YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የአዲስ አበበ የፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ያለመ የቆሻሻ አወጋገድ ማስተር ፕላን እየተዘጋጀ ነው - የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን።
@YeneTube @Fikerassefa
በተያዘው በጀት ዓመት 278 አገልግሎቶች በኦንላይን ሊሰጡ ነው።

እስከ 2012 መጨረሻ ድረስ 278 አገልግሎቶች በኦንላይን ዲጂታል አገልግሎት እንደሚሰጡ የኢኖቪሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የኦንላይን ኤሌክትሮኒክስ አገልግሎት ለመተግበር 34 ተቋማትን በመምረጥ አገልግሎቱን እንዲሰጡ ወደ ተግባር ለማስገባት እየተሰራ መሆኑና ተቋማቱ የሚሰጡትን አገልግሎት ዓይነት በመለየት ወደ ሲስተሙ እንዲገቡ መደረጉን በኢኖቪሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የመንግስት ኤሌክትሮኒክስ አገልግሎቶችና አፕልኬሽኖች ልማትና አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ አሸናፊ ጋዲሳ በተለይም ለኢቲቪ ተናግረዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ዛሬ መስከረም 5 ቀን 2011 ዓም የኖርዌ የውጭ ጉዳይ እና የመከላከያ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አኒከን ሁይትፈልድት እና ልኡካቸውን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ሁለቱ ወገኖች በሁለትዮሽ፣ በቀጠናዊ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ዜና ሹመት!!

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ለስድስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ሹመት ሰጡ።

በዚህም መሰረት ከየካቲት ወር 2011 ዓ.ም ጀምሮ የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ግዛት አብዩ ጌታው የገጠር መሬት አስተዳድርና አጠቃቀም ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።የጎንደር ከተማ ከንቲባ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት ዶ/ር ሙሉቀን አዳነ ጥሩነህ ደግሞ የክልሉ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሆነው መሾማቸው ነው የተመለከተው።

እንዲሁም አቶ ብርሀኑ ጣዕም ያለው የክልሉ ንግድ ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ፣ ዶ/ር ማማሩ አያሌው ሞገስ የክልሉ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጅ ልማት ቢሮ ኃላፊ እና ዶ/ር መለስ መኮንን ይመር የግብርና ቢሮ ኃላፊ በመሆን ተሹመዋል።
ዶ/ር አያሌው ወንዴ መለሰ ደግሞ የጣና ሐይቅና ሌሎች የውሃ ነክ አካላት ጥበቃና ልማት ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው እንዲያገለግሉ መሾማቸውን የክልሉ ርእሰ መስተዳድር ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

ምንጭ: ፋና
@YeneTube @FikerAssefa
የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር የ“ጊፋታ አዋርድ” ሽልማት ተበረከተላቸዉ።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ “ ጊፋታ አዋርድ” የተሰኘ የምስጋናና የእዉቅና ሽልማት ተበረከተላቸዉ፡፡በወላይታ ሶዶ “አርአያዎቻችን በረከቶቻችን ናቸው” በሚል መሪ ሀሳብ ለመጀመሪያ ጊዜ የምስጋናና እውቅና ስነ-ስርዓት ተካሂዷል፡፡ በስነ-ስርዓቱም አቶ ኃይለማርያምን ጨምሮ በተለዩ 5 ዘርፎች በአገርና በአለም አቀፍ ደረጃ በጎ ተጽዕኖ የፈጠሩ 45 ግለሰቦች የምስጋናና የእውቅና ሽልማትም ተበርክቶላቸዋል፡፡

“ጊዜው የይቅርታ ነው” ያሉት አቶ ኃይለማሪያም በነበራቸው የስልጣን ቆይታ ወቅት የተፈጠሩ ስህተቶችን ህዝቡ ይቅር እንዲላቸው በመጠየቅ በቀጣይም ህዝቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የድርሻቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል።
የፕሮግራሙ አስተባባሪ አቶ አንዱአለም ሳይዳ እንዳሉት መቻቻል፣ መከባበር፣ ይቅርታ፣ እርቅና መሰል የብሄሩ ዕሴቶችን በማጎልበት የተጀመረውን አገራዊ የለውጥ ጉዞ ለመደገፍ ዓላማ ያደረገ ስነ-ስርዓት ነው፡፡

ምንጭ፡- ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
⬆️የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ሠርፀ ፍሬስብሐት የሀገር ፍቅር ቴአትር ዋና ዳይሬክተርን ከሀላፊነት አንስተዋል!

ደብዳቤው ላይ እንደሚታየው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቴአትር ቤቱ ከጥበብ ቤትነት ይልቅ ወደ “መጠጥ ሽያጭ ቤትነት” እያደላ መምጣቱን ይገልፃል።
@Yenetube @FikerAssefa
የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪው ሲፒጄ ባወጣው ዘገባ ኤርትራ በዓለም አንደኛ የሚድያ አፈና ፈፃሚ ስትሆን ሰሜን ኮርያ ሁለተኛ፣ እንዲሁም ቱርክመኒስታን ሦስተኛ መሆናቸውን አስታወቀ።

ድርጅቱ አክሎ እነዚህ ሀገራት ውስጥ ሚድያዎች የመንግሥት አፈ-ቀላጤ ከመሆን ውጪ ሌላ ሥራ እንደማይሰሩ ገልፆ በኤርትራ ብቻ በቅርብ ዓመታት ሰባት ጋዜጠኞች የት እንደገቡ እንደማይታወቅ ይፋ አድርጓል።

@Yenetube @FikerAssefa
ሱዳን እና ኤርትራ በወታደራዊ እና ደህንነት ዘርፎች በጋራ ለመስራት ተስማሙ፡፡

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሱዳን የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝታቸውን አጠናቀው በዛሬው ዕለት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፤

የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስማ ሙሃሞድ አብደላህ በኢሳያስ አፈወርቂ በሱዳን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ሁለቱ ሀገራት በወታደራዊ እና ደህንነት ዙሪያ በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሰቸውን ተናግረዋል፡፡

ሀገራቱ በእግረኛ ጦር፣ አየር እና ውሃ ሃይል ወታደራዊ ዘርፎች፤ የመከላከያ ኢንዱሰትሪ እና ጤና አገልግሎት በትብብር ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል ነው ያሉት፡፡

ወሰን ተሻጋሪ ወንጀሎችን መከላል፣ መረጃዎችን መለዋወጥ እና የአቅም ግንባታ ላይ መስራት ሌላው የስምምነት መስክ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡

ምንጭ:- FBC
@Yenetube @FikerAssefa
ለሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች⬇️

የ2012 የትምህርት ዘመን ምዝገባ መስከረም 26 እና 27 ቀን 2012 ዓ.ም የሚከናወን ስለሆነ ከመስከረም 24 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ዩኒቨርሲቲያችን መግባት እንደምትችሉ እያሳወቅን ዘግይተው የሚመጡ ተማሪዎች በቅጣት ምዝገባ የሚካሄደው ትምህርት በሚጀመርበት መስከረም 28 ቀን 2012 ዓ.ም መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች ብቻ ከመስከረም 10 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ግቢ ገብተው ምዝገባ መስከረም 11-12/2012 ዓ.ም የሚካሄድ ይሆናል፡፡

@Yenetube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ ተጨማሪ ዩኒቨርሲቲዎችን የመገንባት እቅድ እንደሌላት አስታወቀች፡፡

አሁን ላይ በኢትዮጵያ 45 የመንግስት ዩንቨርሲቲዎች በየዓመቱ ተማሪዎችን ተቀብለው በማስተማር ላይ ናቸው።

325 ሚሊዮን አካባቢ የህዝብ ብዛት ያላት አሜሪካ ከ3 ሺህ 500 በላይ ዩንቨርሲቲዎች ያሏት ሲሆን ከ1 ቢሊዮን በላይ ህዝብ ብዛት ያላት አፍሪካ ያሏት ዩንቨርሲቲዎች ግን 740 ብቻ ናቸው።

በኢትዮጵያም በየዓመቱ እድሜው ለከፍተኛ ትምህርት የሚደርሰው ህዝብ ብዛት በአማካኝ ስምንት ሚሊዮን ሲሆን ወደ ዩንቨርሲቲዎች ማለትም በግልና በመንግስት ዩንቨርሲቲዎች የሚገቡት ተደምሮ ከአንድ ሚሊዮን በታች እንደሆነ የማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ ሪፖርት ያስረዳል።

ይሁንና ኢትዮጵያ አሁን ላይ ተጨማሪ ዩንቨርሲቲዎችን የመገንብት እቅድ የለኝም ብላለች።

በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ደቻሳ ጉርሙ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለጹት መንግስት በቀጣይ የዩኒቨርሲቲዎችን አቅም የማጠናከር ስራ ላይ ትኩረቱን ያደርጋል፡፡

የዩኒቨርሲቲዎች መብዛት ብቻውን የትምህርት ጥራትን ሊያረጋግጥ ስለማይችል አዲስ ዩንቨርሲቲዎችን ከመገንባት ይልቅ ከዚህ በፊት የተገነቡትን በግብአት ማጠናከርና በቴክኒዮሎጂ ማዘመን ላይ ልዩ ትኩረት ይደረጋልም ብለዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የቅበላ አቅማቸው ከፍላጎቱ ጋር ሲነጻጸር ተመጣጣኝ ነው ወይ ብለን ላነሳንላቸው ጥያቄ በዚህ አመት የሚገቡ ተማሪዎችን ማስተናገድ ይችላሉ፤በሚቀጥሉት አመታትም ግንባታቸው ያልተጠናቀቁ ሶስተኛና አራተኛ ትውልድ የሚባሉት ዩኒቨርሲቲዎች ግንባታቸው ተጠናቆ በሙሉ አቅማቸው መቀበል ስለሚጀምሩ ምንም አይነት ክፍተት አይፈጠርም ብለውናል፡፡

በተጨማሪም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በርካታ ተማሪዎችን በመቀበል እያስተማሩ በመሆኑ ለተወሰኑ አመታት አዳዲስ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች አይከፈቱም ብለዋል ዳይሬክተሩ፡፡

ምንጭ:- EthioFM
@Yenetube @FikerAssefa
#FakeNewsAlert

"ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ከጠ/ሚር ቢሮ ተባረረ" ተብሎ በአንዳንድ የፌስቡክ ገፆች የተፃፈው የሀሰት መረጃ እንደሆነ ከተለያዩ ቦታዎች ለማረጋገጥ ችያለሁ።

Via :- Elias meseret
@Yenetube @Fikerassefa
በአባይ ግድብ ላይ ለዓመታት የተካሄድው ውይይት ውጤት አላመጣም።
-የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

ግብጽ ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታንና የውሃ መሙላት ሂደትን በተመለከተ ለአራት ዓመታት ሲካሄድ የነበረው የሦስትዮሽ ውይይት ምንም ውጤት እንዳላመጣ የግብጹ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚህ ሹህሪ ተናገሩ።
የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ካይሮ ውስጥ ከኬኒያዋ አቻቸው ሞኒካ ጁማ ጋር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው ይህንን የተናገሩት።ሳሚህ ሹህሪ እንዳሉት ሃገራቸው ከአባይ የምታገኘውን የውሃ ድርሻን በከፍተኛ ደረጃ እስካልቀነሰው ድረስ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ግድብ ለመገንባት ያላትን መብት ግብጽ እውቅና እንደምትሰጥ ገልጸዋል።

ምንጭ: ቢቢሲ
@YeneTube @FikerAssefa
በ450 ሚሊዮን ዶላር ወጪ 2 መቶ ሚሊዮን ሰዎችን ማገልገል ይችላል የተባለ የካንሰር ሕክምና ሆስፒታል በኢትዮጵያ ሊገነባ ነው። ግንባታው የምስራቅ አፍሪካ በየነ መንግስታት (ኢጋድ )ድጋፍ እንደሚገነባ እና የአባ አገራትን ዜጎች እንዲያገለግል የታሰበ ነው።

Via አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
ፌዴሬሽኑ የ2012 የውድድር ዘመንን አዲስ አሰራር አስተዋወቀ፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ2012 የውድድር ዘመን የዋንጫ አሸናፊውን መለያ ይፋ አደረገ፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በ2012 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ አዲስ አወቃቀር ማውጣቱ የሚታወስ ነው፡፡ ቡድኖችን 24 በማድረስ ለሁለት በመመደብ እንዲወዳደሩ ነው ሀሳብ ያቀረበው፡፡ ፌደሬሽኑ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ደግሞ የውድድሩ አሸናፊ የሚለይበትን መንገድ ይፋ አድርጓል፡፡

የፕሪሚዬር ሊጉ አሸናፊ የሚሆኑት የየምድቦቹ አሸናፊዎች ወይም አንደኛ ሆነው ያጠናቀቁ ቡድኖች በገለልተኛ ሜዳ ሁለት ዙር ጨዋታ አድርገው አሸናፊ የሆነው የፕሪሚዬር ሊጉ አሸናፊ ይሆናል ብሏል፡፡ አሸናፊው ቡድን ኢትዮጵያን በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ሲወክል ሁለተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው ደግሞ በአፍሪካ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን ይወክላል፡፡

የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ አሸናፊ የሆነው ደግሞ ኢትዮጵያን በሴካፋ እንደሚወክል ተገልጧል፡፡ የሊጉ መከፈልን ተከትሎ የሚፈጠረውን የጨዋታ መቀነስ ለማስተካከል ሦስተኛ የውድድር መርሀ ግብር ለማዘጋጀት እንደታሰበም ሶከር ኢትዮጵያ አስነብቧል፡፡

Via:- AMMA
@Yenetube @Fikerassefa
ኢትዮ ቴሌኮም ⬆️
@Yenetube @Fikerassefa
"አባቴ በግፍ ከተገደለ ዛሬ 80 ቀኑ ነው፤ ከአባቴ አሟሟት ጋር በተያያዘ ያለው እንቆቅልሽ ምንድነው ተብዬ ብጠየቅ የማውቀው ነገር የለም፣ ትክክለኛ ገዳዩ ማን እንደሆነም እስካሁን ግልፅ አይደለም። ያ ገደለ የተባለው ጠባቂም ቢሆን የት እንዳለ አናውቅም፣ ክስ ተመስርቶበታል አልተመሰረተበትም፣ የት ፍርድቤት ነው የሚቀርበው ምንም መረጃ የለም"

የሜ/ጄነራል ገዛኢ አበራ ልጅ - Eliase Meseret
@Yenetube @Fikerassefa
YeneTube
ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስናትን የሞያሌ መንገድ ዘጋች። ኢትዮጵያና ከኬንያ ጋር የሚያስተሳስረው የሞያሌ መስመር የተለያዩ ምርቶች የሚተላለፉበት መንገድ ነበር።ይሁንና ኬንያ በሞያሌ በኩል ከፍተኛ የሆኑ ህገ ወጥ ስራዎች በመበረከቱ መስመሩን ለመዝጋት እንደወሰነች ተገልጿል።የሞያሌ መስመር ኢትዮጵያዊያንና ኬንያዊያን ግብር ሳይከፍሉ በህገወጥ መንገድ ቡና፣ጥራጥሬ፣የጦር መሳሪያና ሌሎች የምርት አይነቶችን…
ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስናትን የሞያሌ መንገድ ዘግታለች በሚል የተሰራጨው መረጃ ሃሰት መሆኑን በኬንያ የኢፌዴሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር መለስ ዓለም ገለጹ።

አቶ መለስ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የሞያሌ መንገድ ተዘግቷል በሚል የተሰራጨው መረጃ ሃሰት መሆኑን፥ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል። ጉዳዩን በተመለከተም የተዘጋ መንገድም ሆነ ድንበር እንደሌለ ጠቅሰው፥ መረጃዎቹ የሃሰትና መሰረተ ቢስ ናቸው ብለዋል።በሞያሌ መንገድ ህገ ወጥ ንግድ ተበራክቷል በሚል ኬንያ የሞያሌን ድንበር ዘግታለች በሚል በዛሬው እለት በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እና ማህበራዊ የትስስር ገጾች መረጃ መውጣቱ ይታወሳል።

Via Fana
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ለሳምንት የታፈነው ሊባኖሳዊ ነጋዴ ትናንት ተለቆ ወደ ጋቦን እንደበረረ ዐረብ ኒውስ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ ሐሰን ጃብር በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲወጣ ነበር የታፈነው፡፡ ሊባኖስ ከቤሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ባለፈው ዐርብ ማብራሪያ ጠይቃ፣ እስከ ዛሬ ሰኞ ምላሽ ካላገኘች የአጸፋ ርምጃ እንደምትወስድ አስጠንቅቃ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር እስካሁን ስለ ጉዳዩ ይፋዊ መረጃ አልሰጠም፡፡ የሊባኖስ ሜዲያዎች ግን የእስራዔል እጅ እንዳለበት ይጠረጥራሉ፡፡

@YeneTube @FikerAssefa