አዴፓ ከነገ ጀምሮ በፖለቲካና በልማት ጉዳዮች ላይ ይመክራል።
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) በፖለቲካና በልማት ጉዳዮች የሚመክር ስብሰባ ከነገ ጀምሮ እንደሚያካሂድ የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።በጽህፈት ቤቱ የህዝብ አደረጃጀት ኃላፊ አቶ አብርሃም አለኸኝ እንደገለጹት በስብሰባው የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን ጨምሮ እስከ ወረዳ ድረስ ያሉ ከ2 ሺህ 500 በላይ አመራሮች ይሳተፋሉ።
ለ3 ቀናት በሚቆየው ስብሰባ ያለፈውን ዓመት የፖለቲካና የድርጅት ስራዎች የእቅድ አፈፃፀም ይገመገማል።ያገጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ መፍትሄዎችም ይታያሉ ብለዋል።የክልሉን ሰላምና ደህንነት በማረጋገጥ፣ የወጣቶችን የስራ እድል ፈጠራ፣ የመሰረተ ልማት አቅርቦት ስራዎች ዋነኞቹ የመወያያ አጀንዳዎች መሆናቸውም ተገልጿል።በ2012 የድርጅትና የልማት ስራዎችን እቅድና የማስፈፀሚያ ስልቶች ቀርበው አመራሩ በሚያደረገው ውይይት ዳብሮ የእቅዱ አካልም ይሆናል ተብሏል።
ምንጭ፡- ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa

የደቡብ ክልል ምክር ቤት በኅዳር የሚካሔደውን የሲዳማ ሕዝበ-ውሳኔ የሚመራ ፅ/ቤት እንዲቋቋም ዛሬ ውሳኔ አሳልፏል። የደቡብ ክልል ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት እንዳለው ሕዝበ-ውሳኔውን የሚያስተባብረው ፅህፈት ቤት ተጠሪነት ለክልሉ ምክር ቤት ይሆናል።
Via:- Eshete Bekele
@YeneTube @Fikerassefa
Via:- Eshete Bekele
@YeneTube @Fikerassefa
በድሬዳዋ ከተማ በተፈጠረ ግጭት ባንክ ቤቶችን ለመዝረፍ ያቀዱና ሌሎችንም የማይገባ ድርጊቶችን ሊፈፅሙ የነበሩ ከ20 በላይ ሰዎች መታሰራቸውን ሸገር ዘግቧል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
በናይሮቢ ትምህርት ቤት ተደርምሶ በተማሪዎች ላይ ጉዳት ደረሰ፡፡
በኬንያ ናይሮቢ አንድ ትምህርት ቤት ተደርምሶ በተማሪዎች ላይ ጉዳት አድርሷል፤ በአደጋውም ቢያንስ ሰባት ተማሪዎች ሞተዋል፤ 57 ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል ገብተዋል፡፡
ከእንጨት የተሠራው ትምህርት ቤት ተማሪዎች በገቡ በደቂቃዎች ውስጥ ነው የተደረመሰው፡፡
አካባቢው ለተሽከርካሪ ምቹ ያልሆነ በመሆኑ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በፍጥነት ደርሰው ዕርዳታ ለማድረግ መቸገራቸውም ነው የተገለጸው፡፡
የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር በአቅራቢያ የሚገኝ የቆሻሻ ማፋሰሻ የትምህርት ቤቱን መሠረት በመቦርቦሩ አደጋው እንደደረሰ ተናግረዋል፡፡
በኬንያ የዓመቱ ትምህርት የተጀመረው ዛሬ ሲሆን ተማሪዎች ከክረምት እረፍት በተመለሱበት ዕለት ነው አደጋው ያጋጠመው፡፡ የትምህርት ቤቶች ደኅንነት ከእረፍት መልስ መፈተሸ አለመፈተሹን ዘገባው ያለው ነገር የለም፡፡
ምንጭ ፡- አብመድ

⬆️⬆️
በድሬዳዋ ከተማ መስከረም አንድ ቀን በግለሰቦች መካከል የተፈጠረ ግጭት ወደ ብሔር ግጭት አድጎ፤ ትናንትና እና ከትናንት በስትያ በተለይም ደቻቱና መጋላ የተባሉ የከተማዋ ክፍሎች ከፍ ያለ ግጭት አስተናግደዋል።በግጭቱ የአንድ ሰው ህይወት ያለፈ ሲሆን፣ በርካቶች ተጎድተዋል። በከተማዋ ዛሬም ውጥረት ያለ ሲሆን የትራንስፖርት አገልግሎትን ጨምሮ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ዛሬም ተዘግተው ውለዋል።የብሔር ግጭቱ የሀይማኖት መልክ ይይዛል የሚል ስጋት ያደረበት ፖሊስ፣ ከትናንት ጀምሮ የእምነት ተቋማትን ሲጠብቅ ታይቷል።
ምንጭ:Ethiopia Live Updates

በደምበጫ ዙሪያ ወረዳ የትራፊክ አደጋ ደርሶ የ16 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡
በምዕራብ ጎጃም ዞን ደምበጫ ዙሪያ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰዎች ሕይወት ጠፍቷል፤ የአካል ጉዳትም ደርሷል፡፡ዛሬ መስከረም 12 ቀን 2011 ዓ.ም እኩለ ቀን አካባቢ በምዕራብ ጎጃም ዞን ደምበጫ ዙሪያ ወረዳ የጨረቃ ከሚባለው አካባቢ አንድ የጭነት አይሱዙ ሁለት መለስተኛ የሕዝብ ማመላለሻዎችንና አንድ ባጃጅ ገጭቶ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ የትራፊክ ባለሙያ ሳጅን ደሳለኝ መኩሪያ ለአብመድ እንዳስታወቁት የጨረቃ ወጣ ብሎ ወደ ደምበጫ አቅጣጫ ከሚገኝ ድልድይ አካባቢ በደረሰው የትራፊክ አደጋ በአንደኛው መለስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ የነበሩት ሰዎች ሙሉ በሙሉ ሳይሞቱ አልቀሩም፤ ከሁለተኛው መለስተኛ የሕዝብ ማመላለሻም በጣት የሚቆጠሩ ሰዎች ብቻ ሕይወታቸው እንደተረፈ ነው የተናገሩት፡፡ በባጃጅ ላይ የነበሩት ተሳፋሪዎች ደግሞ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ጠቁመዋል፡፡
የሟቾች ቁጥር ስንት እንደሆነ ፖሊስ እያጣራ ሲሆን እስካሁን 16 ሰዎች መሞታቸው እየተነገረ ነው፡፡ማሽላ ጭኖ ከጅጋ ወደ አማኑኤል ከተማ ይጓዝ እንደነበር የተገለፀው የጭነት መኪና አሽከርካሪም ጉዳት ደርሶበት ሆስፒታል መግባቱን ነው ሳጅን ደሳለኝ ያስታወቁት፡፡ሁለቱ መለስኛ የሕዝብ ማመላለሻዎች ስንት ሰዎችን ጭነው እንደነበር አለመታወቁ የተጎጅዎችን ቁጥር በትክክል ለማወቅ አለማስቻሉም ነው የተገለጸው፡፡የአደጋው መንስኤ በውል ባይታወቅም ‹‹ከሁኔታው ፍጥነት ይመስላል›› ብለዋል ሳጅን ደሳለኝ ለአብመድ ሲናገሩ፡፡ መርማሪ ፖሊሶች ጉዳዩን እያጣሩና የተጎጂዎችን አስከሬን ለቤተሰብ እየሰጡ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡
Via AMMA

ኢሬቻን በሀዋሳ ለማክበር እንቅስቃ ተጀምሯል።
የኦሮሞ ብሄር የምስጋና በዓል የሆነውን የኢሬቻ በዓል በሀዋሳ ለማክበር እንቅስቃሴ መጀመሩን ኮሚቴው አሳውቆናል፡፡ ይህ ህዝባዊ በዓል የሚከበረው ሀዋሳ በሚገኘው የሲዳማ ባህል አዳራሽ ሲሆን የሚከበርበትን ቀን በቅርቡ ይፋ እንደምያደርጉ አስውቀውናል። በያዝነው ዓመት የተከበረው የሲዳማ ብሄር ዘመን መለወጫ በየፊቼ ጫምበላላ በዓል የሲዳማ ሽማግሌዎች እና አባገዳዎች በተገኙበት በፊንፊኔ ኦሮሞ ባህል ማዕከል መከበሩ ይታወሳል።
Via Maleda Media

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ የአፋር ክልል ፖሊስ አባል ለሆነው ሲራጅ አብደላ የምስጋና የምስክር ወረቀት አበረከቱ።
ዛሬ መስከርም 12 ቀን 2012 ከሰዓት በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ሀገሬና ሕዝቤ ይበልጥብኛል በማለት የሕግ የበላይነትን በማስከበሩ ያላቸውን አድናቆት ገልጸው ወጣት እንደመሆኑ በጣም ብዙ ለሀገሩ መሥራት እንደሚችልና በመልካምነቱ እንዲቀጥል አበረታተውታል። ሕግ አስከባሪዎች ለሀገርና ለወገናቸው ሰላምና ደኅንነት ዘብ በመቆም በሀቀኝነት ማገልገልን እንደ ሲራጅ ካሉ ምስጉን ኢትዮጵያውያን መማር እንደሚያስፈልግ ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ተናግረዋል።
#PMOEthiopia

በአዲስ አበባ ከተማ በኤሌትሪክ አደጋ የሁለት የሰው ሕይወት አለፈ!!
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ በኤሌትሪክ አደጋ የሁለት ሰው ሕይወት ማለፉን ገለጸ፡፡ሁለት ግለሰቦች ያለጥንቃቄ ብረት ይዘው ሲያንቀሳቅሱ የያዙት ብረት ከከፍተኛ የኤሌትሪክ መስመር ጋር በተፈጠረ ንክኪ ሕይወታቸው ማለፉን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡አደጋው የተከሰተው ከቀኑ 6፡00 ሰዓት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ልዩ ቦታው ቡልጋርያ አደባባይ አካባቢ ነው፡፡ኮሚሽኑ ወቅቱ ዝናባማ በመሆኑ መሰል አደጋዎች እንዳይከሰቱ ህብረተሰቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያድርግ እንደሚገባ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡ መሰል ድንገተኛ አደጋዎች ሲያጋጥሙ በ991 ነፃ የስልክ መስመር በመጠቀም መረጃ መስጠት እንደሚቻልም ነው ኮሚሽኑ ያስታቀው፡፡
ምንጭ:ፋና

በደቡብ ክልላዊ መንግሥት የሚተዳደረው የደቡብ ራዲዮና ቴሌቭዥን ድርጅት የሣውላ ኤፍ ኤም 102.2 ራዲዮ ጣቢያን ነገ ያስመርቃል።
Via እሸት በቀለ
@YeneTube @FikerAssefa
Via እሸት በቀለ
@YeneTube @FikerAssefa
በሀዋሳ በኮሌራ ወረርሽኝ የተጠቁ ዜጎች ቁጥር ወደ 102 ከፍ ብሏል።
የክልሉ ጤና ቢሮ እንዳስታወቀው በሀዋሳ በኮሌራ ወረርሽኝ ከተጠቁ ዜጎች 102 ዜጎች መካከል ሁለት ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፡፡በሃዋሳ ከተማ ከነሀሴ 12 ጀምሮ የተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ 102 ሰዎችን ይዟል፡፡ 2 ሰዎች በወረርሽኙ ህይወታቸው ሲያልፍ 4ቱ በማገገሚያ የህክምና መስጫ ጣቢያ እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሆነም ተሰምቷል፡፡
የክልሉ ጤና ቢሮ የጤና እና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ግኝት እና ምላሽ ዋና የስራ ሂደት አቶ ደመላሽ ሽብሩ እንዳሉት የወባ ወረርሺኝም ቢሆን በደቡብ ክልል አስጊ ሁኔታ ላይ ነው ብለዋል፡፡በተለይ ሀዋሳ ከተማ ፣ጋሞ ጎፋ ዞን፣ ደቡብ ኦሞ ዞን ላይ ጫናው የበረከተ ሲሆን ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የወባ ወረርሽኝ ቁጥር በአማካኝ ወደ 2ሺ ከፍ ማለቱን ተነግሯል፡፡ለጤና ኬላዎች መድሀኒቶች በአፋጣኝ እንዲደርሱ በመደረጉ እና የመከላከያ መድሀኒት እንዲረጭ በማድረግ ባለፉት 2 ሳምንታት ቁጥሩን ወደ 1ሺ ዝቅ ማድረግ መቻሉንም አቶ ደመላሽ ተናግረዋል፡፡
ከአየር ንብረት ለውጡ ጋር ተያይዞ ረም በጋ መኖሩ፣ ህብረተሰቡ ወባ የለም በሚል መዘናጋቱ ፣ ለቅድመ መከላከል የሚረጩ ኬሚካሎች እና የወባ መድሀኒቶት እጥረት የወባ ወረርሺኝ ካለፈው ዓመት ቁጥሩ እንዲጨምር ምክንያት ሆኗልም ብለውናል፡፡ግንቦት እና ሚያዚያ ወር ላይ በክልሉ 9 ወረዳዎች ላይ ከፍተኛ የወባ ወረርሽኝ ተከስቶ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ደመላሽ በቀጣይ በጋ ወር ትንኟ ለመራባት ምቹ ሁኔታ ስለሚፈጠርላት አሁንም ስጋት መኖሩን ተናግረዋል፡፡እስከ ታህሳስ ወር ልዩ ጥንቃቄ ስለሚያፈልግ የአጎበር አጠቃቀም እንዲሻሻል ፣ መከላከያ መድሀኒቶች በስፋት እንዲረጩ በማድረግ በክልሉ የቅድመ መከላከል ስራ በስፋት እየተሰራ መሆኑን አቶ ደመላሽ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
ምንጭ:Ethio FM

በኢትዮ ቴሌኮም እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መካከል የቴሌኮም አገልግሎቶች የክፍያ መፈጸሚያ አማራጮች ላይ የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የኢፌዲሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከአሜሪካው የልማት ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤድ) እና ከሕፃናት አድን ድርጅት (ሴቭ ዘ ችልድረን) ጋር ለተማሪዎች ክህሎት ማሳደጊያ በሚል የኹለት ሚሊዮን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ። ድጋፉ ባህር ዳር፣ ሐዋሳ፣ ጅማ፣ ጅግጅጋ፣መቀሌ ዩኒቨርስቲዎችን የሚደርስ ይሆናል።
ምንጭ:አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
ምንጭ:አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ ከኦሮሚያ ት/ት ቢሮ የምስክር ወረቀትና ለላቀ የትምህርት ልማት አጋርነት ሽልማት ተበረከተላቸዉ፡፡ሽልማቱን የኦሮሚያ ክልል ም/ር/መ አቶ ሽመልስ አብዲሳ የሰጡ ሲሆን የጽ/ቤቱ ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ፈንታ በወኪልነት ተቀበልዋል፡፡
@YeneTube @Fikerassefa
@YeneTube @Fikerassefa
አምባሳደር ፍጹም አረጋ ትናንት መስከረም 11 ቀን 2012 ዓ.ም በዋሽንግተን ዲ.ሲ. የቅዱስ ሚካኤል ቤተ-ክርስቲያን 25ኛ ዓመት ኢዮቤልዮ በዓል ላይ በመገኘት መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸውም ህዝበ ክርስቲያኑ አገሩን እንዲወድ፣ ወገኑን እንዲረዳ፣ ባህሉን እንዲያስተዋውቅ ቤተክርስቲያኗ እያከናወነች ላለው አርዓያነት ያለው ስራ ምስጋና አቅርበዋል።በኢትዮጵያ የተጀመረው ለውጥ ግቡን እንዲመታና በአገር ቤትም እዚህም ያለውን ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሚጠቅም ለውጥ እንዲሆን አሁንም በዕውቀት፣ በገንዘብ፣ በስልጠናና በምክር ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።ኤምባሲው በዚህ አገር ለሚገኘው ህብረተሰባችን ቀልጣፋና አርኪ አገልግሎት ለመስጠት ከምንጊዜውም በላይ ዝግጁ መሆኑን ክቡር አምባሳደሩ ገልጸዋል።
ምንጭ:በዋሽንግተን የኢትዮጵያ ኤምባሲ

ከካናዳ መጥቶ የሞተው የ 10 ሚሊዮን ዶላር ሎተሪ እድለኛው ሚካኤል ገብሩ ቀብር ተፈጸመ፡፡ካናዳዊ ዜግነት ያለው ሚካኤል በተወለደባትና በድንገት ባረፈባት ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት ግብአተ መሬቱ መፈጸሙን ሲቢሲ ዘግቧል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
ይህንን ያውቁ ኖሯል?
አዶልፍ ሂትለር ፣ ጆሴፍ ስታሊንና ቤኒቶ ሙሶሎኒ በተለያየ ጊዜ በሰላም ዘርፍ ለኖቤል ሽልማት ታጭተው ነበር።
ስታሊን 23 ሚልዮን
ሂትለር 17 ሚልዮን
ሙሶሎኒ ደግሞ 430 ሺህ ሰዎችን ያስገደሉ ሲሆን ከ430 ሺህ ውስጥ 30,000 የሚሆኑት #በጣሊያን_ወረራ ጊዜ የተገደሉ #ኢትዮጵያዊን ናቸው።