች 3000ሜ መሰናክል የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤቷ መቅደስ አበበ የግሏን ፈጣን ሰዓት በማስመዝብ ከሦስት ቀናት በኋላ ለሚደረግው የፍፃሜ ውድድር አልፋለች።በወንዶች 5000ሜ ያለፈው የዓለም ሻምፕዮኑ ሙክታር ኢድሪስ፣ የዓመቱ ፈጣን ሰዓት ባለቤት ጥላሁን ሃይሌ፣ እንዲሁም ሰለሞን ባርጋ ለፍፃሜ ውድድሩ አልፈዋል። አባዲ ሃዲስ አልተሳካለትም።

Via VOA
@YeneTube @FikerAssefa
“መደበኛ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ማንኛውም ነገር ሊፈጠር ይችላል።

ከጎረቤቷ ሰባት እጅ የምታንስ አገር የሚኖራት ሁለት ምርጫ ነው። አንድም ማፈግፈግ አሊያም ለነጻነት እስከ ሞት መዋጋት። እንዋጋለን። የኑክሌር ጦር መሳሪያ የታጠቀ አገር እስከ ፍጻሜው የተዋጋ እንደሆነ ጣጣው ከድንበር ይሻገራል፣ ፍዳው ለዓለም ይተርፋል” የፓኪስታኑ ጠቅላይ ምኒስትር ኢምራን ክኻን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ሕንድን፣ ፕሬዝዳንት ናሬንድራ ሞዲን አጥብቀው በነቀፉበት ዓለምን ካስጠነቀቁበት ንግግራቸው

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
🔥1
በአፍጋኒስታን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እየተካሄደ ነው።

የከፋ የደህንነት ስጋት ያለባት ሀገሪቱ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱን ሰላማዊነት እንዲያስጠብቁ አሰማርታለች።ሆኖም ድምፅ መስጠት በተጀመረ በአጭር ጊዜያት ውስጥ በካንደሃር በሚገኝ የድምፅ መስጫ ጣቢያ አቅራቢያ ፍንዳታ ተከስቷል።ምርጫው ለሁለት ጊዜ ተራዝሞ ነው ዛሬ እየተካሄደ የሚገኘው። የአሁኑ ፕሬዚዳንት አሽራፍ ጋኒ እና የቀድሞ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዱላህ አብዱላህ ዋነኛ ተፎካካሪዎች ናቸው።37 ሚሊየን ዜጎች ያላት አፍጋኒስታን 10 ሚሊዮኑ ድምፅ ለመስጠት ተመዝግበውባታል።ጥቃት ይደርሳል በሚል ስጋት ድምፅ መስጠት ከሚችሉ ዜጎች መካከል በምርጫው የተመዘገቡት ግማሾቹ ብቻ ናቸው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ/Fana
@YeneTube @FikerAssefa
የጤፍ ቢራ በአሜሪካ ተመረተ ሰኞ ገበያ ላይ እንደሚውል ሰምተናል።

በኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ባለቤትነት በአሜሪካ አገር የተቋቋመው ንጉስ ቢራ ኩባንያ በአሜሪካ ከተመረተ ጤፍ የተዘጋጀ ቢራ ለገበያ አቀረበ። ሰኞ መስከረም 19 ለሚጀምረው ስርጭት 19ሺ 200 ጠርሙስ የጤፍ ቢራ የተዘጋጀ መሆኑ መሆኑን አዲስ ማለዳ ከቢራ ጠማቂው የኩባንያው ቺፍ ፋይናስ ኦፊሰር መኩሪያ ንጉሴ ሰምታለች።

ኩባንያው ቢራው በሚጠመቅበት ቦታ ለተጠቃሚዎች ምርቱን በትኩሱ ለማቅረብ የሚያስችል በመዝናኛ ማዕከል (brew pub)ና የሙዚቃ ኮንሰርት አደራሽ ከፋብሪካው ጀርባ የመግንባት እቅድ እንዳለሁ ገልፀዋል።

Via:- ከማለዳ ጋዜጣ ላይ በየኔቲዩብ የተፃፈ
@YeneTube @Fikerassefa
በዶሃ የሴቶች ማራቶን 28 ሯጮች አቋርጠው ወጡ!

ትናንት እኩለ ለሊት በኳታር፣ ዶሃ በተጀመረው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተካሄደው የማራቶን ሩጫ ላይ የተሳተፉ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ሙቀት ምክንያት ማቋረጣቸው ተሰማ። ሩጫውን በበላይነት ኬኒያዊቷ ሩት ቼፔንጌቲች ያሸነፈች ሲሆን፤ ከ68 ተወዳዳሪዎች 28ቱ በሙቀቱ ከባድነት ምክንያት አቋርጠው መውጣታቸው ተዘግቧል።

እኩለ ለሊት ላይ የተደረገውን ይህ የሴቶች የማራቶን ውድድር ካቋረጡ ተወዳዳሪዎች መካከል ኢትዮጵያዊቷ ሩቲ አጋ አንዷ ነች።የውድድሩ አዘጋጆች ከዋናው ውድድር ቀድመው የማራቶን ውድድሩ እንዲካሄድ ያደረጉት የአየር ጠባዩ ለማራቶን ምቹ ላይሆን ይችላል በሚል እንደሆነ ተነግሯል።የሴቶች ማራቶን ሲካሄድ፤ የሙቀት መጠኑ 32 ዲግሪ ሴንቲግሬድ እንደነበር የተገለፀ ሲሆን፤ ወበቁ ደግሞ ከ70 በመቶ በላይ ነበር ተብሏል።የኢትዮጵያ ማራቶን አሰልጣኝ ሀጂ አዲሎ ሮባ፤ የቶኪዮ ማራቶን አሸናፊዋ ሩቲ ነጋን ጨምሮ ሌሎች ሁለት ተወዳዳሪዎች ማቋረጣቸውን ተናግረዋል።

"በአገራችን ማራቶንን በዚህ የአየር ጠባይ መሮጥ የሚታሰብ አይደለም" ካሉ በኋላ "ምን ያህሎቹ እንደሚጨርሱ ለማየት ጓጉቻለሁ" ብለዋል።የ23 ዓመቷ ቼፔንጌቲች ሩጫውን በ2 ሰዓት ከ32 ደቂቃ ከ43 ሰከንድ በማጠናቀቅ ወርቅ ስታገኝ፤ የባህሬን ዜግነት ያላት ሯጭ ሁለተኛ፣ ናሚቢያዊቷ ሯጭ ሦስተኛ በመሆን አጠናቀዋል።ቼፔንጌቲች፤ "በእንዲህ አይነት ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ አሸንፋለሁ ብዬ አልጠበቅኩም" በማለት ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል ተናግራለች። የብሪታኒያ ፈጣን የማራቶን ሯጭ ቻርሎቴ ፑርዱኤ እና ሌሎች ታዋቂ ሯጮችም አቋርጠው ከወጡት መካከል ናቸው።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
በዳውሮ ዞን የአተት ምልክት መታየቱን የዞኑ ጤና ቢሮ አስታወቆ የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፏል!

በቀን 14/01/2012 ዓ.ም ፣ በቀን 15/01/2012 ሁለት በድምሩ 3 በአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት የተጠቁ ታካሚዎች ወደ ታርጫ ሆስፒታል መግባታቸው ሪፖርት ተደርጎልናል፡፡ ሆኖም መሰል በሽታዎችን ናሙና መመርመር የሚያስችል የመመርመርያ መሳሪያ ዝግጁነት በሆስፒታሉ ባለመኖሩ በቀን 16/01/2012 ዓ.ም ከክልል ጤና ቢሮ ባስመጣነው የአፋጣኝ መመርመርያ መሳሪያ(Rapid test kit) ከታርጫ ዙሪያ ወረዳ ሽና-ጋቡራ ቀበሌ በመጣች ታካሚ ላይ የኮሌራ ባክቴሪያ ተገኝቷል በመሆኑም መላው የዳውሮ ህዝብ በተለይም የታርጫ ዙሪያ ወረዳና የታርጫ ከተማ ነዋርዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደርጉ እንጠቁማለን።

ምንጭ:የዞኑ ጤና ቢሮ
@YeneTube @FikerAssefa
በኬንያ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያን በናይሮቢ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መድኅኒአለም ቤተ ክርስቲያን በመገኘት የመስቀል ደመራ በዓልን በድምቀት አክብረዋል። በቦታውም በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር መለስ አለም ተገኝተው አብረው አክብረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
“ከአቶ ጌታቸው አሰፋ ጋር አንስማማም ለ14 ዓመታት ያህል ኦነግ ነው ብሎ ይከታተለኝ ነበር፤ እርሱ የኦሮሞ ብሔርን ማየት አይፈልግም፤ ኦሮሞ ከሆንክ አንተ ለእርሱ ኦነግ ነህ ማለት ነው ” አቶ ጁነዲን ሳዶ

አቶ ጁነዲን ሳዶ ከአዲስ ዘመን ጋር ካደረጉት ቃለምልልስ መካከል የተወሰዱ ጥቂት ነጥቦች

📌 ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በነበሩበት ጊዜ ምንም የማያወላዳ የህወሃት የበላይነት አለ። ይህ በፖሊሲ ደረጃ ነው።

📌 በምርጫ 97 የኢህአዴግ ደረት ትንሽ አበጥ ያለበት ሁኔታ ነበርና ለተቃዋሚዎች ትኩረት አልተሰጠም።

📌 ከሃይማኖት ጋር ተያይዞ የሚነሱብኝ ጉዳዮች የፖለቲካ ሥራ ነው የተሰራባቸው። የፖለቲካ ሥራውን የሰሩት ሰዎች ደግሞ ከፌዴራል መንግሥቱ ውስጥ ከኢህአዴግም ከኦህዴድም ውስጥ ናቸው።

📌 የደህንነት መስሪያ ቤቱ ነበር የተሳሳቱ መረጃዎችን በሕዝቡ መካከል ሲያሰራጭ የነበረው። በግል ከአቶ ጌታቸው አሰፋ ጋር አንስማማም።

📌 አሃበሽ የሚባል ባዕድ ሃይማኖት እንዲገባ ያደረገው እሱ ነው ይላሉ።

📌 መስኪድ አሰራ ስለሚባለው እኔ በሕይወቴ እስከአሁን ያሰራሁት አንድ መስኪድ ብቻ ነው። እናቴ ስታርፍ አርሲ የተወለድኩበት ቦታ ላይ በአርሲ ባህል «በጌጌሳ» ገንዘብ አሰባስቤ ነው የሰራሁት፤ በልመና።

📌 ለ14 ዓመታት ያህል ኦነግ ነው ብሎ አቶ ጌታቸው አሰፋ ይከታተለኝ ነበር። እርሱ የኦሮሞ ብሔርን ማየት አይፈልግም ኦሮሞ ከሆንክ አንተ ኦነግ ነህ ማለት ነው ለእርሱ።

📌 ኦነጎች በበኩላቸው መንግሥት ውስጥ በመሆኔ የሚቀሰቅስብን እና የሚያስቸግረን እሱ ነው ብለው እኔን የሚጠሉበት ሁኔታ አለ። ይሁንና አቶ ጌታቸው አሰፋ ኦነግ ነው ብሎ ፋይል ከፍቶብኝ ስልኬን እያስጠለፈ በርካታ ችግር አድርሶብኛል።

📌 እኔን ምክንያት አድርገው ባለቤቴን ስላሰሯት ከፍተኛ ብስጭት ውስጥ ገብቼ ነበር። የመጨረሻው ልጄ ከእናቱ ተለይቶ የማያውቅ ገና የአራት ዓመት ሕፃን ነበር። ባለቤቴን ፍቷትና እኔን እሰሩኝ ብል ማንም ሊሰማኝ አልቻለም።

📌 ለህክምና ታይላንድ ነው በቀጥታ የሄድኩት። ታይላንድ ለአንድ ወር በህክምና ቆየሁና ወደዱባይ አመራሁ። ዱባይ ሁለት ወር ቆይቻለሁ። እዚያ ተራ ሥራ እየሰራሁ ኑሮን ለመግፋት አስቤ ነበር ግን አልሆነም።

📌 በኬንያ 12 ወር ቆይቻለሁ። በወቅቱ ትንሽ ከተማ ውስጥ ተደብቄ ነበር። ኬንያ ውስጥ ብዙ ኢትዮጵያውያን ተገድለዋል። ታስረው መጥተውም ደብዛቸው የጠፉ አሉ። እኔ የት እንዳለሁ አቶ ጌታቸው አሰፋ ቢያውቅ ስለሚያስረኝ የምጠቀመው ስልክ እንኳን ኢንተርኔት የሌለው ነበር።

📌 በኋላ ከኬንያ ወደአሜሪካ አቀናሁ። እናም እንኳን የደህንነት ሰዎች ሊደግፉኝ ቀርቶ ሲያሳድዱኝ የነበሩት እነሱ ነበሩ።

📌 አሜሪካ ስገባ ይህ ሁሉ የደረሰብኝ ለበጎ ነው በማለት እራሴን ወደሃይማኖቴ በመመለስ እንደገና ውስጤን ለማየት ቻልኩ፡፡ ለሰዎችም ይቅርታ ማድረግ ጀመርኩ።

📌 አሁን ጌታቸው አሰፋን ባገኘው ቀድሞ እንደምናደድበት አልናደድበትም፡፡ ይልቁንም ሰላም እለዋለሁ። እርሱም አሁን ችግር ውስጥ ነው።

📌 ከለውጡ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ እና አቶ ለማ መገርሳ አሜሪካ በሄዱበት ወቅት አግኝቻቸዋለሁ። ሀገሬ መመለስ እፈልጋለሁ ስላቸው ዶክተር ዐብይ ዝግጁ ከሆንክ አሁኑኑ እንድትመጣ ነበር ያለኝ።

📌 አሁን ገንዘብ ስለሌለኝ አቅም ካላቸው ሰዎች ጋር እየተባበርኩ ለመስራት ነው ሃሳቤ። ባለሀብቶችን ማሰባሰብ እና ማሳመን የሚጠይቅ ሥራ ላይ ተሰማርቻለሁ።

📌 ለውጥ በሚኖርበት ጊዜ ግጭቶች ይጠበቃሉ። ግጭት ባይኖር ነበር ጤነኛ የማይሆነው። እዚህም እዚያም የሚፈነዳዱ ነገሮች በአግባቡ ከተያዙ ወደትክክለኛ መፍትሄ ይመጣሉ። ዋናው ነገር መንግሥት ጠንካራ መሆን መቻል አለበት።

📌 ጠንካራ የሚሊተሪ አቅም ወይም የፖሊስ አቅም ብቻ ሳይሆን የመንግሥት ጥንካሬ በንግግር ቃላት፣ በተግባር ማሳየት፣ በመዋቅር እና በፍትህ ይገለጻል።

📌 መንግሥት የሚችለውን እሰራለሁ የማይችለውን አልችልም ማለት አለበት። የሃሰት ቃል እየተገባ ከሄደ የሕዝብ አመኔታ እና አክብሮቱ ይታጣል።

📌 መንግሥት ቆፍጣና ሆኖ የእራሱን ሰዎች በአግባቡ ማሰማራት ካልቻለ ሕዝቡ አያከብረውም። ከዚህ ባለፈ ግን እንደ አጠቃላይ ሕግ የበላይነት ላይ ማወላዳት አያስፈልግም።

📌 ኢትዮጵያም ሙሉ የምትሆነው ከብሔር ብሔረሰቦቿ ጋር ነው። አንዱን በኢኮኖሚም ሆነ በማህበራዊ ጉዳይ አግልሎ ሌላው ሊያድግ አይችልም። በዚህ ረገድ አንዱ ለአንዱ ስጋት መሆን የለበትም።

📌 ሜቴክ ገንዘብ ስለዘረፈ የትግራይ ሕዝብ አብሮ መጨፍለቅ የለበትም የሚል አስተሳሰብ ይዘን መጓዘ ያስፈልጋል፡፡

📌 ጥቂት የኦዲፒ ባለሥልጣናት ካጠፉ ኦሮሞ ሕዝብን በአንድ ላይ መፈረጅ ኢትዮጵያዊነትን ያላላል። እናም ሁሉም አካታችነትን ሳይለቅ ሁሉም ተከባብሮ ሲኖር ነው ጥንካሬ የምናገኘው።

📌 ክልል መሆን ኢማዕከላዊነትን አያሳይም። ወደፊት እኮ ክልሎችም መልሰው ሊዋሃዱ /Re union/ ሊደረግ ይችላል።

ምንጭ: ኢፕድ
@YeneTube @FikerAssefa
#ኢሬቻ2012 በውቢቷ #ሀዋሳ ከተማ ዛሬ ተከብሯል።

ከተለያዩ ኦሮምያ ክልል የመጡ ቄሮች እና አባገዳዎች ከሲዳማ ህዝብ ጋር ኢሬቻን በሀዋሳ ሲዳማ ባህል አደራሽ አክብረዋል።

@YeneTube @Fikerassefa
በምዕራብ ጎንደር ዞን አማራና ቅማንት በሚዋሰኑባቸው አባቢዎች ባለፉት ጥቂት ቀናት በተፈጸሙ ጥቃቶች በአማራ ልዩ ሀይል አባላት ላይ የሞትና የመቁሰል ጉዳቶች ደረሱ።

ዛሬ ከሽኸዲ ከተማ ወደ ነጋዴ ባህር በሚወስደው ዋና መንገድ ላይ ቅኝት በማድረግ ላይበነበሩ የልዩ ሀይሉ ላይ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት አንድ ፖሊስ ሲገደል ሌሎች ቆስለዋል። በተመሳሳይ ዛሬ በጭልጋ ከተማ በታጣቂዎች በተተኮሰ ጥይት የአንድ የልዩ ሀይል ኣአባል ህይወት አልፏል።

ባሳለፍነው ሳምንት አጋማሽ ከአይከል ከተማ ወደ ዳንጉራ በማምራት ላይ በነበሩ የአማራ ልዩ ሀይል አባላት ላይ ጥቃት መፈጸሙና ጉዳት መድረሱም ይታወሳል።

በሌላ በኩል የቅማንት ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ባወጣው መግለጫ የአማራ ክልል ልዩ ሀይል አባላት በቅማንት ብሔረሰብ አባላት ላይ ጥቃት እየፈፀሙ መሆኑን አስታውቋል።


የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ ዛሬ ባወጡት ዘለግ ያለ ሀተታ ልዩ ሀይሉ ቅማንትን ጨምሮ በአማራ ክልል በሚኖሩ ንዑሳን ብሔረሰቦች ላይ እየፈጸመ ነው ያሉትን ጥቃት ኮንነዋል።

Via Ethiopia Live updates
@YeneTube @FikerAssefa
በሴቶች 10,000 ሜትር ዉድድር ለኔዘርላንድ የምትሮጠው ትውልደ ኢትዮጵያዊት ሲፈን ሀሰን አንደኛ ሆና አጠናቃለች።ለተሰንበት ግደይ ሁለተኛ ወጥታ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ሜዳልያ አስገኝታለች።

@YeneTube @FikerAssefa
የቤንሻንጉል ክልል የ102 ባለሀብቶችን የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሰረዙን አስታወቀ።

በግብርና ኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሰማሩ 102 ባለሀብቶች ፈቃድ መሰረዙንና ይዘውት የነበሩትን 56ሺ ሄክታር መሬት ወደ መሬት ባንክ ማስገባቱን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አስታወቀ፡፡በክልሉ የአካባቢ መሬት አስተዳደርና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ ነፃነት ዘለቀ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ለእርሻ ሥራ ፈቃድ ወስደው ያላለሙ ባለሀብቶች እርምጃ ተወስዶባቸዋል። በክልሉ በግብርና ዘርፍ የተሰማሩ 651 ባለሀብቶች መሆናቸውን ጠቅሰው እነዚህም 350ሺ ሄክታር መሬት ወስደዋል፡፡

ይሁንና መሬቱን የሚያለሙና ያላለሙ በሚል በተደረገ ልየታ 102 የሚሆኑት ሳያለሙ የቀሩ በመሆናቸው እርምጃው መወሰዱን ጠቅሰው በዚህም 56ሺ ሄክታር መሬት ተነጥቆ ለመሬት ባንክ ገቢ መደረጉን ተናግረዋል፡፡የአስር ባለሀብቶች የተበላሸ ብድር መሰረዙን ያነሱት አቶ ነፃነት፤ ከባንክ መሬቱን አሲዘው ብድር የወሰዱ በመሆኑ ባንኩ ‹‹መሬቱን ይዘን ብድር ስለሰጠን የመሬቱ ባለቤቶች ነን›› በሚል ከቢሮው ጋር ያለመግባባት መፈጠሩን አንስተዋል፡፡

ምንጭ: ኢፕድ
@YeneTube @FikerAssefa