የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ- መስተዳድር አቶ #ሙስጠፋ_መሐመድ በብሔራዊ ቤተ-መንግስት እየተካሄደ ባለው የአዲስ ዓመት ዋዜማ ዝግጅት ላይ ከተናገሩት የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች፡-
📌 በዚህች አገር ብሔራዊ መግባባትና አንድነት እንዳይመጣ እያደረጉ ካሉ ነገሮች አንዱ በታሪክ ዙሪያ ያለው ውዝግብ ነው፤ በሀይማኖቶቻችን፣ በባሕሎቻችን፣ ወዘተ ዙሪያ በመካከላችን መቻቻል፣ መግባባት አለ፤ በታሪካችን ዙሪያ ግን ይህ የለም፤ በታሪክ ላይ መነታረክ አስፈላጊ አይደለም፤ አብሮ ለመኖር በታሪክ መስማማት የግድ አይደለም፤ ብዙ ጊዜ ማጥፋት ያለብን ወደፊት በማየት የተሻለች ኢትዮጵያን መፍጠር ላይ ነው፤ መለኪያ መሆን ያለበት ከሚመስሉን ሳይሆን ከማይመስሉን ሰዎች ጋር አብሮ መኖር መቻል ነው፤ አንድ መሆን ከመበታተን አይሻልም? መፋቀርስ ከመጣላት አይሻልም?
📌 ሌላው የወቅቱ የአገራችን ችግር የፖለቲካ ጨዋነት መጥፋት ነው፤ ሕግ ብቻ ዲሞክራሲን ለማስፈን በቂ አይደለም፤ ሕግ ስለማይከለክለን ብቻ አንድን ተገቢ ያልሆነ ነገር ማድረግ የለብንም፤ ልክ ሕግ ስለማያይ፣ ስለማይጠይቀን ብቻ ዝሙትን፣ ስርቆትን፣ ወዘተ መፈፀም እንደማይገባን ሁሉ ማለት ነው፡፡
📌 ሌላው ችግር በተናጠል ችግሮቻችንን ለመፍታት የምንሄድበት መንገድ ነው፤ ችግሮቻችንን ለመፍታት መንቀሳቀስ ያለብን በተናጠል ሳይሆን በጋራ ነው፡፡
📌 እንደ ሀገር የተጠቀሱትን ክፍተቶቻችንን መድፈን ከቻልን የተጋረጠብንን ችግር መሻገር አይሳነንም፤ ለዚህም ባለፈው ዓመት መደላድሎችን ስንፈጥር ቆይተናል፤ መጪው ዓመት ደግሞ የተሻለ ይሆናል የሚል እምነት አለኝ፡፡
ምንጭ:EBC
@YeneTube @FikerAssefa