የሰላም ሚኒስቴር ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ለስድስት ቀናት የሚዘልቅ ስልጠና ለመላው ሠራተኞቹ እያካሄደ ነው። ስልጠናው ልዩ ልዩ ርዕሰ ጉዳዮችን የሚዳስስ ሲሆን ተቋማዊ ራዕዩን በሚገባ የተገነዘበ፣ የሰላምን ሥራ ለመከወን የበለጠ መነቃቃት ያለው እና ለለውጥ ፈር ቀዳጅ የሆነ የሰው ኃይልን ለማደራጀት የታለመ ነው።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
በ10 ሚሊዮን ዶላር በቢሾፍቱ የተገነባው የአህያ ቄራ "በከፊልም ወይም በሙሉ" ለሽያጭ መቅረቡን ፎርቹን ዘግቧል። ቄራው "አህያ ማረድ ከማኅበረሰቡ ባሕልና እምነት ይቃረናል" በሚል የታገደበት የቻይና ኩባንያ ለጠቅላይ ምኒስትሩ አቤት ብሎ ነበር።
Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
አሳዛኝ ዜና‼️
በትግራይ ክልል ላዕላይ ማይጨው ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ሕይወት አለፈ።
በትግራይ ክልል ላዕላይ ማይጨው ወረዳ ዱራ በተባለው አከባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሶስት ሰዎች ሕይወት አለፈ።በትራፊክ አደጋው ሕይወታቸው ካለፈው ሶስት ሰዎች በተጨማሪ ስምንት ሰዎች ላይም ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ነው የተገለጸው።አደጋው ከሽረ ወደ መቐለ ከተማ ተሳፋሪዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ሃይሩፍ ተሸከርካሪ ከሲኖትራክ ጋር በመጋጨቱ የደረሰ መሆኑን የላዕላይ ማይጨው ወረዳ ትራፊክ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።አደጋው ከሚጠበቀው ፍጥነት በላይ በማሽከርከር የተከሰተ እንደሆነም የፖሊስ መረጃ ያመላክታል። አሽከርካሪዎች ከዚህ አደጋ ትምህርት በመውሰድ ፍጥነት በመቀነስ በሰው ህይወት እና ንብራት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት እንዲቀነሱ የላዕላይ ማይጨው ወረዳ ትራፊክ ፖሊስ ጽህፈት ቤት መልዕክቱን አስተላልፏል።
ምንጭ: ፋና

በድሬዳዋ በችኩንጉኒያ ወረርሽኝ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ወደ 20 ሺህ ማሻቀቡ ተገለጸ፡፡
ችኩንጉኒያ ወረርሽኝ ኤደስ በምትባል ትንኝ ንክሻ ወደ ሰው የሚተላለፍ በሽታ ሲሆን ችኩንጉኒያ በሚባል ቫይረስ የሚመጣ ህመም ነው፡፡የችኩንጉኒያ ወረርሽኝ ከሀምሌ ወር ጀምሮ በድሬዳዋ ከተማ የተከሰቱ ሲሆን የተጠቂዎች ቁጥር ባሳለፍነው ሳምንት ከደረሰበት 15 ሺህ አሁን ላይ ወደ 20 ሺህ ከፍ ማለቱን የኢትዮጵያ ህብረትሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል፡፡በወረሽኙ እስከ አሁን ድረስ የሞተ ሰው አለመኖሩንም ኢንስቲትዩቱ ገልጿል። እስካሁን በተደረገ የቤት ለቤት አሰሳ 86 በመቶ የሚሆኑት ቤቶች ወረርሽኙን የሚያስተላልፈው ትንኝ እጭ እንደተገኝባቸው ኢንስቲትዩቱ አስታውቃል፡፡
ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ከድሬዳዋ አስተዳደር፣ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እንዲሁም ከአጋር ድርጅቶች የተውጣጣ ፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድን በቦታው በመገኘት የተቀናጀ ምላሽ በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ነው የተገለጸው፡፡ወረርሽኙን ባጭር ጊዜ ውስጥ ለመቆጣጠር በከንቲባ ፅ/ቤት የሚመራ ግብረሃል ተቋቁሞ በቅንጅት እየተሰራ የሚገኝ ሲሆን ከእነዚህም ዉስጥ የቤት ለቤት ርጭት፣ የቅኝት እና አሰሳ ስራዎች፣ የማህበረሰብ ንቅናቄ፣ የህክምና አገልግሎት በሁሉም ጤና ተቋማቶች እየተከናወኑ እንደሆነ ተገልጿል።ማህበረሰቡ ከበሽታው እራሱን መከላከል እንዲችል ለሃይማኖት አባቶች፣አመራሮች፣ለማህበረሰብ መሪዎች እንዲሁም ለብዙሃን መገናኛ ባለሙያዎች በአጠቃላይ ለ125 ሰዎች ስልጠና መሰጠቱንም ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል፡፡
ምንጭ: Ethio FM

የኮሌራ በሽታ በሶስት ክልሎች ላይ በድጋሚ ተከስቷል ተባለ፡፡
በሀገሪቱ ተከስቶ የነበረውን የኮሌራ ወረርሽኝ በአብዛኛው ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር የተቻለ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት በሶስት ክልሎች ላይ በሽታው ተከስቷል ተባለ፡፡
በአሁን ወቅት ወረርሽኙ በኦሮሚያ ክልል በሻሸመኔ ወረዳ 15 ሰዎች በፈዲስ ወረዳ 20 ሰዎች፣ ሀረሪ ክልል በ6 ወረዳዎች 15 ሰዎች ተይዘዋል ተብሏል።
እንዲሁም በደቡብ ክልል በሃዋሳ ከተማ 14 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተገልጿል።
በወረርሽኙ የተያዙ ሰዎች የህክምና አገልግሎት እያገኙ እንደሆነ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል፡፡
በኢትዮጵያ ከወራት በፊት በተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ 19 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል።
የበሽታው ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰ ቢሆንም ማህበረሰቡ በዚህ ሳይዘናጋ አሁንም አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ኢንስቲትዩቱ አስጠንቅቋል፡፡
Via:- Ethio FM

የህገ ወጥ ንግድ መስፋፋትና የንግድ ስርዓቱ መዋቅራዊ ችግር ለመሠረታዊ የፍጆታ እጥረቱ መንስኤ ሆኗል።
የኢፌዴሪ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የንግድ ስርርዓቱን እና የኑሮ ውድነትን አስመልክቶ ከአምራች ኢንዳስትሪዎች፣ ከአስመጭና ላኪዎች እንዲሁም ከዘርፋ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ምክክር እያደረገ ነው፡፡
በመድረኩ የዘይት፣ የስኳር፣ የዱቄት እና ሌሎች የፍጆታ ምርቶች እጥረት በሕዝቡ ኑሮ ላይ ከፍተኛ ተዕፅኖ እያደረሱ መሆኑ ተነስቷል።
የህገ ወጥ ንግድ መስፋፋት፣ የመንግስት የቁጥጥር ስርዓት መላላት፣ የግብዓት አቅርቦት እጥረት እና የአጠቃለይ የንግድ ስርዓቱ መዋቅራዊ ችግር ለእጥረቱ መንስኤ እንደሆኑ ተጠቅሷል።
Via:- AMMA

ጋምቤላና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ አካባቢዎች ውጥረት ይታያል፤ በደቡብ ክልል የጸጥታ ሁኔታው ፈታኝ ነው ያለው የኖርዌይ መንግሥት ኢትዮጵያ አሁንም ለአገር ጎብኚዎች አስተማማኝ አይደለችም፤ የትራፊክ አደጋም ያሰጋቸዋል ብሏል።
Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
ለዎላይታ ሕዝብ ጥያቄ አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥ ዎሕዴግ ጠየቀ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት የዎላይታ ሕዝብ ላቀረበው ሕገ መንግሥታዊ የክልልነት ጥያቄ በአስቸኳይ ሕገ መንግሥታዊ ምላሽ ይስጥ ሲል፣ የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲዊ ግንባር (ዎሕዴግ) ጥያቄ አቀረበ፡፡ፓርቲው ይህን ጥያቄ ያቀረበው ሰኞ ነሐሴ 27 ቀን 2011 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ዲአፍሪክ ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡
የዎላይታ በክልልነት ደረጃ መደራጀት ጥያቄ ማለት ‹‹ዎላይታ በህልውናው የመቀጠል ጥያቄ እንደሆነ›› የገለጹት የፓርቲው ኃላፊዎች፣ ነገር ግን ደኢሕዴንና የደቡብ ክልል መንግሥት ይህ ጥያቄ ተስተጓጉሎ እንዲቀር ለማድረግ እየሠሩ ነው በማለት ከሷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የፓርቲው ኃላፊዎች በዎላይታና አካባቢው የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳም ጠይቀዋል፡፡
ምንጭ: ሪፖርተር

አዋሽ የወይ ፣ ዳንኪራ የተሰኘ አዲስ ብራንድ ወይን ማምረት ጀምሯል።
በስትሮቤሪ ማርጋሪታና ፒች ቮድካ ጣዕም የቀረበው ምርት የ6% የአልኮል ይዘት እንደሚኖረው ነው የታወቀው።የኩባንያው ምርትና ምርምር ሃላፊ አቶ ብርሃን መንግስቱ ለፎርቹን እንዳስረዱት ምርቱ በ330 ሚሊ ጠርሙሶች የሚታሸግና በአዲስ አበባ በሚገኙ በተመረጡ ሬስቶራንቶች በብር 30 ይከፋፈላሉ።

ከጳጉሜ 1 እስከ 6 ለ1 ሺሕ ዜጎች ነፃ የሕክምና አገልግሎት ይሰጣል።
በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ በጤናው ዘርፍ የሚታየውን ክፍተት ለመሙላት ከጳጉሜ 1 እስከ 6/2011 ”ጳጉሜን ለጤና” በሚል መሪ ቃል ለ1 ሽሕ ሰዎች ነፃ የሕክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ ታውቋል። በውዳሴ ዲያግኖስቲክ ማዕከል የሚሰጠው ነፃ የምርመራና የሕክምና አገልግሎት አጠቃላይ የውስጥ ደዌን ጨምሮ የአንገት ፣ የጉበት፣ የካንሰር፣ የጨጓራ፣ የልብና ተያያዥ ጉዳዮችን ያካተተ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

የሱማሊያ መንግሥት የጁባላንድ ራስ ገዝ አስተዳደር ጸጥታ ሚንስትርን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የሞቃዲሾው ዳልሳን ሬዲዮ ዘግቧል፡፡ ሃላፊው አብዲረሽድ ጀናን ትናንት የታሰሩት ወደ አዲስ አበባ ሊጓዙ ሲሉ ነው፡፡ መንግሥት በጌዶና አጎራባች ክልሎች በተፈጸሙ ወንጀሎች እጠረጥራቸዋለሁ ብሏል፡፡ ራስ ገዟ በቅርቡ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ካካሄደች ወዲህ፣ ከሞቃዲሾ ጋር ውጥረቱ ተባብሷል፡፡
-Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
-Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
የጀርመን ፓርላማ አባላት ከምክትል አፈ ጉባኤ ሽታየ ምናለ ጋር ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን በማዘመን ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
ባለፈው ረቡዕ 29 ሰዎች ጭኖ በሜድትራኒያን ባሕር ላይ የጠፋ ጀልባ ትናንት በጣሊያን ባሕር ኃይል መገኘቱን @alarm_phone አስታውቋል። 19 አዳጊዎችን ጨምሮ የ5 ቤተሰብ አባላት ጭኖ ነበር። ሰዎቹ ጣሊያን ፖዛሎ ገብተዋል።
Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
የጅቡቲዋን ዶራሌ ሁለገብ ወደብ ከዋናው የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ሐዲድ ጋር የሚያገናኘው አጭር የሐዲድ መስመር ግንባታ መጠናቀቁን ካፒታል አስነብቧል፡፡ በመጭው ወር አገልግሎት መስጠትም ይጀምራል፡፡ የመስመሩ መጠናቀቅ ካርጎዎችን በቀጥታ ከወደቡ ወደ ባቡር ለመጫን ያስችላል፤ አገልግሎት አሰጣጡንም ያፋጥናል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
ሆንግ ኮንግ ውስጥ ዛሬ የዓመቱ ትምህርት የሚጀመርበት ቀን ቢሆንም ተማሪዎች ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ውለዋል።
የሁለተኛ ደራጃ ተማሪዎች ትምህርት ቤት መግባታቸውን ትተው ለዲሞክራስያዊ ንቅናቄ ያላቸውን ድጋፍ ለማሳየት ሲሉ በመናፈሻ ቦታ ተሰባስበው ውለዋል።የተቃውሞ ሰልፈኞቹ ንጋት ላይ የባቡር በሮችን በማገድ የሰዎች ማመላለሻ ባቡሮች እንዳይንቀሳቀሱ አድርገው ነበር።ትላንት ደግሞ ዲሞክራስያዊ መብቶችን የሚጠይቁት ተቃዋሚዎች ወደ ዓለምቀፍ አይሮፕላን ማረፍያ ተደራሽነት እንዳይኖር ሲሉ መንገድ ላይ ያሉትን መሰናክሎች በእሳት አጋይተዋል። በአውሮፕላን ማረፍያ ውስጥ ወዳሉት አውቶብሶች የሚያስገባውን በር ዘግተዋል።የትራንዚት ክፍል ባለሥልጣኖች የባቡር አገልግሎትን ለማቆም ተገደዋል። በተቃውሞው ምክንያት አንዳንድ የአውሮፕላን በረራዎች ስለተሰረዙ መንገደኖች ወደ መሀል ከተማ ለመመለስ ለሰዓታታ ያህል በእግር ለመጓዝ እንደተገደዱ ተዘግቧል።
#VOA

ስፖርት!! የኢትዮጵያ ሴቶች ኦሊምፒክ ቡድን የመልስ ጨዋታውን ነገ ከካሜሮን ጋር በያውንዴ ያደርጋል
የኢትዮጵያ ሴቶች ኦሊምፒክ ቡድን የቶኪዮ ኦሎምፒክ የቅድመ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን ነገ ከካሜሮን ጋር በያውንዴ ያደርጋል።ጨዋታው 42 ሺህ ተመልካች በሚያስተናግደው አህማዱ አሂጆ ስታዲየም ከቀኑ 11 ሰዓት ከ30 ይካሄዳል።29 የልዑካን ቡድንን የያዘው የኢትዮጵያ ሴቶች ኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድን ትናንት ያውንዴ መግባቱን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ምንጭ: ዋልታ

የእርዳታ ጥሪ!!
⬆️⬆️ከላይ በፎቶው ላይ የምትመለከቷት እህታችን ቤቴልሄም አሽኔ ትባላለች ፡፡
በጅማ ዩኒቨርስቲ የ3ኛ አመት ተማሪ በነበረችበት ወቅት ባጋጠማት የነርቭ ህመም ግማሽ የሰውነቷን ክፍል ሙሉ በሙሉ ማንቀሳቀስ ተስኗት ( ፓራላይዝድ ሆና ) ትምህርቷንም አቋርጣለች ፡፡
ስለዚህ ቤተሰቦቿ መድሀኒቱንና የህክምናውን ወጪ ለመሸፈን በመቸገራቸው የእኛን እርዳታና ትብብር ይሻሉ።
ስለዚህ እህታችን ቤቲ ሙሉ ጤንነቷ ተመልሶ ወደ ትምህርት ገበታዋ መመለስ እንድትችል ሁላችንም ብዙ ትንሽ ሳንል በቻልነው አቅም እንድንረዳት በፍቅር እንጠይቃለን ፡፡
ቤቲን ለመርዳት ከዚህ በታች ያለውን የባንክ ሂሳብ ቁጥር ይጠቀሙ
ስለትብብርዎ እናመሰግናለን
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000183177293
ገመቹ ተሾመ
#share #share

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዶሪያን የተባለው ኸሪኬን ወይም ከባድ አውሎ ነፋስ የተቀላቀለበት ማዕባል ዛሬ ግራንድ ባሃማ የተባለውን ደሴት አውድሟል። በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶችን አፍርሷል፣ ከፍተኛ ጉዳት አድርሶባቸዋል።ማዕበሉ አደገኛና አውዳሚ እንደሚሆን የአየር ሁኔታ ተንባዮች አስገንዝበዋል።
Via VOA
@YeneTube @FikerAssefa
Via VOA
@YeneTube @FikerAssefa
#Fact
የኢንዶኔዥያ ሀገራዊ ጥቅል ምርት የዛሬ 20 ዐመት ከነበረበት በ1000% አድጓል።
በ1998 እ.አ.አ----105 ቢሊዮን ዶላር
በ2018 እ.አ.አ---- 1.05 ትሪሊየን ዶላር

ከሱዳን ዋና ከተማ ከካርቱም በስተደቡብ 360 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ዛሬ በደረሰ የመኪና አደጋ 15 ሰዎች መሞታቸውን የሱዳን ፖሊስ አስታወቀ
በተቃራኒ አቅጣጫ ይጓዙ የነበሩ ሁለት አውቶብሶች ፊት ለፊት በተጋጩበት በዚህ አደጋ ሌሎች 22 ሰዎች መቁሰላቸውን ፖሊስ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ፖሊስ እንዳለው አንደኛው አውቶብስ ከፊቱ የነበረ መኪናን በፍጥነት አልፎ ለመሄድ ሲሞክር ነበር ከፊት ለፊቱ ይመጣ ከነበረ ሌላ አውቶብስ ጋር የተጋጨው።
ሱዳን የመኪና አደጋ በተደጋጋሚ ከሚደርስባቸው ሃገራት አንዷ ናት። ለአደጋው በምክንያትነት ከሚጠቀሱት መካከል በስርዓት የማይጠገኑ መንገዶች እና የትራፊክ ሕጎችን አለማስከበር ይገኙበታል። የዓለም የጤና ድርጅት በጎርጎሮሳዊው 2018 ሱዳን ውስጥ የመኪና አደጋ ከ10 ሺህ በላይ ሰዎችን ሕይወት እንዳጠፋ አስታውቋል።
ምንጭ ጀርመን ድምፅ
@YeneTube @Fikerassefa