YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኢምግሬሽን፣ ዜግትና ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ ዜጎች ለፓስፖርት 45 ቀናት መጠበቅ እንዳለባቸው መግለጹን ካፒታል አስነብቧል፡፡ ኤጀንሲው ለፓስፖርት ሕትመት የውጭ ምንዛሬ ዕጥረት አለብኝ ብሏል፡፡ አመልካቾች ፓስፖርት ለማግኘት ከመንግሥት ተቋማት የድጋፍ ደብዳቤ፣ የጤንነት ሁኔታ ማረጋገጫ፣ የቪዛ ፍቃድ፣ የአስመጭና ላኪነት ማረጋገጫ የመሳሰሉ ሰነዶችን ማቅረብ አለባቸው፡፡ ለተፋጠነ አገልግሎት 2 ሺህ 182 ብር ሲጠየቅ፣ ለመደበኛው ደሞ 600 ብር ነው፡፡

-Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
በባህር ዳር ከተማ የአማራ ባንክን ለማቋቋም የሚያስችል የአክስዮን ሽያጭ ከተጀመረ ሦስት ሳምንታትን ያስቆጠረ ሲሆን፣ 200 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ አክሲዮን እንደተሸጠ ታውቋል።የባንኩ አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ መላኩ ፈንታ፣ ከአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፣ ባንኩ የሚቋቋመው የአማራን ሕዝብ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማሳደግ እና ሀገራዊ ልማትን ለመደገፍ ነው። ዝቅተኛው የአክሲዮን ሽያጭ ከ10 ሺህ ብር እንደሚጀምርና ይህም ዝቅተኛ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የሚያበረታታ ነው ብለዋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
የኤርትራ መንግሥት ከ18 ዓመት በፊት የሃገሪቱን ፕሬዝዳንት በመተቸታቸው ምክንያት ለእስር የዳረገቻቸውን 11 ፖለቲከኞችንና 17 ጋዜጠኞችን እንድትለቅ አምነስቲ ኢንትርናሽናል ጥሪ አቀረበ።

የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪው አምነስቲ እንዳለው እነዚህ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች የታሰሩት በ1994 ዓ.ም ላይ ነበር። ከዚያ በኋላም ግለሰቦቹ ላይ ይፋዊ ክስ ያልተመሰረተባቸው ሲሆን ታይተውም ሆነ ስላሉበት ሁኔታ ምንም የተሰማ ነገር የለም ብሏል።አምነስቲ የህሊና እስረኞች ያላቸውን እነዚህን ታሳሪዎች የተያዙበትን 18ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ እንዲለቀቁ ለመጠየቅ ለ18 ቀናት የሚቆይ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ መጀመሩንም ገልጿል።

አስራ አንዱ ፖለቲከኞች የታሰሩት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ምርጫ በማካሄድና ለሕግ የበላይነት በመገዛት ሕገ መንግሥቱን እንዲያከብሩ የሚጠይቅ ግልጽ ደብዳቤ በመጻፋቸው ሲሆን 17ቱ ጋዜጠኞች ደግሞ ፖለቲከኞቹ ስለጻፉት ደብዳቤ በመዘገባቸው ነው ተብሏል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
በኦሮምያ ክልል በታጣቂዎች ሰዎች መገደላቸው ተገለፀ።

በኦሮምያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን የጉሊሶ ከተማ ከንቲባ “ማንነታቸው አልታወቀም” በተባሉ ታጣቂዎች መገደላቸውን የወረዳው አስተዳደርና ፀጥታ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።በሌላ በኩል በቄለም ወለጋ ጊዳሚ ቅዳሜ ምሽት ላይ ሁለት ሰዎች “በመንግሥት ታጣቂዎች ተገድለዋል” ሲሉ አንዳንድ ነዋሪዎች ተናግረዋል።የወረዳው አስተዳዳሪ ሰዎቹ መገደላቸው እውነት እንደሆነ ገልፀው “ቀደም ሲል ግን በመንግሥት ወታደሮች ላይ በታጠቀ ኃይል ቦምብ በመወርወሩ ሰዎቹን የገደለው ማን እንደሆነ አልታወቀም” ብለዋል ሲል የዘገበው VOA ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
የአዳማ እና አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ መግቢያ ፈተና ምዝገባ ቀን ተራዘመ!!


ለኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2012 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የምዝገባ ጥሪ ስለመራዘም

የምዝገባ ጊዜ፡-

እስከ መስከረም 7 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ተረዝሟል

ምዝገባው የሚጠናቀቀው፡-

መስከረም 7 ቀን 2012 ዓ.ም ከሌሊቱ 6፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡

የምዝገባ ቦታ፡

የምዝገባ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾች በማንኛውም ስፍራ በኢንተርኔት (online) በ aastu.edu.et እንዲሁም
www.astu.edu.et ድህረ ገፅ በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ፡፡
@YeneTube @Fikerassefa
በኢትዮጵያ የቀዶ ጥገና ህክምና ከሚያስፈልጋቸው 5 ሰዎች መካከል በትክክል የሚስተናገዱት ሁለቱ ብቻ ናቸው ተባለ።

ዓለም አቀፉ የህሙማን ደህንነት ዛሬ በመከበር ላይ ሲሆን ኢትዮጵያ በአገር አቀፍ ደረጃ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሐኪሞች፣ተመራማሪዎችና አመራሮች በተገኙበት እየተከበረ ነው።በመድረኩ ላይ እንደተገለጸው የዓለም የጤና ድርጅት ባሳለፍነው ዓመት በስጠናው ጥናት መሰረት በዓመት 206 ሚሊዮን ዜጎች በህክምና ስህተት ለሞት ይዳረጋሉ።እንዲሁም ከ10 ሰዎች መካከል አንዱ በህክምና ስህተት ምክንያት ህይወቱን ያጣል ተብሏል።

እንደ ድርጅቱ ጥናት ከሆነ ህክምና ፈልገው ወደ ጤና ተቋማት ከሚመጡ ዜጎች ወስጥ 10 በመቶዎቹ በሚፈጠር የህክምና ስህተት ሳቢያ ለተጨማሪ ጉዳት ይዳረጋሉ።በኢትዮጵያ የህክምና ስህተትን አስመለክቶ የተጠና ጥናት ባይኖርም በዚህ ችግር የተጠቁ ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ እንደሚሆን ይገመታል። በየዓመቱም በኢትዮጵያ 98 ሚሊዮን ዜጎች ወደ ህከምና ተቋማት የሚሄዱ ሲሆን የህክምና ስህተቶች እንደሚበዙ ይገመታል።በኢትዮጵያ የቀዶ ጥገና ህክምና ፈልገው ወደ ሆስፒታል ከሚያቀኑ 5 ሰዎች መካከልም ትክክለኛ ህክምና አግኝተው የሚመለሱት ሁለቱ ብቻ እንደሆኑ በበዓሉ ላይ ተገልጿል። በዓለማችን በህክምና ስህተት ምክንያት በዓመት 42 ቢሊዮን ዶላር እንደሚባክን የዓለም የጤና ደርጅት መረጃ ያስረዳል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
በመዲናዋ የኤሌክትሮኒክስ ታክሲ ስምሪት አገልግሎት አሰጣጥን ለመወሰን መመሪያ ወጣ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኤሌክትሮኒክስ የታክሲ ስምሪት አገልግሎት አሰጣጥን ለመወሰን የወጣውን መመሪያ ይፋ አደረገ።የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ በመመሪያው ዙሪያ ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል።የቢሮው ሃላፊ ዶክተር ሰለሞን ኪዳኔ የኤሌክትሮኒክስ ታክሲ ስምሪት አገልግሎት አሰጣጥን ለመቆጣጠር የሚያስችል መመሪያ መውጣቱን ተናግረዋል።

በዘርፉ ለታክሲ አገልግሎት የሚሰማሩ ተሽከርካሪዎች የታርጋ ቁጥራቸውን ወደ ኮድ 1 እንዲቀይሩ እና ቀለም እንዲቀቡ ይደረጋልም ብለዋል።ከዚህ ባለፈም የታክሲ አገልግሎቱን የሚሰጡ አካላት በድርጅት መታቀፍ እንዳለባቸው በመመሪያው መቀመጡንም ገልጸዋል። ሃላፊው አያይዘውም ከዚህ ቀደም ተክልክሎ የነበረው ኮድ 1 ታርጋ ማውጣት መፈቀዱንም አንስተዋል።

ምንጭ: ፋና
@YeneTube @FikerAssefa
ባለፉት ሁለት ቀናት ፣ በሕዳሴው ግድብ ሙሌትና አተገባበር ላይ በግብጿ ካይሮ ላይ ሲመክሩ የነበሩት ሶስቱ አገሮች ውይይታቸውን መቋጨት አልቻሉም፡፡

ያልተቋጨውን ውይይታቸውን ለመቀጠል፣ ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 3/2012 ድረስ በሱዳኗ ካርቱም ተገናኝተው ለመምከር ተስማምተዋል፡፡የግብፅን የመስኖ ልማት ሚኒስቴር መግለጫ ዋቢ አድርጎ አሕራም እንደዘገበው፣ በካይሮ ትናንት እና ከትናንት በስቲያ በታላቁ የህዳሴ ግድብ የቴክኒካዊ አሰራርና የውሃ ሙሌት ቆይታ ዙሪያ ባደረጉት ውይይት መስማማት አልቻሉም፡፡የግብፅ መስኖ ልማት ሚኒስቴር እንደሚለው ከሆነ መስማማት ያልተቻለው ኢትዮጵያ፣ የግብፅና የሱዳንን አዲስ ሀሳብ አልቀበልም ስላለች ነው፡፡

“ስለዚህ” ይላል የሚኒስቴሩ መግለጫ፣ “ስለዚህ ወገንተኝነት ከሌላቸው የባለሙያዎች ቡድን ጋር በካርቱም ለሶስት ቀናት የሚቆይ ስብሰባ ማድረግ አስፈላጊ ሆኗል”በካርቱሙ ውይይት ግድቡ ስለሚሞላበት ሂደትና ስለሚቀረፁለት ህግ ግብፅ የምታቀርበው ሀሳብ ከባለሙያዎቹ ቡድን ጋር ይመከርበታል፡፡የኢትዮጵያና የሱዳንም ሀሳቦች አብረው በቡድኑ ይታያሉ ተብሏል፡፡ከገለልተኛ ኤክስፐርቶቹ ቡድን ጋር ከሚደረገው ውይይት በኋላም፣ የሶስቱ ሃገሮች የመስኖ ሚኒስትሮች በግድቡ የውሃ ሙሌት አተገባበርና ሕግ ላይ ለመምከር መስማማታቸውን የግብፅ የመስኖ ልማት ሚኒስቴር መግለጫ አመልክቷል፡፡

ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ በህዳሴው ግድብ ጉዳይ ሲመካከሩ 5 አመታት ማስቆጠራቸው ይታወሳል፡፡ባለፉት ጊዜያት ንግግራቸው የህዳሴው ግድብን ለመሙላት ኢትዮጵያ የሶስት አመታት ጊዜ ስትወሰን ግብፅ ግን በሰባት አመታት እንዲራዘም ያላትን አቋም አጥብቃ ይዛለች፡፡ወሬውን ያገኘነው ከግብፁ አሕራም ጋዜጣ ነው፡፡

Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
ጎንደር ዩንቨርስቲ!

የ2012 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች መግቢያ ቀናት እንደሚከተለው እንዲሆን ተወስኗል፦

የነባር ተማሪዎች ምዝገባ ከመስከረም 22-23/2012 ዓ.ም

እንዲሁም አዲስ ተማሪዎች ከመስከረም 28-29/2012 ዓ.ም

University of Gondar Registrar
@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ዞን ጎሮ ጎቱ ወረዳ በደረሰ የመኪና አደጋ የ10 ሰዎች ህይወት አለፈ።

ከጅግጅጋ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ አይሱዙ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ጎሮ ጎቱ ወረዳ ሰርገኞች ላይ ባደረሰው የግጭት አደጋ የ10 ሰዎች ህይወት አልፏል።

የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር ስዩም ደገፋ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ አደጋው የደረሰው ትናንት ምሽት 4 ስዓት አካባቢ ሰርገኞች ከሙሽራው ቤት ወደ ሙሽሪት ቤት እያመሩ ባሉበት ወቅት ነው።

በተከሰተው አደጋ የ10 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን፥ በ5 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ እና ቀላል ጉዳት መድረሱን ኮማንደር ስዩም ተናግረዋል።
አደጋውን አድርሶ ያመለጠው ተሽከርካሪም በፖሊስ እየተፈለገ መሆኑ ነው የተገለጸው።

Via:- FBC
@YeneTube @Fikerassefa
እርዳታ / HELP

#ETHIOPIA | ለወጣቱ አቀንቃኝ እርዳታ ተጠየቀ

አርቲስት ሙሉአለም ታከለ "ሐመልማሎ" በተለይም ከኤፍሬም አማረ ጋር "ተሸንፊያለሁ" በሚለው ሥራው በስፋት ይታወቃል።

ሙሌ በደረሰበት የኩላሊት ህመም ዲያለሲስ እንዲያደርግ በሐኪሞች ተነግሮታል።

ከጸሎት ጀምሮ ሁላችንም በምንችለው አቅም ከአርቲስቱ ጎን በመሆን እንርዳው.. [ ጓደኞቹ ]

+251 91 046 0881 ~ [ አስታማሚ : የሺእመቤት ታከለ እህቱ ]

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
Mulualem Takele
የቁጠባ ሂሳብ ቁጥር ~ 1000182044184
Forwarded from YeneTube
There’s a lot to explore around you. Download Ahun, get the best out of your city!

Now available on the Play Store and App Store!!
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.ahun.android


https://apps.apple.com/ke/app/ahun/id1474285014


Join us on telegram

—- https://tttttt.me/Ahun_appc

Follow us on Instagram

https://instagram.com/ahun.app?igshid=ab6oe4ob8485
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በቢሾፍቱ የአባገዳዎች ህብረት ማዕከል ተገኝተዋል፡፡በስፍራው ሲደርሱ የከተማዋ ከንቲባ፣ ነዋሪዎችና አባገዳዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

Via OBN
@YeneTube @FikerAssefa
የቀድሞው የመከላከያ ሠራዊት አመራር የነበሩት እና ከሠራዊቱ ኮብልለው በኤርትራ የኦነግ ሠራዊትን ተቀላቅለው በምህረት ወደ አገር ውስጥ የገቡት ኮለኔል ገመቹ አያናን ጨምሮ ሌሎች 20 ግለሰቦች ከሰኔ 2010 ጀምሮ በግዳጅ ላይ የነበሩ 40 የኦሮሚያ ፖሊስ አባላትን እና 35 የክልሉን ፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ሕይወት እንዲጠፋ ማድረግን ጨምሮ በተለያዩ የሽብር ወንጀሎች ተጠርጥረው ክስ ተመሰረተባቸው።

Via:- AddisMaleda
@Yenetube @Fikerassefa
በአፍሪካ የድህረ ምርት ብክነትን ለመቀነስ የሚደረገው ጥረት የግሉን ዘርፍ ማሳተፍ እንዳለበት ተጠቆመ

በአፍሪካ የምግብ ዋስትና መረጋገጥ ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ጫና እያሳደረ ያለውን የድህረ ምርት ብክነትን ለመቀነስ የሚደረገው ጥረትና ምርምር የግሉን ዘርፍ ማሳተፍ እንዳለበት ተጠቆመ።

ሁሉንም የዘርፉን ባለድርሻ አካላት በጋራ የሚያገናኘው ሁለተኛው የአፍሪካ የድህረ ምርት ኮንግረስና እና ኤግዚቢሽን ዛሬ በአፍሪካ ህብረት በይፋ ተከፍቷል።

ለ3 ቀናት የሚካሄደው መድረክ ሀገራት በድህረ ምርት ብክነት ላይ ትኩረት ያደረጉ ውጤታማ ፓሊሲዎችን፣ ስትራቴጂዎችን፣ ቴክኖሎጂዎችን እና ተሞክሮዎችን በመጋራት ችግሩን በጋራ ለመቅረፍ የሚያስችላቸውን ግንኙነትን ለመፍጠር ያለመ ነው።

በዓለም አቀፍ ደረጃ 1.3 ቢሊዮን ሜትሪክ ቶን ወይም የሰው ልጆች በዓመት ከሚጠቀሙት 30 በመቶ የሚሆንና 1.6 ቢሊዮን ሰዎችን ሊመግብ የሚችል ምርት እንደሚባክን መረጃዎች ያሳያሉ።
በአፍሪካ ደረጃ በዓመት 100 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ምርት ለብክነት የተጋለጠ ሲሆን በኢትዮጵያ ደግሞ የብክነት መጠኑ ከ15-20 በመቶ እንደሚደርስ መረጃዎች ያመለክታሉ።

Via:- FBC
@YeneTube @Fikerassefa
ከስድስት ወራት በፊት በብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት ክትትል የአልቃይዳ የምስራቅ አፍሪቃ ክንፍ ብሎ ራሱን የሚጠራውን የአልሸባብን ዓላማ ለማሳካት በአዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ 10 ቦታዎች የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ዝግጀት ሲያደርጉ ነበር የተባሉት አዲሃመን አብዶ ክስ ተመሰረተባቸው።

ግለሰቡ በኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ታንዛኒያ እና ኢትዮጵያ ላይ በተመሳሳይ ወቅት በተነጣጠሩ ጥቃቶች ላይ የአዲስ አበባ ጥቃት ለማቀናጀት የቦታ መረጣ እንዲያከናውኑ ተመልምለው ነበር ሲል ዓቃቤ ህግ ክሱን መስርቷል።

Via:- AddisMaleda
@Yenetube @Fikerassefa
ኢትዮጵያና ግብጽ በካይሮው የሦስትዮሽ ውይይት ሳይስማሙ እንደተለያዩ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ቀጣዩን ስብሰባም ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 3 ከገለልተኞቹ የባለሙያዎች ቡድን ጋር በካርቱም ለማድረግ ወስነዋል፡፡ ግድቡ በ3 ዐመታት ውሃ ሙሌቱ ይጠናቀቅ የሚለውን የኢትዮጵያ ሃሳብ ግብጽ አልተቀበለችም፡፡ ኢትዮጵያም የግብጽን ሃሳብ ኢፍትሃዊ በማለት በሰነዱ ላይ ሳትወያይበት ቀርታለች፡፡ ግብጽ ትናንት ባወጣችው መግለጫ ኢትዮጵያ በካርቱሙ ስብሰባ ልዩ ትኩረት ሰጥታ እንድትወያይ ጠይቋል፡፡

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
#ዲላ_ዩንቨርስቲ

ለነባር ተማሪዎች ምዝገባ ቀን መስከረም 21 እና 22 በቅጣት መስከረም 23 ብቻ መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሰው ቀን ወደ ዩንቨርስቲው እንድትገኙ ገልጷል።

አዲስ ተማሪዎች ምዝገባ ቀን መስከረም 26 እና 27 በቅጣት መስከረም 28 ብቻ መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሰው ቀን ወደ ዩንቨርስቲው እንድትገቡ አሳስቧል።

@YeneTube @Fikerassefa
#ዲላ_ዩንቨርስቲ

ለነባር ተማሪዎች ምዝገባ ቀን መስከረም 21 እና 22 በቅጣት መስከረም 23 ብቻ መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሰው ቀን ወደ ዩንቨርስቲው እንድትገኙ ገልጷል።

አዲስ ተማሪዎች ምዝገባ ቀን መስከረም 26 እና 27 በቅጣት መስከረም 28 ብቻ መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሰው ቀን ወደ ዩንቨርስቲው እንድትገቡ አሳስቧል።

@YeneTube @Fikerassefa