YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
መከላከያ ሰራዊት የአይ ኤስ አባላትን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለፀ።

የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሰሞኑን የተወሰኑ የአይኤስ አባላትን በቁጥጥር ስር ማዋሉንና ያልተያዙትም በጥብቅ ክትትል ውስጥ መሆናቸውን የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹምና የዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ጀነራል ብርሀኑ ጁላ አስታወቁ፡፡ሰራዊቱ በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት ሀገርና ሕዝብን ከአደጋ ለመጠበቅ እየሰራ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

ጀነራሉ እንዳስታወቁት፤ አይ ኤስ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ለመንቀሳቀስ በተደጋጋሚ ጥረት አድርጎ ቢመክንበትም በአገሪቱ ከተለያዩ አካባቢዎች የመለመላቸው፣ ስልጠና የወሰዱና የተጠመቁ ሰዎች እንዳሉ መንግስት በሚገባ እንደሚያውቅ ተናግረዋል፡፡

‹‹በአሁኑ ወቅት የአይኤስ አባላት ምን እያደረጉ እንዳሉ፣ የት የት ቦታ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኙ፣ ከእነማን ጋር ግንኙነት እንዳላቸው፣ በከተሞች ውስጥ ያሉት ሰዎቻቸው እነማን እንደሆኑ፣ ምን እየሰሩ እንዳሉ፣ እቅዳቸው ምን እንደሆነና ሌሎች መግለጽ የማያስፈልጉ ጉዳዮችም እጅግ ከፍተኛ ክትትል እየተደረገባቸው ነው››ብለዋል ጀነራሉ፡፡

‹‹ሀገራችንንና ሕዝባችንን ከየትኛውም አደጋ ለመጠበቅና ለመከላከል ባለብን አደራና ከባድ ኃላፊነት የተነሳ ቀን ከሌት አንተኛም›› ያሉት ምክትል ጠቅላይ ኢታማጆሩ፤ ‹‹ሰራዊቱ እረፍት የሚባል ነገር አያውቅም፤ ያረፍንበት ጊዜም የለም›› ሲሉ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

እንደ ጀነራሉ ማብራሪያ፤ አንዳንድ ጊዜ የሆነ ሰው እንደተገኘ ሄዶ መያዝና መቆጣጠር ተገቢ አይደለም፤ ምክንያቱም ለአንድ ሰው ተብሎ ብዙ ነገር እንዳይታጣና እንዳያመልጥ በማድረግ በጥንቃቄና በሕግ አግባብ መቆጣጠር ስለሚቻል ሁኔታው አስቸጋሪ አይሆንም፡፡

አይ ኤስ ኢትዮጵያ ገብቻለሁ የሚለው በሕዝቡ ውስጥ ሽብር ለመልቀቅ በማሰብ የተጠቀመበት የሥነልቦና ጦርነት (ሳይኮሎጂካል ዋርፌር) ነው ያሉት ጀነራሉ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ በዚህ የሚፈራና የሚደናገጥ አይደለም፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ገብቶ የአይ ኤስ ኦፕሬሽን አካሂዳለሁ የሚል አቅም እንደሌለው ገልፀዋል፡፡

ምንጭ:የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
@YeneTube @FikerAssefa
ዩንቨርስቲ መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ‼️

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የ2012 የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ወይም ማለፊያ ነጥብን ይፋ አደረገ። የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን እንዳስታወቁት የ2012 የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ወይም ማለፊያ ነጥብ:

1.Social Science ሴቶች መግቢያ ውጤት 164

2. Social Science ወንዶች መውጤት ውጤት 174

3. Natural Science ወንዶች መግቢያ ውጤት 176

4.Natural Science ሴቶች መግቢያ ውጤት 166

5. ለግል ተፈታኞች ለወንዶች 190 እና ከዚያ በላይ

6. ለግል ተፈታኞች ሴቶች 185 እና ከዚያ በላይ

7. ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ክልሎች ናቹራል ወንዶች 166

8. ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ክልሎች ናቹራል ሴቶች 156 እና ከዚያ በላይ

9. ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ማህበራዊ ሳይንስ ወንዶች 164 እና ከዚያ በላይ ሴቶች ደግሞ 154 እና ከዚያ በላይ መሆኑ ተገልጿል።


መስማት ለተሳናቸው በተፈጥሮ ሳይንስ ወንዶች 120 እና ከዚያ በላይ ለሴቶች 115 እና ከዚያ በላይ ሲሆን ማየት ለተሳናቸው ለማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ወንዶች 110 እና ከዚያ በላይ ሴቶች ደግሞ 105 እና ከዚያ በላይ እንዲሁም

በመንግስት እና በግል ተቋማት በግላቸው ከፍለው ለሚማሩ ተፈታኞች በሁለቱም መስክና ጾታ 140 እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተፈታኞች መማር ይችላሉ ተብሏል።


Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ዩንቨርስቲ መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ‼️

#መስማት_ለተሳናቸው በተፈጥሮ ሳይንስ ወንዶች 120 እና ከዚያ በላይ ለሴቶች 115 እና ከዚያ በላይ ሲሆን ማየት ለተሳናቸው ለማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ወንዶች 110 እና ከዚያ በላይ ሴቶች ደግሞ 105 እና ከዚያ በላይ

እንዲሁም በመንግስት እና በግል ተቋማት በግላቸው ከፍለው ለሚማሩ ተፈታኞች በሁለቱም መስክና ጾታ #140 እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተፈታኞች መማር ይችላሉ ተብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
ዩንቨርስቲ መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ‼️

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የ2012 የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ወይም ማለፊያ ነጥብን ይፋ አደረገ። የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን እንዳስታወቁት የ2012 የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ወይም ማለፊያ ነጥብ:

1.Social Science ሴቶች መግቢያ ውጤት 164

2. Social Science ወንዶች መውጤት ውጤት 174

3. Natural Science ወንዶች መግቢያ ውጤት 176

4.Natural Science ሴቶች መግቢያ ውጤት 166

5. ለግል ተፈታኞች ለወንዶች 190 እና ከዚያ በላይ

6. ለግል ተፈታኞች ሴቶች 185 እና ከዚያ በላይ

7. ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ክልሎች ናቹራል ወንዶች 166

8. ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ክልሎች ናቹራል ሴቶች 156 እና ከዚያ በላይ

9. ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ማህበራዊ ሳይንስ ወንዶች 164 እና ከዚያ በላይ ሴቶች ደግሞ 154 እና ከዚያ በላይ መሆኑ ተገልጿል።


መስማት ለተሳናቸው በተፈጥሮ ሳይንስ ወንዶች 120 እና ከዚያ በላይ ለሴቶች 115 እና ከዚያ በላይ ሲሆን ማየት ለተሳናቸው ለማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ወንዶች 110 እና ከዚያ በላይ ሴቶች ደግሞ 105 እና ከዚያ በላይ እንዲሁም

በመንግስት እና በግል ተቋማት በግላቸው ከፍለው ለሚማሩ ተፈታኞች በሁለቱም መስክና ጾታ 140 እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተፈታኞች መማር ይችላሉ ተብሏል።


Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በ24 ክለቦች መካከል እንዲካሄድ ተወሰነ!

👉የኢትዮጵያ ኘሪምየር ሊግ ተብሎ ከተሰየመበት ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ በአንድ ምድብ ተዟዙሮ በሜዳ እና ከሜዳ ውጪ በሚደረግ የደርሶ መልስ ውድድሮችሲካሄዱ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡ይህም በመሆኑ በሀገሪቱኘሪሚየር ሊጉ ይካሄዱባቸው በነበሩ ከተሞች እና አካባቢዎች ከፍተኛ መነቃቃትን ፈጥሮ ቆይቷል፡፡

👉ይህ በእንዲህ እንዳለ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተለያዩ የውድድርሜዳዎች ላይ ከፍተኛ
የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል እየታዩ መምጣታቸው የተለመደ እየሆነ መጥቷል፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው በየአካባቢው የሚንፀባረቁ የፓለቲካ አጀንዳዎች ወደ ውድድር ሜዳ በመምጣታቸው መሆኑ የማይደበቅ ሀቅ ነው፡፡

በመሆኑም ይህንን ችግር መቀነስ ላይ መስራት አስፈላጊ በመሆኑ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ጶጉሜ 1 ቀን 2011 ዓ.ምባደረገው ስብሰባ በ2012 ዓ.ም የኘሪሚየር ሊግ አካሄድ ላይ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ ውድድሮች መካሄድ ያለበትን አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

👉በዚሁ መሠት በ2012ዓ.ም የኢትዮጵያ ኘሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች፡-

1. በ2011ዓ.ም የኘሪሚየር ሊግ ተሳታፊ የነበሩ 16ቱም ክለቦች

2. በ2011ዓ.ም ከሱፐር ሊግ ውድድር ወደ
ኘሪሚየር ሊግ ያለፉ3 ክለቦች

3. በ2011ዓ.ም ከሱፐር ሊግ ውድድር
ከየምድባቸው 2ኛ የወጡ 3 ክለቦች

4. በ2011ዓ.ም በሱፐር ሊግ ከ3ቱም ምድብ 3ኛ ከወጡት የተሻለ ነጥብ ያላቸው 2 ክለቦች ሲሆኑ ቁጥራቸውን ሀያ አራት (24) በማድረግ
በሁለት ምድብ ተከፍለው እንዲጫወቱ
ተወስኗል፡፡

👉 የምድብ አደላደሉም በሊግ ኮሚቴ
አማካኝነት ለክለቦቹ የሚቀርብ ይሆናል፡:

© ሶከር ኢትዮጵያ
@YeneTube @FikerAssefa
የጎንደር ጉምሩክ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎችን ያዘ።

የጎንደር ጉምሩክ መቅረጫ ጣቢያ ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዙን አስታወቀ፡፡የጣቢያው የኢንተለጀንስና ኮንትሮባንድ መከላከል ቡድን አስተባባሪ አቶ ታፈሰ መንግስቱ ለኢዜአ እንዳሉት ባለፈው ሳምንት የተያዙት እቃዎቹ ከጎረቤት አገር የገቡና በሁለት አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪዎች በድብቅ ሲጓጓዙ የተገኙ ናቸው።

ምንጭ:ETV
@YeneTube FikerAssefa
የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝብ በየአካባቢው የተደራጁ «የጎበዝ አለቆችን» እንዳይከተል አዲሱ የክልሉ ምክትል ርዕሠ መስተዳድር ርስቱ ይርዳዉ አሳሰቡ።

አቶ ርስቱ ከተለያዩ የደቡብ ኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ክፍሎች ለተወከሉ ተሰብሳቢዎች ትናንት እንደተናገሩት «በለዉጡ የተገኙ ድሎች» ያሏቸዉን ጥቅሞች ሕዝቡ በየአካባቢዉ ለተደራጁ ኃይላትና «የጎበዝ አለቃ» ላሏቸዉ ወገኖች አሳልፎ መስጠት የለበትም። በደቡብ ኢትዮጵያ በተለያየ ስም የተደራጁ ኃይላት በተለይም ወጣቶች ባገባደድነዉ ዓመት በቀሰቀሱት የጎሳ ግጭት በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል፣ ሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ ተፈናቅሏል፣ በቢሊዮን የሚገመት ሐብት ንብረት ወድሟልም።

በተለይ የሲዳማ ዞን የክልል መስተዳድርነት ሥልጣን ይኑረዉ በሚል ጥያቄ ሰበብ ባለፈዉ ኃምሌ አጋማሽ በተቀሰቀሰዉ ግጭትና ሁከት በትንሽ ግምት ከ50 በላይ ሰዎች ተገድለዋል፣ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ቆስለዋል፣ ግምቱ በዉል ያልታወቀ ሐብትና ንብረት ወድሟል ወይምተዘርፏል።ሁከት፣ግጭት ረብሻዉ የበረደዉ መከላከያ ሰራዊት ጣልቃ ከገባ በኋላ ነዉ።ምክትል ርዕሠ መስተዳድር ርስቱ እንደሚሉት «የህዝብ ተቆርቆሪ» መስለው በየቦታው የሚንቀሳቀሱ አካላት ለዘመናት አብሮ የኖረውን ህዝብ ችግር ውስጥ እያስገቡት ፣ መልካም ስሙንም እያጠለሹት ነዉ።

» አቶ ርስቱ «ሌብነታቸው» እንዳይታወቅባቸዉ በጎሳና በብሄር ስም የተሸሽጉ ወንጀለኞች» ያሏቸዉን ኃይላት ሕዝቡ ለመንግስት አሳልፎ እንዲሰጥም አደራ ብለዋል።የሐዋሳዉ ወኪላችን ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ እንደጠቀሰዉ በክልሉ ሰላም ካልሰፈነ የክልልና የዞን አደረጃጀት መጠየቅ ቀርቶ በሕይወት መኖርም አይቻልም-እንደ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
Dear all Axum University Mechanical, Textile and Civil Engineering interns of of 2011 E.C., the campus entry date for you is 12/01/2012 E.C.

Therefore, on moday 12/01/2012 E.C every intern student who left campus in the second semester of 2011 E.C. should be available in campus and report to his/her department.

Via Sitotaw/YeneTube
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት የ2012 ዓ.ም. መማር ማስተማርና የተማሪዎች ቅበላ ዝግጅትን አስመልክቶ ውይይት አደረገ።

ዶክተር ፋሲል ንጉሴ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ዲን ከ 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ለሚገቡ አዲስ ተማሪዎች በ 4 ዓመት ቆይታ ጊዜአቸው ተማሪዎቹን መሰረታዊ እውቀት ሊያስጨብጧቸው የሚችሉ የትምህርት ዓይነቶች እንደሚሰጡና ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደትን ለማረጋገጥ የሚያስችል በቂ የዝግጅት ምዕራፍ እንደተወጠነ ገልጸዋል፡፡

“ለሰላም መደፍረስ መነሻ የሚሆኑ ጉዳዮችን እየለየን ከሚመለከታቸው ጋር በማቀናጀት መፍትሔ እንዲያገኙ እንጥራለን፤የመማር ማስተማር ሂደቱ መስመሩን ጠብቆ እንዲሄድ የቁጥጥር ሥርአቶችን አጠናክረን እንቀጥላለን ፤ብሔርን፣ሀይማኖትንና ፖለቲካን መሰረት ያላደረጉ የዶርም ድልድሎችን እናደርጋለን” በማለት ዶ/ር ፋሲል በ 2012 ዓ.ም. ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደትን ለማረጋገጥ የምንከተላቸው አቅጣጫዎች በሚል ርእስ ባቀረቡት ፕረዘንቴሽን ላይ ጠቁመዋል፡፡

ምንጭ: አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
HAPPY NEW YEAR!
RJ SHOES presents to you all the latest,variety and catchy brand shoes.
We have all kind of shoes for adults and kids with a fairly affordable price.
👉Adress:-Addis ababa(Gerji mebrat haile)
👉Phone:-+251900628132
:-+251911859997
👉We have a 2 days return policy.
👉Flexible Shoe order with Customers Desire.
👉Delivery to Regional distincts
👉We Are Trustworthy and Best suited for Customers wish.
To Join us on telegram click here👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAE3CCBtJE8NBy8ZShA
Forwarded from YeneTube
የሴቶች አልባሣት እና ኮስሞቲክስ ማዘዝ ምትፈልጉ ገፃችን ላይ ያገኛሉ ከታች ባለው ሊንክ መርጠው ይላኩልን

የአውሮፓ ስታዳርድ
Imported from England
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFW3ZmuRfJiwNyWX7g
Forwarded from YeneTube
ማስታወቂያ⬆️ ጤናማ በሆነ መልኩ ከበቂ የባለሙያ ምክር ጋር የሰውነት ክብደትዎን ለመቆጣጠር እንዲሁም ቦርጮን ለማጥፋት በአማራጭ ያሉ የሰውነት ክብደት መቀነሻዎችን ይጠቀሙ።
@ABENIFAB
+251912690194 @ETHIOAMAZON2
በምዕራብና በደቡብ ኦሮሚያ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች አሁንም እንዳሉ ተገለጸ።

በኦሮሚያ ክልል በምዕራብና በደቡብ ዞኖች አካባቢዎች እስካሁን ታጣቂዎች እንዳሉና እየተንቀሳቀሱ ጥቃት እንደሚፈጽሙ፣ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ፡፡ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ይኼንን ያሉት ቅዳሜ ጳጉሜን 2 ቀን 2011 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡

በ2011 ዓ.ም. የዴሞክራሲ ምኅዳሩን ለማስፋትና አዲስ የፖለቲካ ባህል እንዲመጣ በማለም ከተለያዩ የፖለቲካ ቡድኖች ጋር በመመካከር ለውጥ ማምጣት ቢቻልም፣ በተለይ በአቶ ዳውድ ኢብሳ ከሚመራው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ቡድን ጋር ዕርቅ ለማድረግ ተሞክሮ በሒደቱ ግን አሳዛኝ ክስተቶች ተፈጥረው ነበር ሲሉ አቶ ሽመልስ አስረድተዋል፡፡

ከአስመራ የመጣው የኦነግ ጦር ቀጥታ ወደ ካምፕ ቢገባም፣ በደቡብና በምዕራብ ኦሮሚያ ያለው እንቢ በማለቱ አሳዛኝ ጥፋቶች መከሰታቸውን አውስተዋል፡፡ሆኖም እንቢ ያለውን ቡድን እነ አቶ ዳውድ ‹‹የእኛ አይደለም ሽፍታ ነው›› በማለታቸው በተወሰደ የሕግና የሰላም ማስከበር ሥራ፣ አካባቢዎቹ ወደ ቀድሞ እንቅስቃሴ መመለሳቸውንና የጦርነት ሥጋት እንደሌለባቸው ገልጸዋል፡፡ ሁሉም የአካባቢዎቹ መንገዶች ተከፍተው እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን በመግለጽም፣ አሁን እየተንቀሳቀሱ ጥቃት ከሚፈጽሙ ታጣቂ ቡድኖች ውጪ የጎላ ሥጋት የሚያደርስ ቡድን የለም ብለዋል፡፡

ከለውጡ ቀደም ብሎ በክልሉ ከፍተኛ ሕገወጥነት ይስተዋል እንደነበረ በመግለጽ፣ በተከናወነው የሕግና የፀጥታ ማስከበር ሥራ ሕገወጥነትን መከላከል መቻሉንና ወንጀል ቀንሶ ከፍተኛ መረጋጋት በክልሉ እንደመጣም ጠቁመዋል፡፡በቅርቡ የአቶ ዳውድ ኦነግ በትጥቅ ትግል ላይ ያለ ማንኛውም ቡድን የእኛ ወገን አይደለም በማለት ከታጠቁት ጋር ራሱን መለየቱን፣ እንዲሁም በምዕራብ ኦሮሚያ ከሚንቀሳቀሰው የጃል መሮ ቡድን ከኦነግ ጋር በይፋ መለያየቱን አስታውቀው ነበር፡፡ ምዕራብ ኦሮሚያና ቤንሻንጉል ጉሙዝ አዋሳኝ አካባቢዎች አሁንም በኮማንድ ፖስት ከሚተዳደሩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ምንጭ: ሪፖርተር
@YeneTube @FikerAssefa
በ2012 በጀት ዓመት በመንግስትና በግሉ ዘርፍ አጋርነት በ300 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ወጪ ሁለት የፀሃይ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች እንደሚገነቡ የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።ኢትዮጵያ በመንግስትና በግሉ ዘርፍ አጋርነት17 ፕሮጀክቶች ለመገንባት ጥረት እያደረገች ሲሆን፥ ከእነዚህ ውስጥም 13ቱ የሃይል ማመንጫዎች መሆናቸው ተገልጿል።

Via Fana
@YeneTube @FikerAssefa
በአቃቂ ገበያ ማዕከል ቃጠሎ ጉዳት ለደረሰባቸዉ ነጋዴዎች ድጋፍ እንደሚያደርግ የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር የተቋማዊ አቅምና ድጋፍ ዘርፍ ሚንስቴር ዴኤታ ወ/ሮ ምህረት ምናስብ በዛሬዉ ዕለት በስፍራዉ ተገኝተዉ ተጎጂዎችን ጎብኝተዋል፡፡ የገቢዎች ሚኒስቴር በንግዱ ማህበረሰብ ላይ ድንገት በደረሰዉ አደጋ የተሰማዉን ጥልቅ ሃዘን ገልፀዉ በንግዱ ማህበረሰብ ላይ የደረሰዉ አደጋ በአገሪቱ ገቢ ላይ የደረሰ አደጋ በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በመሆን የአቅሙን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡ መነሻዉ ለግዜዉ ያልታወቀዉ የእሳት አደጋዉ የንግድ መዕከሉን ሙሉ ለሙሉ ያወደመ ሲሆን በቦታዉ ጉዳቱ የደረሰባቸዉ ነጋዴዎች ሌላዉም አካል ድጋፍ እንዲያደርግላቸዉ ጠይቀዋል፡፡

ምንጭ: የገቢዎች ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
#FakeNewsAlert

"ጅማ ውስጥ አንድ የሀይማኖት አባት ተገደሉ፣ ሬሳቸው ተጥሎ ተገኘ" እየተባለ የሚወራው ፍፁም ውሸት እንደሆነ ከክልሉ ባለስልጣናት እንዲሁም ከቤተ- ክህነት ለማረጋገጥ ችያለሁ።

በአዲሱ አመት ለፌክ ዜና አሰራጮች ልቦናውን ይስጥልን!

Via Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
እንቁጣጣሽ ሎተሪ ወጣ!!!

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው እንቁጣጣሽ ሎተሪ ጳጉሜን 06/2011 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ ዕድል አዳራሽ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ በህዝብ ፊት ወጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት የወጡት የአሸናፊ ዕጣ ቁጥሮች እንደሚከተሉት ሆነዋል፡፡

1ኛ. 10,000,000 ብር የሚያስገኘው የ1ኛ ዕጣ ቁጥር -------1662862
2ኛ. 5,000,000 ብር የሚያስገኘው የ2ኛ ዕጣ ቁጥር----------0022646
3ኛ. 2,500,000 ብር የሚያስገኘው የ3ኛ ዕጣ ቁጥር ---------1231149
4ኛ. 1,500,000 ብር የሚያስገኘው የ4ኛ ዕጣ ቁጥር ---------0018527
5ኛ. 1,000,000 ብር የሚያስገኘው የ5ኛ ዕጣ ቁጥር ---------1774633
6ኛ. 500,000 ብር የሚያስገኘው የ6ኛ ዕጣ ቁጥር -----------1703425
7ኛ. 20 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 20,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር -------36808

8ኛ. 20 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 10,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር--------89196
9ኛ. 200 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 5,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር--------7889
10ኛ. 200 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 1,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር-------3883
11ኛ.2,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 500 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር-------788
12ኛ.2,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 250 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር-- ----657
13ኛ. 20,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 100 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር-----52
14ኛ.20,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 50 የሚያስገኘው (የማስተዛዘኛ) ዕጣ ቁጥር----1 በመሆን ወጥቷል፡፡

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር
@YeneTube @FikerAssefa
ብሄራዊ የአንድነት ቀን እና የአዲስ አመት ዋዜማ እየተከበረ ነው።

ቀኑ በተለይም በብሄራዊ ቤተ መንግስት እየተከበረ ይገኛል።በስነ ስርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስን ጨምሮ የሃይማኖት መሪዎች እንዲሁም ታዋቂ ግለሰቦችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

መድረኩንም የሃይማኖት መሪዎቹ በምርቃት ያስጀመሩት ሲሆን፥ መጭው አዲስ አመት የሰላም፣ የፍቅር፣ የጤና እና የብልጽግና ይሆን ዘንድ መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።ጳጉሜን በመደመር እሳቤ ከጳጉሜን 1 ቀን ጀምሮ እየተከበረ ሲሆን በዛሬው እለትም ፍጻሜውን ያገኛል።

Via EBC/FBC
@YeneTube @FikerAssefa
65 ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች የጸደቀውን የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ ላይ እንደገና ተቃውሟቸውን ገልጸዋል፡፡

ፓርቲዎቹ ይህን ያሉት ትናንት በጋራ ባወጡት መግለጫ መሆኑን ሪፖርተር አስነብቧል፡፡ የምርጫ ቦርድ ሃላፊዎችም የማሻሻያ ሃሳቦቻችን ውድቅ አድርገው፣ አፋኙን አዋጅ መደገፋቸው ዲሞክራሲያዊ ሂደቱን ለማፈን የሚፈልጉ አካላት ቦርዱ ውስጥ እንዳሉ ያሳያል ብለዋል፡፡ አዋጁ እንዲሻሻልም ግፊታቸውን እንደሚገፉበት ጠቁመዋል፡፡

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
2012 ዋዜማ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር በመዲናዋ የሚገኙ ዲፕሎማቶች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣኖችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ስነስርዓት እየተከበረ ነው።እኩለ ሌሊት ላይ ልዩ የርችት ትዕይንት ይኖራል !

እንኳን አደረሳችሁ !

@YeneTube @FikerAssefa