YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ነገ የሚከበረውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በዕለቱ ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ላይ 21 ጊዜ መድፍ የሚተኮስ መሆኑን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ለመላው የሃገራችን ህዝቦች!
እንኳን ለ-2012 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን!!

በአሮጌው ዓመት ከድህነት የሚመነጩ እና ወደፊት የማያራምዱ እኩይ አስተሳሰቦች አራግፈን መሻገር ይኖርብናል።በዓዲሱ ዘመን በሃገራችን የታላቅነት ጉዞ ብስራት የሚታወጅበት እና የብልጽግና መሰረት በጋራ የምንጥልበት ይሆናል።

"ማቅ አውልቀን ~ ግምጃ እንልበስ!" በሚል ቅን እሳቤ ለስኬቱ እጅ ለእጅ ተያይዘን እንድንረባረብ አደራ አላለሁ። ዘመኑ ለሁላችንም የሰላም፥ የስራ፥ የአንድነት፥ የትብብር እና የብልጽግና እንዲሆንልን ከልብ እመኛለሁ።


ምክትል ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን
@YeneTube @FikerAssefa
የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ- መስተዳድር አቶ #ሙስጠፋ_መሐመድ በብሔራዊ ቤተ-መንግስት እየተካሄደ ባለው የአዲስ ዓመት ዋዜማ ዝግጅት ላይ ከተናገሩት የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች፡-

📌 በዚህች አገር ብሔራዊ መግባባትና አንድነት እንዳይመጣ እያደረጉ ካሉ ነገሮች አንዱ በታሪክ ዙሪያ ያለው ውዝግብ ነው፤ በሀይማኖቶቻችን፣ በባሕሎቻችን፣ ወዘተ ዙሪያ በመካከላችን መቻቻል፣ መግባባት አለ፤ በታሪካችን ዙሪያ ግን ይህ የለም፤ በታሪክ ላይ መነታረክ አስፈላጊ አይደለም፤ አብሮ ለመኖር በታሪክ መስማማት የግድ አይደለም፤ ብዙ ጊዜ ማጥፋት ያለብን ወደፊት በማየት የተሻለች ኢትዮጵያን መፍጠር ላይ ነው፤ መለኪያ መሆን ያለበት ከሚመስሉን ሳይሆን ከማይመስሉን ሰዎች ጋር አብሮ መኖር መቻል ነው፤ አንድ መሆን ከመበታተን አይሻልም? መፋቀርስ ከመጣላት አይሻልም?

📌 ሌላው የወቅቱ የአገራችን ችግር የፖለቲካ ጨዋነት መጥፋት ነው፤ ሕግ ብቻ ዲሞክራሲን ለማስፈን በቂ አይደለም፤ ሕግ ስለማይከለክለን ብቻ አንድን ተገቢ ያልሆነ ነገር ማድረግ የለብንም፤ ልክ ሕግ ስለማያይ፣ ስለማይጠይቀን ብቻ ዝሙትን፣ ስርቆትን፣ ወዘተ መፈፀም እንደማይገባን ሁሉ ማለት ነው፡፡

📌 ሌላው ችግር በተናጠል ችግሮቻችንን ለመፍታት የምንሄድበት መንገድ ነው፤ ችግሮቻችንን ለመፍታት መንቀሳቀስ ያለብን በተናጠል ሳይሆን በጋራ ነው፡፡

📌 እንደ ሀገር የተጠቀሱትን ክፍተቶቻችንን መድፈን ከቻልን የተጋረጠብንን ችግር መሻገር አይሳነንም፤ ለዚህም ባለፈው ዓመት መደላድሎችን ስንፈጥር ቆይተናል፤ መጪው ዓመት ደግሞ የተሻለ ይሆናል የሚል እምነት አለኝ፡፡

ምንጭ:EBC
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ ቀስ በቀስ የውጭ ምንዛሪ ግብይትን በገበያው ፍላጎት መሠረት እንዲከወን የማድረግ ፍላጎት እንዳላት የብሔራዊ ባንክ ገዢ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) ጥቆማ ሰጥተዋል።

በዝግታ በአቅርቦት እና በፍላጎት ወደሚከወን የውጭ ምንዛሪ ግብይት መሸጋገር እንደሚያስፈልግ የገለጹት የብሔራዊ ባንክ ገዢ «ሽግግሩ የሚኖሩትን ጠቀሜታዎች እና ፈተናዎች መመልከት አለብን። በመጪዎቹ ሶስት አመታት የውጪ ምንዛሪ ግብይት ሥርዓቱን ላላ ማድረግ እንፈልጋለን» ሲሉ በአፍሪካ ላይ ያተኮረው የዓለም የኤኮኖሚ ፎረም በደቡብ አፍሪካ ባለፈው ሳምንት ሲካሔድ ለሬውተርስ ተናግረዋል።

ምንጭ:DW
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዋዜማ ምሽት መርሃ ግብር እያከናወነ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዋዜማ ምሽት መርሃ ግብር እያከናወነ ነው፡፡
በምሽት መርሃ ግብሩ ሃገራዊ አንድነትና ፍቅርን የሚጠናክሩ የተስፋ መልዕክቶች ይተላለፋሉ፡፡የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በዝግጅቱ ተገኝተው ልዩ የበአል የመልካም ምኞት መልዕክት ያስተላልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተለይም ከተማ አስተዳደሩ በክረምት የበጎ አድርጎት መረሃ ግብር በትምህርት፣ በጤናና በአቅመ ደካሞች ቤት መጠገን ስራ ሙሉ ጊዜና ገንዘባቸውን ለሰጡ አካላት የምስጋና ፕሮግራም ይካሄዳል፡፡በምሽቱ የዋዜማ ዝግጅት ለአዲሱ አመት ስጦታ ከቻይና መንግስት የተበረከተው ርችት አምባሳደር አካባቢ እየተገነባ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ግዙፍ ህንፃ ላይ ይተኮሳል፡፡በዚህም ህብረተሰቡ በርችቱ ድምፅ እንዳይደናገጥ ከተማ አስተዳደሩ አስገንዝቧል፡፡

ምንጭ: ዋልታ
@YeneTube @FikerAssefa
መልካም አዲስ ዓመት!🌻🌻🌻🌻
Ayyaana Qaammee Garii! 🌻🌻
Sannad Wacan! 🌻🌻🌻🌻🌻
ርሑስ ሓድሽ ዓመት! 🌻🌻🌻🌻🌻
Happy New Year!🌻🌻🌻🌻🌻
.
.
.
.
ይሄንን ለሁሉም ያካፍሉ!!
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
መልካም አዲስ ዓመት!🌻🌻🌻🌻
Ayyaana Qaammee Garii! 🌻🌻
Sannad Wacan! 🌻🌻🌻🌻🌻
ርሑስ ሓድሽ ዓመት! 🌻🌻🌻🌻🌻
Happy New Year!🌻🌻🌻🌻🌻
.
.
.
.
ይሄንን ለሁሉም ያካፍሉ!!
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
HAPPY NEW YEAR!
RJ SHOES presents to you all the latest,variety and catchy brand shoes.
We have all kind of shoes for adults and kids with a fairly affordable price.
👉Adress:-Addis ababa(Gerji mebrat haile)
👉Phone:-+251900628132
:-+251911859997
👉We have a 2 days return policy.
👉Flexible Shoe order with Customers Desire.
👉Delivery to Regional distincts
👉We Are Trustworthy and Best suited for Customers wish.
To Join us on telegram click here👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAE3CCBtJE8NBy8ZShA
Forwarded from YeneTube
የሴቶች አልባሣት እና ኮስሞቲክስ ማዘዝ ምትፈልጉ ገፃችን ላይ ያገኛሉ ከታች ባለው ሊንክ መርጠው ይላኩልን

የአውሮፓ ስታዳርድ
Imported from England
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFW3ZmuRfJiwNyWX7g
Forwarded from YeneTube
ማስታወቂያ⬆️ ጤናማ በሆነ መልኩ ከበቂ የባለሙያ ምክር ጋር የሰውነት ክብደትዎን ለመቆጣጠር እንዲሁም ቦርጮን ለማጥፋት በአማራጭ ያሉ የሰውነት ክብደት መቀነሻዎችን ይጠቀሙ።
@ABENIFAB
+251912690194 @ETHIOAMAZON2
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፈረንጆች December 16, 2019 ጀምሮ ወደ ሂውስተን ቴክሳስ በሳምንት 3 ጊዜ በረራ ለማድረግ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ እንደሆነ አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
"በመላው ዓለም ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ መልካም አዲስ ዓመት እንዲሆንልን እመኛለሁ:: አዲሱ ዘመን 2012 ለሀገራችን ሰላምና ብልጽግና በጋራ የምንተጋበት ይሁን::"

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ
@YeneTube @FikerAssefa
በሌላ ፕላኔት ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ውሃ ተገኘ።

የሥነ ህዋ ተመራማሪዎች በአንዲት ፕላኔት ላይ ውሃ ለመጀመሪያ ጊዜ ማግኘታቸውን ይፋ አድርገዋል።ግኝቱን በበላይነት የመሩት ተመራማሪ ፕሮፌሰር ጂኦቫንያ ቲኔቲ፤ K2-18b የተባለችው ፕላኔት ላይ ውሃ የመታየቱን ዜና "እጅግ ድንቅ" ብለውታል።

"በፕላኔት ላይ ውሃ ስናገኝ ይህ የመጀመሪያው ነው። ሙቀቱም የሰው ልጅ ሊኖርበት ከሚችለው የሙቀት መጠን ጋር የሚመጣጠን ነው" ብለዋል። K2-18b የተባለው ፕላኔት ከመሬት 650 ሚሊየን ማይል ይርቃል።ከመሬት ሥርዓተ ጸሐይ ውጪ ያሉ ፕላኔቶች ኤክሶፕላኔት ይባላሉ።እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ2020 ይሠራል ተብሎ በሚጠበቅ ቴሌስኮፕ፤ ፕላኔቷ ላይ ሕይወት ባላቸው ነገሮች የሚወጣ አየር ስለመኖሩ እንደሚፈተሽ ተመራማሪዎች ገልጸዋል።

"በህዋ ውስጥ ያለነው የሰው ልጆች ብቻ ነን? የሚለው በሳይንስ ውስጥ ካሉ ጥያቄዎች ዋነኛው ነው" ሲሉ ፕሮፌሰር ጂኦቫንያ ተናግረዋል።የምርምር ቡድኑ ግኝቱ ላይ የደረሰው እንደ ጎርጎሮሳውያኑ ከ2016 እስከ 2017 በሚገኙት ወራት በተደረገ ጥናት ነው። ከK2-18b ክፍል 50 በመቶው በውሀ የተሸፈነ እንደሆነ የሚታመን ሲሆን፤ ምናልባትም ለሰው ልጆች ምቹ መኖሪያ ልትሆን እንደምትችል መላ ምቶች አሉ።ፕላኔቷ ከመሬት ሁለት እጥፍ የምትበልጥም ናት ተብሏል።

ምንጭ፡- ቢቢሲ/ኢቢሲ
@YeneTube @FikerAssefa
ትናንት ምሽት የአዲስ አመት ዋዜማ በባህር ዳር እንዲህ በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል።

Via Nahi/YeneTube
@YeneTube @FikerAssefa